Paul's Letters 1 Thessalonians

Greetings And Thanksgiving

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Coming Lord 1 Thessalonians 1 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 552 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ይህ በተሰሎንቄ ላለችዉ ቤተ ክርስቲያን የጳዉሎስ የመጀመሪያዉ መልዕክት ነው ፡፡ ጳዉሎስ ለዚች ቤተ ክርስቲያን በኋላ ሁለት መልዕክቶችን እንዲፅፍ ያደረገዉ በተሰሎንቄ ሰዎስት ሳንምት ወይም ሰዎስት ሰንበት ያክል አሳልፏል ፡፡ በአዲስ ከተማ ስራን የመጀመር እርምጃን ከጳዉሎስ ብዙ መማር እንችላለን፡ ሞደል አድርጎ መቅረፅ፣ እረዳት መሆን፣ በጥንቃቄ መመልከት/መከታተል እና መዉጣት ፡፡ ለዚህ መፅኀፍ ቃላችን የሚመጣዉ ጌታ ነው ፡፡ 1 ተሰሎንቄ 4 የተስፋ እና የመፅናናት ምዕራፍ ነዉ ምክንያቱም በኢየሱስ ላይ እንደ ሚመጣ ጌታ እይታችንን በእርሱ ላይ እንድናተኩር ስለሚያበረታታን፡ “ እኛ ህያዋን ሆነን ጌታ እስኪመጣ ድረስ የምንቀር ያንቀላፉት አንቀድምም “ (1ተሰ 4፡ 15) ፡፡ “ ያንቀላፉትን “ የሚለዉ የሞቱትን ያመለክታል ፡፡ ቁጥር (16-17) የኢየሱስን ከሰማይ መመለስ እና የሞቱት እና በህይወት ያሉት ከእርሱ ጋር እንደሚዋሀዱ / እንደሚገናኙ ይገልፃል ፡፡ ጳዉሎስ ይህን መልዕክት በተሰሎንቄ ያሉትን ሰዎች “ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለ ነቀፋ ፈጽመዉ ይጠበቁ “ (1ተሰ 5፡ 23) በማለት አጠቃሏል ፡፡

ጳዉሎስ በሁለት ስፍራ ላይ ራሱን እንደ ፀኃፊ ለይቷል፡ በ 1ተሰ (1፡ 1) እና (2፡ 18) ፡፡ ጢሞቲዎስ እና ሲላስ በጳዉሎስ በሁለተኛዉ የአገልግሎት ጊዜው አብረዉት ተጉዘዋል ፤ ሐዋሪያት ስራ 17 እነዚህ ሰዎች ተሰሎንቄን በመጎብኘት በዚያ ከተማ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ጀመሩ ይናገራል ፡፡ የጳዉሎስ ሁለቱ መልዕክቶች ከክርስቶስ ሞጽ 51 በኋላ በቆሮንቶስ እያገለገለ በነበረ ጊዜ የተፃፉ ነበሩ ፡፡ እንደ ማክአርቱር ዮሐንስ ገለፃ “ ቀኑ በቆሮንቶስ አጠገብ ባለ በአጵሎስ ቤተ መቅደስ በተፃፈ ፅሁፍ ቅደም ተከተሉ አረጋግጦታል “ ፡፡ በሐዋሪያት ስራ 18 ከክርስቶስ ሞት 51 በኋላ አገረ ገዚ የነበረዉን ጋልዮስ አመለከተ ፤ ገላትያ ከክርስቶስ ሞት 50 በኋላ የተፃፈ ከነበር ይህ መልዕክት የጳዉሎስ ሁለተኛው ጉዞ አገልግሎት ጋር ይጣጣማል ፡፡

ተሰሎንቄ በቀድሞዉ በዉሃ ላይ የምተገኝ በአሁኑ ጊዜ በግሪክ ወደብ አካባቢ ያለች ሶላንኬ ነው ፤ አገና ባህር በሚደርሰዉ በቀድሞዉ በተርማ ከተማ በተርማን ባህር /ወደብ ላይ ያረፈች ነች ፡፡ ከክርስቶስ ልደት 168 በፊት የሜቄዶኒያ ዋና ከተማ ሆናለች ፤ “ በነፃ ከተማነት “ ሁኔታ ተደሰቱ ማለትም በራሳቸው ነዋሪዎች ተዳድረዋል ፤ ይህ አንዳንድ አይሁዶች “ ጃንሰን እና ከተማዋ በሚገባ ከመታወቋ በፊት መሳባቸዉን “ በሚናገረው በሐዋ (17፡ 5-9) የተደገፈ ነው ፡፡ ተሰሎንቄ የሮማ ግዛት አካል የነበረች እና “ ሁሉንም መቄዶንያ “ ያመለከተ ነበር ፡፡ በስፍራዉም ሁለት መቶ ሺህ ህዝብ ይኖር ነበር ፡፡ ጳዉሎስ ከፊሊጲን ወደ ተሰሎንቄ በግምት 100 ማይል ርቀት ተጉዟል ፡፡

ጳዉሎስ ወደ ከተማዋ በገባ ጊዜ እንደ ልማዱ በአካባቢዉ ያሉ አይሁዶችን ወንጌል ማስተማር ወደ ሚችልበት ምኩራብ ተመለከተ ፡፡ ሐዋ (17፡ 1-4) ወደ ከተማዋ የጳዉሎስን አገባብ ስዕል በደንብ ይስለዋል ፡፡ ለሰዎስት ሰንበቶች ጳዉሎስ በምኩራብ ኢየሱስን እንደ መሲህ አወጀ ፡፡ አንዳንድ አይሁዶች እንዲሁም ግሪኮች እና እግዚአብሄርን የሚፈሩ ሴቶች ወንጌልን በማመን ጳዉሎስን ተቀላቀሉት ፤ በዚህም የአይሁድ መሪዎች በመቅናት ህዝብን በማነሳሳት ከተማዋ ከመታወቋ በፊት ጃንሰን እና አንዳንድ ሌሎች ወንድሞች እስኪመጡ ድረስ አመፁን ጀመሩት ፡፡ ወንድሞችም ጳዉሎስን እና ሲላስን ወደ ቤሪ ላኳቸው ፤ ከዚያም ሲላስና ጢሞቲዎስ በቤሪ እንደ ተቀመጡ ጳዉሎስ በአቴና ላይ ተጓዘ ፤ ቆይቶም/በኋላም ሲላስ እና ጢሞቴዎስ በአቴና ከጳዉሎስ ጋር ተገናኙ ፤ በኋላም ጢሞቴዎስ ተመልሶ ወደ ተሰሎንቄ ሲላክ ሲላስ ደግሞ ወደ ፊልጵስዩስ ተላከ ፡፡ በሐዋሪያት ስራ 18 ጳዉሎስ ጢሞቴዎስ እና ሲላስ እርሱን ወዳገኙበት ስፍራ (ቁጥር 5) ወደ ቆሮንቶስ ሄደ (ቁጥር 1) ፡፡ ጳዉሎስ ጢሞቲዎስ በተሰሎንቄ ያለችዉ ቤተ ክርስቲያን ያለችበትን ሁኔታ ሪፖርት ካመጣለት በኋላ ለተሰሎንቄ የመጀመሪያዉን መልዕክት ፃፈ ፡፡

ትምህርት

1-ተሰሎንቄ (1፡ 1-4)፡ ጳዉሎስ መልዕክቱን በተለመደ ሰላምታው “ ፀጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን “ (ቁጥር 1) በማለት ጀመረ ፡፡ ጳዉሎስ ያለማቋረጥ በፀሎቱ እንደሚያስባቸዉ ተናገረ (ቁጥር 2) ፡፡ ለመሰረታት ቤተ ክርስቲያን መፀለይ በፍፁም አላቆመም ፡፡ ጳዉሎስ “ የእምነት ስራቸዉን፣ የፍቅር ድካማቸዉን እና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ያላቸዉን ተስፋ “ እዉቅና ሰጣቸው (ቁጥር 3) ፤ ጳዉሎስ ሲጓዝ እነዚህ አዲስ አማኞች እያደረጉት የነበረዉ እንዴት መልካም እንደነበር ሰምቷል ፡፡ “ ስራቸዉ በእምነት ተደርጓል “ የሚለዉ ከመንፈስ ቅዱስ የሆነ ነገር እየሰሙ እንደ ነበር እና በዚያም እየተመላለሱ እንደ ነበር ያመለክታል ፡፡ “ ስራቸዉ በፍቅር የተነሳሳ/በፍቅር የተደረገ ነው “ ማለት ፍቅራቸዉን ለመግለፅ ነገሮችን እያደረጉ ነበር ማለት ነው ፤ በእነዚህም ሁሉ በተስፋ በተስፋቸዉ የፀኑ ነበሩ ፡፡ በጌታ የታቀፉ/የተያዙ ነበሩ ፡፡

1-ተሰሎንቄ (1፡ 5-8)፡ ምንም እንኳን ጳዉሎስ በተሰሎንቄ ሰዎስት ሳምንታትን ብቻ ቢያሳልፍም እግዚአብሄር የተለዬ ነገር ስላደረገ በዚያ ያሉ አማኞች “ በመቄዶንያና በአካይያ ላሉ አማኞች ሁሉ “ ምሳሌ ሆኑ (ቁጥር 7) ፡፡ ጳዉሎስ የወሰዳቸዉ አራት ቃላቶች አሉን፡ ምሳሌ፣ ረዳት፣ መመልከት እና መተዉ/መዉጣት ፡፡

ምሳሌ/ሞደ፡ በቁጥር 5 ጳዉሎስ በቃል፣ በኃይል እና በመንፈስ ቅዱስ በማረጋገጫ፣ በማሳመኛ እና በመነሳሳት ለእነርሱ ወንጌልን ሞዴል አደረገላቸው ፡፡ ሰዎች ወንጌልን መስማት ያስፈልጋቸዋል (ሮሜ 10፡ 17) ጳዉሎስም ወንጌልን በመናገር/በማጋራት ምሳሌ ሆነ ፡፡ በሚገባ ክርስቶስ በሞት፣ በመቀበር እና በትንሳኤ ዉስጥ እንዳለፈ የምናምን ከሆነ ስለዚህ ነገር መናገር ያስፈልገናል ( 2ቆሮ 4፡ 13) ፡፡ ጳዉሎስም ወደ እነርሱ በኃይል መጣ ፡፡ ይህ ቃል ትርጉሙ በተፈጥሮ የሆነ ነገር ዉስጥ የሚኖርን ኃይል፣ ሁሉን መቻል፣ ችሎታ እና ጥንካሬ ከሆነዉ ዱናሚስ ከሚለዉ የግሪክ ቃል የመጣ ነው ፡፡ በሌላ ቋንቋ የእግዚአብሄር መንፈስ ኃይልን ስለሰጣቸው ወንጌልን መናገር ይችላሉ ማለት ነው ፤ ምስክሮቹ ለመሆን የእግዚአብሄር መንፈስ ያስፈልገናል (ሐዋ 1፡ 8) ፡፡ መንፈሱ ብቻ ወንጌልን እንድንናገር አያደርግም ወንጌል የእግዚአብሄር ኃይል ስለሆነም ነዉ እንጂ ፤ የሚቀያየሩ ናቸው ፡፡ ሮሜ (8፡ 14)፡ “ በእግዚአብሄር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሄር ልጆች ናቸዉና “ ፡፡ ወንጌልን ስንናግ በማረጋገጫነት፣ በእርግጠኝነት፣ በማሳመን እና በመነሳሳት/በኃይል ማድረግ ይገባናል ምክንያቱም እኛ በወንጌል ስላመንን ፡፡ ስለወንጌል ሁሉም ነገር እዉነት እንደሆነ በምናምን ጊዜ የእግዚአብሄር መንፈስ ወደፊት እሳትን ያመጣል ፡፡

ረዳት፡ ሰዎችን ከሩቅ መምራት አንችልም ፤ ወንጌልን ለመናገር/ለማጋራት በመንገዶች ላይ እና በጎረቤቶች ላይ የተዋሀድን/የቀረብን መሆን ያስፈልገናል ፡፡ ጳዉሎስ ወንጌልን በመናገር ሂደት ላይ ደገፋቸዉ/ረዳቸው (ቁጥር 5) ፡፡

መጠበቅ/መከታተል፡ ተሰሎንቃዊያን ጳዉሎስን እና ጌታን የመሰሉ በመሆን ከመንፈስ ቅዱስ በሆነ ደስታ መልዕክቱን በደስታ ተቀበሉ ፤ ጳዉሎስ በእምነት ጳዉሎስ ምሳሌ እንደሆነዉ ለመምሰል መጀመራቸዉን መመልከት ችሎ ነበር ፡፡

መዉጣት/መተው፡ ከተሰሎንቄ በመዉጣት መልዕክቱ በመቄዶኒያ እና በአክያ ሁሉ እና “ በእግዚአብሄር ዘንድ የሚሆን እምነታችሁ በሁሉ ስፍራ ተወርቷል “ (ቁጥር 8) ፡፡ ምስክርነታቸዉ እንዴት እንደ ሰፋ ማን ያውቃል ? ምንም እንኳን ጳዉሎስ እና ሲላስ ከተሰሎንቄ ቢወጡም መልዕክቱ መስፋቱን ቀጽሏል ፡፡ ያ የእግዚአብሄር ስኬታማ እንቅስቃሴ ነበር ፡፡

መደምደሚያ

ስለ 1 ተሰሎንቄ የተገረምኩት ለዚህ ነዉ ምክንያቱም ምንም እንኳን ጳዉሎስ በዚያ ካሉት ሰዎች ጋር ሰዎስት ሳምንት ብቻ ቢቆይም ለእነርሱ ለኢየሱስ ተገቢ ምስክሮች ለመሆን በቂ ነበር ፡፡ እናንተም የበረታችሁ እንድትሆኑ እፀልያለሁ ፡፡

ጥያቄዎች

  1. በተሰሎንቄ የነበረችዉ ቤተ ክርስቲያን እንዴት ነበር የተጀመረችዉ ? (ሐዋ 17፡ 1-9)
  2. የጳዉሎስ የመጀመሪያ ለዉጦች አይሁዶች ከነበሩ በሚገባ እንደሚረዱት ምን እርግጠኛ አደረገው ? (ሐዋ 17፡ 2-3, 1ዮሐ 2፡ 13)
  3. በተሰሎንቄ ያለችዉ ቤተ ክርስቲያን የትኛው ባህሪይ ጳዉሎስን ደስተኛ አደረገው ?
  4. በተሰሎንቄ ላሉት ወንጌል እንዴት መጣላቸው (1 ተሰ 1፡ 5) ? ወንጌልን ከሌሎች ጋር በመጋራት ለምን ሙሉነት/በራስ መተማመን ሊሰማችሁ ይችላል (ኢሳ 55፡ 11, ማቴ 28፡ 19-20, ሮሜ 1፡ 16, 1ቆሮ 2፡ 4-5) ? ሌሎችን በኢየሱስ ስም ማገልገል የሚያስደንቅ እና የሚጠቅም ነው ነገር ግን ለምን ቀስ በቀስ ወንጌልን መናገር አስፈላጊ ነው ? (ሮሜ 10፡ 13-17)
  5. ጳዉሎስ በተሰሎንቄዋዊያን ዉስጥ ያስተዋላቸዉ አደጋዎች ምን ነበሩ ? 1 ተሰ (1፡ 3) ከ 1ተሰ 1፡ 9-10 ጋር አወዳድሩ
  6. በ 1ተሰሎንቄ 1 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Thessalonians 1:5, 8 a

“For our gospel did not come to you in word only, but also in power, in the Holy Spirit, and with much assurance. You know what kind of men we were among you for your benefit . . . For the Lord’s message rang out from you, not only in Macedonia and Achaia, but in every place that your faith in God has gone out.”

ወንጌልን ለሌሎች ስትናገሩ በቃል ብቻ መሆን የለበትም ፡፡ ይልቁንም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እንጂ ፡፡ የክርስቶስ ኃይል ህይወትን ይለውጣል ፡፡ ጌታ ወንጌልን እንዲትናገሩ ሲመራችሁ ይህን አስታውሱ ጉዳዩ ስለ እናንተ ወይም እናንተ እንዴት አሳምራችሁ እንደምትናገሩ አይደለም ፡፡ ይህ ጥልቅ ስሜት ነው ፤ ይህ ምስክርነት ነው ደግሞም የመንፈስ ቅዱስ መገኘት ነው እንዲሁም በእናንተ ውስጥና ይህንን የምስራች በሚሰሙት ሰዎች ህይወት ውስጥ የሚሰራ ኃይል ነው ፡፡ ልብን የሚነካው መንፈስ ቅዱስ እንጂ የሚያማምሩ ቃላት አይደሉም ፡፡

መንፈስ ቅዱስ በሚሰራባቸው በእነዚያ ደቂቃዎች ውስጥ ነው ያቺ ህይወት የምትለወጠው ፡፡ ስለዚህም ለሌሎች ምስክርነታችሁን ተናገሩ ፡፡ በመታዘዝ ስትራመዱ ፤ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ስትወጡ በእግዚአብሔር ዘንድ የሆነው የእምነታችሁ ቃል ይሰማል ፡፡ በማህበረሰባችሁ ፣ በቤተሰባችሁ ደግሞም በትዳራችሁ ውስጥ ለውጥን ማየት ከፈለጋችሁ በፍጹም መሰጠት ፣ በትህትና ፣ በዕምነት ፣ በፍቅርና በተስፋ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተመላለሱ ፡፡ እናንተ በነገር ሁሉ ስትታገሱ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ነፍሳትን ይነካል ይለውጣልም ፡፡

“ ወንጌላችን በኃይልና በመንፈስ ቅዱስ በብዙ መረዳትም እንጂ በቃል ብቻ ወደ እናንተ አልመጣምና፤ በእናንተ ዘንድ ስለ እናንተ እንዴት እንደ ነበርን ታውቃላችሁ …….. ከእናንተ ወጥቶ የጌታ ቃል በመቄዶንያና በአካይያ ብቻ አልተሰማምና፥ ነገር ግን ምንም እንድንናገር እስከማያስፈልግ ድረስ፥ በእግዚአብሔር ዘንድ የሚሆን እምነታችሁ በሁሉ ስፍራ ተወርቶአል ። “

  • 1ኛ ተሰሎንቄ 1፡5 ፤ 1፡8

ተጨማሪ ጥቅስ

1ኛ ቆሮንቶስ 2:4 — “ ቃሌም ስብከቴም መንፈስንና ኃይልን በመግለጥ ነበረ እንጂ፥ በሚያባብል በጥበብ ቃል አልነበረም ። “

1ኛ ተሰሎንቄ 1:3 –“ የእምነታችሁን ስራ የፍቅራችሁንም ድካም በጌታችንም በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን የተስፋችሁን መጽናት በአምላካችንና በአባታችን ፊት ሳናቋርጥ እያሰብን “

2ኛ ጢሞቴዎስ 1:7–8 — “እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንምና ። እንግዲህ በጌታችን ምስክርነት ወይም በእስረኛው በእኔ አትፈር፥ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር ኃይል መጠን ስለ ወንጌል አብረኸኝ መከራን ተቀበል ፡፡ “