Paul's Letters Colossians

The True Nature of Christ

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Firstborn Colossians 2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 549 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ዛሬ ወደ ቆላስይስ 2 ከመጓዛችን በፊት ወደ ቆላስይስ 1 መጨረሻ ላይ እንድንመለስ እፈልጋለሁ ፡፡ ጳዉሎስ እግዚአብሄር ኢየሱስ በኩር እንደሆነ የሚለዉን ዜና እንዲናገር ባላደራ አድርጎት ለነበረዉ አገልግሎቱ እየገለፀ ነበር (ቆላ 1፡ 26-27) ፡፡ የጳዉሎስ ስራ አይሁዶች እና አሕዛቦች በክርስቶስ አንድ እንደሆኑ ተገልጦ የነበረዉን “ ሚስጥር “ መናገር ነበር ፡፡ ሁሉም በክርስቶስ እንዲያድጉ እና የእርሱ መልክ እንዲኖራቸዉ ፈለገ (ቆላ 1፡ 28) ፡፡ ጳዉሎስ አድርጎት የነበረዉ በዉስጡ ባለዉ በክርስቶስ ኃይል የተነሳ እንደሆነ እዉቅና ሰጠ (ቆላ 1፡ 29) ፤ ሀሳቡም በምዕራፍ 2 ላይ ተደርጓል /ተገልፆአል ፡፡

ትምህርት

ቆላስይስ (2፡ 1-4)፡ ጳዉሎስ በአካል ሊያገኛቸዉ ስለማይችላቸው ተጋደለ/ቆሰለ (ቁጥር 1) ፡፡ የጠነከሩ እና በፍቅር የተሳሰሩ በመሆን መረዳታቸዉን በማረጋገጥ በክርስቶስ የእግዚአብሄር ሚስጥር እዉቀት እንዲኖራቸዉ ፈለገ (ቁጥር 2) ፡፡ ጳዉሎስ በክርስቶስ የተገኘዉ ሁሉም እዉቀት እና ጥበብ እንዲኖራቸዉ ፀለዬ (ቁጥር 3) ፤ ጳዉሎስ በእስር ቤት ስለ ነበር በፍፁም በቆላስይስ እና ሎዶቂያ የነበሩትን አላገኛቸዉም ነበር ነገር ግን ምርጥ ጓደኞቹ እንደነበሩ በማድረግ ለእነርሱ በትልቅ መነሳሳት ፀለዬላቸው ፡፡ በቁጥር 4 ለምን በትጋት እንደፀለየላቸው ገለፀ - ማንም በኃሰት ትምህርት በመምጣት አያታልሏቸዉም (“ በክርክር እንዳያሳምኗቸው “ ) ፡፡

ቆላስይስ (2፡ 5)፡ ዋይርስቤ ቁጥር 5-7 በክርስቶስ “ የፍጥረት እድገት “ በማለት ይገልፃል ፡፡ ጳዉሎስ አንባቢዎቹን በመንፈስ ከእነርሱ ጋር እንደ ነበር እና እያደረጉት ባለዉ ነገር እንደተደሰተ ነገራቸው ፤ በመቀጠልም መንፈሳዊ እድገትን ለመግለፅ ሰዎስት ስዕሎችን ሰጥቷል ፡፡ የመጀመሪያው በቁጥር 5 ማዘዝ እና መጠንከር በሚሉት ሁለት ቃላቶችች የሰራዊትን ስዕል ተጠቀመ ፡፡ ዋይርስቤ ስርዓትን “ እያንዳንዱን ወታደር በተገቢዉ ስፍራ በሰራዊት ደረጃ ቅደም ተከተል ማስቀመጥ “ እንደሆነ ሲገልፅ ብርታት ወይም ፅናትን ደግሞ “ ለጠላት ጠንካራ ግንባርን የሆነን የወታደር አሰላለፍን እንደሚወክርል “ ይገልፃል ፡፡ ወታደሮች ጠላትን ለመዋጋት በቅደም ተከተል በመቀመጥ እና ከፊት መስመር ላይ የተቀመጡ ነበር - አማኞች የሚያደርጉት የጳዉሎስ ስዕል ነበር ፡፡

ቆላስይስ (2፡ 6)፡ ጳዉሎስ በጉዞ ላይ የሚመላለሱን መንፈሳዊ ተጓዦችን ምስል ይጠቀማል ፤ መንፈሳዊ ጉዞ ትልቅ ጉዞ ሲሆን መንፈሳዊ ተጓዥ ደግሞ ጉዞዉን የሚያደርገዉ ነበር ፡፡ ጳዉሎስ አንባቢዎቹን ወደ እድገት በመንፈሳዊ እድገት ጉዞ ላይ “ እንዲመላለሱ “ አበረታቸው (ኤፌ 2፡ 2, 10, 4፡ 1, 5፡ 2, 8, 15) ፡፡

ቆላስይስ (2፡ 7)፡ እዚህ ላይ ጳዉሎስ ብዙ ስዕሎችን ይጠቀማል ፡፡ ስር መስደድ ከመሬት ጋር የጠለቀ እና ቋሚ የሆነ ግንኙነት ያለዉን አንድ ዛፍ ያመለክታል ፤ ማቋቋም ወይም መገንባት በእምነት መሰረት ላይ ስለ ተገነባ አንድ ህንፃ ይናገራል ፡፡ ተምራችሁት የነበረው በእምነት ተምራችኋቸዉ የነበረዉን ሁሉ ያመለክታል ፡፡ መትረፍረፍ / ሞልቶ መፍሰስ ዳርቻዎቹ ላይ ሞልቶ የሚፈስን ወንዝ ስዕል ያመለክታሉ (ሕዝቅኤል 47, ዮሐ 7፡ 37-39) ፡፡

ዋይርስቤ የእነዚህን ስዕሎች አስፈላጊነት “ መንፈሳዊ ስር (አንድ ክርስቲያን) በክርስቶስ ስር ከሰደደ ሌላ ምንም አይነት አፈር አይፈልግም ፤ ክርስቶስ እርግጠኛ መሰረቱ ከሆነ ለመንቀሳቀስ ሌላ አያስፈልገዉም ፡፡ በቃሉ እያጠናና እያደገ ከሆነ በቀላሉ በኃሰት አስተምሮ አያሳስብም ፤ እንዲሁም ልቡ በምስጋና እየተትረፈረፈ ከሆነ በክርስቶስ ካለዉ ሙሉነት መመለስ አያስብም ፤ ስር የሰደደ፣ ያደገ፣ ታላቅ/አመስጋኝ አማኝ ከትክክል ዉጪ የሚመራ አይሆንም “ ፡፡

ቆላስይስ (2፡ 8-10)፡ ጳዉሎስ አንባቢዎቹን በክርስቶስ ላይ የተመሰረቱ እንዲሆኑ እንጂ ፍልስፍና እና ወግ የሚጠቀሙትን በመከተል የተማረኩ እንዳይሆኑ አስጠነቀቃቸው (ቁጥር 8) ፡፡ የሚያታልሉ በመምጣት ከእምነት በማስገደድ “ ምርኮኝነት “ ስለሚወስዷችሁ አይኖቻችሁን በክርስቶስ ላይ አድርጉ ፡፡

መደምደሚያ

በትምህርቱም አለም እንኳን ጥበብን በመፈለግ እና ከክርስቶስ ጋር ያለን የግንኙነት ትኩረት የማጣት የሚይዝ አደጋ አለ ፤ በሪቫይቭ ት/ቤት ፍላጎታችን ያ ነው - በመፅሀፍ በሌሎች ኑሮ ላይ በደንብ በማፍሰስ / በማስተማር በእዉነቱ በክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ማድረግ ፡፡ በአሁኑ ጊዜ አለማችን የቆላስይስ ግልባጭ ሲሆን በክርስቶስ ላይ በማትኮር ተቀምጠን በእረሱ ዉስጥ በላዉ በእግዚአብሄር ተፈጥሮ ሙሉነት እንሳል (ቁጥር 9-10) ፡፡ ከዚህ ዉጪ ማንኛዉም ነገር ለእርሱ ወንጌል የኃሰት ትምህርት፣ ዉሸት/ማጭበርበር እና አደገኛ ነው ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Ephesians (Colorado Springs: David C. Cook, 1989), p. 124.

  2. Wiersbe, p. 124.

  3. Wiersbe, p. 125.

ጥያቄዎች

  1. በቆላስይስ 2 ጳዉሎስ መፅናት (ቆላ 2፡ 5)፣ ስር መስደድ እና መገንባት (ቆላ 2፡ 7)፣ በእምነት መመስረት (ቆላ 2፡ 7) እና በእርሱ ሙሉ መሆን (ቆላ 2፡ 10) የሚሉ ቃላትን ተጠቅሟል ፤ አላማዉ ምን እንደ ነበር ምን ታስባላችሁ ?
  2. በቆላ (2፡ 3) ጳዉሎስ ምንን እንደ መዝገብ አመለከተ/ጠቀሰ ? እነዚህ ነገሮች እንዴት መዝገብ ናቸዉ የትስ ሊገኙ ይችላሉ ?
  3. እነዚህ መዝገቦች በደንብ በተሰሩ ነገሮች/አፈ ታሪኮች የተሸድን እንዳንሆን እንዴት ይጠብቁናል ? (ቆላ 2፡ 8)
  4. ኃይማኖታዊ ትዕዛዛትን መከተል እና የሰዎች ትምህርትን በመከተል አስተዋይ ወይም መንፈሳዊነት መከሰቱ ጥቅሙ ነውን (ቆላ 2፡ 20-23) ? በመንፈስ ለመመላለስ ምንም ነገር ሳይኖራችሁ በመንፈሳዊነት የምትገለጡበትን መሰረት በማድረግ ዉሳኔ አድርጋችሁ ታውቃላችሁ ?
  5. ከክርስቶስ አካል አንፃር ምን እንክብካቤ እድገትን ያስተዋዉቃል ? (ኤፌ 2፡ 19-22, 4፡ 11-16, ቆላ 2፡ 19)
  6. በቆላስይስ 2 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Colossians 2:6–7

“Therefore, as you have received Christ Jesus the Lord, walk in Him, rooted and built up in Him and established in the faith, just as you were taught, overflowing with gratitude.”

ክርስቶስን ከተቀበላችሁ በኋላ ከእርሱ ጋር መመላለስ እንድሁም በወንጌሉ ምስጢር ማደግ ጀምራችኋል ፡፡ ልክ መምህር ፣ ሃኪም ወይም የውበት ባለሙያ ለመሆን እንደሚማር ተማሪ የተማራችሁትን ወደ ተግባር መቀየር የሚያስፈልግበት ጊዜ ደርሷል ፡፡ መማርን ፈጽማችሁ ስለማታቆሙ ስለዚህ አሁን የተማራችሁትን ወደ ተግባር የመቀየር ጊዜ ነው ፡፡ ክርስቶስን እንደ ጌታው እና እንደ አዳኙ እንደተቀበለ ሰው ጌታ እንደሚመራችሁ ደግሞም መንፈስ ቅዱስ በሁሉም ጥበብና እውቀት እንደሚሞላችሁ በማመን በእምነት ተመላለሱ ፡፡

አብልጣችሁ በክርስቶስ ኃይል ብርታት ስትመላለሱ ፣ የበለጠ በእርሱ ስር ትሰዳላችሁ ፡፡ ወጀብ ሊመጣ ይችላል ነገር ግን አይወስዳችሁም ፡፡ በኃይማኖትም ስለጸናችሁ አትናወጡም ፡፡ በእርሱ ስራችሁን ትሰድዱ ዘንድ በክርስቶስ መገኘት ውስጥ ኑሩ ፡፡ በምስጋና ደግሞም አዳኛችሁን ክርስቶስን በማገልገል መንፈስ ተመላለሱ ፡፡ ጌታን ስታመልኩ ከፊታችሁ ላለው ነገር በሚያስፈልጋችሁ ሁሉ ያግዛችሁ ዘንድ የክርስቶስ ሰላም ከእናንተ ጋር ይሆናል ፡፡

“ እንግዲህ ጌታን ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ተቀበላችሁት በእርሱ ተመላለሱ፤ ሥር ሰዳችሁ በእርሱ ታነጹ፥ እንደ ተማራችሁም በሃይማኖት ጽኑ፥ ምስጋናም ይብዛላችሁ ። “

  • ቆላስያስ 2፡6-7

ተጨማሪ ጥቅስ

ኤርምያስ 17:7–8 — “ በእግዚአብሔር የታመነ እምነቱም እግዚአብሔር የሆነ ሰው ቡሩክ ነው ። በውኃ አጠገብ እንደ ተተከለ ፥ በወንዝም ዳር ሥሩን እንደሚዘረጋ ሙቀትም ሲመጣ እንደማይፈራ ቅጠሉም እንደሚለመልም ፥ በድርቅ ዓመትም እንደማይሠጋ ፍሬውንም እንደማያቋርጥ ዛፍ ይሆናል ፡፡ “

ሮሜ 10:9–10 — “ ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና ፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና ፡፡ “

ቆላስያስ 2:2 — “ ልባቸው እንዲጸናና፥ በፍቅርም ተባብረው በማስተዋል ወደሚገኝበት ወደ መረዳት ባለ ጠግነት ሁሉ እንዲደርሱ የእግዚአብሔርንም ምሥጢር እርሱንም ክርስቶስን እንዲያውቁ እጋደላለሁ ፡፡ “