Paul's Letters Ephesians

Paul's Ministry To The Gentiles

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ The Head Ephesians 3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 540 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ዶር.ቶም ኮንስታብል በምዕራፍ 3 “ ጳዉሎስ እንደ ገና ለአንባቢዎቹ በመፀለይ እንደጀመረ (ቁጥር 1, 14) ነገር ግን በይበልጥ ስለ ቤተ ክርስቲያን ራሱን በመተርጎም እንደሚነግራቸው “ አመልክቷል ፡፡

ትምህርት

ኤፌሶን (3፡ 1-5)፡ በመጀመሪያዎቹ አምስት ጥቅሶች ጳዉሎስ ለኤፌሶናዊያን ለእርሱ ምን አስፈላጊ እንደ ሆነ ይገልፅላቸዋል ፡፡ እዳየ ዮሐንስ በቁጥር 1 “ ጳዉሎስ በሁለቱ ምዕራፎች አሁን የአሕዛብም የአይሁድም የሁለቱም ንብረት ስለሆኑት የእግዚአብሄር በረከቶች ብሏቸዉ የነበሩትን ለዚህ ምክንያት እንደሚያመለክታቸው “ ይገልፃል ፡፡ ቀድመን እንደገለፅነው ጳዉሎስ በሮም በእስር ቤት እንደ ነበር እና “ የክርስቶስ እስረኛ እንደ ነበር “ (ቁጥር 1) ፤ ጳዉሎስ አገልግሎቱ ለአሕዛብ እንደ ነበር ለእግዚአብሄር የተንበረከከ ነበር (ቁጥር 1) ፡፡ በቁጥር 2 “ መጋቢነት “ የሚለዉ ቃል ባላአደራ ወይም የሰዉን ቤት የሚያስተዳድር በማለት ሊተረጎም ይችላል ፡፡ ጳዉሎስ ለአሕዛብ የእግዚአብሄር ፀጋን ባለአደራነት ኃለፊነት ተሰጥቶት እንደ ነበር እየገለፀ ነበር ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ባለአደራነትን “ የትልቅ ቤተሰብ ወይም ቢዝነስ ሁሉንም የፋይናንስ ጉዳዮች በጥንቃቄ የሚመለከት የአንድ ሰዉ ስራ “ በማለት ሲገልፅ እንዲሁም ደግሞ “ ጳዉሎስ ለእግዚአብሄር ቤት እና መልካሙን ዜና ለመናገር የክርስቶስን ባለጠግነት ለማደል በእግዚአብሄር ኢኮኖሚይ ባለአደራነት የታመነ ነበር “ ፡፡

በቁጥር 3 ጳዉሎስ ለእርሱ የተገለጠዉን “ ሚስጥር “ ያመለክታል ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ የኃይማኖት አገልጋይነት (ባላደራነት) ለኤፌሶን ጥቅም እግዚአብሄር ለጳዉሎስ ሰጥቶት የነበረዉ ቀድሞ ሚስጥር ነበር ፤ አሁን እግዚአብሄር ለአሕዛብ በጳዉሎስ አገልግሎት በይበልጥ ሙሉ ለሙሉ ይህን ሚስጥር እየገለጠው ነበር ፡፡ ሚስጥሩ በክርስቶስ አካል በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ አይሁዶች እና አሕዛቦች ሁለቱም እኩል ቁመና እንደነበራቸው እንደ ነበራቸው “ ይገልፃል ፡፡

የመፅኀፍ ቅዱስ እዉቀት ማብራሪያ “ ሚስጥራትን “ የሚጠቅሱትን የአዲስ ኪዳን ፅሁፎችን ይለያል፡

  • ማቴ (13፡ 11) እና ሉቃ (8፡ 10) ስለ መንግስተ ሰማይ እና ስለ እግዚአብሄር መንግስት በቅደም ተከተላቸዉ ይናገራሉ ፡፡
  • ሮሜ (11፡ 25 እና 16፡ 25-26) በኢየሱስ በኩል ስለሚመጣዉ የድነት እቅድ እስራኤል የደነደነ ልብ እንደ ነበራቸዉ ይገልፃሉ ፡፡
  • 1ቆሮ (4፡ 1) እና 15፡ 51 ስለ አዲስ ኪዳን መገለጥ እና ዳግም ምፅዓት ይናገራሉ ፡፡
  • ኤፌ (1፡ 9, 3፡ 2-4) ስለ እግዚአብሄር ፍቃድ፣ ስለ እግዚአብሄር ፀጋ አስተዳደር እና ስለ ክርስቶስ ናቸው ፤ ኤፌ (3፡ 9 እና 5፡ 32) ስለ ክርስቶስ እና ስለ ቤተ ክርስቲያን ይናገራል ፡፡
  • ቆላ (1፡ 26-27) በእኛ ዉስጥ ስላለዉ ክርስቶስ ይናገራል ፡፡
  • 2ተሰ (2፡ 7) ያለ ህግ ስለሚመጣው የኃይል ሚስጥር ያጋራል ፡፡

አርኖልድ ፍሩችታንባም እንደ ሚስጥራት የተገለፁትን አራት የቤተ ክርስቲያን ባህሪያትን ያቀርባል፡

አይሁድ እና አሕዛብ በቤተ ክርስቲያን አንድ የሚሆኑ ናቸው (ኤፌ 3፡ 1-12) ፡፡

ክርስቶስ በእያንዳንዳችን አማኞች ዉስጥ ያድራል (ቆላ 1፡ 24-27) ፡፡

ቤተ ክርስቲያን እንደ ክርስቶስ ሙሽራ ትሰራለች (ኤፌ 5፡ 22-32) ፡፡

ቤተ ክርስቲያን ትነጠቃለች (1ቆሮ 15፡ 50-58) ፡፡

ፍሩችታንባም “ እነዚህ አራት ሚስጥሮች ቤተ ክርስቲያን ከእስራኤል የምትለይበትን ጥራቶች ይገልፃል “ በማለት ይገልፃል ፡፡

ጳዉሎስ ኤፌሶዊያን ቃሉን እያነበቡ ስለ ነበር ስለ ሚስጥሩ ጳዉሎስ ምን እያለ እንደ ነበር አሁን መረዳት እንደሚችሉ ይገልፃል (ቁጥር 4) ፡፡ ጳዉሎስ ይህ መገለጥ በቀድሞዉ ትዉልድ ለማንም ያልተሰጠ እንደ ነበር ገለፀ ይህ ማለትም ይህ መገለጥ ለጳዉሎስ የተሰጠም አልነበረም (ቁጥር 5) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ጴንጤ ቆስጥነት እንደ ብሉይ ኪዳን አስተዳደር ስለ እግዚአብሄር እዉቀት እና ስለፀጋዉ ትልቅ ጉዳይ ከመሆኑ በፊት በሌላ እድሜ የኖሩ ሰዎች እንደ ነበሩ ፤ ይሁን እንጂ ያ ዕዉቀት በክርስቶስ ኢየሱስ እንደምንቀበለዉ መገለጥ ሁሉም የያዙት አልነበረም …. በአንድ አካል ዉስጥ ከአይሁዶች ጋር እኩል መሆኑ ከዚህ በፊት ያልተገለጠ ሚስጢር ነበር “ ፡፡

ኤፌሶን (3፡ 6-13)፡ ዋይርስቤ ቁጥር 6 አሕዛቦች “ ከአብርኃም ጋር ባለዉ ኪዳን መሰረት (ገላ 3፡ 29) እግዚአብሄር ከሰጣቸዉ መንፈሳዊ ብልፅግናዎችንም ከአይሁዶች ጋር በአንድነት የሚወርሱ እና እንደሚጋሩ “ እንደሚያሳይ ይገልፃል ፡፡ በቁጥር 7 ጳዉሎስ “ በእግዚአብሄር ፀጋ የዚህ ወንጌል አገልጋይ ተደርጎ እንደ ነበር “ ይገልፃል ፤ አንዳንድ ትርጓሜዎች “ በአገልጋይ “ ስፍራ ላይ “ አገልግሎትን “ ይጠቀማሉ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ጳዉሎስን ከመከሰስ ወደ ቅዱስ፣ ከፈሪሳዊነት ወደ ሐዋሪያነት ክርስቲያኖችን ከአሳዳጅነት ወደ ክርስቶስን ሰባኪነት ለመቀየር መለኮታዊ ፀጋን እንደወሰደ ፤ ቀጥሎም ጳዉሎስን የእግዚአብሄር አገልጋይ ማድረግ እንዲቻል መለኮታዊ ኃይል እና ስልጣን እንደ ወሰደ “ ይገልፃል ፡፡ ጳዉሎስ - ከቅዱሳን ሁሉ ያንስ ለነበረው ለእርሱ (ቁጥር 8) የዚህ ሚስጥር ፀጋ ተሰጥቶት እንደ ነበር ደግሞ ይናገራል (1ጢሞ 1፡ 15) ፤ የጳዉሎስ አሳይመንት ወንጌልን ለአሕዛብ የመስበክ (ቁጥር 8) እና የቤተ ክርስቲያንን ሚስጥር ለሁሉም መግለፅ ነበር (ቁጥር 9) ፡፡ በቁጥር 10 ጳዉሎስ ስራው “ የእግዚአብሄር ብዙ የጥበብ ስራዎች “ እንደ ነበርና በሰማያት ላሉ ባለስልጣናት እና አስተዳዳሪዎች ይታወቃል አለ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ የእግዚአብሄር ብዙ እጥፍ ጥበብ የቤተ ክርስቲያን አባል በመሆን ለመለዓክት የሚታይ ይሆናል…. መለዓክትም ፀጋዉ በእኛ ዉስጥ ሲሰራ በመመልከት ስለ እግዚአብሄር ፀጋ ይማራሉ (1ቆሮ 11፡ 10) “ ፤ ይህ ሁሉ የእግዚአብሄር ዉስጣዊ እቅድ አካል ነበር (ቁጥር 11) ፡፡ በክርስቶስ ስራ ምክንያት ወደ እግዚአብሄር ባለን መግባት ድፈረት እና መተማመን ሊኖረን ይችላል (ቁጥር 12) ፤ ጳዉሎስ ኤፌሶዊያንን ይሁ የእግዚአብሄር እቅድ ስለ ነበር በእስራቱ የሚያንጓጡጡት /ተስፋ የሚያስቆርጡት እንዳይሆኑ ነገራቸው (ቁጥር 13) ፡፡

ኤፌሶን (3፡ 14-21)፡ በቁጥር 14 ጳዉሎስ እንዴት እንደሚፀልዩ ኤፌሶዊያንን ማስተማር ጀመረ ፤ ጳዉሎስ በሰማይና በምድር በሁሉም ላይ አባት ከነበረዉ/ከሆነዉ ከእግዚአብሄር ፊት እንበረከካለሁ አለ (ቁጥር 15) ፡፡ ኤፌሶዊያን በእግዚአብሄር ኃይል በመንፈሱ በኩል የጠነከሩ እንዲሆኑ ፀለየላቸው (ቁጥር 16) ፤ በተጨማሪም ጳዉሎስ ኤፌሶዋዊያን በክርስቶስ ፍቅር በመፅናት እና የእግዚአብሄርን ፍቅር ጥልቀት መረዳት እንዲችሉ ፀለየላቸው (ቁጥር 17-19) ፡፡ ጳዉሎስ ይህን ፀሎት አይሁዶች ወይም አሕዛቦች በአንድ ላይ በክርስቶስ አካል ላይ ይመጣሉ በሚለዉ ክርክር ላይ ይናገራል ፡፡ የጳዉሎስ ምላሽ የእግዚአብሄር ፍቅር ሊይዙት ከሚችሉት ማንኛዉም ነገር በላይ እንደነበር ነበር ፡፡ በቁጥር 20 ጳዉሎስ አምላክን ማመስገኑን ጀመረ - በፀሎቱ መጨረሻ ላይ ባርኮቱ/መባረኩ፡ “ እንግዲህ እንደሚሰራው ኃይል መጠን ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ ይልቅ እጅግ አብልጦ ሊያደርግ ለሚቻለው ፤ ለእርሱ በቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ኢየሱስ እስከ ትዉልዶች ሁሉ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን ፤ አሜን “ ፡፡

መደምደሚያ

ከእግዚአብሄር ፀጋና ኃይል የተነሳ ጳዉሎስ እግዚአብሄር አይሁዶችን እና አሕዛቦችን በአንድ ላይ የክርስቶስ አካል እንዲሆኑ ማምጣት እንደሚችል አምኗል ፡፡ኢየሱስ የአካሉ ራስ ነው ፡፡

2 John Eadie, Commentary on the Epistle to the Ephesians, 2d ed. (Edinburgh: %. & T. Clark, 1883; reprint ed. Minneapolis: James and Klock, 1977), pp. 208–209; quoted in Thomas L. Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Ephesians, p. 65; available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/ephesians.pdf.

  1. Thomas L. Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Ephesians, p. 64; available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/ephesians.pdf.

  2. Constable, p. 65.

  3. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1535.

  4. Nelson’s Commentary, p. 1535.

  5. MacArthur, p. 1654.

  6. Arnold G. Fruchtenbaum, “Israel and the Church,” Issues in Dispensationalism, ed. Wesley R. Willis and John Master (Chicago: Moody Press, 1994), pp. 117–118; quoted in Constable, p. 67.

  7. Fruchtenbaum, p. 117–118.

  8. Nelson’s Commentary, p. 1535.

  9. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Ephesians (Colorado Springs: David C. Cook, 1989), p. 28

  10. Nelson’s Commentary, p. 1535

ጥያቄዎች

  1. ጳዉሎስ በእስርቤት እያለ በኤፌ (3፡ 6) ለህዝቡ የእግዚአብሄርን እቅድ አስቀመጠ ፤ ይህ እቅድ ከቀድሞዉ ኪዳን እንዴት የተለዬ ነው (ዕብ 10፡ 1-18) ? በሁለቱ መካከል ተመሳሳይነት ነበር ?
  2. በኤፌ (3፡ 12) በአዲሱ ትርጉም ጳዉሎስ፡ “ በእርሱ ዘንድ ባለ እምነታችን በኩል በመታመን ድፍረትና መግባት በእርሱ አለን “ አለ ፤ በእግዚአብሄር መገኘት ፊት በድፍረት ትመጣላችሁ ? ካልመጣችሁስ ለምን?
  3. ሊደረስበት አይችልም ብላችሁ ስላሰባችሁት ነገር ፀልያችሁ ታውቃላችሁ ? በኤፌ (3፡ 20) በአዲሱ ትርጓሜ ጳዉሎስ እግዚአብሄር ከምንጠይቀዉ እና ከምናስበዉ በላይ “ በብዛት ማድረግ እንደሚችል “ ተናግሯል ፡፡ በአይምሯችሁ ስለማይቻል ነገር ጠይቃችሁ ታውቃላችሁ ? አዎ ከሆነ ምን ነበር የለም ካላችሁ ለምን ?
  4. በኤፌሶን 3 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Ephesians 3:14–15

“For this reason I kneel before the Father from whom every family in heaven and on earth is named.”

ጳውሎስ በእግዚአብሔር አብ ፊት ተንበርክኮ አማኞች በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ይበረቱ ዘንድ ጸለየ ፡፡ ጳውሎስ አማኞች እግዚአብሔር ለእነርሱ ያለውን ፍቅር እንድረዱና እንድቀምሱ ደግሞም እስከ እግዚአብሔር ፍጹም ሙላት ደርሰው ይሞሉ ዘንድ ወደደ ፡፡ ጳውሎስ በኤፌሶን ላሉ አማኞች መንፈሳዊ ጤንነት አሰበ ፡፡ እነርሱ በቀላሉ ተስፋ ሊቆርጡ እንደሚችሉ ስለተረዳ በጉልበቱ ተንበርክኮ መጸለዩን ቀጠለበት እናም በግልጽ ስለ አማኞች ወደ እግዚአብሔር ጮኸ ፡፡

በምትጸልዩበት ጊዜ ተንበርክካችሁ ታውቃላችሁ ? ጳውሎስ ለሚጨነቅላቸው ተንበርክኮ በመጸለይ አሳየ ፤ ይህንን በሚቀጥለው ጊዜ ስትጸልዩ መሞከር ብልህነት ነው ፡፡ መንበርከክ ትህትናን ያሳያል ፡፡ ምናልባት ለአካላችሁ ምቾትን ላይሰጣችሁ ይችላል ፡፡ ሁሉንም ነገር ለክርስቶስ መስጠት አለባችሁ የማይመቿችሁንም ነገሮች በማድረግም ጭምር ፡፡ እናንተ ከምትጠይቁትና በውስጣችሁ እየሰራ ያለው የእርሱ ኃይል ሊሰራ ይችላል ብላችሁ ከምታስቡት የበለጠና የላቀ ነገር ማድረግ እንደሚችል በማመን ፣ በእግዚአብሔር ፊት ተንበርክካችሁ ጸልዩ ፡፡ ጭንቀቶቻችሁን ሁሉ ለእርሱ ስጡትና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ይሞላችሁ ዘንድ ጠይቁት ፡፡ ተንበርክኮ መጸለይን ልማዳችሁ አድርጉት !

“ ስለዚህ ምክንያት በሰማይና በምድር ያለ አባትነት ሁሉ ከሚሰየምበት ከአብ ፊት እንበረከካለሁ ፡፡ “

  • ኤፌሶን 3፡14-15

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 95:6 — “ ኑ፥ እንስገድ ለእርሱም እንገዛ፤ በእርሱ ባደረገን በእግዚአብሔር ፊት እንበርከክ ፡፡ “

ኤፌሶን3:20–21 — “ እንግዲህ በእኛ እንደሚሠራው ኃይል መጠን ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ ይልቅ እጅግ አብልጦ ሊያደርግ ለሚቻለው ፥ ለእርሱ በቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ኢየሱስ እስከ ትውልዶች ሁሉ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን ። “

ፊልጵስዩስ 2:9–11 — “ በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው ፤ ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ ፥ መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው ። “