Paul's Letters Ephesians

Walk In Love and Light

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ The Head Ephesians 5 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 542 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ማክአርቱር የምዕራፍ 5 መልዕክት “ በቤተ ክርስቲያን ለመታመን እንደ እግዚአብሄር መስፈረት “ ያጠቃልለዋል ፡፡

ትምህርት

ኤፌሶን (5፡ 1-7)፡ በቁጥር 1-2 ጳዉሎስ አንባቢዎቹን የእግዚአብሄር እንዲመስሉ ይነግራቸዋል ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ አማኞች የእግዚአብሄርን ምሳሌነት የሚከተሉ ናቸው ፤ ጠላቶቹ በነበርን ጊዜም እንኳን ይወደናል ፡፡ እንደሚመስል አማኞች ራስን የመሰዋት አይነቱን ፍቅር ያሳያሉ “ በማለት ይገልፃል ፡፡ ማክአርቱር እግዚአብሄርን መምሰል የሚለዉን “ እርሱን በምድር ላይ በማገልገል እርሱን መስሎ በማደግ የሆነ ኃይለኛው የመቀደስ አላማ እንደሆነ “ ይገልፃል ፤ ማክአርቱር “ የክርስቲያን ህይወት አማኞች በአዲስ መወለድ እንደገና በተፈጠሩበት መልክ በአዳኙና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እንደተቀረፀው እግዚአብሄራዊ ባህሪን እንዲያደርጉ የተሰራ ነው “ በማለት ቀጠለ ፡፡ በ 1ጴጥ (1፡ 15-16) በየቀኑ በብዙ ጌታን ከመምሰል የሚበልጥ ታላቅ ጥሪ ወይም አላማ የለም ፤ ያም በፍቅር እንድንመላለስ ይፈቅድልናል ፡፡

ቁጥር 2 የኢየሱስን ህይወት “ ለእግዚአብሄር መዓዛ ያለዉ መባና መስዋዕት “ እንደ ሆነ ይገልፀዋል ፤ ማክአርቱር በመስቀል ላይ የክርስቶስን መስዋእት “ የወደቀዉን የሰዉ ልጅ በማስደሰት የሰማይ አባቱን አከበረ ምክንያቱም ይህ በደንብ ሙሉና ፍፁም በሆነ መንገድ የእግዚአብሄር ሉዓላዊነት፣ ፍፁምነት፣ የማይለወጥ እና መለኮታዊ አይነት የሆነዉን ፍቅር ስለሚያሳይ እንደሆነ “ ይገልፃል ፡፡ በዘሌዋዊያን አምስት መስዋዕቶች በእግዚአብሄር የታዘዙ ነበር ፤ ማክአርቱር የመጀመሪያ ሰዎስቱን፡ “ 1) የሚቃጠል መስዋዕት (ዘሌ 1፡ 1-17) ሲሆን የክርስቶስን ፍፁምነት ያሳያል፣ 2) የእህል ቁርባን (መስዋዕት) (ዘሌ 2፡ 1-6) ሲሆን አባቱን ለማስደሰት ህይወቱን በመስጠት ለእግዚአብሄር የኢየሱስ ሙሉ መሰጠትን ያሳያል በተጨማሪም 3) የደህንነት መስዋዕት (ዘሌ 3፡ 1-17) ሲሆን በሰዉና በእግዚአብሄር መካከል አስታራቂነቱን ያሳያል “ በማለት ያስቀምጣል ፡፡ እነዚህ ሰዎስቱ ለእግዚአብሄር የሚያስደስት የመዓዛ ሽታ ነበሩ ፤ ማክአርቱር የመጨረሻ ሁለቱን “ የኃጢዓት መስዋዕት (ዘሌ 4፡ 1-5፡ 13) እና የእዳ መስዋዕት (ዘሌ 5፡ 14- 6፡ 7) ለእግዚአብሄር አስቀያሚ ነበሩ ምክንያቱም ክርስቶስን ኃጢዓትን እንደተሸከመ ስላሳዩ (ማቴ 27፡ 46) ፤ በመጨረሻም ቤዛነት/መዋጀት በተፈፀመ ጊዜ ሙሉ ስራዉ እግዚአብሄርን ሙሉ ለሙሉ አስደስቶታል “ በማለት ይገልፃል ፡፡

በሁሉም ድርጊታችን ክርስቶስን መምሰል አለብን ፡፡ ትክክል ላልሆነ ለወሲባዊ ድርጊት ወይም ስስት በህይወታችን ኃጢዓት እንዲሆን መፍቀድ አንችልም (ቁጥር 3) ወይም ደግሞ ከአፋችን ሸካራና የሞኝነት ወይም የቀልድ ንግግር እንዲወጣ መፍቀድ አንችልም (ቁጥር 4) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ የክርስቲያን ህይወት በእንከን፣ በሞኝነት ንግግር፣ በሸካራ ፌዝ ዝቅ ያለ መሆን የለበትም “ ምክንያቱም “ እግዚአብሄርን ስለማያከብሩት እና እኛን ስለመቤዠቱ ምስጋናን የሚሰጡ ስላልሆኑ “ በማለት ይገልፃል ፡፡ ጳዉሎስ ምግባረ ብልሹ የነበሩ፣ ስስታሞች እና ጣዖት አምላኪዎች በእግዚአብሄር መንግስት ርስት እንዳልነበራቸው እና የእግዚአብሄር ቁጣ ይገጥማቸዋል አለ (ቁጥር 5-6)፡፡ እግዚአብሄር ኃጢዓትን አይታገስም/አያልፍም ፤ ጳዉሎስ ኤፌሶዋዊያንን “ በከንቱ ንግግር ከሚያታልሏችሁ “ (ቁጥር 6) ኃሰተኛ አስተማሪዎች ራሳቸዉን ጠብቁ በማለት አጥብቆ በመንገር “ የእነርሱም አጋር/ተባባሪ እንዳይሆኑ “ (ቁጥር 7) ስላስጠነቀቃቸው በመንገዳቸው ቅዱስ፣ ንፁህ እና ፍፁም የሖነ ምንም ነገር አያገኙም ፡፡

ኤፌሶን (5፡ 8-14)፡ ጳዉሎስ በብርኃን መኖርን ከጨለማ ኑሮ ጋር ወደ ማነፃፀር ተጓዘ ፡፡ ማክአርቱር “ ጨለማን ያልተለወጠ ህይወትን ባህሪይ እንደ እዉነት ክፍተት እና በኃሳብ ጥሩነት እና ተገቢ ጉዳዮች ላይ ያለ ክፍተትን ይገልፃል “ በማለት ይናገራል ፡፡ ጳዉሎስ አማኞች በፊት በጨለማዉስጥ እንደነበሩ እና አሁን ግን በብርኃን እንደሚኖሩ ገልፆአል (ቁጥር 8) ፤ አማኞች በፍቅር እና በብርኃን መመላለስ ይገባቸዋል ፤ በብርሀን መኖር የዚያ ብርሀን ፍሬ እንድናፈራ ያደርገናል - ቸርነት፣ ቅድስና እና እዉነት - ስለዚህም እግዚአብሄርን ምን እንደሚያስደስተዉ መለየት እንችላለን (ቁጥር 9-10) ፡፡ አማኞች ፍሬ የለለዉን የጨለማ ስራ በማስወገድ በዚያ ፋንታ የሚያሳፍሩ በጨለማ የተሰሩትን ስራዎች ማጋለጥ አለባቸው (ቁጥር 11-12) ፤ በሌላ በኩል በብርኃን የታየዉ ሁሉ በግልፅ የሚታይ ነው (ቁጥር 13-14) ፡፡

መደምደሚያ

በክርስቶስ እንደ አስተዋይ እንዴት እንደምንመላለስ ትኩረትን ስንሰጥ ለእርሱ ክብርን እናመጣለን ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville, Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1697.

  2. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1538.

  3. 3 MacArthur, pp. 1697-1698.

  4. 4 MacArthur, p. 1698.

  5. 5 MacArthur, p. 1698.

  6. 6 MacArthur, p. 1698.

  7. 7 Nelson’s Commentary, p. 1538.

  8. 8 MacArthur, p. 1698.

ጥያቄዎች

  1. በኤፌሶን 5 መሰረት የእግዚአብሄርን ቁጣ የሚያመጡ አንዳንድ ነገሮች ምንድን ናቸው ? ቁጣዉን ለማስወገድ ምን ማድረግ እንችላለን ?
  2. የተሸዱ እንዳይሆኑ የኤፌሶን ቤተ ክርስቲያ ምን እንድታደርግ ጳዉሎስ መከራቸው ?
  3. በኤፌ (5፡ 16) ጳዉሎስ ምን አድርጉ አለ ? አብዛኃኛዉን ጊዜአችሁን ለመስራት ይህ ለእናንተ ምን ማለት ነው ? ይህ እግዚአብሄር እንድታደርጉት ከሚፈልገዉ ነገር ጋር ይጣጣማል ብላችሁ ታስባላችሁ ?
  4. በኤፌ (5፡ 22-30) ባሎች እና ሚስቶች እንዴት ማድረግ ስላለባቸዉ ነገር ይናገራል ፤ ይህ ለምን አስፈለገ፣ በዚህ ምዕራፍስ ይህን ጳዉሎስ ከምን ግንኙነት ጋር አወዳደረው ?
  5. በኤፌሶን 5 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Ephesians 5

“Therefore, be imitators of God, as dearly loved children. And walk in love, as the Messiah also loved us and gave Himself for us,a sacrificial and fragrant offering to God.”

ህጻናት ልጆች የአባታቸውን ጫማ አድርገው ለመሄድ ሲሞክሩ ደግሞም አባቱን ወይም አቧቷን እንደሆነች ለማስመሰል ሲሞክሩ አይታችሁ ታውቃላችሁ ? አስቂኝ ሊሆን ይችላል ነገር ግን የልጆቹ ልብ ልክ እንዳኣባቱ ወይም እንዳባቷ ለመራመድ ፈልጓል ፡፡ በተመሳሳይ መንገድ እንደ ክርስቶስ ደቀመዝሙር እናንተም የሰማዩ አባታችሁን መምሰል አለባችሁ ፡፡ ልክ ክርስቶስ መሲሁ እንደወደዳችሁና ራሱን ለአብ መልካም መኣዛ ያለው መስዋዕት አድርጎ እንዳቀረበ ሁሉ እናንተም በፍቅርና በብርሃን መመላለስ ይገባችኋል ፡፡ ራስ ወዳድ ባለመሆን በፍቅርና በብርሃን መመላለስን እናንተ እንዴት ታዩታላችሁ ? ጥበበኞች እንጂ ጥበብ የጎደላቸው አትሁኑ ፡፡ ለራሳችሁ ጥሩ የሆነውን ብቻ ሳይሆን ቀድማችሁ ስለሌሎች አስቡ ፡፡ ሞኞች አትሁኑ ነገር ግን የእግዚአብሔር ፍቃድ ምን እንደሆነ እወቁ ፡፡ ሰውን ሳይሆን እግዚአብሔርን ፍሩ ፡፡ በጨለማ ሳይሆን በክርስቶስ ብርሃን ተመላለሱ ፡፡

ዛሬ እስኪ አስቡት የሰማዩ አባታችሁን ጫማ አድረጋችሁ በእርሱ ጫማ ስትራመዱ እናም የእርሱን ፍቅር ስትመስሉ ፡፡ መጀመሪያ ቀልድ ሊመስል ይችላል ነገር ግን በጊዜ ሂደት ስታድጉ ፣ ትለምዱታላችሁ እናም የሰማዩ አባታችሁ ፍቅር ከእናንተ ይፈሳል ፡፡ ፍቅሩን መግለጽ ማካፈል ትችሉ ዘንድ ፣ በፍቅሩ ኑሩ ፡፡

“ እንግዲህ እንደ ተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትከተሉ ሁኑ፥ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ በፍቅር ተመላለሱ ። “

  • ኤፌሶን 5፡1-2

ተጨማሪ ጥቅስ

ኤፌሶን 5:15–21 — “ እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ ፤ ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ ። ስለዚህ የጌታ ፈቃድ ምን እንደ ሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ ። መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና ፤ በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ ፤ ለጌታ በልባችሁ ተቀኙና ዘምሩ ፤ ሁልጊዜ ስለ ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አምላካችንንና አባታችንን ስለ ሁሉ አመስግኑ ። ለእያንዳንዳችሁ በክርስቶስ ፍርሃት የተገዛችሁ ሁኑ ። “

1ኛ ጴጥሮስ 1:14–16 — “ እንደሚታዘዙ ልጆች ባለማወቃችሁ አስቀድሞ የኖራችሁበትን ምኞት አትከተሉ ። ዳሩ ግን ፦ እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ ። “

1ኛ ዮሐንስ 1:6–7 — “ ከእርሱ ጋር ኅብረት አለን ብንል በጨለማም ብንመላለስ እንዋሻለን እውነትንም አናደርግም ፤ ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል ። “