Paul's Letters Philippians

Reaching For The Goal

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Exalted One Philippians 3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 546 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ለፊልጵስዮስ መፅኀፍ አንድ ቃላችን ወይ ዓረፍተ ነገራችን የሚበልጠዉ/ከፍ ከፍ ያለዉ የሚል ነው ፡፡ በምዕርፍ 3 ጳዉሎስ ወደ ፊልጵስዩስ የእግዚአብሄርን ፍቃድ እንዲያደርጉ መናገሩን ቀጠለ ፤ ዋይርስቤ ምዕራፍ ሰዎስትን ወደ ሰዎስት ክፍል ይከፍለዋል፡ የጳዉሎስ ትላንት/ቀድሞ (ቁጥር 1-11)፣ የጳዉሎስ አሁን (ቁጥር 12-16) እና የጳዉሎስ ወደፊት (ቁጥር 17-21) ፡፡

ትምህርት

ፊልጵስዩስ (3፡ 1-11)፡ ዋይርስቤ የኃላዉን/ቀድሞዉን በመመለከት ጳዉሎስን አዲስ ዋጋ በሆነዉ ዉጤት እንደ “ ሒሳብ ሰራተኛ “ ይገልፀዋል ፡፡ ጳዉሎስ ስለ እነርሱ በማሰብ እየፃፈ እንደ ነበር ይገልፃል - ሊጠብቃቸው (ቁጥር 1) ፤ ትኩረቱ/አሳቡ እምነትን እና ስራን በአንድ ላይ ወደ አንድ ክርስቲያናዊ ባህሪይ ስለቀላቀሉት አይሁድ አስተማሪዎች ነበር (ቁጥር 2) ፡፡ ጳዉሎስ ስለ እነርሱ ሰዎስት ቃላትን ተጠቅሟል ፤ የመጀመሪያው ጳዉሎስ “ ዉሾች” ብሎ ጠራቸዉ አይሁዶች ለአሕዛብ የሚጠቀሙበት ተመሳሳይ ቃል ፤ “ ዉሾች “ የሚለዉን ቃል በመጠቀም ጳዉሎስ “ እነዚህን ኃሰተኛ አስተማሪዎችን ለመልካም ሰዎች የተናቁ ከሆኖ ቆሻሻ ጥንብ አንሳዎች ጋር እያወዳደረ ነበር “ ፡፡ ዋይርስቤ እነዚህን ኃሰተኛ አስተማሪዎች “ በጳዉሎስ ተረከዝ ላይ በመፍጠን ከስፍራ ስፍራ እርሱን በመከተል የኃሰት ትምህርታቸዉን ያጮኻሉ “ በማለት ይገልፃቸዋል ፡፡ ሁለተኛው ጳዉሎስ “ በተለዬ በስራ ህግ ኃጢዓተኞች በስራና በእምነት ይድናሉ ብለዉ የሚያስተምሩትን “ “ ክፉ ሰራተኞች “ በማለት ጠራቸው ፤ ጳዉሎስ መልካም ስራቸው ክርስቶስ ካደረገዉ ይልቅ ሰራተኞች ባደረጉት ላይ ማብራሪያን ስለሚያስቀምጥ ስራቸው በእዉነት ክፉ እንደነበር ይገልፃል ፡፡ በመጨረሻም ጳዉሎስ “ ስጋን የሚገርዙ “ በማለት ጠራቸው ፡፡ የኢየሱስ በመስቀል ላይ መሞት የአካላዊ ግርዛትን ወደ መንፈሳዊ ግርዛት ቀይሮት ሳለ የአይሁድ አስተማሪዎች መገረዝ ለድነት ያስፈልጋል በማለት አስተምረዋል ፡፡ ዋይርስቤ በአይሁድ አስተማሪዎች ያሉ ችግሮችን “ መፅሀፍ ቅዱስ ስለ ስጋ ምንም መልካም ነገር አያወራም ይሁን እንጂ በአሁኑ ጊዜ ብዙ ሰዎች በአጠቃላይ እግዚአብሄርን ለማስደሰት ማድረግ የሚችሉት ሁሉ ላይ የተደገፈ ነው ፤ በምድር ላይ ስጋ የእግዚአብሄርን መንገድ ያበላሻል ፤ መንፈሳዊ ህይወት ትኩረት እስከሆነ ድረስ ምንም ትርፍ የለዉም ፤ በዉስጡም ምንም መልካም ነገር የለዉም ፤ ምንም የሚያስደንቅ ነገር በስጋ ላይ በመታመን አናስቀምጥም ! “ በማለት ያጠቃልላል ፡፡

ጳዉሎስ “ እኛ “ (አማኞች) “ የተገረዝን “ ስለሆንን በአካላዊ መገረዝ ላይ እምነትን ወይም ልበ ሙሉነትን እንደማናስቀምጥ ይገልፃል (ቁጥር 3) ፡፡ ጳዉሎስ አንዴ በመገረዙ የተደገፈ ስለ ነበርና እንደ አይሁድ ከእግዚአብሄር የሆነ መሆን መብቱ እንደ ነበር መግለፁን ቀጠለ (ቁጥር 4-6) ፡፡ አንድ ጊዜ ጳዉሎስ በህግ ስር በነበረዉ ብቃት መታበይ ችሏል ፡፡ ዋይርስቤ “ በኃይማኖት ላይ የሚደገፉ ሰዎች አብዛኛዉን ጊዜ በአደረጉት ነገር ይታበያሉ ፤ እዉነተኛ ክርስቲያን ለመታበይ/ለመመከታ ምንም ነገር አይኖረዉም ፡፡ መመካቱ በክርስቶስ ብቻ ነው !” በማለት ይናገራል ፡፡ ጳዉሎስ እዉነተኛ አይሁድ ነበር፣ አሁን ደግሞ ሙሉ ክርስቲያን እና በአዲስ መስፈረት የኖረ ነበር ፡፡ ዋይርስቤ በጳዉሎስ ላይ ይህን ለዉጥ “ በራሱ ላይ እና በሌሎች ላይ በተመለከተ ጊዜ የጢሮሱ ሳዉል ፃድቅ እንደሚሆን ራሱን ተመለከተ ፤ ነገር ግን ራሱን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በማወዳደር አዬ ! ከዚያም በዚያ ለኢየሱስ ክርስቶስ ፅድቅ ግምገማዉን፣ ዋጋዉን እና የፅድቅ ስራዎችን በመተዉ ተቀየረ ! “ በማለት ይገልፃል ፡፡

በመቀጠልም ጳዉሎስ በመንፈሳዊ መገረዝ ዉስጥ አግኝቶት የነበረዉን ነገር ሁሉ አጋራቸው ፡፡ መጀመሪያ ጳዉሎስ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስ የሚበልጥ/የላቀ ዋጋን ማወቅን ተቀብሎ ነበር - ከክርስቶስ ጋር ግላዊ ግንኙነትን አግኝቶ ነበር (ቁጥር 8) ፤ ሁለተኛው ጳዉሎስ ኢየሱስ ክርስቶስን በመማመን ከተመሰረተ ፅድቅ ከእግዚአብሄር ፅድቅን ተቀብሎ ነበር (ቁጥር 9) ፡፡ ሰዎስተኛው አሁን ጳዉሎስ ከክርስቶስ ጋር ህብረት ነበረው (ቁጥር 10) ፡፡ ጳዉሎስ እነዚህን ነገሮች ለመቀበል ማድረግ የሚችለዉ ምንም ነገር አልነበረም፣ እንደ ፀጋ ስጦታ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀላለ የመጣ ነበር ፡፡ የጳዉሎስ ግብ “ እርሱን እና የትንሳኤዉን ኃይል ማወቅ ነበር ! “ ጳዉሎስ ስለ ኢየሱስ መከራን ለመቀበል ፍቃደኛ ነበር ምክንያትም በግል ስለሚያውቀው ፤ ልክ እንደ ሒሳብ አዋቂ ቀድሞ ከክርስቶስ ተቀብሏቸዉ የነበሩትን ሁሉንም ነገሮች ቆጠረ ፡፡

ፊልጵስዮስ (3፡ 12-16)፡ በእነዚህ ቁጥሮች ዋይርስቤ የጳዉሎስን መገኘት/መቅረብ “ አዲስ ኃይል “ እንዳለዉ “ አትሌት “ ይገልፀዋል ፡፡ ጳዉሎስ በመንፈሳዊ ነገር ሙሉ የመሆን ግቡን ላይ እንዳልደረሰ ነገር ግን በክርስቶስ ባለዉ በሁሉም ኃይሉ እዛ ግብ ላይ ለመድረስ እየሰራ እንደሆነ ይገልፃል (ቁጥር 12) ፤ ራሱን የመጨረሻ መስመሩ ላይ ለመድረስ እንደሚገፋ ሯጭ ይገልፃል (ቁጥር 13) ፡፡ ጳዉሎስ አንድ ግብ ስለ ነበረዉ ጊዜዉን በዚያ ግብ ላይ በማትኮር አሳለፈ - “ በክርስቶስ ኢየሱስ ከፍ ከፍ ያለዉን የእግዚአብሄር መጠራት “ (ቁጥር 14) ፤ ጳዉሎስ ፊልጵስዩሳዊያንን በተመሳሳይ መንገድ እንዲኖሩ አበረታታቸው (ቁጥር 15) ፡፡

ፊልጵስዩስ (3፡ 17-21)፡ በእነዚህ ጥቅሶች ዉስጥ ዋይርስቤ የጳዉሎስን ወደፊት “ አዲስ ራዕይ “ እንዳለዉ “ አዲስ ዜጋ “ ይገልፁታል ፡፡ ጳዉሎስ አንባቢዎቹን እንዲከተሉት እና እርሱን እንዲመስሉ አበረታታቸዉ እንጂ እንደ አይሁድ አስተማሪዎች እንዲሆኑ አይደለም (ቁጥር 18) ፡፡ ጳዉሎስ በቁጥር 19 ጠላት የሆኑ አስተማሪዎችን፡ “ መጨረሻቸው ጥፋት ነው ሆዳቸዉ አምላካቸዉ ነው ክብራቸው በነዉራቸው ነው አሳባቸው ምድራዊ ነው “ (ቁጥር 19) ፤ ነገር ግን እኛም እንደ አማኝ በሰማይ ዜጎች ነን ፡፡ ያን ዜግነት ለማሸነፍ አንሮጥም ምክንያቱም ይህ ቀድሞዉኑ የእኛ ስለሆነ ፤ ስለዚህም በምድር ላይ የምንኖር ነን ነገር ግን ቤታቸን በሰማይ ነው (ቁጥር 20) ፡፡

መደምደሚያ

ጳዉሎስ ከክርስቶስ የተነሳ ማን እንደ ነበር አብራራ፡

  • ጳዉሎስ በክርስቶስ ተቀባይነትን ያገኘ እንደ ነበር ያውቃል (ዮሐ 1፡ 12, 15፡ 15, ሮሜ 5፡ 1) ፡፡ ከክርስቶስ የተነሳ የተገፋ፣ ያልተወደደ፣ የቆሸሸ ወይም የሚያሳፍር የነበረዉን ዉሸቱን መተዉ ችሏል፣ እዉነታው በክርስቶስ ሙሉ ለሙሉ ተቀባይነት መሆኑ ነው ፡፡
  • ጳዉሎስ በክርስቶስ ደህንነት ተደርጎለት እንደ ነበር ያውቃል (ሮሜ 8፡ 1-2, 28, 33-34) ፤ ጥፋተኛ፣ ያልተጠበቀ፣ ብቸኛ ወይም የተተወ ነበር ከክርስቶስ የተነሳም ሙሉ ለሙሉ ደህንነቱ የተጠበቀ ነበር ፡፡
  • ጳዉሎስ በክርስቶስ አስፈላጊ እንደ ነበር ያውቃል (ማቴ 5፡ 13-14, ዮሐ 15፡ 5, 16, ሐዋ 1፡ 8) ፤ ዋጋ የሌለዉ፣ ብቁ ያልሆነ፣ ረዳት የሌለው ዉም ተስፋ የሌለዉ ነበር ከክርስቶስ የተነሳም አስፈላጊ ነበር ፡፡

እናንተም በክርስቶት ተቀባይነት ያገኛችሁ ናችሁ ፤ በክርስቶስ ደህንነታችሁ የተጠበቀ ነው ፤ እንዲሁም በክርስቶስ አስፈላጊዎች ናቸው ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Ephesians (Colorado Springs: David C. Cook, 1989), p. 83.

  2. Wiersbe, p. 83.

  3. Wiersbe, p. 84.

  4. Wiersbe, p. 84.

  5. Wiersbe, p. 84.

  6. Wiersbe, p. 85.

  7. Wiersbe, p. 85.

  8. Wiersbe, p. 86.

  9. Wiersbe, p. 83.

  10. Wiersbe, p. 83.

ጥያቄዎች

  1. በፊል (3፡ 2) ጳዉሎስ እንደ “ ዉሻ “ ማንን አመለከተ (ሐዋ 15፡ 1) ? የክፉ ሰራተኞች ትምህርቶች ምን ነበሩ? (ገላ 6፡ 12-13)
  2. ከማንኛዉም ሰዉ በላይ ስለ ስጋዉ እንዲመካ የሚፈቅድለት የጳዉሎስ ማስረጃዎች ምን ነበሩ ? ስለ እነዚህ ነገሮች የጳዉሎስ አመለካከት ኢየሱስን ባገኘዉ ጊዜ እንዴት ተቀየረ ?
  3. ክርስቲያኞች መታመናቸዉን ማስቀመጥ የሌለባቸዉ የት ላይ ነው ? መተማመናችሁን የት ላይ ማስቀመጥ አለባችሁ ? ከክርስቶስ በበለጠ መታመናችሁን ምን ወይም ማን ላይ ታስቀምጣላችሁ ?
  4. ክርስቶስን መከተል በመጀመሩ ጳዉሎስ ምን ጥቅሞችን አገኘ ?
  5. ጳዉሎስ ምን አንድ ነገርን ለማድረግ ፈለገ ? ይህ የአስተሳሰባችሁ መንገድ ነው ?
  6. እዉነተኛ ዜግነታችሁ የተወሰነዉ የት ነው ? በዚያ ስትሆኑ ምን ይፈጠራል ?
  7. በፊልጵስዩስ 3 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Philippians 3:10–11

“My goal is to know Him and the power of His resurrection and the fellowship of His sufferings, being conformed to His death, assuming that I will somehow reach the resurrection from among the dead.”

አለማ ያለህ ሰው ነህን ? ጳውሎስን ኢየሱስ ከለወጠው በኋላ የጳውሎስ ኑሮ ስለራሱ ማግኘትና ስኬት አልነበረም ፡፡ ጌታውን ኢየሱስ ክርስቶስን ከማወቅ ጋር ሲያነጻጽረው ሌላውን እንደ ጉዳት ቆጠረው ፡፡ ጳውሎስ የህይወት ዓላማው ፡- ኢየሱስን በግሉ ማወቅ ማግኘት ፣ የትንሳዔውን ኃይል ማወቅ ፣ ከክርስቶስ ጋር መከራን መቀበል ደግሞም ክርስቶስን በሞቱ እንኳ ሳይቀር መምሰል እንደሆነ በግልጽ አስቀምጧል ፡፡

በህይወት ስትኖር ይህ አለም በስራ ዘመንህ ለማሳካት የሆነ ግቦች እንድታስቀምጥ ሊያደርግህ ይችላል ልክ ፡- የሆነ አይነት የአኗኗር ዘይቤ እንድኖርህ ፣ ከቤተሰብህ ጋር ወደ ተለያዩ ቦታዎች እንድትጓዝ ወይም ደግሞ ጡረታ መውጣትም ለሆን ይችላል ፡፡ ሆኖም ግን ጳውሎስ አስረግጦ ይናገራል “ ከእነዚህ ሁሉ “ የትኛውም ነገር ለህይወቱ ረብ እንደሌለው ፡፡ ምንም እንኳ ክርስቶስን በፍጹም ማወቅ ማለት ስለርሱ መከራን መቀበል ፣ በየቀኑ ስለርሱ መሞት ወይም ደግሞ አካላዊ ሞትን መሞት ማለት ቢሆንም ፣ በጳውሎስ አሳብ ውስጥ የነበረው እንድ ነገር ግን ክርስቶስን በፍጹም ማወቅ ነበር ፡፡ ጳውሎስ የኢየሱስን የትንሳዔ ኃይል በየቀኑ መኖር ይፈልግ ነበር ፡፡ እርሱ ወደ ኋላ ዞሮ አያይም ነበር ይልቁንም በፊቱ ባለው ላይ ያተኩር ነበር ፡፡ ዛሬ ለህይወትህ ግብን ዓላማን ያሳይህ ዘንድ ጌታን ጠይቅ ፡፡ አይኖችህን በኢየሱስ ላይ ስታደርግ በአሳብህ ውስጥ የሚገኘው እንድ ነገር ምን ይሆን ? ያንን ነገር ጻፈው ፣ ልታየው በምትችለው ቦታ ላይም ለጥፈው ከዚያም ያን መፈጸም እንድትችል ጌታ እንድረዳህ ጸልይ ፡፡

“ እርሱንና የትንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ፥ በመከራውም እንድካፈል፥ ወደ ሙታንም ትንሣኤ ልደርስ ቢሆንልኝ፥ በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ ። “

  • ፊልጵስዩስ 3፡10-11

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 27:4 — “እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት እርስዋንም እሻለሁ፤ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፥ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ ። “

ማቴዎስ 6:33 — “ ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል ። “

ፊልጵስዩስ 3:13–14 — “ ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ገና እንዳልያዝሁት እቈጥራለሁ፤ ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ በኋላዬ ያለውን እየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ፥በክርስቶስ ኢየሱስ ከፍ ከፍ ያለውን የእግዚአብሔርን መጥራት ዋጋ እንዳገኝ ምልክትን እፈጥናለሁ ። “