The Danger Of Heresy
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Firstborn Colossians 3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ጳዉሎስ በምዕራፍ 2 ስላቀረበዉ አስተምሮ ተግባራዊ አተገባበር በቆላስይስ 3 መናገር ጀመረ ፤ በዚህ ት/ቤት ለምን እያደረግን ያለንበት ትልቅ አካል/ነገር ነው - ስለዚህ ከመፅሀፍ የተማርናቸዉን ነገሮች ተግባራዊ ማድረግ እንችላለን፡፡ በ 2ነገስት 22-23 ወደ ንጉስ ኢዮአስ መልሶ ይወስደኛል ፤ ኢዮአስ የጌታን ህግ በማግኘት እስራኤላዊያንን ወደ ህጉ ትምህርቶች መመለስ እንደሚያስፈልጋቸው ነገራቸው ፡፡ ህዝባችንን ቃሉ በሚለዉ በእምነት እንዲመላለሱ እየጠራን ነው ፤ እነዚህን ነገሮች በኑሮአችን ላይ መተግበር እንደምንችል ተስፋ አደርጋለሁ እፀልያለሁም ፡፡
ዋይርስቤ “ በጳዉሎስ ዘመን የነበሩ አምላክ የለሽ ኃይማኖቶች ስለ ግላዊ ስብዕና በጣም ትንሽ ወይም ምን እንዳላሉ አስተዉሉ ፡፡ አንድ አምላኪ በጣዖት ስር ሊደፋ መስዋዕቱን ሊያቀርብ ይችላል እንዲሁም ተመሳሳይ የቀድሞ የኃጢዓት ህይወት ይኖራሉ ፡፡ ሰዉ ከባህሪዉ ጋር ያመነዉ ነገር በቀጥታ ግንኙነት ካልነበረው ማንም ስለ እምነታቸው አይፈርድባቸው “ በማለት ፅፏል ፡፡ እንደ ክርስቲያን እምነታችን በራሳችን እንዴት እንደምንገልፅ ያብራራናል ፡፡
ያለፉት ምዕራፎች ሁሉም ነገር የተፈጠሩት ክፉ ነገርን በመዉረስ ነው ከሚለዉ የግሪክ ፍልስፍና የእምቢተኝነትን/የልክ ነኝ ባይነትን ስህተት ለማረም የተፃፉ ነበሩ ፡፡ “ መንፈሳዊ “ እዉነታዎች ብቻ መልካም ነበሩ ፤ ስለሆነም እግዚአብሄር አለምን እንደፈጠረ እንዲሁም ደግሞ ክርስቶስ በአካል እንደ መጣ አላመኑም ፡፡ ጳዉሎስ ይህን ክርስቶስ የሁሉም ፈጣሪ እና ድጋፍ እንደሆነ፣ የቤተ ክርስቲያን እና የስልጣናት ሁሉ የበላይ ራስ እንደሆነ በግልፅ አስተካከላቸው ፡፡
መንፈሳዊ ደካማነት ከሁለቱ በአንዱ መንገድ የሰዉን ስብዕና ይጎዳል፡
- ባለ መንፈሳዊ እዉቀት ሞልቃቃነት፡ ሰዉነት ክፉ እና መንፈስ መልካም ከሆነ በስጋ የተፈፀመ ምንም ነገር መንፈስን ሊጎዳ ይችላል ፤ ለሁሉም ስጋዊ ፍትወት ፍላጎት በመሰጠት በምንም ነገር ራሳቸዉን ይክዳሉ ፡፡ የእግዚአብሄር ፀጋ ስለነበራቸው በሰዉነታቸዉ ማድረግ የፈለጉትን ማንኛዉንም ነገር ማድረግ ችለዋል ፡፡ ዛሬ ያን እናያለን !
ኤስቴቲዝም / ራስን በኃይል የሚክዱት ሰዉነት መጥፎ ስለሆነ ሁሉንም ፍላጎት መካደ አለበት በማለት ምክንያት ያቀርባሉ ፡፡ ሰዉነትን መካድ መንፈስ ከፍ/ስለሚያሳድግ ፤ የጳዉሎስ ተቃራኒዎች በቆላስይስ ራሳቸዉን መናኛዎች/ከንቱዎች ነበሩ ፡፡ ጥብቅ የሆነዉ የአይሁድ ህግ ጥብቅ ከሆነ ራስን ከመካድ ኃይማኖታዊ ስርዓቶች ጋር ተያይዟል ፤ ጳዉሎስ እንደዚህ አይነቱ ኃይማኖታዊ ስርዓት ጥቅም አልባ እና መንፈሳዊ ዋጋ እንዳልነበረው አስጠነቀቀ (ቆላ 2፡ 20-23) ፡፡
በክርስቶስ አምላክነት ላይ ያላቸዉ ተቃዉሞ በኃሳባቸዉ/በተግባራቸዉ ዉስጥ ወይም ደግሞ ሰዉነታቸዉን በመጉዳት ዉስጥ ድነትን እንዲፈልጉ ይመራቸዋል ፤ ጳዉሎስ በቆላስይስ እየዳሰሰ/እያወራ ለነበረው ነገር መነሻ ሀሳብ ነው ፡፡ ጳዉሎስ ይህ ስለ ፍልስፍና፣ ስለ ህግ ወይም ስለ ስጋዊነት ሳይሆን ስለ ክርስቶስ እንደሆነ አጥብቆ ተናገረ ፡፡
ትምህርት
ቆላስይስ (3፡ 1-2)፡ በቁጥር 1 “ እንግዲህ “ የሚለዉ “ ይህ ከሆነ “ ማለት ነው ፡፡ ቆላስይሳዊያን ክርስቶስን ከማወቃቸዉ የተነሳ “ ከመሲሁ ጋር ተነስተዉ ስለ ነበር “ “ ከላይ የሆነወን ይፈልጋሉ “ (ቁጥር 1) ፡፡ ጳዉሎስ ቤተ ክርስቲያኗን ከክርስቶስ ጋር ካላቸዉ ግንኙነት የተነሳ ሰማያዉ በሆነ እዉነታዎች ላይ ሀሳባቸዉን እንዲያተኩር አበረታታቸው ፡፡ “ ፍቅራችሁን/ስሜታችሁ አስቀምጡ “ ለሚለዉ ቃል ጥቅም ላይ የዋለዉ ይህ የሚቀጥል ዉሳኔ እንደ ነበር አብራርቷል ፡፡
ቆላስይስ (3፡ 3-4)፡ ጳዉሎስ የቆላስይሳዊያን የቀድሞ ህይወት የሞተ እንደ ነበር አብራርቷል ፡፡ የመስቀሉ ስራ ቆላስይሳዊያንን ከኃጢዓት ይቅርታ ለማድረግ ብቻ አልነበረም ወደ ሰማይ መሄድም እንዲችሉም እንጂ ፤ የመስቀሉ ስራ አዲስ ፍጥረት በማድረግ ይኖሩበት ከነበረዉ መንገድ በተለዬ እንዲኖሩ አስገደዳቸው ፡፡ በክርስቶስ ካላቸዉ እምነት የተነሳ የቆላስይሳዊያን “ ህይወት በእግዚአብሄር ከክርስቶስ ጋር ተሰሯል “ (ቁጥር 3) ፡፡ ተሰዉሯል የሚለዉ ቃል አገባቡ/አተረጓጎሙ እግዚአብሄር ቀድሞ ያዘጋጀዉ እና የአሁን እዉነታነት/ገሃድነት የነበረዉ የሆነ ነገር ማለት ነበር ፤ አሁን ኢየሱስ “ ህይወታችሁ ነው “ (ቁጥር 4) ፡፡ ጳዉሎስ ይህን ኃሳብ በገላ (2፡ 19-20) “ እኔ ለእግዚአብሄር ሕያዉ ሆኜ እኖር ዘንድ በሕግ በኩል ሞቼ ነበርና ፡፡ ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ ፤ እኔም አሁን ሕያዉ ሁኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል ፤ አሁንም በስጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሄር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረዉ ነው “ በማለት አብራርቷል ፡፡ ቆላስይሳዊያን ክርስቶስ በእነርሱ ዉስጥ እንደሚኖር በተረዱ ጊዜ የሁል ጊዜ ኑሮአቸዉን እንዴት እንደሚኖሩ ጨዋታ ቀያሪ ይሆናል ፡፡ ኢየሱስ የአለም ብርኃን እንደ ነበር (ዮሐ 8፡ 2) እና ደቀ መዛሙርቱም የአለም ብርኃን እንደ ነበሩ ነገራቸው (ማቴ 5፡ 14) ፤ ሁለቱም እንዴት እዉነት ሊሆኑ ቻሉ ? ክርስቶስ በአማኞች ዉስጥ ስለሚያድር በዉስጣችን ባለዉ በክርስቶስ እዉነት ስንኖር ብርኃኑ በእኛ በኩል ማብራት ይችላል ፡፡ ብርኃን ለመሆን አንተጋም ከዚያ ይልቅ ብርሃኑ ብቻ በዉስጣችን እንዲበራ እንፍቀድ ፡፡
ጳዉሎስ ክርስቶስ አንድ ቀን “ እንደሚገለጥ “ ተናገረ ፤ አንድ ቀን ኢየሱስ በሙሉ ክብሩ ይታያል ፡፡ በተመሳሳይ መንገድ “ ከእርሱ ጋር በክብር እንገለጣለን “ (ቁጥር 4) ፡፡ ጳዉሎስ “ ለሌላ ነገር ለምን መኖር እንፈልጋለን ? ኢየሱስ እንዲኖረን ከምንፈልገው በላይ በጣም የሚበልጥ ነገርን ሰጥቶናል! “ እያለ የሚጠይቅ ይመስላል ፡፡
ቆላስይስ (3፡ 5-9)፡ የቆላስይስ ቤተ ክርስቲያን ከገጠማት የመንፈሳዊ እዉቀት ችግር የተነሳ ጳዉሎስ “ በአለማዊ ተፈጥሮ የእነርሱ የነበሩትን “ ተግባራት ዘረዘረ (ቁጥር 5) ፡፡ በቁጥር 5 ከተዘረዘሩት ተግባራት ዉስጥ አንድኛዉም የአማኝ ህይወት መገለጫ አልነበረም ፡፡ በአደረጓቸዉ ክስተቶች ጳዉሎስ እንዲመላለሱበት ኢየሱስ ለእነርሱ የተሸለ ነገር ስለ ነበረዉ ንስኃ እንዲገቡ እና በመፅኃፍ ቅዱሳዊ እምነት ለመኖር እንዲመለሱ ቆላስይሳዊያንን ጠራቸው ፡፡ ኤፌ (5፡ 3) አማኞች “ ለቅዱሳን እንደሚገባ ግን ዝሙትና ርኩሰትን ሁሉ ወይም መመኘትን በእናንተ ዘንድ ከቶ አይሰማ “ በማለት አስጠነቀቃቸው ፡፡
ቆላስይስ (3፡ 12-17)፡ ጳዉሎስ አንባቢዎቹን የቀድሞዉ ልምዳቸዉን እንዲተዉ ነገራቸው ፡፡ ክርስቶስ አማኞችን የሰጠዉ “ አዲሱ ሰው/ማንነት “ “ የፈጣሪዉን መልክ “ የተሸከመ ሲሆን አሮጌዉ ማንነት ደግሞ ስጋ ብቻ ነበር ፡፡ ይህ ለዉጥ “ በፈጣሪአቸዉ መልክ ላይ በተመሰረተ እዉቀት “ በኩል ሆኗል (ቁጥር 10) ፤ ኤፌ (1፡ 17) “ የክብር አባት የጌታችንም የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ “ ይላል ፡፡
ቆላስይስ (3፡ 12-17)፡ ጳዉሎስ የቀድሞዉ ልምድ በአዲሱ የሚቀየር እንደ ነበር ተናገረ ፡፡ “ እንደ እግዚአብሄር ምርጦች “ አማኞች ቅዱስ እና የተወደዱ ናቸው ፡፡ በተቀበሉት በድነት ብርኃን ቆላስይሳዊያን ከኢየሱስ ጋር ባላቸዉ ግንኙነት ይኖር ነበር ፡፡ በኢየሱስ ህይወት የታዩት ባህሪያት፡- ርህራሄ፣ ቸርነት፣ ትህትና፣ ደግነት፣ ትዕግስት፣ ይቅር ባይነት እና ፍቅር (ቁጥር 12-14) በኑሮአቸዉ ላይ ይታያሉ ፡፡ ፍቅር ክርስቶስን የመምሰል ከሁሉም የሚበልጠዉ መገለጫ የሚሆን ነበር ፡፡ እነዚህ ሁሉ ባህሪያት እንደ አማኝ ራሳቸዉን “ በጥበብ ሁሉ እርስ በእርስ ለመማር….. በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ በጸጋው በላባችዉ ለእግዚአብሄር ለመዘመር “ በሚሰጡት ላይ በራሳቸዉ ሰሩ (ቁጥር 16) ፡፡
የኔልሰን ማብራሪያ የእግዚአብሄር ሰላም “ ሙሉ ለሙሉ ለእግዚአብሄር ፈቃድ በምንማረክ እና ሙሉ እኛነታችን ለእርሱ በመታዘዝ አንድ በሆን ጊዜ በልባችን ላይ ያስተዳድራል “ ይላል ፡፡
መደምደሚያ
በድል እንድትመላለሱ እና ኢየሱስን በህይወታችሁ ላይ በማስቀመጥ ለመጠራታችሁ እንደሚገባ እንድትኖሩ እንደ ኢየሱስ ተከታዮች የሚያስፈልጋችሁ ሁሉም ነገር ተሰጥቷችኋል ፡፡ ወደ ቀድሞዉ/ወደ አሮጌዉ ማንነታችሁ መመለስ የለባችሁም ፡፡ በድል አድራጊነት በአዲሱ ማንነታችሁ መመላለስ ትችላላችሁ ፤ ክርስቶስ በሚገለጥ ጊዜ ሁሉም እንደሚገባ ይሆናል !
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Ephesians (Colorado Springs: David C. Cook, 1989), p. 133.
Earl Radmacher, Ronald B . Allen, H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 1999), p. 1566.
Nelson’s Commentary, p. 1567.
ጥያቄዎች
-
በቆላ (3፡ 5-9) ላይ አሰላስሉ ፡፡ በራሳችሁ ህይወት በዚያ ዝርዝር ላይ ንስኃ ልትገቡበት እና ልትተዉት የሚያስፈልጋችሁ ነገር አለ ? አዎ ከሆነ አሁን ትንሽ ደቂቃ በመዉሰድ ስለ ጉዳዩ ፀልዩ
-
ቆላ (3፡ 13) እግዚአብሄር ይቅር እንዳለን ይቅር ማለት አለብን ይናገራል ፡፡ በመፀለይ ይቅርታ ልታደርጉለት የሚያስፈልገዉ ሰዉ እንዳለ ጌታን ጠይቁ ፤ የሆነ ሰዉ ወደ አይምሯችሁ ከመጣ ይቅርታ ልታደርጉላቸዉ እንደመረጣችሁ በመፀለይ ጌታን ንገሩት ፡፡ ወደ አይምሮ ለሚመጡት ሁለ ይህ ይሰራል ፡፡
-
በቆላ (3፡ 18-19) ለባሎች እና ለሚስቶች የተለዬ ንግግር ተደርጓል ፤ በመፅሀፍ ላይ ሌላ የት ስፍራ ላይ ይህ ግንኙነት ተነግሯል ? (ኤፌ 5፡ 22-25)
-
በቆላስይስ 3 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Colossians 3:12–14
“Therefore, God’s chosen ones, holy and loved, put on heartfelt compassion, kindness, humility, gentleness, and patience, accepting one another and forgiving one another if anyone has a complaint against another. Just as the Lord has forgiven you, so you must also forgive. Above all, put on love—the perfect bond of unity.”
የእግዚአብሔር ልጆች ሆይ ፣ ተመርጣችኋል ፡፡ ተቀድሳችኋል ፡፡ ተወዳችኋል ፡፡ በቃ ይሄን ቶሎ እመኑ ተቀበሉ ፡፡ ዛሬ ለህይወታችሁ እነዚህን ተስፋዎች ተቀበሉ ፡፡ ለመጠራጠርም ሆነ ለመጠየቅ ምንም ምክንያት የላችሁም ፡፡ ጠላት በአሳባችሁ ውሸቶችን ሊያስገባ ይችላል ነገር ግን እነዚህን አሳቦች ምርኮኛ አድርጉ ፡፡ ዛሬ ይህንን ተቀበሉ ፡- ተመርጣችኋል ፤ ቅዱሳን ናችሁ ፤ ተወዳችኋል ፡፡
አሁን ግን በህይወታችሁ ከእነዚህ ተስፋዎች ጋር ስለምትመላለሱ ለሌሎች የክርስቶስን ፍቅር እንድትወክሉና ለእርሱ እጅና እግር የመሆን ኃላፊነት አለባችሁ ፡፡ ስለዚህም ርኅራኄን ፣ ቸርነትን ፣ትኅትናን ፣ የዋኅነት ፣ ትዕግስት እና ይቅር መባባልን ልበሱ ፡፡ እነዚህን ልክ እንደ ልብስ በየቀኑ ልበሱ ! ከእነዚህ ሁሉ ይልቅ ግን የፍጻሜ ማሰሪያ የሆነውን ፍቅርን ልበሱት ፡፡ ከሁሉም በላይ ፍቅርን ፡፡ ልክ እናንተ እንደተወደዳችሁ ሁሉ ሌሎችንም ውደዱ ፡፡ የክርስቶስን ፍቅር ያለ ዋጋ በስጦታ እንደተቀበላችሁ አስቡ ፡፡ ኢየሱስ እናንተን የተቀበላችሁ ልክ እንዲሁ እንዳላችሁ ነው ፤ እርሱ የወደዳችሁ በማይለወጥ ፍቅር ነው ፡፡ እርሱ ሌሎችን እንዴት መውደድ እንዳለባችሁ አሳይቷችኋል ፡፡ ዛሬ የገጠማችሁ ምንም ይሁን እናንተ ግን ፍቅርን ልበሱ ደግሞም እንደ ምርጦች ፣ እንደ ቅዱሳንና እንደተወደዱ የእግዚአብሔር ልጆች መመላለስን አትዘንጉ ፡፡
“ እንግዲህ እንደ እግዚአብሔር ምርጦች ቅዱሳን ሆናችሁ የተወደዳችሁም ሆናችሁ፥ ምሕረትን፥ ርኅራኄን፥ ቸርነትን፥ ትህትናን፥ የዋህነትን፥ ትዕግሥትን ልበሱ ፤ እርስ በርሳችሁ ትዕግሥትን አድርጉ፥ ማንም በባልንጀራው ላይ የሚነቅፈው ነገር ካለው፥ ይቅር ተባባሉ፤ ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉ ፤ በእነዚህም ሁሉ ላይ የፍጻሜ ማሰሪያ የሆነውን ፍቅርን ልበሱት ። “
- ቆላስያስ 3፡12-14
ተጨማሪ ጥቅስ
1ኛ ቆሮንቶስ 13:13 — “ እንዲህም ከሆነ፥ እምነት ተስፋ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው ። “
ኤፌሶን 2:8–9 — “ ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም ፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም ። “
1ኛ ዮሐንስ 5:2–3 — “ እግዚአብሔርን ስንወድ ትእዛዛቱንም ስናደርግ የእግዚአብሔርን ልጆች እንድንወድ በዚህ እናውቃለን ። ትእዛዛቱን ልንጠብቅ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነውና፤ ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።