The Firstborn
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Firstborn Colossians 1 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ይኖሩባት በነበረዉ ከተማ በቆላስያ ተሰይመዉ ለነበሩት ለቆላስይስ በላከዉ መልዕክት ላይ የጳዉሎስን መልዕክት መመልከታችንን ቀጥለናል ፤ ጳዉሎስ ቆላስያን ያልጎበኘበት መልካም አድል አለው ፡፡ ይህ መልዕክት በቆላስያስ ለነበረች ቤተ ክርስቲያን እናአጠገቧ ለነበረች ጎረቤቷ ለሌዶቂያ ይነበብ የነበር (ቆላ 4፡ 16) ፡፡ ጳዉሎስ ቆላስይስ እና ፊልሞናን ከክርስቶስ ሞት 60-62 በኋላ በሮም እስረኛ በነበረ ጊዜ ፃፋቻ (ቆላ 4፡ 3, 10, 18, ፊልሞ 1, 9, 10, 23) ፡፡ ቆላስይስ እና ፊልሞና ተመሳሳይ ሰዎችን ጠቅሰዋል፡ ጳዉሎስ ሁለቱንም ሲያገለግል በዙሪያዉ የነበሩ ሰዎች ጢሞቲዎስን፣ ማርቆስን፣ ሉቃስን፣ ደማስን፣ አክርጳን፣ አናሲሞስን፣ አርስጥሮኮስ እና ኤጳፍራ ናቸው ፡፡
የቆላስይ ከተማ በአሁኗ ቱርክ የምትገኝ ነበረች ፤ ማክአርቱር “ ቆላስይስ የራዕይ 1-3 ሰባቱ አብያተ ክርስቲያን ክልል ከኤፌሶን በስተምስራቅ 100 ማይል ርቀት ላይ ትገኝ እንደ ነበር “ ፅፏል ፡፡ ከተማዋ በሸለቆና በተራራ በተከበበዉ ላክይ ወንዝ አጠገብ አርፋለች/የተቀመጠች ነች ፡፡ ቆላስይስ በአምስተኛዉ ክፍለ ዘመን ጥቁር ሱፍ እንደ አምራችነት እና አቅላሚነት በንግድ ዋና መስመር መገኛኛ ላይ እያደገች የነበረች ከተማ ነበረች ፡፡ በጳዉሎስ ዘመን አሕዛቦች በመጀመሪያ ደረጃ በሎዶቂያ ባለዉ ዋና መንገድ እና በዙሪያ ባሉ መኖሪያ ስፍራዎች የሰፈሩ ነበሩ ፤ ይህ ለማስታወስ አስፈላጊ ነዉ ምክንያቱም በአይሁዶች እና በአሕዛቦች የተቀላቀለ ህዝብ እዉነትን እንዲቃወሙ ለማስነሳት ታላቅ አድል ነበር ፡፡ በአዲስ በክርስትና ትምህርት የአይሁዶችን ህጋዊነት እና አምላክን በሚክዱ ፆም እና ፀሎት ለመቀላቀል ፈተና ይኖራል ፡፡
በቆላስይስ ያለችዉ ቤተ ክርስቲያን በኤፌሶን በጳዉሎስ በሰዎስተኛዉ የአገልግሎት ጊዜ ላይ የተጀመረች ነበረች ፡፡ ቤተ ክርስቲያኗ ጳዉሎስ በኤፌሶን እያስተማረ በነበረ ጊዜ ክርስቶስን ተቀብሎ በነበረው በኤጳፍራ እንጂ በጳዉሎስ የተመሰረተች አልነበረችም (ቆላ 1፡ 5-7) ፡፡ ቤተ ክርስቷና ከተመሰረተች ከብዙ አመታት በኋላ ቤተ ክርስታኗን የሚያስፈራ እዉነትን መካድ ተነስቷል ፤ በቤተ ክርስቷና ዉስጥ የተሰራጨዉ የእዉነት ክህደት “ እግዚአብሄር መልካም ነው ሁኔታ/ችግር ደግሞ ክፉ ሲሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእግዚአብሄር በተከታይነት የሚመጣ የሚመስል እንደ ነበርና ከእግዚአብሄር የሚያንስ እንደሆነ (እዉነተኛ ማንነቱን እንዲክዱ ሰዎችን የሚመራ ) ያም ሚስጥር ከመፅሀፍ በላይ የሆነ እዉቀት ለማስረዳት እና ለድነት አስፈላጊ የነበረ “ የግል መንፈሳዊ እምነት ነበር ፡፡
በቆላስይስ ያለች ቤተ ክርስቲያን በመሰረታዊ እምነታቸዉ ዉስጥ በአይሁዶች ህጋዊነት ተቋቁሟል ፡፡ ማክአርቱር ቆላስይሳዊያን “ ለድነት የመገረዝን አስፈላጊነት፣ የብሉይ ኪዳን ህግ ስርዓት አከባበረን (የአመጋገብ ህጎችን፣ በዓላትን እና ሰንበትን) እና ድርቅ ያሉ ስርዓቶችን “ ይዘዉ እንደ ነበር ፅፏል ፡፡ ቆላስይሳዊያን መለዓክትን እና ረቂቅ የሆነ የአምላክ ክስተትን አምልከዋል ፡፡ ኤጳፍራ የቆላስይስን ቤተ ክርስቲያን የመሰረተዉ አቅጣጫ ከጳዉሎስ ምክርን እና ትዕዛዝን በመፈለግ በመጓዙ ተሸፈነ ፤ ይህ የመታዘዝ እና የደቀ መዝሙርነት ትክክለኛ መልክ ነው ፡፡
ቆላስይስ ከኤፌሶን፣ ከፊልጵስዩስ እና ከፊልሞና ጋር የእስራት መልዕክት በመባል ተጠቅሰዋል ምክንያቱም ጳዉሎስ በሮም በእስራት እንደ ነበር ስለፃፋቸው ፡፡ ቆላስይስ ገጥሟቸዉ በነበረዉ ክህደት ላይ እንደ ማስጠንቀቂያነት የተፃፈ ነበር ፡፡ ኤጳፍራ መልዕክቱን አልመለሰም ይልቁንም አናሲሞስ መለሰው ፤ አናሲሞስ ወደ የቆላስይስ ቤተ ክርስቲያን አባል ወደ ነበረዉ አገልጋዩ ወደ ፊልሞና የተመለሰ የሚላክ አገልጋይ ነበር ፡፡
ሁልጊዜ ለእያንዳንዱ መፅሀፍ የምንጠቀምበት አንድ ቃል አለን ፤ ለቆላስይስ እየተጠቀምንበት ያለዉ አንድ ቃል በኩር የሚል ነው ፡፡
ትምህርት
ቆላስይስ (1፡ 1-14)፡ በመጀመሪያዎቹ 14 ቁጥሮች አላስተምርም ፡፡ የጳዉሎስ ሰላምታ በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ቁጥሮች ዉስጥ ነው ፤ በመቀጠልም በቁጥር (3-8) ጳዉሎስ ምስጋናዉን በመግለፅ ስለ ቤተ ክርስቲያን የሚያመሰግን ነበር ፡፡ በቁጥር (9-14) ጳዉሎስ አንድ ፀሎት ነበረው ፤ እነዚህ ቁጥሮች እንደ ማበረታቻ እና እንደ ማጠንከሪያ ቃል የሚያገለግል ነበር ፡፡ ከዚህ በመቀጠል በምዕራፉ በቀረዉ ክፍ ላይ እዉነትን ስለመካድ ወደ መድረስ መሻገር ይመጣል ፡፡
ቆላስይስ (1፡ 15-23)፡ እነዚህ ጥቅሶች ስለ ክርስቶስ አምላክነት ናቸው ፡፡ ቆላስይሳዊያን ኢየሱስ በእዉነት አምላክ እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ጠየቁ ፤ የግል መንፈሳዊነት የኢየሱስን አምላክነት እንደካደ አስታዉሱ ፤ ነገር ግን ኢየሱስ አምላክ ነው ፡፡ እዚህ ላይ ጥቅም ላይ የዋለዉ “ መልክ “ (ቁጥር 15) የሚለዉ ቃል ትርጉሙ በግሪክ ኮፒይ ወይም የሚመስል ማለት ነው ፡፡ ማክአርቱር “ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሄር ፍፁም መልክ - በትክክል የሚመስለዉ እና የእግዚአብሄር ቅርፅ ሲሆን (ዮሐ 1፡ 14, 14፡ 9, ፊል 2፡ 6) ከዘላለም የሆነም ነበር…. ጳዉሎስ ኢየሱስ የእግዚአብሄር መወከያ እና መግለጫ ሁለቱንም እንደሆነ ያብራራል ….. በሁሉም መንገድ ሙሉ ለሙሉ እግዚአብሄር ነው “ ፡፡
በቁጥር 15 ላይ ጥቅም ላይ የዋለዉን በኩር የሚለዉ ቃል ላይ እንድታተኩሩ እፈልጋለሁ ፡፡ ማክአርቱር “ በኩር ለሚለዉ የግሪክ ቃል በዘር ግንድ መጀመሪያ የተወለደን ሊያመለከት ይችላል ነገር ግን አብዛኛዉን ጊዜ በስልጣን ወይም በደረጃ ከሁሉም መብለጥን ያመለክታል “ በማለት ፅፏል ፡፡ በግሪክ እና በአይሁድ ባህል ጳዉሎስ “ በኩር “ ለሚለዉ እየፃፈ የነበረው መወለድን ቅደም ተከተል ሳይጠብቅ ዉርስ ተትቶለት ስለ ነበረዉ ልጅ ነበር ፡፡ ለምሳሌ የእስራኤል ሕዝብ “ እንደ መጀመሪያ “ ሕዝብ የሚታዩ ናቸው ፤ በመኖር የመጀመሪያዎቹ ህዝቦች ባይሆኑም በእግዚአብሄር የተመረጡ ህዝቦች ነበሩ (ዘጸ 4፡ 22, ኤር 3፡ 19) ፡፡
ማክአርቱር “ በዚህ አገላለፅ በኩር በብዙ ምክንያት በግልፅ መጀመሪያ የተፈጠረ ሳይሆን የሚበልጥ ደረጃ ያለዉ ማለት ነው ( መዝ 89፡ 27, ራዕ 1፡ 5)፡ 1) ክርስቶስ “ መጀመሪያ የተገኘ “ ወይም “ ብቻዉን የሚገኝ “ ሁለቱንም ሊሆን አይችልም (ዮሐ 1፡ 14, 18, 3፡ 16, 18, 1ዮሐ 4፡ 9) ፤ 2) በኩር የብዙ ከሆነ መደብ ዉስጥ የሆነ አንድ መደብ ነው (ቁጥር 18, ሮሜ 8፡ 29) ነገር ግን እዚህ ጋር ያለዉ “ ፍጥረት “ በነጠላ ቅርፅ ነው ፡፡ 3) ጳዉሎስ ክርስቶስ የተፈጠረ እንደሆነ እያስተማረ ከነበር ለመቃወም እየፃፈ ከነበረዉ እዉነትን ከካዱት ጋር እየተስማ ነበር ማለት ነው፡፡ 4) ለክርስቶስ ፍጥረት እና የሁሉም ነገር ፈጣሪ ሁለቱንም መሆን የማይቻል ነው (ቁጥር 16) ፡፡ ስለዚህም ኢየሱስ በኩር ነዉ ማለት በፍጥረት ሁሉ ላይ የመዉረስ የበላይ ስልጣን እና የባለቤትነት መብት አለዉ ማለት ነው (ዕብ 1፡ 2, ራዕ 5፡ 1-7, 13) “ በማለት ፅፏል ፡፡
መደምደሚያ
እግዚአብሄር አለምን በክርስቶስ ሰራ ፡፡ አምላክ ሰዉነቱን ለመስጠት በሰዉ ስጋ ዉስጥ ስለመጣ ይቅር ልንባል እንችላለን ፡፡ የዚህን ምዕራፍ ከላይ ከላይ ያለዉን ክፍል በትንሹም አከነዋል ፤ ይህ በብዙ ስለ ክርስቶስ እና ስለ አምላክነቱ የት ላይ ማጥናት መጀመር እንደምትችሉ ስዕልን ይስላል ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishing, 2005), p. 1729.
MacArthur, p. 1729.
MacArthur, p. 1729.
MacArthur, p. 1729.
MacArthur, p. 1729.
MacArthur, p. 1729.
MacArthur, p. 1730.
MacArthur, p. 1733.
MacArthur, p. 1733.
MacArthur, p. 1733.
MacArthur, p. 1733-34
ጥያቄዎች
-
በቆላ (1፡ 7-9) በቆላስይ ስለ ነበረችዉ ቤተ ክርስቲያን ከኤጳፍራ ለሰማዉ/ለተቀበለው ዜና የጳዉሎስ ምላሽ ምን ነበር ? በተለዬ ስለ እነርሱ በምን ፀለዬ ? (ቆላ 1፡ 9-12)
-
በቅዱሳን ርስት ተቃፋዮች እንድንሆን እግዚአብሄር እንዴት ብቁ አደረገን (ሮሜ 5፡ 8, ኤፌ 2፡ 8-9, ቆላ 1፡ 12) ? ክርስቶስ ብቻ የድነትን መስፈርት እንደሚያሟላ ረስታችሁ ታውቃላችሁ ? (ቆላ 2፡ 10)
-
ለሰዎች ክርስቶስ የማይታየዉ አምላክ/እግዚአብሄር መልክ እንደሆነ እንዴት ትገልፁላቸዋላችሁ (ዮሐ 14፡ 9, ቆላ 1፡ 15, 2፡ 9, ዕብ 1፡ 3) ? ወደ ክርስቶስ መልክ እንዴት እንሰራለን ? (ሮሜ 8፡ 29, 2ቆሮ 3፡ 18, ገላ 3፡ 27, ኤፌ 4፡ 22-24)
-
በቆላ (1፡ 21-22) በክርስቶስ ሞት ወደ እግዚአብሄር የቀረቡት እንዴት ይታረቃሉ ? በቆላ (1፡ 23) ጳዉሎስ “ በእምነት ስትቀጥሉ “ በሚለዉ ቃል ማስተማሩን ለምን እንደቀጠለ ምን ታስባላችሁ ?
-
በቆላስይስ 1 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Colossians 1:16–17
“For everything was created by Him, in heaven and on earth, the visible and the invisible, whether thrones or dominions or rulers or authorities—all things have been created through Him and for Him. He is before all things, and by Him all things hold together.”
በዚህ እውነት በደበዘዘበት ግራ በሚያጋባ ዓለም በደንብ ማስተዋል ይገባችኋል ፡፡ ምንድን ነው ትክክለኛው እውነት ? የምታምኑትን ለማጠንከርና ለማጽናት ወደ እግዚአብሔር ቃል ተመለሱ ፡፡ ጳውሎስ ለቆላስያስ ቤተክርስቲያን መልዕክቱን ሲጽፍ መሰረታዊ ወደሆነው ነገር ተመለሰ ፡፡ ጳውሎስ ክርስቶስ በፍጥረቱ ላይ የበላይ እንደሆነ አብራራ ምክንያቱም እርሱ ሁሉን ነገር ፈጥሮአልና ፡፡ አዎን ፣ እግዚአብሔር በሰማይ ያለውን በምድር ያለውን ነገር ሁሉ ደግሞም የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት ሁሉ እርሱ ፈጥሯል ፡፡ መዘንጋት የሌለባችሁ እውነት ፡- እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ፈጥሯል ፡፡
በህይወታችሁ ነገሮች የማይቻሉ ተስፋ የሚያስቆርጡ ሲሆኑባችሁ ፣ ከፍጥረት ሁሉ በኩር እንደሆናችሁ አስታውሱ ፡፡ ክርስቶስ ከሁሉ በፊት ነው ነገር ሁሉም በእርሱ ተጋጥሟል ፡፡ ክርስቶስ ሁሉንም ነገር አጋጥሞ ይዟል ፡፡ በችግሩ ውስጥ እርሱ አለ ፡፡ እርሱ በደስታም ውስጥ አለ ፡፡ ኢየሱስ ሁልጊዜ ሁሉንም ነገር አጋጥሞ ይዟል ፡፡ እርሱ ስለሚወዳችሁ ፣ ስለሚያስብላችሁ እናም ሁሉንም ነገር እርሱ ስለፈጠረ ሁሉንም ነገር አጋጥሞ ይዟል ፡፡ በህይወታችሁ ውስጥ እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር አጋጥሞ እንደያዘ ለማሰብ ለማሳየት ጥረት አድርጉ ፡፡ እግዚአብሔር ለህይወታችሁ በደንብ የሚያያይዝ ማጣበቂያ ሙጫ ደግሞም የእጅ ላስቲክ እንደሆነ እመኑ ፡፡ ለእናንተ ያለው ፍቅር አያልቅምና በህይወታችሁ ውስጥ ሁሉንም ነገር በአንድ ይዞ እርሱ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነው ፡፡
“የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ፤ ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል ፤ እርሱም ከሁሉ በፊት ነው ሁሉም በእርሱ ተጋጥሞአል ። “
- ቆላስያስ 1፡16-17
ተጨማሪ ጥቅስ
ዮሐንስ 1:2–3 — “ ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ ። ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም ። “
ሮሜ 8:28 — “ እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን ። “
ዕብራውያን 1:1–3 — “ ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ ፥ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን ፤ እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።