Unity And Diversity In The Body
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ The Head Ephesians 4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በምዕራፍ 3 ጳዉሎስ ክርስቶስ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ነበርና አይሁድና አሕዛቦች ሁለቱም የእርሱ አካል የቤተ ክርስቲያን ለመሆን የተዋሀዱ እንደነበሩ ገልፆአል ፡፡ ኤፌሶን 4 በዚህ መሰረት ላይ ይገነባል ፡፡
ትምህርት
ኤፌሶን (4፡ 1-6)፡ በቁጥር 1 ጳዉሎስ ኤፌሶዊያዊያንን እግዚአብሄር እንዲያደርጉት ጠርቷቸዉ በነበረው “ መመላለስ “ እንዲመላለሱ ይጠራቸዋል ፤ በትህትና፣ በበጎነት፣ በትዕግስት፣ እርስ በእርስ በፍቅር በመቀባበል፣ ሁላችንንም በሚያስተሳስር አንድነት እና ሰላም ይመላለሱ ነበር (ቁጥር 2-3) ፡፡ ጳዉሎስ ሰዎስት ጥሩ ባህሪያትን ይዘረዝራል፡ ትህትና፣ በጎነት እና ትዕግስት ፤ ኮንስታብል ትህትናን “ በእግዚአብሄር ፕሮግራም ተገቢ የሆነ የራስ ግምገማ ሲሆን “፣ ጨዋነት ወይም የዋህነት ደግሞ “ የራስ ማረጋገጫ ተቃራኒ …. ስሜቱን የሚቆጣጠር ሰው ባህሪይ ነው “ በተጨማሪም ትዕግስት ወይም መታገስ “ በቁጣዉስጥ/በመከራ ዉስጥ ሆኖም መታገስ “ ማለት እንደ ሆነ ይገልፃል ፡፡ የእነዚህ ጥሩ ባህሪዎች ዉጤት “ እርስ በእርስ በፍቅር መቀባበል፣ በሚያስተሳስረን ሰላም በመንፈስ አንድነትን መጠበቅ ነው “ (ቁጥር 2-3) (ማቴ 5፡ 9) ፡፡ ሰላም ጠባቂዎች እንድንሆን አልተጠራንም በሰላም እንድንያያዝ እንጂ ፡፡ ይህ የታሰበበት መሆን አለበት !
በቁጥር (4-6) ጳዉሎስ አንድነት የሚኖረንብንን ሰባት መንገዶች ይዘረዝራል ፤ በክርስቶስ አንድ አካል አለን (ኤፌ 1፡ 23)፣ በመንፈስ ቅዱስ አንድ መንፈስ አለን (1ቆሮ 12፡ 13, ኤፌ 2፡ 22)፣ በትንሳኤዉ በኩል የዘላለማዊነት አንድ ተስፋ አለን (1ጴጥ 1፡ 3, 3፡ 15)፣ አንድ ጌታ አለን (ኤፌ 1፡ 22-23, ቆላ 1፡ 18)፣ አንድ እምነት አለን (ኤፌ 2፡ 8-9), በክርስቶስ ሞት በኩል አንድ ጥምቀት አለን (ሮሜ 6፡ 3) እና የሁሉ አባት የሆነ አንድ እግዚአብሄር አለን (ዘዳ 6፡ 4, 2ነገ 19፡ 15) ፡፡ በእነዚህ ሁሉ የተባበርን/ህብረት ነን ፡፡
ኤፌሶን (4፡ 7-11)፡ በመቀጠል ጳዉሎስ ከአንድነት ወደ ብዙኃነት ተጓዘ ፡፡ በክርስቶስ ስጦታ መሰረት ሁሉም አማኝ የእግዚአብሄርን ፀጋ ተቀብለዋል (ቁጥር 7) ፡፡ ሆሄነር “ ክርስቶስ ወደ ሰማይ ለማረጉ መጀመሪያ ዝቅ ወዳለዉ ወደምድር አካል ዝቅ ብሎ እንደነበር ፤ ምናልባትም ይህ የኢየሱስ ሞትን እና መቃብርን የሚያመለክት እንደሆነ “ ይገልፃል ፡፡ ኮንስታብል “ በሞቱ ኢየሱስ ክርስቶስ በኃጢዓት ላይ ድልን ማግኘቱን እና ለቤተ ክርስቲያን እንደ ስጦታ የሚሰጣቸዉን እንደተቤዣቸዉ “ መግለፁን ይቀጥላል ፡፡ ኢየሱስ እኛን ለማዳን እንደወረደ እና ለእያንዳንዳችን በግል ስጦታን በሰጠበት ስፍራ ተመልሶ ወደላይ አረገ (ቁጥር 8-11) ፤ ቁጥር 11 የቲቲአር አንዱ ቁልፍ ነው ፡፡
ኤፌሶን (4፡ 12-14)፡ እነዚህ ስጦታዎች (ሐዋሪያት፣ ነቢያት፣ ወንጌላዊያን፣ ሰባኪዎች እና አስተማሪዎች) 1) በአገልግሎት ቅዱሳንን ለማሰልጠን እና 2) የክርስቶስን አካል ለመስራት/ለማነፀ የተሰጡ ነበሩ (ቁጥር 12) ፡፡ እነዚህ ስጦታዎች ለተወሰነ ጊዜ የተሰጡ ናቸው - “ ሁላችንም በእምነት እና በእግዚአብሄር ልጅ እዉቀት አንድነት ላይ እስክንደርስ ድረስ “ በክርስቶስ ሙሉነት እስከምናድግ ድረስ (ቁጥር 13) ፡፡ እነዚህ ሁሉ ነገሮች እነዚህ ነገሮች ወደ ፍሬአማነት እስኪመጡ ድረስ ይቀጥላሉ ፡፡
በሲንድይ ያዕቆብ የአገልግሎት ሳይት the ministrysite www.generals.org መሰረት፡
- በሁሉም ወራት 1,800 ፓስተሮች አገልግሎትን ይተዋሉ ፡፡
- በአስር አመት ዉስጥ ከፓስተሮች 40 ፐርሰንቱ በአገልግሎት ዉስጥ አይቆዩም ፡፡
- ከሁሉም ፓስተሮች 50 ፐርሰንቱ ስራን መስራት እንደማይችሉ ይሰማቸዋል ፡፡
- ከፓስተሮች 80 ፐርሰንቶቹ አገልግሎታቸዉ በመጥፎ ቤተሰባቸዉን እንደሚጎዳ ያምናሉ ፡፡
- ከፓስተሮች 40 ፐርሰንቶቹ ድብረት የደረሰባቸዉ ወይም ከአገልግሎታቸው ዉጪ መዉጣትን በመፈለግ ይጠፋሉ ፡፡
- 33 ፐርሰንቶች ደግሞ በአምስት አመታቸዉ ዉስጥ ከአገልግሎት ይጠፋሉ ፡፡
ለፓስተር “ ይህን ሁሉ እንድታደርጉ እንፈልጋለን “ እንዳልን ተረዱን ፤ ነገር ግን ጳዉሎስ ኤፌሶዊያንን የቤተ ክርስቲያን ስራ እንዲቀጥል ከፈለጉ የአንድ ሰዉ (የፓስተሩን) ንግግር ብቻ ሳይሆን ብዙ ድምፆች እንደሚያስፈልጉት ይነግራቸዋል ፤ ስለዚህም በአምስት እጥፍ አገልግሎቱ ስለተጠቀመባቸው ስለሌሎቹ አንዳንድ ድምፆች እናዉራ ፡፡
ሐዋሪያነት፡ የእጃችሁን ስዕል ይስላል ፤ የሐዋሪያ ስፍራ በአዉራ ጣት የሚወከል ነው ፡፡ አዉራ ጣት ከቀሩት ጣቶች ጋር ተቃራኒ የሆነ ስራን አይሰራም ይልቁንም መላዉ እጅ እንዲሰራ የታዘዘዉን ከሌሎቹ ጣቶች ጋር በመሆን ይሰራል እንጂ ፡፡ ሐዋሪያ በአስተዳደርነት በመስራት (ከነቢያት ጋር በአንድ ላይ) በትክክለኛዉ አስተምሮና መንፈሳዊ መዋቅር መሰረትን ያስቀምጣል (ኤፌ 2፡ 20) ፡፡ አንድ ሐዋሪያ በክርስቶስ አካል ዉስጥ መሰረት ጣይ፣ ጀማሪ ወይም ተግባር/ስራ ሰጪ/አከፋፋይ ፈጣሪ ነው (1ቆሮ 3፡ 10) ፡፡ ሐዋሪያ ወይም በግሪክ “ ሐዋሪያዎ/አፖስትሎ “ በመጀመሪያ በሮማዊያን አዲስ ምድርን ለመያዝ ባህላቸዉን ለማጥናት ተልኮ የነበረን ሰዉ ለመግለፅ ይጠቀሙበት የነበረ “የተላከ “ ማለት ነው ፡፡ “ እግዚአብሄር ወደ ጠራቸዉ አዲስ ምድር የእግዚአብሄርን ሰዎች የምንመራ ነን ? “ በማለት ይጠይቃሉ ፡፡
ነቢይ፡ ነቢይ የመጀመሪያዉ ወይም አመልካች ጣት ሲሆን በመገለጥ በማገልገል አማኞችን መንገድን ያሳያል ፡፡ የነቢይነት አገልግሎት ከትንቢት ስጦታ የተለዬ ነው - መንግስታዊ አይነት ስልጣንን እና ከፍተኛ የኃላፊነት ሚናን የተሸከመ ነው ፡፡ ትንቢት የመናገር ስጦታ ለመምከር፣ ለመገሰፅ እና ለማነፅ ሲሆን ነቢይ በመሪነት፣ በትዕዛዝ፣ በግሳፄ፣ በፍርድእና በመገለጥ ስፍራዎች ላይ ይገኛል/ይፈስሳል ፡፡ ነቢያት የእግዚአብሄርን ፍቃድ በማወቅ በተለይም ለዚህ ዘመን ከእግዚአብሄር እና ከእዉነቱ ጋር የተዋሀዱ ናቸው ፡፡ ሁኔታቸዉን በመጠየቅ “ የእግዚአብሄር ሰዎች ድምፁን በመስማት በትክክል ምላሽ ይሰጣሉን ? “ በማለት ይጠይቃሉ ፤ ርዕሱ/ኃሳቡ “ ወደ እግዚአብሄር የሚሰማና የሚያደምጥ “ ማለት ነው ፡፡
እረኛ፡ የቀለበት ጣት ወይም የሰርግ ቀለበት ጣት ስለ መንጋዉ ያለዉን የእረኛን ጥንቃቄ መሰጠት ይወክላል ፡፡ ፓስተር ለመጠበቅ እና የሚያስፈልግን ለመስጠት ከአካባቢዉ ቅዱሳን ጋር በእረኝነት ግንኙነት የተሳሰረ ነው ፤ የግንኙነት የፍቅር እና መንፈሳዊ እድገትን መስመርን በማብቀል ደቀመዛሙርት በማድረግና በማሳደግ የእግዚአብሄርን መጋ በመንፈሳዊ ብስለት በመጠበቅ ላይ የሚያተኩሩ የማህበረሰቡ ጠባቂዎች ናቸው ፡፡ ስያሜአቸዉም “ የእግዚአብሄርን ህዝብ የሚጠብቅ “ ማለት ሲሆን “ የእግዚአብሄር ሰዎች ለክርስትና የህይወት አኗኗር የተጠበቁ እና የተዘጋጁ ናቸዉን ? “ በማለት ይጠይቃሉ ፡፡
ወንጌል ሰባኪነት፡ መካከለኛዋ ጣት ወንጌል ሰባኪን የሚያሳይ ሲሆን እስከ አለም ድረስ የሚደርስ ወንጌል ሰባኪነትን ይወክላል ፡፡ የነፍስ አሸናፊዎች ናቸው ነገር ግን ይህን አገልግሎት ያልያዙ ነፍስን ለማሸነፍ ሸክም ያላቸዉ በክርስቶስ አካል ዉስጥ ብዙዎች አሉ ፡፡ ወንጌል ሰባኪነት የመጀመሪያ የነፍሳት አሸናፊ አይደሉም ነገር ግን ቤተ ክርስቲያንን በማነቃቃት ሰዎችን ወደ ድርጊት ለማንቀሳቀስ የተጠሩ ናቸው ፡፡ ወንጌል ሰባኪነት ሌሎችን ለጉዳዩ ይመለምላል ፤ ስያሜአቸው “ መልካሙን ዜና የሚያመጣ “ ማለት ነው ፡፡ “ አዲስ ሰዉ ወደ እግዚአብሄር መንግስት ገብቷል ? “ በማለት ይጠይቃሉ ፡፡
አስተማሪ፡ አስተማሪዎች አስፈላጊ እና ባላንስ የምትሰጠው ትንሻ ጣት ናቸው ፡፡ አስተማሪ በእግዚአብሄር ቃል መርህ ትዕዛዝ በኩል ቤተ ክርስቲያንን በእዉነት ይተክላል ፡፡ የአስተማሪ ልብ ለእዉነት ሲሆን ፍላጎታቸዉም ቤተ ክርስቲያን የመፅኀፍን እዉነት በሚገባ በዝርዝር መረዳቷን እርግጠኛ መሆን ነው ፡፡ ብዙጊዜ የክርስቶስን አካል ለማስተማር በተለዩ እዉነቶች ስፍራ ላይ አብራሪዎች፣ ስነ መለኮት አስተማሪዎች ወይም ደግሞ የተለዬ ሸክም ወይም ማብራሪያ ያላቸዉ ናቸው ፡፡ አስተማሪዎች በመረዳት ይገልፃሉ ፤ ሌሎችን ወደ ተሻለ የእግዚአብሄርን ፍቃድ መለየት መፅሀፍ ቅዱሳዊ መነሻ እንዲኖራቸው ፣ ሌሎችን ወደ ጥበብ በመምራት የሚረዱ፣ ማህበረሱን ለክርስቶስ ቃል የታመነ ሆኖ እንዲቀመጥ የሚረዱ እና የሚተላለፍ አስተምሮን የሚገነቡ ናቸው ፡፡ ስያሜአቸው “ እዉነትን የሚፈልጉ እና የሚያጋሩ “ ሲሆን “ የእግዚአብሄር ሰዎች ራሳቸዉን በመፅሀፍ እና በመፅሀፍ ቅዱስ መርሆች በሚገባ አስገብተዋልን ? በመርሆቹስ እየኖሩ ነውን ? “ በማለት ይጠይቃሉ ፡፡
መደምደሚያ
አንዳንድ የእናንተ ጥያቄዎች በዚህ ዘመንስ የሐዋሪያት እና የነቢያት ተግባር አሁንም አሉ የሚል ነው ፡፡ በመፅኀፍ ቅዱስ ላይ ባነበብኩት መሰረትና በቀመስኩት/በገጠመኝ መሰረት ያሉ ይመስለኛል ፡፡
Hoehner, Harold W. "Ephesians." In The Bible Knowledge Commentary: New Testament, pp. 613-45. Edited by John F. Walvoord and Roy B. Zuck. Wheaton: Scripture Press Publications, Victor Books, 1983, quoted in Constable, p. 90; available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/ephesians.pdf
Thomas L. Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Ephesians, pp. 83-84; available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/ephesians.pdf.
Charles Wesley; quoted in Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Joshua(Nashville: Thomas Nelson Publications, 2003), 2 Constable, pp. 90-91.
Diane Lake, “Do You Know Why Fivefold Ministry is Essential?” Available online at https://www.generals.org/articles/single/do-you-know-why-fivefold-ministry-is-essential/.
ጥያቄዎች
-
በእግዚአብሄር እንደተጠራችሁ ይሰማችኋል ? ጳዉሎስ ሕዝቡን “ በእግዚአብሄር በተጠሩበት መጠራት ህይወታቸዉን እንዲመሩ “ ነገራቸው (ቁጥር 1) ፤ ይህ ጥሪ ለእናንተ በህይወታችሁ ምን ይመስላል ?
-
ጳዉሎስ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን ስጦታ ሰጠ አለ - ሐዋሪያትን፣ ነቢያትን፣ ፓስተሮችን፣ ወንጌል ሰባኪዎችን እና አስተማሪዎችን - ለአገልግሎት ስራ የእግዚአብሄርን ሰዎች ለማዘጋጀት እነዚህ ስጦታዎች ተሰጡ ፡፡ ሁሉም ከእነዚህ ምድብ በአንዱ ዉስጥ ይወድቃል ? ከእነዚህ ዉስጥ በአንዱ ዉስጥ እንደወደቃችሁ ይሰማችኋል ? አዎ ከሆነ የትኛው ? የእናንተ ቤተ ክርስቲያን በእነዚህ በአምስቱ ስጦታዎች እየሰራች ነው ? አይደለም ከሆነ የሆነ ነገር እንዳጣች ይሰማታል ?
-
ኤፌ (4፡ 22) አዲሱ ትርጓሜ “ የቀድሞዉ የኃጢዓት ሰዉነታችሁን አስወግዱ “ ይላል ፤ በመፅሀፍ ላይ ሌላ የት ስፍራ ተመሳሳይ የሆነ ነገርን ይናራል (2ቆሮ 5፡ 17, ቆላ 3፡ 5-10) ? መንፈሳችሁ መታደስ እና መነሳሳት ያስፈልገዋል ? ጥቂት ደቂቃን በመዉሰድ አይምሯችሁን እና ልባችሁን እንዲያድስ እግዚአብሄርን ጠይቁት ?
-
በኤፌሶን 4 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Ephesians 4:1–3
“Therefore I, the prisoner for the Lord, urge you to walk worthy of the calling you have received, with all humility and gentleness, with patience, accepting one another in love, diligently keeping the unity of the Spirit with the peace that binds us.”
እግዚአብሔር እንደ አማኝ በተጠራችሁበት መጠራት እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ ይሻል ፡፡ ለራሳችሁ ጥሪያችሁ ምን እንደሆነ እንኳ እንደማታውቁ ታስቡ ይሆናል ! ባጠቃላይ ኢየሱስ አማኞች እግዚአብሔርንና ሌሎችን እየወደዱ አስቀድመው የእግዚአብሔርን መንግስት ይሹ ዘንድ ያዛል ፡፡ ምናልባት እግዚአብሔር ሌሎች የተለያዩ ጥሪዎችና በመንገዳችሁ መታዘዝን የሚጠይቁ ጥያቄዎች ይኖሩታል ነገር ግን ቀድማችሁ በየቀኑ የእግዚአብሔርን መንግስት ፈልጉ ፡፡ ኢየሱስ አለም የርሱ ታላቅ ፍቅር አዳኝ እንደሆነ ሊያውቅ የሚችለው አማኞች በአንድነት ሲኖሩ እንደሆነ ተናግሯል ፡፡ በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ አንድነት ቁልፍ ነው ፡፡
በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ መለኮታዊ ኃይልና ውበት የሚቀጣጠለው አማኞች የተሰጧቸውን የተለያዩ ስጦታዎች በትህትና እና በፍቅር ሲጠቀሙ ነው ፡፡ ስለዚህ እንዴት ነው ታድያ የመንፈስን አንድነት ማጠንከርና መጠበቅ የምትችሉት ? በትሕትና ሁሉና በየዋህነት በትዕግሥትም ፤ እርስ በእርሳችሁም በፍቅር ተቀባበሉ ሰላምንም ለመጠበቅ ትጉ ፡፡ ስለዚህም ነው ጳውሎስ ለአማኞች አንድነትን መጠበቅ የሚችሉበትን መንገድ የሚናገረው ፡፡ ያለ ትህትና ይህንን በራሳችሁ ማድረግ እንደማትችሉ እወቁ ፡፡ ጌታ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ይሞላችሁ ዘንድ ጠይቁ ከዚያም ምን እንደሚፈጠር ተመልከቱ ፡፡ በትህትና ከመመላለስ ውጪ የመንፈስ አንድነት ሊኖር አይችልም ፡፡
“ እንግዲህ በጌታ እስር የሆንሁ እኔ በተጠራችሁበት መጠራታችሁ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እለምናችኋለሁ ፤ በትሕትና ሁሉና በየዋህነት በትዕግሥትም፤ እርስ በርሳችሁ በፍቅር ታገሡ ፤ በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ ። “
- ኤፌሶን 4፡1-3
ተጨማሪ ጥቅስ
2ኛ ዜና 7:14 — “ በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ ሰውነታቸውን አዋርደው ቢጸልዩ፥ ፊቴንም ቢፈልጉ፥ ከክፉ መንገዳቸውም ቢመለሱ፥ በሰማይ ሆኜ እሰማለሁ፥ ኃጢአታቸውንም ይቅር እላለሁ፥ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ ። “
1ኛ ቆሮንቶስ 1:10 — “ ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሁላችሁ አንድ ንግግር እንድትናገሩ በአንድ ልብና በአንድ አሳብም የተባበራችሁ እንድትሆኑ እንጂ መለያየት በመካከላችሁ እንዳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችኋለሁ ። “
1ኛ ጴጥሮስ 5:5–6 — “እንዲሁም፥ ጐበዞች ሆይ፥ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል ። እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።