Paul's Ministry To The Gentiles
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Exalted One Philippians 1 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የፊልጵስዩስ መፅሀፍ ሰላሳ ሰዎስተኛ ጥናታችን እና የጳዉሎስ ሌለኛዉ የእስር ቤት መልዕክት ነው (ደብዳቤ) ፡፡ በፊልጲስዮስ ላሉ አማኞች የፃፈዉ መልዕክት እስካሁን እንዳጠናናቸው ልክ እንደ ሌሎቹ የጳዉሎስ መልዕክቶች በሐዋሪያት ስራ የጳዉሎስን ጉዞ መግለፁን ይቀጥላል ፡፡ ፊልጲስዮስ ጳዉሎስ የመጀመረባት በሜቄዶኒያ የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ነበረች ፡፡ ጳዉሎስ ከክርስቶስ ሞት በኋላ 60-62) አካባቢ በሮም በዚያ በመጀመሪያ እስራቱ መልዕክቱን ፅፏል ፤ የዚያም ማስረጃ (በፊል 1፡ 13, 4፡ 22) ላይ፣ በሐዋሪያት ስራ (28፡ 16, 30-31) መፅሀፍ ላይ እና በቆላ (4፡ 2-4) ላይ የሚገኝ ነው ፤ ይሁን እንጂ አንዳንድ ምሁራን መፅሀፉበዚያ የጳዉሎስ የሁለት አመት እስራት ማብቂያ አጠገብ በባህሩ ላይ ከሚገኘው ከቂሳሪያ እንደተፃፈ ያምናሉ ፡፡ በፊል (1፡ 20) መሰረት ጳዉሎስ እስራቱ መጨረሻዉ እየመጣ እንደ ነበር ተስፋ አድርጓል ፡፡
የፊልጲስዮስ ከተማ መጀመሪያ ክርኒዴስ ተብሎ የተጠራ ወይም በአጠገቡ ያለችን ትንሽ ምንጭ ያመለክት የነበር ትንሽ ምንጭ ዉሃ ነበር ፤ ከተማዋ የታላቁ አሌክሳንደሪያ አባት የነበረዉን ሜቅዶን ፊሊፕ 2 በማክበር እንደገና ተሰየመች ፡፡ በአጠገቧ የወርቅ ማዕድን ማዉጣት ስለ ነበር ብዙ ሰዎችን ወደ ስፍራ ስቧቸዋል ፡፡ ከክርስቶስ ልደት በፊት በአራተኛዉ ክፍለ ዘመን ፊሊፕ ከተማዋን እና በዙሪያዋ ያሉትን ስፍራዎች በመያዝ/በመቆጣጠር ከተማዋም ከክርስቶስ ልደት በፊት በሁለተኛዉ ክፍለ ዘመን ላይ በመቄዶኒያ የሮማዉያን ግዛት አካል ሆነች ፡፡ ከአመታት በኋላ ዝናዋ እየታወቀ በመጣ ጊዜ ከክርስቶስ ልደት 42 በፊት በሮማዊያን የህግ ምክር ቤት ከጁሌስ ቄሳሪያ ሞት በኋላ ቄሳሪያን ይረዱ የነበሩት የአንቶንይ እና ኦክታቪን ሰራዊት ሁለቱም ቄሳሪያን ይቃወሙ የነበሩትን የቡርቱስ እና ካሹን የሁለቱንም ሰራዊት አሸነፉ ፤ በመቀጠልም የአዉራጃዋ/የከተማዋ የአዲሱ የሮማዊያን አስተዳደር መንደር ሆነች ፡፡
ጳዉሎስ በሁለተኛዉ የአገልግሎት ጉዞዉ ላይ ቤተ ክርስቲያንን መሰረተ ፤ ጳዉሎስ በፊልጲስዮስ በደረሰ ጊዜ ጥቂት አይሁዶች ብቻ በዚያ ነበሩ ፡፡ በዚያ ከምኩራብ ለመዉጣት በጣም ጥቂት አስር የሚደርሱ ወንድ የአይሁድ ህዝቦች ስለ ነበሩ በከተማዋ የአይሁድ ሴቶች በጋንጊቴስ ወንዝ አጠገብ ከከተማዋ ዉጪ ይሄዱ ነበር ፡፡ ጳዉሎስ በዚያ ሴቶችን በማግኘት (ሐዋ 16፡ 13) ወንጌልን ሰበከላቸው ፤ በፊልጲስዮስ የመጀመሪያዋ አማኝ ሊድያ የምትባል አንድ ሴት ነበረች ፡፡ በኃብት እና ለመገናኛነት ለቤተ ክርስቲያን በትልቅ ቤት የተሳካላት የቢዝነስ ሴት ነበረች ፡፡ እድል በመሸጥ ባሪያ ከነበረችዉ ክፉዉ ከተቆጣጠራት ሌላ ሴት በኩል ወዲያዉኑ ተቃዉሞ መጣ ፤ ለጩኸቷና ለእርግማኗ ምላሽ ጳዉሎስ ክፉዉን በማስወጣት ጌታዋን እንዲበሳጭ አደረገዉ ምክንያቱም ከዚህ በኋላ ገንዘብ ልትሰራለት ስለማትችል ፡፡ ጳዉሎስና እና ሲላስ በህዝቡ በመያዝ አስገርፏቸዉ በነበረዉ እና በሰንሰለት በእስር ቤት አስሯቸዉ ወደ ነበረዉ ጌታ ፊት አመጧቸው (ሐዋ 16) ፡፡ ሰንሰለታቸዉ ተሰባበር በሮቹም በምድር መናወጥ ተከፈተ ነገር ግን ጳዉሎስ እና ሲላስ በነበሩበት ተቀምጠው ነበር ፤ ጠባቂዎም ባገኛቸዉ ጊዜ በዚያ ቤት ካሉት ሰዎች በተጨማሪም ክርስቶስን ተቀበለ ፡፡ በቀጣዩም ቀን ጌቶቹ ጳዉሎስ እና ሲላስ የሮማዉ ዜጋ ቢሆንም እንኳን ጳዉሎስ እና ሲላስ ያለ ህግ ተይዘዉ እንደ ነበር በማግኘት እንዲለቁም ጳዉሎስን እና ሲላስን ጠየቋቸው ፡፡ ጳዉሎስ ፊልጲስዮስን ሁለት ተጨማሪ ጊዜ ጎብኝቷል - አንዴ ወደ አተንስ እና ቆሮንቶስ ሲጓዝ በሰዎስተኛ የአገልግሎት ጉዞዉ መጀመሪያ ላይ ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ ሲመለስ ነበር ፡፡ ጳዉሎስ በፊልጲስዮስ ቤተ ክርስቲያንን ይወዳል (ፊል 4፡ 15-16) ፤ በፊልጲስዮስ የነበረች ቤተ ክርስቲያን ለኢየሩሳሌም ስጦታ በልግስና ይሰጡ ነበሩ ፤ ጳዉሎስን ለማረጋገጥ ጳዉሎስን ለማገልገል መጥቶ የነበረዉን ኤፍሮዲተስን በማካተት ላኩ ፡፡ ኤፍሮዲተስ ወደ ሮም በጉዞ ላይ እያለ ወይም ደግሞ ከጳዉሎስ ጋር እንደ ነበር በኃይለኛዉ ታሞ ነበር ፡፡ ጳዉሎስ ስለጤንነቱ ሲል ኤፍሮዲተስን መልሶ ወደ ፊልጲስዮስ በመላክ ከእርሱ ጋር በዚያ ለነበሩ ቤተ ክርስቲያን መልዕክት ላከ ፡፡
ማክአርቱር በፊልጵስዮስ ላለች ቤተ ክርስቲያን የጳዉሎስ መልዕክት አምስት አላማዎችን ይለያል ፤ የመጀመሪያው ጳዉሎስ በለጋስነት ስለመስጠታቸው ሊያመሰግናቸዉ ፃፈ ፤ ሁለተኛው ጳዉሎስ ኤፍሮዲተስ መልሶ ለምን ወደ ፊልጵስዮስ እንደላከዉ ለመግለፅ ስለመፈለግ ፤ ሰዎስተኛው ጳዉሎስ በሮም ያለበትን ሁኔታ ማሳወቅን ሊሰጣቸዉ ስለፈለገ ፤ አራተኛው ጳዉሎስ ስለ አንድነት ሊያበረታታቸው ፤ አምስተኛው ጳዉሎስ በዚያ ያሉትን አማኞች ከሃሰተኛ አስተማሪዎች አስጠነቀቃቸው የሚሉት ናቸው ፡፡ በተጨማሪም ጳዉሎስ እስከ መስቀል ሞት ድረስ ራሱን ትሁት ስላደረገው(ማር 10፡ 45) ከፍ ከፍ/ስለሚበልጠው ስላለዉ ፅፏል (2፡ 5-11) ፡፡ የመፅሀፉ ሁለተኛው ጭብ ደስታ ነው ፤ ጭብጡ ስለ ደስታ በመጥሀፉ ዉስጥ አምስት የተለያዩ የግሪክ ቃሎችን በመጠቀሙ በጣም በማስፋፋት ደስታን 15 የተለያየ ጊዜ ጠቅሶታል ፡፡
ትምህርት
ፊልጵስዮስ (1፡ 1)፡ የመጀመሪያዎቹ 11 ጥቅሶች የጳዉሎስን ሰላምታዎች ይይዛሉ ፡፡ ጳዉሎስ በክርስቶስ ያለዉን ስፍራ ለመግለፅ “ ባሪያ “ ወይም “ በነፃ እንደሚያገለግል “ የሚለዉን ቃል ተጠቀመ (ቁጥር 1) ፡፡ ማክአርቱር ቃሉን “ ከጌታዉ ጋር በደስተኝነትና በታማኝነት የተሳሰረን ፍቃደኛ አገልጋይን እንደሚወክል “ ይገልፃል (ያዕ 1፡ 1, 2ጴጥ 1፡ 1, ይሁዳ 1) ፡፡ “ ባለ ራዕዮችን እና ዳቆኖችን በማካተት በፊሊጵስዮስ ያሉትን ሁሉንም ቅዱሳን ደረሳቸው …” ፡፡ ጳዉሎስ በዚያ የነበሩትን ሁሉንም አማኞች አያዉቃቸዉም ምክንያቱም በዚያ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ ቤተ ክርስቲያን እያደገች ስለ ነበር ፡፡
ፊልጵስዮስ (1፡ 2-8)፡ ከእግዚአብሄር አብ ፀጋና ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ከሆነ ሰላም በተለመደ ሰላምታዉ ይቀጥላል (ቁጥር 2) ፡፡ በቁጥር (3-6) ንግግሩ የተለመደ አልነበረም ነገር ግን በእርሱና በፊልጵስዮስ ጉባኤ መካከል የነበራቸዉን ግላዉ የቀረበ ግንኙነትን የሚያሳይ ይመስላል ፡፡ በፍርድ ሳይሆን በደስታ ስለ እነርሱ ፀለየላቸዉ ምክንያቱም ከመጀመሪያዉ ጀምረው የክርስቶስን ስራ መስራት አቁመዉ ስላልነበር ፡፡ ጳዉሎስ በዚያ ያለችዉ ቤተ ክርስቲያን ስለ ክርስቶስ ተምረዉት ከነበረዉ ትምህርት ዞር ይላሉ የሚል ሀሳብ አልነበረዉም ፤ ከእርሱ ጋር እዉነተኛ ቤተሰባዊነት እና በመካከላቸዉ የጠለቀ ፍቅር ነበር (ቁጥር 7-8) ፡፡ በቁጥር 6 “ በኢየሱስ ክርስቶስ ቀን “ የሚለዉ ሀረግ የጌታን ቀን አያመለክትም ነገር ግን “ የመጨረሻ ድነትን፣ ሽልማትን እና የአማኞችን ክብር ይመስላል “ ፡፡
ፊልጵስዮስ (1፡ 9-11)፡ ጳዉሎስ በኃይለኛዉ “ በክርስቶስ ፍቅር “ እንደናፈቁት ያሳዉቃል ፤ ይህ ቃል “ በአንድ ሰዉ መላዉ ማንነት የሆነን የርህራሄ ፍቅርን በመግለፅ “ ወይም ደግሞ “ ለኃይለኛ ስሜት መስተጋብር የሚሰጡ የሰዉነት አካላትን በማመልከት “ ላይ የተመሰረተ የግሪክ ቃል ነው ፡፡ ጳዉሎስ ፍቅራቸዉ በእዉቀት እና በመለየት እንዲያድግ እየፀለየላቸዉ እንደ ነበር ነገራቸው (ቁጥር 9) ፤ የሚበልጠዉ እና ንፁሁ እንዲሁም እንከን ያለበትን መለየት እንዲችሉ ፈለገ (ቁጥር 10) ፡፡ የጳዉሎስ ፍላጎት ዉጤት ፊልጵስዮሳዊያን በእግዚአብሄር ፅድቅ የተሞሉ በመሆን ክብርን በማምጣት እንዲያስደስቱት ነበር (ቁጥር 11) ፡፡
ፊልጵስዮስ (1፡ 12-26)፡ በቁጥር 12-26 ጳዉሎስ ችግሮቹን/ሁኔታዎቹን ከፊልጵስዮስ ሰዎች ጋር ይጋራል / ይነጋገራል ፤ መጀመሪያው በእስር ቤት መሆኑ “ ስለ ወንጌል የተደረገ እንደነበር “ እና ስለ ክርስቶስ ሲል በእስር ቤት መሆኑ የንጉስ ጠባቂን እና የሮማዊያን ህዝብን ያሳይ እንደ ነበር ገይገልፃል (ቁጥር 12-13) ፡፡ ሁለተኛው ሌሎች አማኞች የእርሱን እስራት ካዩ በኋላ ወንጌልን ለመናገር በጣም ፈርተዉ እንደ ነበር ነገራቸው (ቁጥር 14) ፤ ሰዎስተኛው “ በሐዋሪያነቱ ስልጣን እና ኃይል፣ ስኬት እና የመምሰል ስጦታ ከመቅናታቸው የተነሳ “ በጳዉሎስ ጠላቶች በእርሱ ላይ መናገር መጀመራቸውን (ቁጥር 15-17) ፡፡ አራተኛው ጳዉሎስ ሰዎች በምንም ቢሰብኩ ወይም ፍላጎታቸዉ ምንም ቢሆን ክርስቶስ እስከ ተሰበከ ድረስ ችግር እንደሌለበት ተናገረ ! በምዕራፉ በቀረዉ ላይ ጳዉሎስ ታግሷቸዉ ስለ ነበሩት መከራዎች እና በህይወቱ ላይ ምንም ነገር ቢፈጠርም ለጌታዉ ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ማምጣት እንደሆነ መግለጫን ሰጠ ፡፡
መደምደሚያ
ጳዉሎስ ለእርሱ መኖር ማለት ሁሉንም ህይወቱን ለክርስቶስ ጥሪ መስጠት እና መሞት ማለት በጌታ መገኘት ፊት መሆን ማለት እንደሆነ አጥብቆ ተናገረ ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville, Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1708.
MacArthur, pp. 1708-1709.
MacArthur, pp. 1709-1710.
MacArthur, p. 1710.
MacArthur, p. 1711.
MacArthur, p. 1711.
MacArthur, pp. 1711-1712.
MacArthur, p. 1712.
MacArthur, p. 1713.
ጥያቄዎች
-
ጳዉሎስ እግዚአብሄር እርሱ በቅዱሳን የጀመረዉን ስራ እንደሚፈፅመዉ እርግጠና ነበር ፤ እግዚአብሄር በእኛ የሚሰራዉን ስራ እና በእርሱ ስልጠና በኩል እያደረግን ያለነዉን ስራ ግለፁ (ኤፌ 2፡ 10, ፊል 1፡ 6, 2፡ 13, 2ጢሞ 2፡ 15, ዕብ 13፡ 20-21)
-
በፊል (1፡ 9-11) ስለ ቤተ ክርስቲያን የጳዉሎስን ፀሎት አንብቡ ፤ ስለ እነርሱ የተለዬ ነገር ምን ጠየቀ ? ተመሳሳይ ፀሎት የምትፀልዩለት እንዲኖራችሁ ከዚም ፀሎቱን ለራሳችሁ እንድትፀልዩ እግዚአብሄርን ጠይቁት ፡፡
-
የጳዉሎስ የእስራት ሁኔታ/ችግር እንዴት የወንጌል ቅድሚያ መያዣ ሆነ (ፊል 1፡ 12-14) ? አስቸጋሪ ሁኔታዎች ወንጌልን ለመናገር አጋዥ ከሆኑ እንዴት ገጥሟችኋል ወይም መስክራችኋል ?
-
ስለ ክርስቶስ ከራስ ፍላጎት በመነጨ ወንጌልን መስበክ ምን ይመስላል (ፊል 1፡ 17) ? በዚህ መንገድ ወንጌል ሲሰበክ የጳዉሎስ ምላሽ ምን ነበር ?
-
በፊል (1፡ 27) ራሳቸዉን ለክርስቶስ ወንጌል የተገባ አድርገዉ እንዲኖሩ ለፊልጵስዮስ ያዘዛቸዉን የጳዉሎስን ትዕዛዝ ግለፁት (ኤፌ 4፡ 1-3, ቆላ 1፡ 10)
-
በፊልጵስዮስ 1 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Philippians 1:3–5
“I give thanks to my God for every remembrance of you, always praying with joy for all of you in my every prayer, because of your partnership in the gospel from the first day until now.”
የፊልጵስዮስ ቤተክርስቲያን ጳውሎስን በአገልግሎቱ አበረታተውትና አግዘውት ነበር ፡፡ ጳውሎስ ለእነርሱ እንደጻፈው ፡- እርሱ በደስታ ያስታውሳቸው ነበር ደግሞም ወንጌልን ከእርሱ ጋር አብረው ስለሰሩ ስለእነርሱ እግዚአብሔርን ያመሰግን ነበር ፡፡
ዛሬ ከጌታ ጋር ስለነበራችሁ ጉዞ ወደ ኋላ መለስ ብላችሁ አስቡ ፡፡ በህይወታችሁ በጌታ እንድታድጉ ያበረቷችሁን ያገዟችሁን ሰዎች አስታውሱ ፡፡ በወንጌል ከእናንተ ጋር አብረዋችሁ የሚሰሩ ሰዎች እንዲኖሩ የሙሉ ጊዜ አገልጋይ መሆን አይጠበቅባችሁም ፡፡ የወጣቶች መጋቢ ሊሆን ይችላል ፤ በትምህርት ቤት ውስጥ ያለ መምህር ፤ የስራ ቦታ ጓደኛ ወይም ከጌታ ጋር ያለውን ጉዟችሁን የሚደግፍ የቀድሞ ጓደኛም ሊሆን ይችላል ፡፡ ዛሬ ስለ አብሮ ሰራተኝነታቸው እግዚአብሔርን ለማመስገን ጊዜ ውሰዱ ፡፡ ቀጥላችሁ ስለእነርሱ ጸልዩ ፡፡ የበለጠውን ፣ ንጹህ የሆነውንና ነቀፋ የሌለበትን ነገር መፈጸም ይቀጥሉ ዘንድ በእውቀትና በማስተዋል ማደግን እንዳያቋርጡ ስለ ፍቅራቸው ጸልዩ ፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ በሚገኘው የጽድቅ ፍሬ ይሞሉ ዘንድ ጸልዩ ፡፡ ከዚያም እነርሱንና በህይወታችሁ ውስጥ ያሳረፉትን በጎ አሻራ ባስታወሳችሁ ጊዜ ሁልጊዜ እግዚአብሔርን እንደምታመሰግኑ ለእነርሱ በደብዳቤ ወይም በአጭር መልዕክት ለማሳወቅ ጊዜ ውሰድ ፡፡
“ ሁልጊዜ በጸሎቴ ሁሉ ስለ እናንተ ሁሉ በደስታ እየጸለይሁ፥ ከፊተኛው ቀን እስከ ዛሬ ድረስ ወንጌልን በመስበክ አብራችሁ ስለ ሠራችሁ፥ ባሰብኋችሁ ጊዜ ሁሉ አምላኬን አመሰግናለሁ ። “
- ፊልጵስዩስ 1፡3-5
ተጨማሪ ጥቅስ
ፊልጵስዩስ 1:9–11 — “ ለእግዚአብሔርም ክብርና ምስጋና ከኢየሱስ ክርስቶስ የሚገኝ የጽድቅ ፍሬ ሞልቶባችሁ፥ ለክርስቶስ ቀን ተዘጋጅታችሁ ቅኖችና አለ ነውር እንድትሆኑ የሚሻለውን ነገር ፈትናችሁ ትወዱ ዘንድ፥ ፍቅራችሁ በእውቀትና በማስተዋል ሁሉ ከፊት ይልቅ እያደገ እንዲበዛ ይህን እጸልያለሁ ። “
2ኛ ጢሞቴዎስ 2:1–2 — “ እንግዲህ፥ ልጄ ሆይ፥ አንተ በክርስቶስ ኢየሱስ ባለው ጸጋ በርታ ። ብዙ ሰዎች የመሰከሩለትን ከእኔም የሰማኸውን ሌሎችን ደግሞ ሊያስተምሩ ለሚችሉ ለታመኑ ሰዎች አደራ ስጥ ። “
ቲቶ 2:3–4 — “ እንዲሁም አሮጊቶች ሴቶች አካሄዳቸው ለቅዱስ አገልግሎት የሚገባ፥ የማያሙ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይገዙ፥ በጎ የሆነውን ነገር የሚያስተምሩ ይሁኑ፤ ቆነጃጅትም ፣ ባሎቻቸውን የሚወዱ፥ ልጆቻቸውን የሚወዱ፥ ራሳቸውን የሚገዙ እንዲሆኑ ይምከሩአቸው ።
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።