Everyday Reminders
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Exalted One Philippians 4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ይህ የፊልጵስዩስ መፅሀፍ የመጨረሻዉ ክፍል ነው ፡፡ ይህ በችግሮች ዉስጥ ላለች ቤተ ክርስቲያን የተፃፈ አልነበረም የማበረታቻ እና የማጠንከሪያ መልዕክት ነበር እንጂ ፡፡ ጳዉሎስ መልዕክቱን እንደ ጨረሰ መልካሙን ዜና ማሰራጨቱን ለመጠበቅ በማበረታታት መንደርደሪያን ሰራ ፡፡ በምዕራፍ 4 ለቤተ ክርስቲያን ብስለት አስፈላጊ የነበሩ ነገሮችን ጳዉሎስ ጥቂት የመጨረሻ የሁልጊዜ መሰረታዊ ማንቂያዎችን ሰጠ ፡፡
በአሁኑ አለማችን ላይ የሁል ጊዜ አስታዋሽ ስለሆኑ አንዳንድ ነገሮች አስቡ፡
- ሰራተኞች ወደ ስራ ከመመለሳቸዉ በፊት እጆቻቸዉን መታጠብ አለባቸው ፡፡
- እባክዎ እንስሳቶችን አይመግቡ ፡፡
- ጥንቃቄ - ትኩስ ቡና ፡፡
- ለመግባት ባዶ የመዋኛ ገንዳ - አይገባም/አይዋኝም ፡፡
- ስትወጡ እባክዎ መብራቱን ያጥፉት ፡፡
እነዚህን ነገሮች እናዉቃለን - የታወቁ/ግልፅ ናቸው ! ነገር ግን አሁንም ሰዎች እንድናስታዉሳቸዉ ያስፈልጋቸዋል ፡፡ ጳዉሎስ አንባቢዎቹን ለማስታወስ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ዝርዝርን ይዘረዝርላቸዋል ፡፡
ትምህርት
ፊልጵስዩስ (4፡ 1-2)፡ የጳዉሎስ ቃል “ የምወዳችሁ “ የሚል ነበር (ቁጥር 1) ፡፡ ጳዉሎስ በፊልጵስዩስያዊያን በማገልገል በዚያ ቤተ ክርስቲያንን በመገንባት አገዛቸው ፤ ወደ እነርሱ በመናገር ለማዳመጥ ፍቃደኛ እንዲሆኑ የፈቀደላቸው ከእነርሱ ጋር የረጅም ጊዜ ግንኙነት ነበረው ፡፡ ጳዉሎስ ሁሉም በአንድ ላይ ፈፅመዉት የነበረዉን ለማስታወስ ለእነርሱ እንደ “ ደስታዉ እና ክብሩ “ ጠቀሳቸው ፡፡ ጳዉሎስ እደርሳለሁ፣ ለመናገር፣ ለማዘዝ ወይም ለማስተማር በሁለቱ ሴቶች ኤዎድያንና ሲንጤኪንንም መካከል መለያየት ከመድረሱ በፊት “ እመክራለሁ “ የሚል ቃል ትርጉም ያለዉን ተጠቅሟል (ቁጥር 2) ፡፡ አለመስማማታቸዉ ምን እንደ ነበር አናዉቅም፣ ይህ ጳዉሎስ ስም የሰጠበት የመጀመሪያ ጊዜ ነው ፡፡ በመቀጠልም ጎን ባለመያዝ/ባለማዳላት በእኩል ትዕዛዝን ሰጠ ፤ የተጠቀመዉ ቋንቋ የረጋ ማሳሰቢያ ነበር ፡፡ በቁጥር 2 ጳዉሎስ እርስ በእርሳቸዉ በጌታ እንዲስማሙ ጠየቃቸው ፤ በመቀጠልም የመጀመሪያው የሁልጊዜ ማሳሰቢያው፡ በአካሉ ዉስጥ አንድነትን እንዲከታተሉ ፡፡ አለመስማማታቸዉ ከእጃቸው ከመዉጣቱ በፊት አንድነት እንዴት እንደሚጠበቅ ሴቶቹ ለመሪዎቹ ምሳሌ እንዲሆኑ ፈለገ ፡፡
ፊልጵስዩስ (4፡ 3)፡ ጳዉሎስ እንዲናገራቸዉ እና እንዲያበረታቸዉ ካስቻሉት ከቤተ ክርስቲያኑ መሪዎች ጋር የነበረዉን ግንኙነት ለማሳየት “ እዉነተኛ ጓደኛ “ የሚል ሀረግን ተጠቅሟል ፡፡ “ ሄይ አዛዡ አብረን የሰራንባቸዉን የቀድሞዉን መልካም ቀኖች ታስታዉሳለህ ? እነዚህን ሴቶች ለመርዳት ልትሄዱ ትችላላችሁ ? እያለ ነበር ፡፡ ሁለተኛዉ የሁል ጊዜ ማሳሰቢያው፡ መልካም ግንኙነት የእዉነተኛ ግንኙነት ምንዛሬዎች ናቸው ፡፡
ፊልጵስዩስ (4፡ 4)፡ ጳዉሎስ በጌታ ታላቅ ደስታን እንዲያሳዩ አዘዛቸው ፡፡ የሁል ጊዜ ማሳሰቢያ፡ የግብዣ ብቻዉን የሚታይ አትሁኑ ፤ በሌላ ቋንቋ በደስታ ክስተት ላይ ተስፋ የሚያስቆርጥ ነገር አታምጡ !
ፊልጵስዩስ (4፡ 5-6)፡ ምክንያታዊ በመሆን ብስጭት/ጭንቀት እንዲገዛችሁ አትፍቀዱ ፡፡ ጭንቀት በጊዜዉ ምክንታዊ አለመሆንን አያመነጭምን ? ተጨንቃችሁ ታዉቁ ከሆነ ወይም በተጨነቀ ሰዉ ዙሪያ ሆናችሁ ታዉቁ ከሆነ ያ ጭንቀት ዉሳኔን ትክክል እንዳይሆን ሊያደርገዉ እንደሚችል ታውቃላችሁ ፡፡ በጭንቀት አዉድ ምክንያታዊ አለመሆን ማርከሻ እንደሆነ አምናለሁ ፤ የሁል ጊዜ ማሳሰቢያ፡ የተረጋጋችሁ፣ የፀናችሁ እና በፀሎት የተዘጋጃችሁ ሁኑ፡፡
ፊልጵስዩስ (4፡ 7)፡ ይህ የሁልጊዜ ማሳሰቢያ እግዚአብሄር በሰላመ እንዲቆጣጠራችሁ ይፈቅድለታል ፡፡
ፊልጵስዮስ (4፡ 8)፡ ጳዉሎስ ፊልጵስዩስያዊያንን እዉነት በሆነዉ ነገር፣ የተከበረ በሆነዉ ነገር፣ ጭምተኝነት በሆነዉ ነገር፣ ንፁህ በሆነዉ ነገር፣ ፍቅር በሆነዉ ነገር፣ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር፣ በጎነት በሆነዉ ነገር እና ምስጋና በሆነዉ ነገር እንዲኖሩ ነገራቸው ፡፡ የሁል ጊዜ ማሳሰቢያው፡ ትክክል የሆነዉን ነገር አድርጉ ፤ ስለ ጌታ በምታዉቁት እና እዉት በሆነዉ ነገር ተቀመጡ ፡፡
ፊልጵስዩስ (4፡ 9)፡ ጳዉሎስ ተምረዋቸዉ የነበሩትን ነገሮች እንዲተገብሯቸዉ ነገራቸዉ ምክንያቱም ምን ማድረግ እንዳለባቸዉ ይህን የማሳሰቢያ ዝርዝር ሰጥቶአቸዉ ስለ ነበር ፡፡ ማሳሰቢያ፡ ትክክል የሆነዉን ነገር አድርጉ ፡፡ ጳዉሎስ ያሳሰባቸዉ ሁሉም ነገር አላማ የነበረዉ እና ከማሳሰቢያዉ ጋር የሚገናኝ ታላቅ ትርጉም ነበረው ፡፡
ፊልጵስዩስ (4፡ 10-20)፡ ጳዉሎስ ፊልጵስዩሳዊያንን በግልፅ ሳይጠይቃቸዉ በተለዬ ገንዘብ ስለላኩለት አመሰገናቸው ፡፡ ይህን ሲፅፍ የተሰማዉን የመሪነቱን ስሜት እና ማረጋገጫዎች አስቡ ፤ በብዙ ጉዞዎች በደንብ አስተምሯቸዉ የነበሩት ሰዎች ባስቀመጠላቸዉ በመኖር አሁን ደግሞ መልሰዉ ወደ እርሱ ህይወት እያፈሰሱ ነበር ፤ ይህ ጳዉሎስን ለመባረክ እና ስላገለገላቸዉ ለማመስገን እድሎችን የሚመለከቱ ይመስላል ፡፡ ጳዉሎስ በዙሪያዉ ያሉትን ሰዎች በዘሩት ፍሬ የተባረኩ እንዲሆኑ ፈለገ ፡፡
መደምደሚያ
እግዚአብሄር አገልግሎትን ለማድረግ የሚያስፈልገዉን ያውቃል ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ለተቀባዩ ትክክለኛ ፍላጎት የበረዉን ብቻ ለማግኘት ማን እና ምን ያክል እንድንባርክ በኃሳባችን ዉስጥ ያስቀምጣል ፡፡ ጳዉሎስ ይህን መልዕክት ለፊልጵስዩስ እነርሱን በሚያበረታታ መንገድ እና በአገልግሎት መንገድ ላይ በመሄዳቸዉ ሊያመሰግናቸዉ ፃፈው ፡፡
ጥያቄዎች
-
በዚህ በምድር ላይ ጳዉሎስ ደስታዉን ከየት አገኘው ? (1ተሰ 2፡ 19-20, 3፡ 9)
-
በሁሉም ሁኔታዎች እና ችግሮች መካከል ክርስቲያኖች ምን ያደርጋሉ ? (ዮሐ 16፡ 33, ያዕ 1፡ 2-4)
-
ለመበሳጨት ትልቁ ርካሽ ነገር ምንድን ነው (መዝ 1፡ 2, ማቴ 6፡ 26-33) ? በሁሉም ጭንቀቶቻችን እና ብስጭቶቻችን እግዚአብሄርን መታመን ምንድን ነዉ ዉጤቱ ? (ኢሳ 26፡ 3)
-
ጳዉሎስ እንደ ጠቀሰዉ ክርስቲያኞች ማሰብ ያለባቸዉ ነገሮች ምንድን ናቸው ? እዉነት በሆነዉ በማንኛዉም ነገር ላይ ማሰብ ማለት ምን ማለት ነው ? (ዮሐ 16፡ 13, 17፡ 17, ኤፌ 4፡ 20-21, 2ጢሞ 2፡ 25)
-
ከፊል (4፡ 13) ኋላ ያለዉ አዉድ/ትርጉም ምንድን ነው ? ሁሉንም ነገር ጳዉሎስ እንዴት ማድረግ ችሎ ነበር (2ቆሮ 12፡ 10, ገላ 2፡ 20, ኤፌ 3፡ 16-20) ? ያ ለእኛም ይሰራል ? ለምን ?
-
ጳዉሎስ እግዚአብሄር ፊልጵስዩሳዊያንን የሚያስፈልጋቸዉን ይሰጣቸዋል ለምን አለ (ምሳ 3፡ 9, ፊል 4፡ 18)? ያለ ጥርጥር እግዚአብሄር እንደ ነበር ስታዉቁ በጊዜ እናንተን ወይም ቤተ ክርስቲያናችሁን የሚያስፈልገዉን ሲሰጥ ገጥሟችኋል ያውቃል ?
-
በፊልጵስዩስ 4 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Philippians 4:6–7
“Don’t worry about anything, but in everything, through prayer and petition with thanksgiving, let your requests be made known to God. And the peace of God, which surpasses every thought, will guard your hearts and minds in Christ Jesus.”
ሰላም የሚገኘው ከኢየሱስ ነው ፡፡ ሰላምን በመላው አለም መፈለግ ትችላላችሁ ነገር ግን የኢሱስ ሰላም ብቻ ነው እርካታን የሚሰጠው ፡፡ ጳውሎስ ፡- “ በጸሎት ከምስጋና ጋር ልመናችሁን ለእግዚአብሔር አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ “ ይላል ፡፡ ከዚያም እግዚአብሔርን ማክበርና ማመስገን ጀምሩ ፡፡ ከዚህ የትህትና ፣ ራስን አሳልፎ የመስጠትና የአመስጋኝነት ቦታ ነው የሰላም አምላክ የሆነው እግዚአብሔር በእናንተ ላይ የሚመጣው ፡፡ ይህ ፎርሙላ ነውን ? አይደለም ፡፡ ህግ ነውን ? አይደለም ፡፡ ይህ ተስፋ ነው ፡፡ ጳውሎስ ፡- “ከእኔ የተማራችሁትንና የተቀበላችሁትን የሰማችሁትንም ያያችሁትንም እነዚህን አድርጉ፤ የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል “ ይላል ፡፡
እያንዳንዱ ቀን የራሱ ጭንቀት አለው ፤ “ አንዲህ ቢሆንስ “ ደግሞም “ እኔ አላውቅም “ የምንለው የህይወት ገጽታ ፡፡ ነገር ግን አስታውሱ ከጭንቀት የሚገኝ ምንም በጎ ነገር የለም ፡፡ አዎን ፣ ስለዚህ መጨነቅ አቁሙ ፡፡ ልመናችሁን ለእግዚአብሔር አስታውቁ ፡፡ ከዚያም አመስግኑ ፡፡ አሳባችሁን እውነት በሆነው ፣ ጭምትነት ባለበት ፣ ጽድቅ በሆነው ፣ ንጹህ በሆነው ፣ ፍቅር ባለበት ፣ መታዘዝ ባለበትና ልክ በሆነው ነገር ላይ አድርጉ ፡፡ ስለሚያስጨንቋችሁን ተራ ነገሮች በማሳብ ጊዜያችሁን አታጥፉ ! ፍቅር ስላለበትና እውነት ስለሆነው ስታስቡ ፣ የኢየሱስ ሰላም በእናንተ ላይ ይመጣል ፡፡ ዛሬ ይህንን አድርጉትና ኢየሱስ አሳባችሁንና ልባችሁን ሲለውጥ ተመልከቱ ፡፡
“ ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ ። አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል ። “
- ፊልጵስዩስ 4፡6-7
ተጨማሪ ጥቅስ
ማቴዎስ 6:34 — “ ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል ። “
ኤፌሶን 5:20 — “ ሁልጊዜ ስለ ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አምላካችንንና አባታችንን ስለ ሁሉ አመስግኑ ። “
ፊልጵስዩስ 4:8–9 — “ በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ ፤ ከእኔ የተማራችሁትንና የተቀበላችሁትን የሰማችሁትንም ያያችሁትንም እነዚህን አድርጉ፤ የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።