Paul's Letters Colossians

The Master/Servant Relationship

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Firstborn Colossians 4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 551 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ምዕራፍ 4 በፅሁፉ መካከል ላይ በማይመች ነጥብ ይጀምራል ፡፡ በምዕራፍ 3 ጳዉሎስ ስለ ክርስቲያናዊ ቤተሰብ ስርዓት ፅፏል - ሚስቶች ለባሎቻቸዉ መገዛት እንደ ነበረባቸው፣ ልጆች ለቤተሰቦቻቸው መገዛት እንደ ነበረባቸው እና አገልጋዮች ለጌቶቻቸው መገዛት እንደ ነበረባቸው ፅፏል ፡፡ በቆላ (4፡ 1) ጳዉሎስ እነዚህን የቤተሰባዊ ትዕዛዞች በመጨረስ የአገልጋዮችን ጌቶች አገልግዮቻቸዉን እንዲያከብሯቸው ነገራቸው ፡፡

በዚያ አገባብ ዛሬ ስለ ጌቶች/አገልጋዮች፣ አለቆች/ሰራተኞች እና መሪዎች/ቡድኖች እናወራለን ፡፡ ጳዉሎስ አገልግሎትን ለብቻ ማድረግ ጥበብ እንዳልነበር እና ሁልጊዜ አገልግሎትን እንደ ቡድን መስራት ጥበብ እንደ ሆነ እየተናገረ ነበር ፡፡ በመፅሀፍ ላይ የቀረቡት ቡድኖች እና አጋሮች ላይ እንመልከት፡

  • ጴጥሮስ እና ዮሐንስ
  • ጴጥሮስ፣ ዮሐንስ እና ሐዋሪያቶች
  • ጴጥሮስ፣ ዮሐንስ፣ ሐዋሪያቶች፣ የቀሬና እና
  • አቅላ እና ጵርስቅላ
  • ጢሞቲዎስና ሲላስ
  • በርናባስ እና ማርቆስ
  • በርናባስና ጳዉሎስ

ጳዉሎስ በመላዉ አለም ዉስጥ ወንጌልን ለማሰራጨት መሸከም እንደሚችሉ የሚያዉቃቸዉን ሰዎች ቡድን በመገንባት ስራ ላይ እንደ ነበር አምናለሁ ፤ አንድን ቡድን በመገንባት ላይ ብቻ በምን እንደሚሰብክ እየተገበረ ሳይሆን ቡድንን ለመጠበቅ በመጣ ጊዜ በምን እንደሚሰብክ ተግባራዊ እያደረገም እንጂ - የሰዎች እየቀጠለ ያለዉ መሪነት ፡፡ ጳዉሎስ በጌታና/በአገልጋይ ግንኙነት ዉስጥ ነበር ፤ በአገልጋይና/በጌታ ግንኙነት ዉስጥ ሰዎስት መንገዶችን ልናይ እንችላለን ፡፡ ባሪያ/አገልጋይ 1) ያለፍቃደኝነት ጌታዉን እያገለገለ የነበረ ሰዉ ማለት ነው፣ 2) ያለ ምንም ካሳ ጌታዉን ያገለግል የነበረ ባሪያ ማለት ነው ወይም 3) በካሳ/በክፍያ በፍቃደኝነት ጌታዉን ያገለግል የነበረ ባሪያ ማለት ነው ፡፡ ለዚህ ዉይይት አላማ ቢያንስ በሁለቱ ምርጫዎች ላይ እንመለከታለን - በፍቃደኝነት እያገለገለ የነበረን ሰው ፡፡

ትምህርት

ቆላስይስ (4፡ 1-4)፡ ጳዉሎስ ጌቶችን አገልጋዮቻቸዉን በፍትህ እና በሚገባ እንዲመለከቷቸዉ አዘዛቸው (ቁጥር 1) ፡፡ በፍትሀዊነት ማለት “ በትክክል “ እና በሚገባ ማለት ደግሞ “ በሚመች ሁኔታ “ በማለት መረዳት ይቻላል ፡፡ ኤፌ (6፡ 5-9) ጌቶች እንዴት ሊታዩ እንደሚገባቸዉ እና ጌቶች እንዴት ባሪያዎቻቸዉን መመልከት እንደ ነበረባቸው ተጨማሪ ማብራሪያን ይሰጣል - ጌቶች እና አገልጋዮች ሁለቱም እርስ በእርሳቸዉ “ ከልባችሁ የእግዚአብሄርን ፍቃድ በማድረግ “ (ቁጥር 6) ክርስቶስን በመታዘዝ መተያዬት ነበረባቸው ፡፡ በቆላ (4፡ 2) ጳዉሎስ እግዚአብሄር ቡድንን እንዴት እየተጠቀመ እንደነበር በንቃት የሚያዩ እንዲሆኑ እርስ በእርሳቸዉ ያለማቋረጥ እንዲፀልዩ አዘዛቸው ፡፡ በቁጥር (3-4) ጳዉሎስ እግዚአብሄር የእግዚአብሄርን ቃል እንዲናገሩ በርን መክፈትን እንዲቀጥልላቸዉ እና የእግዚአብሄርን ቃል ግልፅ እንዲያደርገዉ ለጳዉሎስ እንዲሰጠው ለቡድኖቹ ( “ ለእኛ “) በመፀለይ ጠየቀ ፡፡ በመቀጠልም ጳዉሎስ በጥበብ እንዲመላለሱና በሌሎች ፊት በክብር እንዲናገሩ አበረታታቸው (ቁጥር 5-6) ፡፡

ቆላስይስ (4፡ 7-14)፡ በቁጥር 7 ጳዉሎስ ቡድኑን መሰየም/መጥራት ጀመረ፡

ቲኪቆስ (ቁጥር 7-8) በጳዉሎስ መልዕክት አራት ጊዜ ተጠቅሷል (ኤፌ 6፡ 21-22, ቆላ 4፡ 7, 2ጢሞ 4፡ 12, ቲቶ 3፡ 12) ፤ ጳዉሎስ ቲኪቆስን የጳዉሎስን የእስራት ቃል እንዲያመጣና በዚያ ያሉትን ሰዎች እንዲያበረታታ ወደ ቆላስይስ ላከው ፡፡ ቲኪቆስ ሊታመን የሚገባዉ እና የእረኝነት ልብ ነበረው፣ ጳዉሎስም በሚገባ ተመልክቶአቸዉ እንደ ነበር እርግጠኛ ለመሆን ፈለገ ፡፤

አናሲሞስ (ቁጥር 9) ቀድሞ አገልጋይ የነበር ከጌታዉ ሮጦ ከጳዉሎስ ጋር በመገናኘት የዳነ ነበር ፤ ጳዉሎስ አናሲሞስን ከተቆጣጣሪዉ ከቲኪቆስ ጋር በመላክ ጳዉሎስ በሚገባ የሚመለከት እንዲሆን ፈለገው (ፊል 10-12, 17-19) ፡፡

አርስጥሮኮስ (ቁጥር 10) በአንዳንድ በጳዉሎስ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ዉስጥ አብሮት ነበር - በአመፅ፣ በእስራቱ፣ መርከቡ በተሰበርች ጊዜ በእነዚህ ሁሉ ነገሮች ከጳዉሎስ ጋር ተቀመጠ ፡፡ ጳዉሎስ አርስጥሮኮስን ብዙ ነገሮችን ታግስ ስለ ነበር እና አክብሮቶችን ስላገኘ በሚገባ እንዲሚለከታቸዉ ፈለገው ፡፡

ማርቆስ (ቁጥር 10) የማርቆስን ወንጌል ፅፏል በተጨማሪም በመጀመሪያዉ የአገልግሎት ጉዞ ላይ ጳዉሎስን ከበርናባስ ጋር አንድ ላይ በመሆን እንደ ረዳት አብሮት ነበር ፡፡ ማርቆስ ዮሐንስ በመጨረሻም እነርሱን በመተዉ ወደ ቤቱ በመሄድ ዝም አለ ፤ ጳዉሎስ በሁለተኛዉ ጉዞ ላይ ከበርናባስ ጋር ማርቆስ ዮሐንስን ለመዉሰድ እምቢ አለ ነገር ግን ቆይቶ ከእርሱ ጋር ታረቀ (2ጢሞ 4፡ 11) ፡፡ ማርቆስ እንደ ገና ታድሶ ከነበር በኋላ ማርቆስን በሚገባ መመልከት ፈለገ ፡፡

ኢዮስጦስ (ቁጥር 11) የህብረቱ ሰራተኛ እና ለጳዉሎስ አፅናኝ ነበር ፤ ጳዉሎስ በሚገባ የተመለከተ እንዲሆን ፈለገው ፡፡

ኤጳፍራ (ቁጥር 12-13) በቆላስይስ የነበረችዉ ቤተ ክርስቲያን መስራች ነበር (ቆላ 1፡ 7-8)፣ እና የክርስቶስ አገልጋይ ነበር (ቆላ 4፡ 12) ፡፡ ኤጳፍራ ጠንካራ ሰራተኛ እና የጳዉሎስ የፀሎት ጦረኛም ነበር ፤ የጳዉሎስ ክፍል ተጋሪም ነበር ፤ ጳዉሎስ በሚገባ እርሱን ለመመልከት ፈለገ ፡፡

ሉቃስ (ቁጥር 14) የሉቃስ ወንጌልን እና የሐዋሪያት ስራ መፅሀፍን ስፅፏል ፡፡ ወደ ኢየሩሳሌም እና ወደ ሮም ሲሄድ የጳዉሎስ የጉዞ ጓደኛ እና ታላቅ እረዳት እና አበረታች ነበር ፡፡ ሉቃስ በግሪካዊያን ዋጋ የሚሰጠዉ ነበር ምክንያቱም ሀኪም ስለ ነበር ፤ ጳዉሎስ በሚገባ እርሱን ለመመልከት ፈለገ ፡፡

ዴማስ (ቁጥር 14) በፊልሞን 24 እንደ ህብረት ሰራተኛ አብሮ ሰርቷል (ከማርቆስ፣ ከሉቃስ፣ እና አርስጥሮኮስ ጋር ) ነገር ግን በአለም ፍቅር በመዉደቅ ጳዉሎስን ተለይቶታል (2ጢሞ 4፡ 10) ፡፡ እርሱን ለመግለፅ ሌላ መግለጫ የተሰጠ ስላልነበር በጳዉሎስ ፊት ሞገስን ያጣ አስመስሎ ያደርገዋል ፡፡ ጳዉሎስ በሚገባ የታዬ እንዲሆን ፈለገ ፡፡

ቆላስይስ (4፡ 15-18)፡ በምዕራፍ 2 ጳዉሎስ በሎዶቂያ በፍፁም አማኝ አግኝቶ እንዳልነበር ነገር ግን ወደ እነርሱ ማስተማሩን እንደቀጠለ ገልፆአል (ቁጥር 15) ፡፡ ጳዉሎስ ለቆላስይስ የተላከዉ መልዕክት ሎዶቂያዊያንን እንዲያጋሩአቸዉ እና ለሎዶቂያዊያን የላከዉን መልዕክት ቆላስይሳዊያን እንዲያነቡት አዘዘ (ቁጥር 16) ፡፡ ይህ በመፅሀፍ ላይ ያልተፃፈ ከጳዉሎስ ሌላ መልዕክት እንዳለ ያመለክታል ፡፡ በመቀጠልም ጳዉሎስ ሩቅ ቢሆንም እንኳን አክሪጳን አበረታታ ምክንያትም የእግዚአብሄር መንግስት ሲያድግ የማየት ፍላጎት ስለ ነበረው እና በሚገባ ለማድረግ አማኝ ሰራተኞችን እንደሚወስድ ስለሚያውቅ (ቁጥር 17) ፡፡ ይህ የመሪነት እና የደቀ መዝሙርነት ታላቅ ምሳሌ ነው ፤ ለዚያም ነዉ አገልግሎትን ብቻችንን የማናደርገው ! ጳዉሎስ ቃሉ በእግዚአብሄር ፀጋ እንደሆነ አጠቃለለ ፡፡

መደምደሚያ

ጳዉሎስ ለቤተ ክርስቲያን፣ በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ለሚሰሩ እና ስለ ክርስቶስ ምክንያት ለሆኑት ፍቅር ነበረው ፡፡ ጳዉሎስ ይህን በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ እና በሰራተኞች ላይ በሚያስተምርበት በኩል አሳዬ በተጨማሪም ለእነርሱ ያለዉን አመለካከት ያለማቋረጥ በአገልግሎቱ አሳዬ ፡፡

ጥያቄዎች

  1. በቆላ (4፡ 5) በማስተዋል የመኖር ምሳሌዎች ምንድን ናቸው ?
  2. ንግግራችሁን እንዴት “ የከበረ እና በጨዉ የተቀመመ “ እንዴት ማድረግ ትችላላችሁ (ቆላ 4፡ 6) ? “ በጨዉ የተቀመመ “ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ምን ታስባላችሁ ? እነዚህን ንግግሮች በጨዉ ካልተቀመመ ንግግር ጋር እንዴት ታመጣጥኑታላችሁ ?
  3. በቆላስይስ 4 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Colossians 4:8–9

“I have sent him to you for this very purpose, so that you may know how we are and so that he may encourage your hearts. He is with Onesimus, a faithful and dearly loved brother, who is one of you. They will tell you about everything here.”

ጳውሎስ ይህንን መልዕክት ለቆላስያስ ቤተክርስቲያን ሲጽፍ ስለ ወንጌል እስር ላይ ሁኖ ነበር ፡፡ እርሱም በደብዳቤው መጨረሻ ላይ በወንጌል አብረውት ሰራተኛ የሆኑትን ብዙዎችን አንስቱዋል ፡፡ ጳውሎስ ብቻውን አልነበረም ፤ እምነታቸውን የሚያራምዱና እንደ ወንጌል አምባሳደር ስጦታቸውን የሚጠቀሙ ከጎኑ ብዙ ሰዎች ነበሩት ፡፡ ለምሳሌ ፡- ቲኪቆስ እና አናሲሞስ የአማኞችን ልብ ያጽናኑ ዘንድ ስለ እነ ጳውሎስ ወሬን ይዘው ተልከው ነበር ፡፡ የጳውሎስ ጓደኛ የሆነው ኤጳፍራም ስለ አማኞች በጸሎት መጋደሉን ቀጥሎ ነበር ፡፡ ጳውሎስ ለአማኞች አብዝቶ ይጨነቅ ነበርና በአገልግሎቱ ይረዱት ዘንድ ከእርሱ ጋር የሚመሳሰል አሳብ ያላቸውን ሰዎች በዙሪያው ሰብስቦ ነበር ፡፡

ጌታ በሰጣችሁ ጸጋ እንዴትም ይሁን የምታገልግሉት ነገር ግን ጥሪያችሁን ለመፈጸም ያግዙዋችሁ ዘንድ በዙሪያችሁ ሌሎችን ሰብስቡ ፡፡ በዙሪያችሁ ማንም ከሌላችሁ የሚያግዛችሁ ፣ የሚጸልይላችሁና የሚገስጻችሁን ሰው ይሰጣችሁ ዘንድ ጌታን ለምኑ ፡፡ ልክ ብረት ብረትን እንደሚስለው ሁሉ የራሳችሁን እምነት ታበረቱ ዘንድ እግዚአብሔር ከሌሎች ጋር እንድትሰሩ አድርጎ ነው የፈጠራችሁ ፡፡ በጸሎት ትጉ ደግሞም የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ለመናገር ስለ ተከፈቱ በሮች ምስጋናችሁን አታቋርጡ ፡፡

“ ወሬያችንን እንድታውቁና ልባችሁን እንዲያጽናና፥ ከእናንተ ከሆነውና ከታመነው ከተወደደውም ወንድም ከአናሲሞስ ጋር ወደ እናንተ የምልከው ስለዚህ ምክንያት ነው፤ የዚህን ስፍራ ወሬ ሁሉ ያስታውቁአችኋል ። “

  • ቆላስያስ 4፡8-9

ተጨማሪ ጥቅስ

ቆላስያስ 4:12–13 — “ ከእናንተ የሆነ የክርስቶስ ባሪያ ኤጳፍራ ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉ ተረድታችሁና ፍጹማን ሆናችሁ እንድትቆሙ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ በጸሎቱ ይጋደላል ። ስለ እናንተ በሎዶቅያም በኢያራ ከተማም ስላሉቱ እጅግ እንዲቀና እመሰክርለታለሁና ። “

1ኛ ጴጥሮስ 4:10 — “ ልዩ ልዩን የእግዚአብሔርን ጸጋ ደጋግ መጋቢዎች እንደ መሆናችሁ፥ እያንዳንዳችሁ የጸጋን ስጦታ እንደ ተቀበላችሁ መጠን በዚያው ጸጋ እርስ በርሳችሁ አገልግሉ ፡፡ “

3ኛ ዮሐንስ 1:8 — “ እንግዲህ ከእውነት ጋር አብረን እንድንሠራ እኛ እንዲህ ያሉትን በእንግድነት ልንቀበል ይገባናል ። “