Spiritual Work Ethic
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Liberator Galatians 6 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
እግዚአብሄር በአሁኑ ዘመንም በገላትያዊያን ቤተ ክርስቲያን መጠቀም እንዲቻል የጳዉሎስን መልዕክት ለገላትያዊያን እንዳነሳሳዉ አምናለሁ ፡፡ ገላትያ 6 “ የመንፈሳዊ ስራ ስነ ምግባር “ በማለት ማጠቃለል ይቻላል ፡፡ በአሁኑ ጊዜ በስራ በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ፍቅር/ጥላቻ አለን ፤ ወደ ድነት በመጣ ጊዜ በእግዚአብሄር ፀጋ እንጂ በስራችን አይደለም ፡፡ ይሁን እንጂ እንደ አማኝ በዉስጣችን ከሚኖረዉ ከመንፈስ ቅዱስ ዉስጥ የመልካም ስራ ሂደትን እናሳድጋለን ፡፡
ገላትያ 5 በሚያስተምር ጊዜ ፓስተር ቶም እንዳለው ሰዎችን መዉደድ ተፈጥሮአዉ ይሆናል ፤ የመንፈስ ፍሬ ከኑሮአችን የሚወጣ በዙሪያችን ያሉትን የሚስብ የበሰለ ፍሬ እንዲሆን የታቀደ ነው ፡፡ ስለዚህ ከህግ ካልመጣው በዉስጣችን ስላለዉ መንፈስ የተወሳሰበ የስራ ስነ ምግባር እንዳለ አምናለሁ ፡፡ በምዕራፍ 6 ትምህርት ወደ መንፈሳዊ ድነት የስራ ስነ ምግባርን አላመጣም ፤ ህጉ ስራን እንዴት መደረግ እንዳለበት ከሚለዉ መንፈስ እንዴት እንድንሰራ ወደ ሚመራን ፈጣን የሆነ የታሰበበት ገለፃ አለ ፤ የገላትያ መፅሀፍ መላው አላማው በስጋ እና በመንፈስ መካከል ስላለዉ ዉጥረት ነው ፡፡
ትምህርት
ገላትያ (6፡ 1-5)፡ በቁጥር 1 ጳዉሎስ ገላትያዊያንን ሰዉ ወድቆ ከነበር እና በኃጢዓት ጥፋተኛ ከነበር ስለ ነገሩ ያወቁ መንፈስ ቅዱስ እንደመራቸዉ እንዲይዙት ነገራቸዉ ምክንያቱም እነርሱም ሊፈተኑበት ስለሚችሉ ፡፡ ያጠፋዉን በቅንነት በማቅናት ምላሽ ይሰጣሉ፣ በመንፈስ ፍሬ አክላ በሆነው ፤ ህጉን በማይከተሉት ላይ ስለሚደርሰዉ ቅጣት የሚገልጣን ፅሁፍ በገላትያ ከእነዚህ ጥቅሶች ጋር አነፃፅሩ ፡፡ ጳዉሎስ የክርስቶስን ህግ እንደሚፈፅም አንዱ የሌላዉን ሸክም እንዲሸከም ያዛቸዋል (ቁጥር 2)
ህጉ በመክሰስ ኃላፊነትን ያዞራል - ኃጢዓት ካደረግን ኃጢዓት እንዳደረግን እናዉቃለን ፡፡ ኃጢዓት ዉጤት እንዲኖረዉ የተቀመጠ ነው ፤ ህጉ ሰዎችን ወደ ህግ አስፈፃሚዎች በማምጣት ኃጢዓት የሰሩትን በማግኘት ይቀጣቸዋል ፤ ይሁን እንጂ በመንፈስ ሰዎችን ለማጥፋት አንሞክርም ልናመጣቸዉ እንሞክራለን እንጂ ፡፡ ቁጥር 1 ከማንም የተሸላ ራሳችንን እንደምናዉቅ ያሳስበናል ፡፡ በመንፈስ ቁጥጥር ስር ካልነበርን ኃጢዓት በቀላሉ ያሸንፈናል ፡፡
በቁጥር (4-5) መሰረት ከዚህ በኋላ የሚያስፈልግ ሰዉ ለመሆን አንመለከትም በመንፈስ ህይወት ስላለን እንደሰታለን እንጂ ፡፡ የመንግስቱ ሀሳብ አይነት ሰዎች እንሆናለን ፤ በመንፈስ ከመኖራችን የተነሳ ኃጢዓት ያደረጉትን እና ንስኃ የገቡትን ይቅር ማለት እንችላለን ፡፡ በመንፈስ ከመኖራችን የተነሳ ያደረግነዉን ስለምናዉቅ በፍጥነት ንስኃ እንገባለን ፡፡
በቅርቡ በራሴ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ፅሁፍ ላይ በመስበክ በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ የምንፈተንበት ክፍል በተጠያቂነት እንደሆነ ጉባኤዬን ነግሬአቸዋለሁ ፤ ጉባኤዬን በሁሉም ነገሬ እግዚአብሄርን መዉደድ እንደምፈልግ ነግሬአቸዋለሁ ፤ እዉነቱን መከተል እና ቃሉን መታዘዝ እፈልጋለሁ ፤ የልቤ ፍላጎት ያ ነው ፡፡ አሁን ህይወቴ ምን መሆን እንደሚፈልገዉ አይነት መስፈርት ከነበራቸው ሊይዙይ የቻሉት መስፈርቶች አላቸው ፡፡ ያ ህይወቴን የማረከ ስራ ስራ እንዲሆን እፈልጋለሁ እንዲሁም ይህ በዙሪያ ላሉት የታዬ እንዲሆን እፈልጋለሁ ፡፡ በመቀጠልም ለክርስቶስ ፀንተዉ መኖር የሚፈልጉትን ጠየኩ ፤ በአንድ ላይ የቆሙትን በመመልከት አንዱ የሌላዉን ሸክም እንዲሸከም ነገርኋቸው ፡፡ ያም በሌሎች ላይ ለማረጋገጥ፣ እንድናበረታታቸው እና ሸክማቸዉን ለመሸከም እንድንረዳ ይፈቅድልናል ምክንያቱም ይህን በእግዚአብሄር መንግስት ማድረግ ስለምንፈልግ ፡፡ እግዚአብሄርን እንወደዋለን በማለት ራሳችንን ማስገዛት መቻል አለብን በዚያም መንገድ በመኖር ተጠያቂ በመሆን ሰዎች እንዲይዙት እንፈልጋለን ፤ ያ የእነዚህን ጥቅሶች መረዳታችንን ከፍቷል ፡፡
ገላትያ (6፡ 6-10)፡ ቁጥር 6 የእግዚአብሄርን ህግ የሚሰብከ/የሚያስተምሩ በምላሹ መልካም ነገርን ይቀበላሉ ስለሚለዉ ተለዋጭ ህግ ነው ፤ ህጉ ሳይሆን መንፈሱ ይህን ይፈልገዋል ፡፡ ህጉ ይህን የራስ/የግል ያደርገዋል፣ መንፈስ ይህን የአስር አለቃ ያደርገዋል ፡፡ በቁጥር 7 አለማቀፋዊ ህግ ነው - ሰዉ የዘራዉን ያንኑ ያጭዳል የሚለው ፤ ሰዉ የስጋን ነገር ከዘራየስጋን ነገር ያጭዳል ፤ በመንፈስ የሚዘራ ሰዉ ግን የዘላለም ህይወትን ያጭዳል (ቁጥር 8) ፡፡ በመታዘዝ ለማጨድ መልካምን ለማድረግ መታከት የለብንም (ቁጥር 9) ፤ ስለሆነም በተሰጠን እድል ሁሉ ለሁሉም ሰዉ መልካምን ነገር ማድረግ አለብን (ቁጥር 10) ፡፡
መደምደሚያ
ሁላችንም በስጋ/በመንፈስ ሀሳብ እንታገላለን ፤ ለትንሽ ክስተት የሚያረኩንን ነገሮች ማሳደድ ቀላል ነው ፡፡ በልምድ ሽልማቱ ወዲያዉኑ ሲሆን ለሽልማቱ መታገስ በጣም አስቸጋሪ ነው ፡፡ በሌላ ሰዉ የሚፈለግን ነገር ሰወች በሚያይ ጊዜ ይቀናሉ ፤ አይሁዶች ሁሉም ሰዎች መሆን የሚፈልጓቸዉ አይነት ሰዎች ነበሩ ነገር ግን መሲሀቸዉን አልተረዱትም ፤ ስለሆነም እግዚአብሄር ሰዎችን ወደ እርሱ ለመሳብ ምሳሌ የሆነ ኑሮ ያላቸዉን ሌሎች የህዝብ ቡድኖችን ስለሳበ የእግዚአብሄር ሰዎች በሆኑት ይቀናሉ ፡፡
ጥያቄዎች
-
በገላ (6፡ 1) ጳዉሎስ የገላትያን አማኞች ከትክክለኛዉ መንገድ ለመመለስ ተፍጠዉ የነበሩትን የህብረቱ አማኞችን ለማስተካከል እንዲረዱት ነገራቸው ፤ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ራሳችሁን አግኝታችሁት ታውቃላችሁ ? ዉጤቱ ምን ነበር ?
-
ገላ (6፡ 7-9) ለማያምን እንዴት ትገልፁታላችሁ ? በመፅሀፍ ሌላ የት ስፍራ ላይ መዝራት እና ማጨድ ተጠቅሷል (ምሳ 11፡ 18, ሆሴ 10፡ 12, 2ቆሮ 9፡ 6) ?
-
በግል አስተያየታችሁ በገላ (6፡ 15) ጳዉሎስ ምን እያለ ነበር ? ያን መፅሀፍት በምን ይተካዋል (ሮሜ 6፡ 14, 7፡ 1-6, 2ቆሮ 5፡ 17, ገላ 2፡ 19, ኤፌ 2፡ 15, ዕብ 7፡ 18-19) ?
-
በገላትያ 6 በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Galatians 6:1–2
“Brothers, if someone is caught in any wrongdoing, you who are spiritual should restore such a person with a gentle spirit, watching out for yourselves so you also won’t be tempted. Carry one another’s burdens; in this way you will fulfill the law of Christ.”
በክርስቶስ የሆነ ወንድም ወይም እህት ኃጢአትን ሲሰራ ስታዩ ልታዝኑ ትችላላችሁ ፡፡ ብዙዎች ስለ ኃጢአት ተግባራቸው ሌሎች እንድጠይቋቸውም ሆነ እንድቃወሟቸው አይፈልጉም ፡፡ ነገር ግን እንደ ክርስቶስ ደቀመዛሙርት ይህን ልታደርጉ ተጠርታችኋል ፡፡ ስለዚህ ምን ታደርጋላችሁ ? በኃጢአት ውስጥ ያለን ወንድም ወይም አህት ለማነጋገር ስታስቡና እነርሱን ወደ ድሮው ህይወታቸው ለመመለስ ስትሹ ራሳችሁን እንዲህ በማለት ጥይቁ ፡- በዚህ ሁኔታ ውስጥ እግዚአብሔርን ወይስ ሰውን ነው የምፈራው ? በመንፈስ ወይስ በስጋ ነው እየተራመድኩኝ ያለሁት ?
በመንፈስ ስትመላለሱ መንፈስ በትክክለኛው ጊዜ ሌሎችን በየወኅነትና በፍቅር ትመልሱ ዘንድ በመለኮታዊ መንገድ ይመራችኋል ፡፡ በድፍረት ተራመዱ መንፈስም ይመራችሁ ዘንድ ፍቀዱለት ፤ በህይወታችሁ ያለውን የመንፈስ ጫና በጎ ተጽዕኖ ፈጽሞ እንዳታጠፉ ፡፡ በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ እንድኛው ኃላፊነታችሁ በክርስቶስ ፍቅር ሌሎችን ስለራሳቸው ተጠያቂ እንድሆኑና የራሳቸውን ሸክም እንድሸከሙ ማድረግ ነው ፡፡ በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ የየውሃት እና የፍቅር ተጠያቂነት ሊያመጣ የሚችለውን ልዩነት አስባችሁት ታውቃላችሁ ? አትፍሩ ፡፡ መንፈስ የሚመራችሁ ከሆነ ያ የሚመራችሁ መንፈስ ደግሞ በተጨማሪ የሌላውንም ሰው ልብ ያዘጋጃል ፡፡ ይህም የመንፈስ መለኮታዊ ስራ ነው ደግሞም የተትረፈረፈ የእግዚአብሔር ጸጋ አንድነትን ያስገኛል ፡፡
“ወንድሞች ሆይ፥ ሰው በማናቸውም በደል ስንኳ ቢገኝ፥ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ እንደዚህ ያለውን ሰው በየውሃት መንፈስ አቅኑት፤ አንተ ደግሞ እንዳትፈተን ራስህን ጠብቅ ። ከእናንተ እያንዳንዱ የአንዱን ሸክም ይሸከም እንዲሁም የክርስቶስን ሕግ ፈጽሙ ። “
- ገላትያ 6፡1-2
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 56:4 — “ በእግዚአብሔር ቃሉን አመሰግናለሁ፤ በእግዚአብሔር ታመንሁ፥ አልፈራም ሰው ምን ያደርገኛል ? “
ገላትያ 6:9–10 — “ ባንዝልም በጊዜው እናጭዳለንና መልካም ሥራን ለመሥራት አንታክት ። እንግዲያስ ጊዜ ካገኘን ዘንድ ለሰው ሁሉ ይልቁንም ለሃይማኖት ቤተ ሰዎች መልካም እናድርግ ። “
ያዕቆብ 5:19–20 — “ ወንድሞቼ ሆይ፥ ከእናንተ ማንም ከእውነት ቢስት አንዱም ቢመልሰው ፥ ኃጢአተኛን ከተሳሳተበት መንገድ የሚመልሰው ነፍሱን ከሞት እንዲያድን፥ የኃጢአትንም ብዛት እንዲሸፍን ይወቅ ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።