The Work Of The Trinity
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ The Head Ephesians 1 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ይህ ክፍል ጥናታችንን ለኤፌሶን በጳዉሎስ መልዕክት ላይ ይጀምራል ፡፡ ለኤፌሶን ዓረፍተ ነገራችን/ሀረጋችን ራስ የሚል ነው (ኤፌ 1፡ 22, 5፡ 22-23) ፡፡ በመፅሀፍ ቅዱስ ላይ ሁሉም 66 መፅሀፍ የሚያመለክተዉ እና የሚያንፀባርቀው አንድን ነገር ነው - ኢየሱስ ክርስቶስ የመላዉ መፅሀፍ ቅዱስ ፍፃማ መሆኑን ነው ፡፡ ራሱ በኤፌሶን ኢየሱስ እንዴት እንደቀረበ ይገልፃል ፡፡ የኤፌሶን ከተማ በእስያ ክፍለ ሀገር በሮም የምትገኝ ነበረች (በአሁኗ ቱርክ ትገኛለች) ፡፡ በኤፌ (1፡ 1) ጳዉሎስ ራሱን እንደ ፀሀፊ ለይቷል ፤ ጳዉሎስ በሮም ከክርስቶስ ሞት 60-62 በኋላ በእስራት እያለ ለኤፌሶን ፃፈ (ሐዋ 28፡ 16, 30-31) ፡፡ በእስር ቤት እያለ ጳዉሎስ ለኤፌሶን፣ ለፊልጲስዮስ፣ ቆላስያስ እና ፊልሞን አብዛኛዉን ጊዜ የእስራት መልዕክት ተብለዉ የተጠቀሱትን መልዕክቶች ፅፏል ፡፡
መጀመሪያ ጳዉሎስ የክርስትና እንቅስቃሴ ተቃዉሞን የሚመራ ከብንያም ነገድ የሆነ ሣዖል ብሎ የተጠራ አንድ አይሁዳዊ ነበር ፡፡ በመንገድ ላይ የተነሳዉን ኢየሱስን ባገኘዉ ጊዜ ክርስቲያኖችን ለማሰር በደማስቆ መንገድ ላይ ነበር ፤ ጳዉሎስ በቀድሞዉ ክርስትና ክርስቲያኖችን ከመከታተል ከታላቅ ሰባኪዎች አንዱ ወደ መሆን ተቀየረ ፡፡
ጳዉሎስ መጀመሪያ በሁለተኛዉ የአገልግሎት ጉዞዉ ኤፌሶንን ጎበኘ ፡፡ ከዚያም በሄደ ጊዜ በዚያ አገልግሎቱን እንዲቀጥሉ አቅላን እና ጵርስቅላን ተዋቸው ፤ ጳዉሎስ በሰዎስተኛው የአገልግሎት ጉዞው በመመለስ አቅላና ጵርስቅላ ጀምረዉት የነበረዉን የቤተ ክርስቲያን ትግል ለማጠንከር በዚያ ያሉትን ሀሰተኛ አስተማሪዎች በመሞገት አገልግሎቱን እንዲጠብቅ ጢሞቲዎስን በመተዉ ረዳቸው ፡፡
የጳዉሎስ መልዕክት በኤፌሶን ላለች ቤተ ክርስቲያን በዚያ ካደረገዉ ጉብኝት ከዘጠኝ እስከ አስር አመታት ባለዉ ጊዜ የተፃፈ ነበረ ፤ በመልዕክቱ ላይ የከተማዋ ስም ስላልተጠቀሰ ብዙ ምሁራን መልዕክቱ በጥቂት በእስያ በነበሩ ቤተ ክርስትያናት ይዘዋወር እንደ ነበርና መጀመሪያ ለኤፌሶን እንደተላከ ያምናሉ ፡፡ በኤፌሶን 6 መሰረት ቲኪቆስ መልዕክቱን ለኤፌሶን ለማድረስ የጳዉሎስ መልዕክት አድራሽ ሆነ ፡፡
በግል አስተያየቴ ከጳዉሎስ መልዕክቶች አንዱ ለኤፌሶን የፃፈው ነበር ፡፡ ጳዉሎስ በእስርቤት የሞከረ ለመሆን በሮም ነበር ፤ ለጳዉሎስ ነገሮች መልካም አይመስሉም ፤ ይሁን እንጂ የጳዉሎስ ትኩረት ክርስቶስን ነግሯቸዉ በነበሩት ላይ ነበር ሀሳቡም በእምነት በጌታ እንዲቀጥሉ ነበር ፡፡
ትምህርት
ኤፌሶን (1፡ 1-6)፡ ጳዉሎስ መልዕክቱን ሁልጊዜ በተለመደ ሰላምታው ጀመረ፡ “ በኤፌሶን ላሉት ቅዱሳን በክርስቶስ ኢየሱስም ላሉት ምእመናን ፤ ከእግዚአብሄር ከአባታችን ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን “ (ቁጥር 1-2) ፡፡ ጳዉሎስ ከአንዱ ሰጪ/ባለስልጣን (ከእግዚአብሄር አብ እና ኢየሱስ ክርስቶስ) የመጡትን በረከቶች (ጸጋና ሰላምን) ጠቅሷል ፡፡ ጳዉሎስ አንባቢዎቹን በክርስቶስ በሁሉም መንፈሳዊ በረከቶች እንደተባረኩ እና ከምድር/ከአለም ጅማሬ በፊት በእርሱ የተመረጡ እንደነበሩ ማስታወሱን ቀተለ (ቁጥር 3-4) ፡፡
የኔልሰን ማብራሪያ ገለፃ “ አስቀድን እንደተመረጥ “በሚለዉ ይጀምራል፡ “ አስቀድሞ መወሰን/መምረጥ የግፍ ዉሳኔ ወይም የእግዚአብሄር ፍርድ አይደለም የእግዚአብሄር የፍቅር ምርጫ አካል እንጂ “ ፤ ፍቅር ከስሜት በላይ ምርጫ ነው ፡፡ ምንም ነገር ቢፈጠር እግዚአብሄር እኛን መዉደድን እንደመረጠ መዉደድን እንመርጣለን ፤ እግዚአብሄር መርጦናል፣ አስቀድሞ ወስኖኗል እንዲሁም ልጆቹ አድርጎናል (ቁጥር 4-5) ፡፡ በዉድ ልጁ ሞገስን/መወደድን ሰጠን (ቁጥር 6) ፤ የአብ ስራ በምርጫ ዉስጥ ይመጣል ፡፡
ኤፌሶን (1፡ 7-12)፡ የልጁ ስራ ቤዛነታችን ነው (ቁጥር 7-8) ፡፡ “ ክርስቶስ የፍቃዱን ሚስጥር ለእኛ የታወቀ አደረገው “ ፤ የኔልሰን ማብራሪያ ሚስጥር የሚለዉን ቃል “ ሚስጥር ለመፈለግ ጨዋታ አይደለም ወይም ደግሞ የጥቂቶች እና የመጀመሪያዎች እዉቀት አይደለም በጳዉሎስ ዘመን እደ ኃይማኖት ሚስጥር ነው ፤ በጳዉሎስ አጠቃቀም ሚስጥር የሚለዉ ቃል በአንዱ የተደበቀ ወይም የተሰወረ አሁን በእግዚአብሄር ተገልጦ የነበረዉን የእግዚአብሄር ፍቃድን ምልከታ ያመለክታል (ሮሜ 11፡ 25) “ በሚለዉ በዚህ መንገድ ይገልፃል ፡፡ በብሉይ ኪዳን ሰዎቹ ሚስጥሩን አልተረዱትም ነገር ግን ለእኛ ተገለጠ ፤ እንደ ክርስቶስ አምባሳደሮች እንደ አዳኝና ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የመጣዉን ሚስጥር የሚታወቅ ማድረግ እንችላለን ፡፡ እንደ እግዚአብሄር ፍቃድ ተወስኖ የነበረውን ዉርስም ተቀብለናል ፡፡
መደምደሚያ
ኤፌሶን 1 በድነታችን ዉስጥ ስለ ስላሴ ማብራሪያን ይሰጣል፡ 1) የእግዚአብሄር አብ በመመረጣችን ዉስጥ ይሰራል፣ 2) የልጁ የኢየሱስ ስራ በቤዛነታችን ዉስጥ ይሰራል እና 3) የመንፈስ ቅዱስ ስራ ጥበቃን ያደርግልናል ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1680.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1530.
Nelson’s Commentary, p. 1530.
Nelson’s Commentary, p. 1531.
Nelson’s Commentary, p. 1532.
MacArthur, p. 1683.
ጥያቄዎች
-
በኤፌ (1፡ 3) ላይ ስለ ተጠቀሱት መንፈሳዊ በረከቶች ምን ታስባላችሁ ?
-
ለልጅነት ማን መረጠን፣ መቼ ነበር የተመረጥነው እና ሂደቱስ ምን ነበር (ሉቃ 19፡ 10, ዮሐ 15፡ 16, ኤፌ 1፡ 4-6, 11, 2፡ 18-19) ?
-
በኤፌ (1፡ 4) መሰረት እንደ አንድ እንደተመረጠ እግዚአብሄር እንዴት ያየናል ? እናንተን እግዚአብሄር በሚያይባችሁ መንገድ ራሳችሁን ታዩታላችሁ አይደለም ካላችሁ ራሳችሁን እንዴት ነዉ የምታዩት ? ትክክለኛዉ እይታ የትኛው ነው ? አስተሳሰባችሁን እንዴት ልትቀይሩት ትችላላችሁ ? (ሮሜ 12፡ 2, 1ቆሮ 2፡ 12-16, 2ቆሮ 10፡ 5, ፊል 4፡ 8)
-
በኤፌ (1፡ 18-19) የልቦና አይኖቻችን እንዲበሩ ስለመፀለዩ የጳዉሎስ ምክንያት ምን ነበር ? ይህ ፀሎት በህይወታችሁ ዉስጥ እንዴት መልስ ይሆናል ትላላችሁ ?
-
ክርስቶስ በቤተ ክርስቲያን ላይ በምን ራስ የሆነ እንደሚመስል (ኤፌ 1፡ 22, 3፡ 10, 4፡ 11-16, 5፡ 23-32) ? በአዲሱ ትርጉም ኤፌ (1፡ 23) “ እርስዋም አካሉና ሁሉን በሁሉ የሚሞላ የእርሱ ሙላት ናት “ ፤ ይህ በአጠቃላይ የአሜሪካን ቤተ ክርስቲያን የምታዩበት ነው ? አይደለም ከሆነ ያ እንዴት ሊቀየር ይችላል ?
-
በኤፌሶን 1 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Ephesians 1:7-8
"We have redemption in Him through His blood, the forgiveness of our trespasses, according to the riches of His grace that He lavished on us with all wisdom and understanding."
ትቀበሉት ዘንድ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን ነጻ ስጦታ አድርጎ ወደ ምድር ላከው ፡፡ የሰማዩ አባታችሁ የበጎ ነገር እና የድንቅ ስጦታዎች ሁሉ ሰጪ ነው ፡፡ በኢየሱስ ስታምኑ በደሙ ፣ በበደላችሁ ስርየትና የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ በመሆን ቤዛነትን ተቀብላችኋል ፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር አብ ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ በጸጋ ባለጠጋ ነውና በእናንተ ላይ በጸጋ ላይ ጸጋን ያበዛላችኋል ፡፡ ዛሬ ከመጠን ያለፈውን የእርሱን ጸጋ ትቀበሉ ዘንድ እንደሚገባችሁ ልታምኑ ያስፈልጋችኋል ፡፡ “ከመጠን ያለፈ“ ማለት የማይታመን ባለጠግነት ፤ ረቂቅ የሆነ ወይም ደግሞ ውብና ድንቅ የሆነ ማለት ነው ፡፡ ብዙ ቤተሰቦች ልጆቻቸውን ሁሉም አይነትና መጠን ባላቸው መልካም ስጦታዎች ማትረፍረፍ ይፈልጋሉ ፡፡ የሰማዩ አባታችሁ እናንተ ማሰብ ከምትችሉትም በላይ ማብዛት ይችላል ፡፡ በእርሱ እውቀት በሚያስፈልጋችሁ ጸጋ ፣ ጥበብና ማስተዋል ሁሉ ያትረፈርፋችሁ ዘንድ ወስኗል ፡፡
ዛሬ ተነስታችሁ ይህንን እውቀት ተቀበሉ ፡፡ የሰማዩ አባታችሁ እናንተን በሰጦታ በማንበሽበሽ ደስ ይሰኛል ፡፡ በእናንተ ላይ ጸጋ ፣ ጥበብንና ማስተዋልን ያፈሳል ፡፡ እጆቻችሁን አንስታችሁ የእርሱን ድንቅ ስጦታዎች ተቀበሉ ፡፡
“ በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት ። ጸጋውንም በጥበብና በአእምሮ ሁሉ አበዛልን ። “
- ኤፌሰን 1፡7-8
ተጨማሪ ጥቅስ
ዮሐንስ1:16-17 — “ እኛ ሁላችን ከሙላቱ ተቀብለን በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጥቶናልና ሕግ በሙሴ ተሰጥቶ ነበርና ፤ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሆነ ። “
ኤፌሰን 3:20 — “ እንግዲህ በእኛ እንደሚሠራው ኃይል መጠን ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ ይልቅ እጅግ አብልጦ ሊያደርግ ለሚቻለው “
2ኛ ጴጥሮስ1:2 — “ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።