A Brick In The Temple
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ The Head Ephesians 2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ጳዉሎስ ኤፌሶንን ለሁሉም ቤተ ክርስቲያንት በኃይል ተጮሆ እንዲነበብ ፃፈው ፡፡ በጊዜዉ አንድ አንቀፅ መልዕክት/ደብዳቤ እንደተቀበላችሁ ታነባላችሁ ? በእርግጥ አይደለም ፡፡ ስለዚህ እነዚህን መልዕክቶች በአንድ በማስቀመጥ በሙሉነት መነበብ ያስፈልጋቸዋል ፤ መልዕክቱ በዚያ መንገድ የተሻለ መረዳት ስላለው እናንተም በመጮኽ እንድታነቡት አበረታታችኋለሁ ፡፡ በሚያስደንቅ ሁኔታ በማጥናት የመልዕክቱን ሙሉዉን ሀሳብ ለማግኘት ወደ ክፍሎች ከመከፋፈል በፊት የመልዕክቱን ሙሉ ሀሳብ ማግኘት አስፈላጊ ነው ፡፡ ጳዉሎስ ለእኛ ሁለት ስዕሎችን ስሏል፡ 1) በቁጥር 1-3 ከክርስቶስ በፊት እና 2) በቁጥር 4-6 ከክርስቶስ በኋላ ፡፡ ይህ መልክ ከሞት ወደ ህይወት የመቀየር እና በጠለቀ ልብ ላይ ማን እንደ ነበር እና ማን እንደሆንን ነው ፡፡
ትምህርት
ኤፌሶን (2፡ 1-3)፡ ጳዉሎስ የቀደመዉ መልክ እንዴት ጥቁር እንደ ነበር ለመግለፅ ሙታን/ሙት የሚለዉን ቃል ተጠቀመ ፤ ያ ሞት የኃጢዓት ዉጤት ነበር ፤ ኃጢዓት ይገላል ፤ ያጠፋልም ፡፡ አንዳንድ ማብራሪያዎች ኤፌሶን በብዛት መንፈሳዊ አለም ላይ እና ከሌሎች አዲስ ኪዳን መፅሀፍት በይበልጥ የሚገፋ እንደሆነ ይፅፋሉ ፡፡ እግዚአብሄር በህይወት እንድትኖሩ ይፈልጋል፣ ሰይጣን ደግሞ ሙታን እንድትሆኑ ይፈልጋል ፤ ይህ ትግል ሁላችንንም የሚገጥመን ጦርነት ነው (ቁጥር 2) ፡፡ ጳዉሎስ እኛም በብዛት በእንደዚህ አይነት ተመሳሳይ ሁኔታ ስር መኖራችንን አብራርቷል (ቁጥር 3) ፤ ባህል የምንፈልገዉን ማንኛዉንም ነገር ለማድረግ እንደችሎታ ነፃነትን ይገልፃል ፡፡ በዚያ ችግሩ በኃጢዓት ነው ፤ የምንፈልጋቸዉ ነገሮች መጨረሻቸዉ በራስ ላይ ጥፋት የሚያደርሱ ናቸው ፡፡ እነዚህ ጉጉቶች ከጋብቻ በፊት ካለ ወሲብ እና ወደ ቀይ መብራት ለመሮጥ ወይም ደግሞ አንድ ተጨማሪ አንድ የሀርሼይ መሳምን ለመብላት ከጋብቻ ዉጪ ከሆነ ወሲብ ሁሉንም ምክንያታዊ እንድንሆን በኃይል ምክንያቶች የሚሆኑን ናቸው ፡፡
ጳዉሎስ የሰዉ ልጅን “ ከፍጥረታችሁ የቁጣ ልጆች ነበራችሁ “ በማለት ገልፆአል ፡፡ ቁጣ በኃጢዓት ምክንያት የሚመጣ በኃጢዓት ላይ የእግዚአብሄር ቅዱስ ቁጣ እና ፍርድ ነው ፡፡ እግዚአብሄር ኃጢዓትን ይጠላል በኑሮአችን ዉስጥ ኃጢዓት የሚያደርገዉን ይንቃል ፤ ነገር ግን ከእግዚአብሄር ፍቅር በተቃራኒ የእግዚአብሄርን ቁጣ ለማየት እናዘነብላለን ፡፡ ስለዚህም ከእነዚህ መካከል ለመምረጥ መገደድ ይሰማናል በእግዚአብሄርም ፍቅር ላይ ማትኮርን እንመርጣለን ፤ በእርግጥ ሁለቱ ተቃራኒዎች አይደሉም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸዉ እንጂ ፡፡ እግዚአብሄር ህይወታችንን የሚሰርቀዉን ነገር የማይጠላዉ ከሆነ ሙሉ ለሙሉ የወደደ ሊሆን አይችልም ፡፡
ኤፌሶን (2፡ 4-6)፡ እግዚአብሄር ካልወደደን በኑሮአችን/በህይወታችን ዉስጥ ኃጢዓት ስለሚያመጣዉ ዉጤት አይጠነቀቅም ማለት ነው ፡፡ ሙታን ነበርን በስጋ ፍላጎታችንም የኃጢዓትን ተፈጥሮአችንን የምናስደስት ነበር ፡፡ ሙት የሚለዉ ቃል የዓረፍተ ነገሩ ትኩረት አይደለም ፡፡ ሙታን ነበርን ነገር ግን ሞት በዘላቂነት በእኛ ላይ አይሰለጥንም / አይገዛንም ፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ የተገኘ ተስፋ አለን ፡፡ ጳዉሎስ ቁጥር 4 “ ነገር ግን “ በማለት ይጀምራል ፤ መሀሪና ባለጠጋ አምላካችን “ ከወደደን ከታላቅ ፍቅሩ የተነሳ “ ህያዋን አደረገን (ቁጥር 4-5) ፡፡ ቅጣቱ ስለተከፈለ የኃጢዓት ባርነታችን ለዘላለም ተሰብሯል ፤ የዳንን ብቻ አይደለንም እግዚአብሄር ከኃጢዓት ሞት ወደ ህይወት በማንሳት ከክርስቶስ ጋር በሰማይ አስቀመጠን (ቁጥር 6) ፡፡
ኤፌሶን (2፡ 7-10)፡ እግዚአብሄር እንዲህ አይነቱን ለምን ያደርጋል ? እግዚአብሄር እርሱ ምን እንደሚመስል ለአለም ለማሳየት ይህን አደረገ ፡፡ እኛ የእግዚአብሄር የሚታይ እረዳቶች ነን ፤ ሰዎች በእኛ ላይ በተመለከቱ ጊዜ የተቀበልነዉን የፍቅርንና የድነትን ስጦታ ነፀብራቅ ማየት አለባቸው ፡፡ ቁጥር 8-9 የኤፌሶን መፅሀፍ ዋና ሀሳብ እና በስዓት ማሰሪያ ሰማያዊ ስፍራዎች ላይ ናቸው ፤ እነዚህን ጥቅሶች ያዙ/አስታዉሱ ምክንያቱምየድነትን የሚያስደንቅ ኃይለኛ መልዕክትን ስለሚናገሩ - ድነት በእምነት በኩል በፀጋ ነው ፡፡ ለመልካም ስራ ዳንን እንጂ በስራ አልዳንም፣ ስለተነገረን አልነበረም በእግዚአብሄር ምህረት ምላሽ እንጂ (ቁጥር 10) ፡፡
በፊት እና በኋላ የነበረዉን በአንድ ላይ ሲቀመጡ - በክርስቶስ ህይወት፣ ሞት እና ትንሳኤ ተገዝተናል፡
- ሙታን ነበርን አሁን ግን ህያዋን ነን ፡፡
- ጽድቅ የጎደለን ነበርን አሁን ግን ነፅተናል ፡፡
- የቁጣ ዉጤቶች ነበርን ነገር ግን አሁን በእግዚአብሄር ይቅር ባይነት ቆመናል ፡፡
በዚያ ብርሃን ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ እንደተወደደ ታላቅ ሙሽራ የወንጌልን ተልዕኮ የልብን እና ጠንካራን ስራ ታደርጋለች ፤ ይህ እግዚአብሄርን እንድናደርገዉ የሰጠን ዋጋ የሚያስከፍል፣ የሚያስቀይም እና በብዙ ተቃዉሞ የሚበዛበት ስራ ነው ነገር ግን ለሁሉም ዋጋ መክፈል፣ እምባ እና ግጭቶች ዋጋ አለው ፡፡ መንፈሳዊ ህይወታችሁ የበፊቱ መልክ ነዉ ወይስ የኋላው መልክ ነው ? በፊት የነበረዉ ከሆነ በዚህ ሳምንት ሁሉንም ቀን ቁጥር 8-10 እንድታነቡ እሞግታችኋለሁ ፤ የእግዚአብሄር ቅዱስ መንፈስ በእነዚህ ቁጥሮች ላይ በትክክለኛ የህይወት መንገድ ምን ማለት እንደሆኑ ይገልፅላችኋል ፡፡ የኋላዉ ነዉ ከሆነ እግዚአብሄር በዚህ ሳምንንት ለእናንተ ያዘጋጀዉን መልካም ስራ ተስፋ አድርጉ ፡፡ እግዚአብሄር ያዘጋጀላችሁን እድሎች ለማየት ዙሪያችሁን ተመልከቱ ፡፡
ኤፌሶን (2፡ 11-12)፡ ቤቱ የሚሰራባቸሀ ሸክላዎች እንድትሆኑ በእግዚአብሄር ተመርጣችኋል ፤ ምርጥ የግንባታ መስሪያ እቃዎች መሆን አለብን ፡፡ ከክርስቶስ በፊት ግን ኑሮአችን መሰናክል ነበር ፤ ከእግዚአብሄር የሚለዩን ግንቦች እና መክፈያዎች ኃይማኖታዊና ማህበራዊ ሁለቱም እዉን ናቸው ፡፡ አይሁዶች ወርሰዉት በነበረዉ እድል እና ከሌሎች ከሁሉም ህዝቦች በለያቸዉ አካላዊ ግንብ የተጠነቀቁ ነበሩ ፤ በቤተ መቅደስም እንኳን ግንቦች አይሁዶችን ከሌሎች ለመለየት የተገነቡ ነበር ፡፡ መገረዝ ከእግዚአብሄር ጋር ያላቸዉን የተለዬ ግንኙነት የሚያሳይ ዉጫዊ ምልክት ነበር ፤ በኃጢዓታችን ከእግዚአብሄር የተለየን ነበርን (ቁጥር 1-10) ፡፡
ኤፌሶን (2፡ 13-18)፡ “ አሁን ግን “ ግንቡ ስለተወገደ በእኛ እና በእግዚአብሄር መካከል ያሉ መለያዎች/መሰናክሎች ከዚህ በኋላ እንደማይኖሩ ያሳስበናል (ቁጥር 13-14) ፡፡ በኢየሱስ ሞት እርስ በእርስ አይሁዶችን ከአሕዛብ ጋር አስታረቃቸው (ሰላምን አደረገ) ፤ ሀሳቡ እንደ ልጆቹ ወደ አንድ አዲስ የተዋሀደ ህዝብ ለማድረግ ኢየሱስ እርስ በእርስ የለየንን ግንብ ለመቅደድ፣ ለማጥፋት እና ለመደምሰስ የመጣ መሆኑ ነው ፡፡ ጥሪአችን ለእግዚአብሄር እዉነት በመቆም በእግዚአብሄር ፀጋ እንድንኖር እና እንድናገለግል ነው ፡፡
ኤፌሶን (2፡ 19-22)፡ ጳዉሎስ አንባቢዎቹን በሁሉም መብቶች እና እድሎች በዚያ ዜግነት በሚሄደዉ ሁሉ የእግዚአብሄር መንግስት ዜጋ እንደሆኑ ያሳስባቸዋል ፤ ያ ማለት ሁለት አካል አይደለንም - አንድ አካል ነን ፤ ለመንፈስ ቅዱስ እንደ ማደሪያ ስፍራ የክርስቶስ አካል እና የእግዚአብሄር ቤተ መቅደስ ሁለቱንም ነን ማለት ነው ፡፡ የሜንዲ ስዕል ኢሳያስ “ የተፈተነ፣ የከበረ እና መሰረቱ የፀና “ እና “ የሚያምንበት አይናወጥም “ (ኢሳ 28፡ 16) በማለት ከገለፀ የማዕዘን ድንጋይ የሚመጣዉን የእግዚአብሄርን ክብር ያሳያል ፡፡ የማዕዘን ድንጋይ የስትራክቸር በጣም አስፈላጊ ክፍል እና በጥንካሬነቱና በእዉነተኝነቱ በጥንቃቄ የሚመረጥ ነበር ፤ የማዕዘን ድንጋይ የህንፃን አቅጣጫ የሚያስቀምጥ፣ ክብደቱን የሚሸከም እና የቀረዉን ስትራክቸር በአንድ ላይ የሚያስተሳስር ነው ፡፡ እንደ ቤተ ክርስቲያን ለእኛ ኢየሱስ ማለት ያ ነው - ሁላችንንም በአንድ የሚያስተሳስር እና በአንድ የሚይዘን ነው (ቁጥር 21) ፡፡ እንደ አማኝ የእግዚአብሄር ብቻ መኖሪያ ስፍራ ስለሆነ የዚያ ህንፃ/ቤተ መቅደስ አካል ነን ፡፡
መደምደሚያ
ሸክላዎች ከሆናችሁ ራሳችሁን እንዴት ታዩታላችሁ ? ወደ ቤተ ክርስቲያን የምትሄዱ ሰዎች ናችሁ ወይስ ቤተ ክርስቲያን የሆናችሁ ናችሁ ? በእነዚህ ሁለት ጥያቄዎች ትልቅ ልዩነት ስላለ መልሳችሁን ማወቅ አስፈለጊ ነው ፡፡ ወደ ቤተ ክርስቲያን ብቻ የሚሄዱ ከዚያም ወደ ቤት በመሄድ ህይወታቸዉን ተፅዕኖ በማያደርግ መንገድ ላይ የሚቀጥሉ ሰዎች አለ ፡፡
ሁሉም ነገር ተቀይሯል ፤ ቤተ ክርስቲያኖቹ እንድንሆን ለእኛ ለሙሽሮቹ ክርስቶስ ሞቷል ፡፡
በኑሮአችን በእግዚአብሄር የተቀረጣን ባዶ ስፍራ እንድንሞላ ኢየሱስ ስለ እኛ ሞተ ፤ ያ መልካም ዜና ነው ፡፡
በኑሮአችን አላማ ባለዉ ቅርፅ የተቀረፀውን ባዶ ስፍራ ለመሙላት እንድናደርገው በመጀመሪያ ለእኛ ያዘጋጀዉን ስራ ኢየሱስ ስለ እኛ ስለሞተ መልካሙን ስራ ማድረግ እንችላለን ፡፡
ኢየሱስ እኛን ሸክላዎች በማድረግ የቅዱስ ቤተ መቅደሱ አካል ዉስጥ ያካትተናል ፡፡
በቅድሚያ እንድናደርገው እግዚአብሄር ለእኛ ያዘጋጀዉን መልካም ስራ እንድንሰራ በክርስቶስ ኢየሱስ የተፈጠርን የእግዚአብሄር ሰራተኞች ነን ፡፡ ሸክላ/የግንብ/መስሪያ ድንጋዮች ሁኑ !
ጥያቄዎች
-
ኤፌ (2፡ 1) እና ሮሜ (6፡ 23) ፤ በእነዚህ ጥቅሶች የተናገረዉን ሞት ግለፁ ፡፡
-
በኤፌ (2፡ 8-9) ጳዉሎስ በስራ ሳይሆን በእምነት በፀጋ በኩል እንደዳንን አስተማረ ፤ በኤፌ (2፡ 10) ስለተጠቀሱት መልካም ስራዎች እንዴት እንረዳቸዋለን (ሮሜ 9፡ 32, 1ጢሞ 6፡ 18, ዕብ 10፡ 24, ያዕ 2፡ 26, 3፡ 13) ?
-
በኤፌ (2፡ 14) ላይ የተጠቀሰዉ ሰላም ለሌላ የጠላት ቡድን የቀረበ/የሚገኝ ነው ? ብዙ ጊዜ አንዱ በሌላዉ ላይ ጠላት የሆኑ ጥቂት ቡድኖች ምንድን ናቸው ? ኤፌ (2፡ 16) ከአይሁዶች እና ከአሕዛብ በተጨማሪም ለሌሎች ቡድኖች እንደ ተስፋ መልዕክት ታዩታላችሁ (ገላ 3፡ 28) ? የታረቁ ታላቅ ጠላትነቶች ምንድን ናቸው (ሮሜ 8፡ 7-9, ኤፌ 2፡ 13, ቆላ 2፡ 13-14) ?
-
ኤፌሶን 2 ክርስቶስ ሰላማችን እንደሆነ እና በመምጣት ሰላምን እንደሰበከ (እንደተናገረ) ይነግረናል ፤ በአዲስ ኪዳን መጀመሪያ የታወጀዉ መልዕክት ሰላም ምንድን ነው (ሉቃ 1፡ 79, 2፡ 10-14) ? በወንጌል ላይ ኢየሱስ የተናገረዉን ሰላም የት ላይ ልታገኙት ትችላላችሁ ?
-
በኤፌሶን 2 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ አሳያችሁ ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Ephesians 2:14
“For He is our peace, who made both groups one and tore down the dividing wall of hostility.”
በምህረቱ ባለጠጋ ደግሞም ጸጋው ብዙ የሆነ እግዚአብሔር እርሱ ሰላማችሁ ነው ፡፡ ክርስቶስ የመጣው በእምነት ለሚያምኑ ለእነርሱ ሰላም ይሆንላቸው ዘንድ ነው ፡፡ በጌታ ላይ ብቻ ስትደገፉ ስትኖሩ ፤ በራሳችሁ መታገልን ስታቆሙ ፤ በደንብ ስትረጋጉና ፍቃዳችሁን በደስታ ለእርሱ አሳልፋችሁ ስትሰጡ ስትማርኩ ከዚያም ክርስቶስ ሰላማችሁ ይሆናል ፡፡ እጆቻችሁን በመዘርጋት ወደላይ አንሱ ፡፡ “ በአንተ አምናለሁ ፤ ምህረትህን እቀበላለሁ ፤ ጸጋህን እቀበላለሁ ፤ ፍቅርህን እቀበላለሁ “ በማለት ወደ ጌታ ጸልዩ ፡፡
እግዚአብሔር ሁሉም ነገር በእጁ ነው ፡- ጉዳዮቻችሁ ፣ ጭንቀቶቻችሁ ፣ ችግሮቻችሁ ደግሞም ኀዘናችሁ ሁሉም ፡፡ ክርስቶስ የመጣው እናንተ ሰላም ይኖራችሁ ዘንድ ነው ፡፡ እርሱ በህይወታችሁ ሰላም ይኖራችሁ ዘንድ እንደኛውና ብቸኛው መተማመኛ ነው ፡፡ እርሱ በዚህ አለም የሚገኝ ብቸኛው እውነተኛ ሰላም ነው ፡፡ ኢየሱስ ብቻ ፡፡ ምንም ነገር ሰላምን አይሰጣችሁም ፡፡ ምንም ነገር ፡፡ ስለዚህ ሌላ መፈለጉን አቁሙና እርሱን ተቀበሉ ፡፡ በእርሱም ሰላም ውስጥ ማረፍ ትችሉ ዘንድ በደንብ ተረጋጉ ፡፡ ስለ ሰላሙም ሁልጊዜ እርሱን አመስግኑት ፡፡
“ እርሱ ሰላማችን ነውና ሁለቱን ያዋሐደ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ ፡፡ “
- ኤፌሶን 2፡14
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 85:8 — “ እግዚአብሔር አምላክ የሚናገረውን እሰማለሁ፤ ሰላምን ለሕዝቡና ለቅዱሳኑ ልባቸውንም ወደ እርሱ ለሚመልሱ ይናገራልና ። “
ዮሐንስ 16:33 — “ በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ ። “
ኤፌሶን 2:17 — “ መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን፥ ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን የምስራች ብሎ ሰበከ :: “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።