Paul's Letters Philippians

Jesus' Incarnation

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Exalted One Philippians 2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 545 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በመፅሀፉ ዉስጥ ጌታን እንዴት እንደምናየው ለመወከል ለፊልጵስዩስ ቃላችን ከፊል (2፡ 9) የሚበልጥ/ከፍ ከፍ ያለዉ የሚል ነው ፡፡ ምዕራፍ 2 ለክርስቲያን አስፈላጊ መፅሀፍ እና ከኃሰተኛ ሀይማኖች ኋላ ይመጣል ፡፡

ትምህርት

ፊልጵስዩስ (2፡ 1-4)፡ ማክአርቱር የመጀመሪያዎቹን አራት ጥቅሶች እንደ ጳዉሎስ ጥሪ “ በትህትና አንድ እንዲሆኑ “ ያጠቃልላሉ ፤ ቁጥር 1 ይህ ምን እንደሚመስል መግለጫዎችን ይሰጣል፡ “ በክርስቶስ መበረታታትን “፣ “ በፍቅር መፅናትን “ በመንፈስ ህብረት ማድረግን “ እና “ ርህራሄና ምህረት “ ፤ “ የፍቅር መፅናት “ “ ጎን ለጎን/በአንድ ላይ በመምጣት እና በመረዳዳት መመካከር እና መተናነፅ “ በማለት መረዳት የሚቻል ሲሆን “ የጌታ ቀርቦ መምጣትን እና ረጋ ባለ የቃል ሹክሹክታ በአማኝ ጆሮ ዉስጥ ማስደሰትን ወይም መምከረን “ ያመለክታል ፡፡ “ ህብረት “ በዉስጥ በሚኖረዉ መንፈስ ቅዱስ የተሰጠን የጋራ የዘላለማዊ ህይወትን አጋርነትን “ ይገልፃል ፡፡ እነዚህ ንግግሮች “ ከሆነ “ ብለዉ መጀመራቸውን “ ስለዚህ “ ብሎ መረዳት የተሸለ ሊሆን ይችል ፡፡ በኑሮአቸዉ አማኞች እነዚህ ነገሮች ስለነበሯቸው ጳዉሎስ በዚህ ሲኖሩ ኑሮአቸዉ ምን እንደሚመስል ነገራቸው - እርስ በእርስ በሙሉ አንድነትና ትህትና እንደሚኖሩ (ቁጥር 2) ፤ ተመሳሳይ ነገርን ያስባሉ (ተመሳሳይ አሳቢ ይሆናሉ)፣ ክርስቶስ ለእነርሱ ያለዉን የሚመስል ፍቅር ይኖራቸዋል፣ ከሌሎች ጋር ተመሳሳይ ፍቅርን ይጋራሉ በተጨማሪም ተመሳሳይ ግብን ይጋራሉ (በአንድ አላማ ላይ ፍላጎት ይኖራቸዋል) ፡፡ እነዚህን ነገሮች በአንድነት ማሳካት የጳዉሎስን ደስታ ሙሉ ያደርገዋል ፡፡ አድን/የተዋሀዱ ስለነበሩ መጀመሪያን ያን አንድነት የሚሰብር ነገር ላይ ራሳቸዉን የሚያስቀምጥ ምንም ነገር እንዳያደርጉ አበረታታቸው (ቁጥር 3) ፤ ሌሎችን ከእነርሱ እንደ ተሻሉ/ይበልጥ አስፈላጊ አድርገዉ ይመለከታሉ (ቁጥር 3-4) ፡፡ ማክአርቱር “ የራስ ወዳድነት ፍላጎትን/ጉጉትን “ ወደ “ ተቃዋሚነት፣ ተፎካካሪነት፣ የአንድ ወገን ደጋፊነት ወደ ሚመራ “ እንደ “ ጠብ /ሁከት “ ይገለፃል፣ እንዲሁም “ ትዕቢተኝነትን “ እንደ “ የራስ ወዳድነት ፍላጎት ወደ ሆነ መነሳሳት የግልን ክብርን መከታተል የሚለዉን ያመለክታል “ ፡፡ “ ሌሎች ከእናንተ ይበልጥ አስፈላጊ እንደሆኑ መቁጠር/ማሰብ “ “መሰረታዊ የትህትና ትርጓሜ “ ነው ፡፡ የጳዉሎስ ትዕዛዝ የራሳችንን ፍላጎት አንመለከትም አንችልም ማለት አይደለም የራሳችንን በተመለከትንበት መጠን በማመጣጠን የሌሎችንም ፍላጎት በተመሳሳይ መመልከት ማለት ነዉ እንጂ ፡፡

ፊልጵስዩስ (2፡ 5-11)፡ በቁጥር 5 ጳዉሎስ ፊልጵስዩሲያዊያንን ክርስቶስ እንዳደረገዉ ኑሮአቸዉን የራስ ወዳድነት በሌለበት ትህትና እንዲኖሩ አበረታታቸው (ማቴ 11፡ 29, ዮሐ 13፡ 12-17) ፡፡ የቀድሞ ቤተ ክርስቲያን ቁጥር 6-11 እንደ ዝማሬ ዘምራዋለች ፡፡ ክርስቶስ በእግዚአብሄር መልክ ሲኖር (ቁጥር 6) ፤ ጳዉሎስ “ መሆን/ሳለ “ (ቁጥር 6) “ የሰዉን ተፈጥሮ ባህሪይ የሚያብራራ - በራሱ ምን ማለት እንደ ሆነ እና ራሱ ምን እንደ ሆነ “ የግሪክ ቃል ከመጠቀም ይልቅ ለሚለዉ ያልተለመደ ቃልን ተጠቀመ ፡፡ ኢየሱስ ቀድሞ፣ አሁን እና ወደ ፊት ከእግዚአብሄር ጋር አለ ፤ ነገር ግን ኢየሱስ “ እንደ ባሪያ በመሆን “ ያን ወደ ጎን በመተዉ ሰዉ ነበር ፡፡ አምላካዊዉን ባህሪይ ባዶ አደረገ (ሆን ብሎ)፣ የሰዉን ኃጢዓት በመዉሰድ (ያለምንም ኃጢዓት) በመስቀል ላይ ሞተ (አድርጎት ለነበረማዉ ምንም ነገር ሳይሆን አድርገነዉ ለነበረዉ ነገር) (ቁጥር 7-8) (ማቴ 27፡ 46, 2ቆሮ 8፡ 9, ቆላ 1፡ 22, ዕብ 2፡ 14, 17፣ 4፡ 15) ፡፡ ዮሐ (1፡ 1) ይህን የአምላክነትን ፅናት ይገልፃል፣ በቁጥር 14 “ ቃል ስጋ ሆነ “ የሚለዉ ንግግር በሰዉ አምሳል ለመሆን ራሱን ባዶ ማድረጉን ያሳያል ፡፡ ማክአርቱር በስነ መለኮት ኢየሱስ እንደ እግዚአብሄር ያለዉን ፍጥረቱን ባዶ አደረገ ማለት ምን ማለት ነው (ኬኖሲስ በሚለዉ ቃል ተወክሏል ) ፡፡

“ ይህ አምላክነትን ባዶ ማድረግ ወይም አምላክነትን ወደ ሰዉነት መቀየር ሳይሆን በራስ መተዉ ነበር ፤ ይሁን እንጂ ኢየሱስ በብዙ ስፍራዎች/ነገሮች ላይ መብቱን ተዉ ወይም ወደ ጎን አደረገ፡ 1) ሰማያዊ የሆነ ክብሩን - በምድር ላይ እያለ ከእግዚአብሄር ጋር ፊት ለፊት የነበረዉን ክብር እና የዚያን ክብር የማያቋርጥ ዉጫዊ እይታን እና ሰዋዉ ደስታን ተወ ፣ 2) በማንም ላይ ጥገኛ ያልሆነ ስልጣኑን - ስጋን በለበሰ ጊዜ ክርስቶስ ሙሉ ለሙሉ ራሱን ለአብ/ለአባቱ ፍቃድ አስገዛ፣ 3) መለኮታዊ መብቱን - የመለኮታዊ ባህሪዉን በፍቃዱ ማሳየትን ወደ ጎን በማስቀመጥ ለመንፈስ ምሪት ራሱን አስገዛ ፣ 4) ዘላለማዊ ብልፅግናዉን - በምድር ላይ ክርስቶስ ድሀ ነበር ያለዉም ጥቂት ነበር እና 5) ከእግዚአብሄር ጋር ያለዉን የሚመች ግንኙነት - በመስቀሉ ላይ እያለ ስለ ሰዉ ኃጢዓት የአብ/የአባቱ ቁጣ ተሰማው “ ፡፡

ዋይርስቤ በመፅሀፍ ላይ የክርስቶስ ባህሪይ የሌላቸዉን እና የክርስቶስ ተቃራኒ የሆኑትን ይገልፃል፡

  1. ሉሲፈር (ኢሳ 14፡ 12-15)፡ “ ለእግዚአብሄር ዙፋን ከቀረቡ መልዓክቶች አንዱ የሆነ ነበር ነገር ግን በእግዚአብሄር ዙፋን ላይ መሆን ፈለገ ፤ ሉሲፈር እኔ አለ ኢየሱስ ደግሞ እነርሱ አለ “ ፡፡
  2. አዳም (ዘፍ 3፡ 1-7)፡ “ ሉሲፈር በራሱ ተቃዋሚ በመሆኑ ባቻ አልረካም፣ ኤደን ገነትን በመዉረር ሰዉን ተቃዋሚ እንዲሆን ፈተነ ፤ አዳም የሚያስፈልገዉ ሁሉም ነገር ነበረው፣ በመሰረቱም በእግዚአብሄር ፍጥረቶች ላይ ንጉስም ነበር፣ ነገር ግን ሰይጣን እግዚአብሄርን ትመስላለህ አለው ! “

ዮሐንስ ሄነርይ ጆወት “ ምንም የማያስከፍል አገልግሎት ምንም አይፈፅምም “ አለ ፡፡ ሉሲፈር እና አዳም ሁለቱም ወደ ላይ ለመዝለል ፈለጉ ፡፡ ሉሲፈር ተመሳሳይ ነገር በማድረግ ኢየሱስን ለመፈተን ሞከረ ፤ ይሁን እንጂ ኢየሱስ ህይወቱን ስለ እኛ ሰጠ ፤ ሁሉንም ነገር አስከፈለው ፡፡

በቁጥር 9 እግዚአብሄር ኢየሱስን አድርጎት ስለ ነበረዉ ነገር ከፍ ከፍ በማድረግ በሰማይ፣ በምድር እና ከምድር በታች ካሉ ስሞች በላይ አስቀመጠው ፡፡ ሁሉም ሰው ክርስቶስን እንደ ጌታና አዳኝ የተቀበሉ ቢሆኑም ባይሆኑም በእርሱ ፊት በመደፋት ጌታ እንደሆነ ይናገራሉ (ቁጥር 10-11) ፡፡ ሁሉም ሰዉ “ በሰማይ ያሉትን መለዓክት (ራዕ 4፡ 2-9), የዳኑት መንፈሶች (ራዕ 4፡ 10-11), በምድር ላይ ያሉ ታዛዥ አማኞች (ሮሜ 10፡ 9)፣ በምድር ላይ የማይታዘዙት አመፀኞች (2ተሰ 1፡ 7-9)፣ ሰይጣን እና በሲዖል የጠፉት ሰዎችን (1ጴጥ 3፡ 18-22) “ ያካትታል ፡፡ ሁሉም ለክርስቶስ ይሰግዳሉ ፡፡

መደምደሚያ

ዋይርስቤ “ ሌላው በክርስቲያን መዝገበ ቃላት ላይ ቁልፍ ቃል ነው “ በማለት ያብራራል ፤ ፍሬ ነገሩ/ጭብጡ ከክርስቶስ ጋር ያለን ግንኙነት አንዱ ከሌላዉ ጋር እንዴት እንደሚኖር የሚወስን ነው፡

እርስ በእርስ የምንመራረጥ ነን (ሮሜ 12፡ 10) ፡፡

እርስ በእርስ እንበረታታለን (1ተሰ 5፡ 11) ፡፡

አንዳችን የሌላዉን ሸክም እንሸከማለን (ገላ 6፡ 2) ፡፡

እርስ በእርስ አንፈራረድም/አንወነጃጀልም (ሮሜ 14፡ 13) ፡፡

ሌሎችን የመዉደድ እና ቅድሚያ የመስጠት/ከፊት የማስቀመጥ አመለካከት የሚኖራችሁ የክርስቶስ አመለካከት በሚኖራችሁ ጊዜ ነው ፡፡ ክርስቶስ እኛን በመዉደድ ራሱን ባዶ ማድረጉን ስናንፀባርቅ ራሳችንንም ባዶ እንድናደርግ እፀልያለሁ ፤ በኑሮአችን ሌሎች የሚያዩት ብቸኛዉ ነገረ ክርስቶስ ይሆናል ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville, Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1715.

  2. MacArthur, p. 1715.

  3. MacArthur, p. 1715..

  4. MacArthur, p. 1715.

  5. MacArthur, p. 1715.

  6. MacArthur, p. 1715.

  7. MacArthur, p. 1716.

  8. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Ephesians (Colorado Springs: David C. Cook, 1989), p. 74.

  9. Wiersbe, p. 74.

  10. Wiersbe, p. 74.

  11. MacArthur, p. 1717.

  12. Wiersbe, p. 74.

ጥያቄዎች

  1. ኢየሱስ ክርስቶስ የነበረዉን አመለካከት በራሳችሁ ቃል ስታስቀምጡት እኛም አለን (ዮሐ 6፡ 38, 17፡ 5, ፊል 2፡ 3, 5-8) ፤ ከሌሎች ከሁሉም ክርስቶስን ከፍ ከፍ ያደረገዉ ማነው (ኤፌ 1፡ 20-22, ፊል 2፡ 9-11) ? ይህ ለእግዚአብሄር አብ እንዴት ክብርን ያሳያል ?
  2. ጳዉሎስ ፊልጵስዩስን የድነታቸዉን ስራ በፍራት እና በመንቀጥቀጥ መስራት እንዲቀጥሉ አበረታታቸው (ፊል 2፡ 12-13) ፤ ኤፌ (6፡ 5-6) ያ ምን እንደሚመስል እንድትረዱ እንዴት ይረዳችኋል ?
  3. ፊል (2፡ 14) እንዴት ያሳምናችኋል ወይም ይሞግታችኋል ? ይህን በምናደርግ ጊዜ ዉጤቱ ምንድን ነው ? (ፊል 2፡ 15-16)
  4. በፊል (2፡ 15) “ በአለም ላይ እንደ ከዋክብት ታበራላችሁ “ ማለት ምን ማለት ነው ? (ማቴ 5፡ 14-16, ዮሐ 8፡ 12, ኤፌ 5፡ 8, ቆላ 1፡ 13)
  5. “ ደስታ “ እና “ መደሰት “ የሚሉት ቃሎች በፊልጵስዩስ ዉስጥ በጳዉሎስ ብዙ ጊዜ የተጠቀሱ ናቸው(ደስታ - ፊል 1፡ 4, 25, 2፡ 2, 29, 4፡ 1) (መደሰት - ፊል 1፡ 18, 2፡ 17, 18, 28፣ 4፡ 4,10) ፤ ጳዉሎስ በደስታ እና መደሰት ላይ ህን ማብራሪያ ለምን እንዳስቀመጠ ምን ታስባላችሁ ? ደስታን እየኖርችሁበት ነዉ መደሰትንስ ያለሟቋረጥ እየተገበራችሁት ነዉ አይደለም ከሆነ ያን እንዴት ልትቀይሩት ትችላላችሁ ?
  6. በፊልጵስዮስ 2 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Philippians 2:3–5

“Do nothing out of rivalry or conceit, but in humility consider others as more important than yourselves. Everyone should look out not only for his own interests, but also for the interests of others.”

“ ከራሳችሁ ይልቅ ሌሎች እንደሚሻሉ ቁጠሩ ፡፡ “ እነዚህ በጳውሎስ የተነገሩት ንግግሮች በግልጽ ከባህል የሚቃረኑ ናቸው ፡፡ በዛሬው ጊዜ እያንዳንዱ ባህል የሚነግረን ፡- መጀመሪያ እኔ ፣ እኔ ትልቅ ፣ ለኔ ብዙ ፣ እኔ የተሸልኩ ፣ ራስህን አሻሽል ፣ ራስህን እርዳ ፣ ራስህን አበርታ ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር የሚለን ፡- አመለካከታችሁን እንደ ኢየሱስ አድርጉ ነው ፡፡ ኢየሱስ ራሱን ትሁት አደረገ ፡፡ እርሱ በእርግጥ የማይገባው ቢሆንም እንኳ እስከ ሞት ድረስ ታዘዘ ፡፡ የመላውን ዓለም ፍላጎትንም ከራሱ ፍላጎት አስበለጠ ፤ ስለዚህም ሁሉን ነገር ተው ፡፡ ይህ ነው የኢየሱስ አመለካከት በትህትና ራስን አሳልፎ መስጠት ፡፡

ቀናችሁን ስታሳልፉ ፡- ከራሴ ይልቅ ሌሎችን አስፈላጊ አድርጌ እቆጥራለሁን ? በማለት ራሳችሁን ጠይቁ ፡፡ በትህትና እየተመላለስኩ ነውን ? የራሴን ብቻ ሳይሆን የሌሎችንም ፍላጎት ምን እንደሆነ ለማወቅ እጥራለሁን ? ከባድ ሊሆን ይችላል ፡፡ ሆኖም ግን ይህ ምልከታ ሰዎችንና ኃላፊነቶችን በሚገባ ቅንጅት ውስጥ ያስገባል ፡፡ ሰዎች መግባት ይችሉ ዘንድ በሩን ክፍት አድርጉት ወይም ሰልፍ ስትሰለፉ መጨረሻ ላይ ይሁን ፡፡ ከመናገራችሁ በፊት ቆም በሉ ፤ የሰዎችንም ልብ ለማወቅ አዳምጡ ፡፡ የራሳችሁን ፕሮግራም መሰረዝ ቢያስፈልግ እንኳ እየሰረዛችሁ ፣ ታዘዙ ፡፡ ለማንም ሳታሳወቁ መልካም ነገርን አደርጉ ፡፡ ጌታ ራሳችሁን ዝቅ እንድታደርጉ እናም በጊዜው ደግሞ እግዚአብሔር ከፍ እንደሚያደርጋችሁ ይናገራል ፡፡ በዚህ ተስፋ ኑሩ ፡፡

“ ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር፤ እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት፥ ለባልንጀራው ደግሞ እንጂ።በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን። “

  • ፊልጵስዩስ 2፡3-5

ተጨማሪ ጥቅስ

ፊልጵስዩስ 2:5–8 — “ በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን።እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ ። “

ያዕቆብ 4:6 — “ነገር ግን ጸጋን አብልጦ ይሰጣል ፤ ስለዚህ፦ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል ፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል ይላል ። “

1ኛ ጴጥሮስ 5:6–7 — “ እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ ፤ እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት ። “