Paul's Letters Ephesians

Children And Parents

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ The Head Ephesians 6 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 543 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ይህ በኤፌሶን የመጨረሻዉ ምዕራፍ እና ሽፋን የሚመስል አይነት ነው - ስለመንፈሳዊ ዉጊያ እና ስለ እግዚአብሄር የጦር ዕቃ ልብስ የሚያወራ ፡፡ በኤፌ (6፡ 10-20) ጳዉሎስ ኤፌሶዋዊያንን ለመንፈሳዊ ዉጊያ ዕለት ዕለት ራሳቸዉን እንዲያዘጋጁ ያበረታታቸዋል ፡፡ ኤፌሶዋዊያን ማየት ከማይችሉት ጠላታቸዉ ጋር እየተዋጉ ነበር ፤ ማየት የማንችለዉን ጠላታችንን እየተዋጋን ነው ፡፡ ይህን መንፈሳዊ ጦርነት ስንዋጋ የእግዚአብሄር የጦር እቃ ልብስ በማንሳት ያለማቋረጥ እንፀልያለን ፤ ዛሬ ይህ የትምህራትችን አጠቃላይ ጊዜ የማሳልፍበት ስፍራ እንደሚሆን አስቤአለሁ ነገር ግን ቃሉን ሳጠናው ቁጥር አራትን በፍፁም በማለፍ አላደርግም ፤ በእነዚህ ጥቅሶች ላይ በልጆች ላይ ሳጠና ስለልጆች ብቻ ሳይሆኑ ስለቤተሰብም እንደሆኑ ተረድቻለሁ ፡፡ በልጆች በኩል ጀምረን ልጆች ቤተሰቦቻቸዉን የሚታዘዙባቸዉን አራት ምክንያቶች እንመለከታለን ፤ በመቀጠልም በቤተሰብ በኩል እንመለከታለን ፡፡ በእነዚህ በመጀመሪያዎቹ አራት ጥቅሶች እግዚአብሄር መሆን ስለ ሚያስፈልገኝን የቤተሰብ አይነት አሳመነኝ ፡፡

ትምህርት

ኤፌሶን (6፡ 1)፡ እንደ ጳዉሎስ ንግግር ክርስቲያን ለነበሩ “ ልጆች “ እየፃፈ ነበር ፡፡ ጌታን ያዉቁታል ፡፡ በእነዚህ ልጆች መጀመሪያ ሀሳብ ነበረው ፡፡ በምንም መንገድ/ሁኔታ ፍፁም ቤተሰብ አይደለሁም ወይም ልጆቼ ፍፁማን አይደሉም ፤ በዚህ ዉስጥ በማወራ ጊዜ መፅኀፍት በሚለዉ ለመመላለስ እየሞከርኩ እና የጳዉሎስ ፅኁፍ እንዴት እንደረዳኝ እያሳየኋችሁ ነው ፡፡

ልጆች በሁሉም ነገር ቤተሰቦቻቸዉን መታዘዝ አለባቸው ምክንያቱም እግዚአብሄርን ስለሚያስደስተው (ቆላ 3፡ 20) ፤ ቤተሰብን ማክበር/መታዘዝ ልጆች በጌታ መሆናቸዉን የሚያሳይ ድርጊት ነው ፡፡ ማክአርቱር “ በቤት ዉስጥ ያለ ልጅ በእርሱ ላይ እንደ ተሾመ እንደ እግዚአብሄር ወኪል/ተወካይ በትህትና በመታዘዝ በቤተሰብ ስልጣን ስር ለመሆን ቤተሰብን ማክበር እግዚአብሄርን ማክበር ስለሆነ ፍቃደኛ የሚሆን እንደሆነ “ ፅፏል ፡፡ ቤተሰቦች የልጆች አደራ/ኃላፊነት አለባቸው ምክንያቱም ያ እግዚአብሄር ያቀደዉ መንገድ ስለሆነ ፤ አንዱ ለሌላው ይታዘዛል/ይገዛል ፡፡ ለባሎቻቸዉ የሚገዙ ሚስቶች ሲኖሩ፣ ሚስቶቻቸዉን የሚወዱ ባሎች ሲኖሩ እና ለቤተሰቦቻቸው የሚገዙ ልጆች ሲኖሩ በቤት ዉስጥ ስምምነትን ታያላችሁ ፡፡

ልጆች ቤተሰቦቻቸዉን ማክበር ያለባቸዉ ሌለኛዉ ምክንያት መታዘዝ ትክክል ስለሆነ ነው ፡፡ ዋይርስቤ “ ስለ ድርጊቱ ትክክለኛነት የሚያከራክር የተፈጥሮ ስርዓት አለ፣ የእግዚአብሄር ትዕዛዝ አለ ፤ ቤተሰብ ልጆችን ወደ አለም ካመጧቸው እና ከልጅ የተሸለ እዉቀት እና ጥበብ ስላላቸው አንድ ልጅ ቤተሰቡን መታዘዙ ትክክል ነው “ በማለት ፅፏል ፡፡ በአሁኑ ዘመን ባህልልጆቻቸዉን ደስተኛ ለማድረግ ቤተሰቦች ልጆቻቸዉን እንዲያከብሩ ነግረናቸዋል ፤ ያ እግዚአብሄር እንዲሆን ከሚፈልገዉ መንገድ ተቃራኒ ነው ፡፡

ኤፌሶን (6፡ 2)፡ መታዘዝ ትዕዛዝ ነው ፡፡ ዋይርስቤ “ የህጉ ቅዱስነት አሁንም የእግዚአብሄር ቅዱስነት መገለጥ እና በኑሮአችን ቅድስናን ለማድረግ መንፈስ ቅዱስን በእኛ ዉስጥ እንዲሰራ የሚያደርግ ነው (ሮሜ 8፡ 1-4) “ በማለት ፅፏል ፡፡ከመንፈስ ቅዱስ የተነሳ ቤተሰቦቻችንን በማክበር ድርጊት መመላለስ እንችላለን ፡፡ ዋይርስቤ “ ሁሉም 10 ትዕዛዝት ሰንበትን ቀን ቅዱስ አድርጎ ከመጠበቅ ዉጪ እንዲጠብቋቸዉ ለክርስቲያኖች በአዲስ ኪዳን መልዕክቶች ዉስጥ ተደግመዋል “ በማለት ፅፏል ፡፡ ማክበር የሚለዉን ቃል በምትሰሙ ጊዜ ወደ አይምሯችሁ ምን ይመጣል ? ማክበር ማለት በቀላሉ መታዘዝ ከሚለዉ የሚበልጥ ነው ፤ ለመጠንቀቅ/ለማሰብ እና አክብሮትን ለማምጣት በመፈለግ አክብሮትን እና ፍቅር ማሳየት ማለት ነው ፡፡ ቤተሰቦች በመንፈስ በመመላለስ ልጆቻቸው እንዲሰሟቸዉ በመፈለግ ዉስጥ ዉጥረት አለ ነገር ግን ሁልጊዜ ልጆች ያን አያደርጉም ምክንያቱም በአለም ዉስጥ እየኖሩ ስለሆነ ፡፡

ኤፌሶን (6፡ 3)፡ መታዘዝ በረከትን ያመጣል ፡፡ ይህን ጥቅስ እንደ ገና አንብቡ ፡፡ ልጆቻችሁ ገና በልጅነታቸዉ የሚሞቱ ከሆነ የማይታዘዙ ነበሩ ማለት አይደለምን ? አይደለም ፤ ይህ ሁልጊዜ ምክንያት እንደማይሆን እንድትረዱ እፈልጋለሁ ፡፡ ልጆቻችሁ እናንተን የሚያከብሩ እና የሚታዘዙ ከሆኑ ኑሮአቸዉን ሊያሳጥሩ የሚችሉ ነገሮችን የኃጢዓትን መልካም ንግግር እና አደጋን ይዘላሉ/ያልፋሉ ፡፡ ከቤተሰብ ርቆ መሄድ ከእግዚአብሄር መንገድ ርቆ መሄድ ስለሆነ በበዙ ልጆችን የማይታዘዙ ያደርጋቸዋል ፡፡

ኤፌሶን (6፡ 4)፡ “ አባቶች “ እናቶችን እና አባቶችን ያመለከተ ከግሪክ የመጣ ቃል ነበር ፤ ይህ ለሁለቱም ቤተሰቦች ነው ፡፡ ማክአርቱር “ አምላክ የለሽ በሆነዉ አለም በጳዉሎስ ዘመን በአይሁድ ቤቶችም እንኳን አብዛኞቹ አባቶች በአስገዳጅና በጭቆና ስልጣን ቤተሰባቸዉን አስተዳድረዋል ፤ የሚስቶች እና የልጆች ፍላጎት እና ደህንነት አልፎ አልፎ ይታይ እንደ ነበር “ ፅፏል ፡፡

ቤተሰቦች ልጆቻቸዉን ማስቆጣት የለባቸውም ፡፡ ዋይርስቤ “ ጳዉሎስ ቤተሰቦችን ልጆችን ለማስቆጣት መሪነታችሁን/የማስተዳደር ስልጣናችሁን አትጠቀሙ በማለት ነገራቸው “ በማለት ፅፏል ፡፡ የማበሳጨት ተቃራኒ ማበረታታት ነው ፤ ልጆቻችሁን ማስደሰት አስፈላጊ ነው ፡፡ ዋይርስቤ “ ያልፀና እና በመቅጣት ዉስጥ ፍትሀዊ ባለመሆን፣ በቤት ዉስጥ አድሎ አድሎን በማሳየት፣ ቃል በመግባት እና ቃሉን ባለመፈፀም እና ቃላል የሆኑ ችግሮችን ማድረግ ለልጆች በጣም አስፈላጊ ናቸው (ልጆቻችሁን እያስቀጣችኋቸዉ ነው ) “ በማለት ፅፏል ፡፡

ቤተሰቦች ልጆቻቸዉን ማሳደግ አለባቸው ፡፡ እዚህ ጋር ጥቅም ላይ የዋለዉ ማሳደግ የሚለዉ ቃል መመገብ ከሚለዉ ከኤፌ (5፡ 29) ላይጥቅም ላይ ከዋለዉ ቃል ጋር ተመሳሳይ ነው ፡፡ አንድ ቤተሰብ የልጅን አካላዊ ፍላጎት (ምግብ፣ መጠለያ፣ ልብስ) ከማሟላት በላይ ማሟላት ያስፈልገዋል ፤ በተጨማሪም በፍቅር እና በማበረታታት መንፈሳዊና ስሜታዊ ፍላጎቶችን ማማላት/ማቅረብ አለባቸው ፡፡ ይህ የመቅጫ/የመገሰጫ ጊ የለም ማለት አይደለም ነገር ግን ለማሳደግ በመውደቅ በልጆቻችን ህጋዊ መሆን አንችልም ፤ ልጆቹ እንዲወድቁ ስለማልፈልግ አንዳንድ ጊዜ የቤተሰቤን የማሳደግ ድርሻ ላይ በመርሳት በእጄ ላይ ባለ ድርጊት አተኩራለሁ ፤ ያ ልጆቼን የሚያበሳጫቸዉ ነው ፡፡ በምሳሌ ለማስተማር፣ በተመጣጠነ የህይወት መንገድ ለማስተማር ራሴን መሞገት ይጠበቅብኛል ፤ ለዚህ ትምርት ጥሩዉ ምሳሌ በሉቃ (2፡ 52) ላይ ይገኛል - የኢየሱስ ቤተሰብ አስተምሮ እና አስተዳደጉ ፡፡

ቤተሰቦች ልጆቻቸዉን መቅጣት አለባቸው ፡፡ ዋይርስቤ “ ማሳደግ የሚለዉ ቃል በመገሰፅ ዉስጥ የማስተማር ሀሳብ ይይዛል…. የፀና፣ የፍቅር ተግሳፅ ለልጅ ማረጋገጫን ይሰጣል “ በማለት ፅፏል ፡፡ ልጆቻችሁን ለመቅጣት አትፍሩ ፡፡

ቤተሰቦች ልጆቻቸዉን ማዘዝ እና ማበረታታት አለባቸው ፤ ሁሉም ነገር በእግዚአብሄር ቃል መሰረት መሆን አለበት ፡፡

መደምደሚያ

እነዚህን ጥቅሶች በምናነብ ጊዜ ጳዉሎስ “ ልጆች ቤተሰቦቻቸዉን በማክበር እና በመታዘዝ እግዚአብሄርን ማስደሰት ያስፈልጋቸዋል ይህም ትክክል ነገር ነው ፤ ቤተሰቦች እግዚአብሄርን እየመሰሉ እንደሆነ እርግጠኞች በመሆን ራሳቸዉ ላይ መመልከት እንደሚያስፈልጋቸው “ እያለ እንደሆነ እመለከታለሁ ፡፡ በግልፅ ኤፌሶዋዊያን በዚህ ነገር ትግል ላይ ነበሩ ፤ ጠላት የቤተሰብን ህይወት አጥቅቶ የነበር እና እያጠቃ ያለ ቤተሰብን የሚበታትን ነው ፡፡ ሀሳባችሁ ያልተረጋጋበት ማንኛዉምንም ስፍራ ላይ መንፈስ ቅዱስ መንቀሳቀስ እንዲጀምርበት ፍቀዱለት ፤ በመፀሀፍም እንኳን ቤተሰቦች ልጆቻቸዉን ችላ ሲሉ እናያለን፡ ዳዊት አቢሰሎምን አሞላቀቀ፣ ኤሊ ልጆቹን ለመቅጣት ችላ በማለቱ በህዝቡ ላይ ዉርደትን መጡ፣ ቤተሰቡን ወደ መከፋፈል የመራው ሚስቱ ያዕቆብን ብትወደዉም ይስሐቅ ኤሳዉን አሞላቀቀዉ ፡፡ በቤተሰባችን ላይ ትኩረትን አጥተናል ፤ ከክርስቶስ እና ከልጆቻቸው ጋር በመተሳሰር የሚጓዙ ቤተሰቦች ያስፈልጉናል ፡፡ ልጆች ቤተሰቦቻቸዉ ያስፈልጓቸዋል ፤ በቤተሰባችን ዉስጥ ክርስቶስን ማሳየት/ማንፀባረቅ ያስፈልጋል ፡፡

10 MacArthur. p. 1703.

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville, Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1705.

  2. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Ephesians (Colorado Springs: David C. Cook, 1989), p. 53.

  3. Wiersbe, p. 53.

  4. Wiersbe, p. 53.

  5. Wiersbe, p. 53.

  6. Wiersbe, p. 53.

  7. Wiersbe, p. 53.

  8. Wiersbe, p. 53.

  9. Wiersbe, p. 53.

  10. Wiersbe, p. 53.

  11. Wiersbe, p. 54.

  12. Wiersbe, p. 54.

  13. Wiersbe, p. 54.

  14. Wiersbe, p. 54.

  15. Wiersbe, p. 54.

  16. Wiersbe, p. 54.

ጥያቄዎች

  1. በመፅሀፍ ላይ ሌላ የት ስፍራ ልጆች አባቶቻቸዉ እና እናቶቻቸዉን እንዲያከብሩ ሲነገሩ እናያለን (ዘጸ 20፡ 12, ዘዳ 5፡ 16, ማቴ 15፡ 4, 19፡ 19, ማር 7፡ 10, ሉቃ 18፡ 20) ? ከሌሎቹ ትዕዛዛት በንፅፅር ስለዚህ ትዕዛዝ የተለየዉ ነገር ምንድን ነው ? በግል አስተያየታችሁ ልጆች ሁልጊዜ ይህን ትዕዛዝ ቢታዘዙ በአሁኑ ጊዜ አለም እንዴት የተለየች ትሆናለች ?
  2. በኤፌ (6፡ 4) “ አባቶች ሆይ ልጆቻችሁን ለቁጣ አታስነሷቸው “ የሚለዉ ፅሁፍ/ንግግር ምን ማለት እንደሆነ ምን ታስባላችሁ (ቆላ 3፡ 21) ? በመፅሀፍ ቅዱስ ዉስጥ ለዚህ ምሳሌ የሚሆን ማሰብ ትችላላችሁ (2ሳሙኤል 14) ? በራሳችሁ ህይወትስ ?
  3. ከክፉ ራሳችንን ለመጠበቅ “ የምንለብሳቸዉን “ ስድስት ነገሮች ጥቀሱ (ኤፌ 6፡ 14-17) ፤ ብዙ ጊዜ የእግዚአብሄርን የጦር እቃ ልብሳችሁን እንዴት ትለብሳላችሁ ? ይህ ለምንድን ያስፈልጋል ?
  4. “ ሁልጊዜ በመንፈስ መፀለይ “ ምን ይመስላል (ኤፌ 6፡ 18) ?
  5. በኤፌሶን 6 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Ephesians 6:10–12

“Finally, be strengthened by the Lord and by His vast strength. Put on the full armor of God so that you can stand against the tactics of the Devil. For our battle is not against flesh and blood, but against the rulers, against the authorities, against the world powers of this darkness, against the spiritual forces of evil in the heavens.”

እንደ ክርስቶስ ተከታይ በመንፈሳዊ ውጊያ ውስጥ እንደሆናችሁ አስታውሱ ፡፡ ይህ ውጊያ ከስጋና ከደም ጋር አይደለም ነገር ግን በሰማያዊ ስፍራ ካሉ ኃይሎች ጋር እንጂ ፡፡ እናንተ ለእግዚአብሔር ክብርን ለመስጠት ስትሹ በሌላ በኩል ደግሞ ሰይጣን በህይወታችሁ ውስጥ ያለውን ሁሉ ሊሰርቅ ፣ ሊገድልና ሊያጠፋ ያሴራል ፡፡ እርሱ የእናንተን ጊዜ ፣ ደስታ ፣ አንድነት ፣ ጥንካሬና አሳብ ይፈልጋል ፡፡

በውጊያ መሃል በድያብሎስ ሽንገላ ላይ ጸንታችሁ ትቆሙ ዘንድ ጌታ ጥሪን ያቀርብላችኋል ፡፡ የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ ጌታ መንፈሳዊ የጦር ዕቃን ይሰጣችኋል ፡፡ ጠላት በትዳራችሁ ላይ ወይም በቤተሰባችሁ ላይ ፤ በልጆቻችሁ ላይ ወይም በአገልግሎታችሁ ላይ ሲነሳ ፣ በሰላም ወንጌል ተጫምታችሁ ቁሙ ፡፡ ከፍተኛ ግራ መጋባት ጥርጣሬም ሲገባችሁ ፣ የእምነት ጋሻችሁን አንሱ ፡፡ እግዚአብሔር አምላካችሁ በእናንተ ውስጥ ብርቱ ነው ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተራመዱ ፡፡ ድልን ትቀዳጃላችሁ ! ተስፋ እንዳትቆርጡ ! ይልቁንም በጌታ በርቱ ፤ የጦር ዕቃችሁንም አንሱ ፡፡ የጦር ዕቃችሁን መልበስ ስትረሱ ወይም ወደ ውጊያችሁ ጌታን ሳትጋብዙት ስትቀሩ ትዝላላችሁ ፡፡ ስለዚህ አሳባችሁን በክርስቶስ ላይ አድርጉ ፡፡ የጠላት ሽንገላ በኢየሱስ ስም ኃያል ተሸንኋል ፡፡

“ በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ ። የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ ። መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ ። “

  • ኤፌሶን 6፡10-12

ተጨማሪ ጥቅስ

2ኛ ቆሮንቶስ 10:3–5 — “ በሰው ልማድ ምንም እንኳ የምንመላለስ ብንሆን፥ እንደ ሰው ልማድ አንዋጋም ፤ የጦር ዕቃችን ሥጋዊ አይደለምና፥ ምሽግን ለመስበር ግን በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ ነው ፤ የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን ሁሉ እንማርካለን :: “

ኤፌሶን 6:4 — “ እናንተም አባቶች ሆይ፥ ልጆቻችሁን በጌታ ምክርና በተግሣጽ አሳድጉአቸው እንጂ አታስቆጡአቸው ። “

ኤፌሶን 6:13–17 — “ ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም ፥ ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ አንሡ ። እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ ፥ የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ ፥ በሰላም ወንጌልም በመዘጋጀት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ ፤ በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ ፤ የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው ። “