Paul's Letters Galatians

Walk By The Spirit

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Liberator Galatians 5 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 536 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ገላ (5፡ 1) ለገላትያ አንድ ቃላችንን ይሰጠናል፡ ክርስቶስ ነፃ አዉጪ ነው ፡፡ ክርስቶስ ነፃ እንድንሆን ነፃ አዉጥቶናል ፡፡ ክርስቶስ ነፃነትን ገዝቶልናል ስለ ነፃነትም ክርስቶስ ነፃ አዉጥቶናል ፤ የምዕራፉ የመጀመሪያዉ ግማሽ በነፃነት ለመመላለስ ተጠርተናል እንጂ በባሪነት አይደለም ፤ የመጨረሻዉ ግማሽ በስጋ ሳይሆን በመንፈስ እንድንመላለስ ተጠርተናል ፡፡

ትምህርት

ገላትያ (5፡ 1)፡ በመጀመሪያዉ ቋንቋ “ ፀንቶ መቆም “ (ቁጥር 1) የሚለዉ ጥሪ እንደ ህይወት አኗኗር እና ልምድ፣ ለሁሉም የባርነት ቀንበር ባለመገዛት ፀንቶ መቆም ማለት ነው ፡፡ ከማይክ ብሬን የኪዳን ስዎስት መዓዘን ተብሎ የሚጠራው ለባርነት ቀንበር እንዴት እንደማንታዘዝ እንድንረዳ ይረዳናል ፡፡ ሀሳቡን ለማሳየት የሰዎስት መዓዘን ስዕል በመጠቀም እግዚአብሄር በሰዎስት መዓዘኑ አናት ላይ ነው ፤ በክርስቶስ ያለን ማንነት ከሰዎስት መዓዘኑ በቀኝ በኩል ላይ ነው ፤ መታዘዝ ደግሞ በሰዎስት መዓዘኑ በግራ በኩል ላይ ነው ፡፡ ማንነታችን ከአብ/ከአባት ነው ፤ ወንድ እና ሴት ልጆቹ በመሆን የተቀበልን ሆነናል ፡፡ በመታዘዛችን በምንፈስ ጊዜ ከማንነታችን የተነሳ ህይወት አለ ፡፡ መታዘዛችን በክርስቶስ ካለን ማንነት በሚፈስስ ጊዜ የሚገልፅ፣ ነፃ የሚያወጣ እና ከእግዚአብሄር ጋር ባለን ትስስር እንደሰታለን ፤ በህጉ በምንሄድ ጊዜ ግን ማንነታችንን ለማግኘት መታዘዛችንን እንጠቀማለን ፡፡ በሚገባ ጠንክረን ከሰራን በሚገባ ካደረግን ማንነታችንን እንደምናገኝ እናስባለን ፤ ነገር ግን በጥንካሬአችን ማንነታችንን ማግኘት አንችልም ፤ ይህ ወደ ባርነት ይመራል ፡፡ ጳዉሎስ ገላትያዊያንን ደግመዉ ለባርነት ቀንበር፣ ለአለም ደስታ/ለዳንስ እና ለህጉ መሰላል እንዳይያዙ አሳሰባቸው ፡፡

ገላትያ (5፡ 2-6)፡ ጳዉሎስ ድነትን ለማግኘት መገረዝን እንደ መንገድ የመረጡትን ሁሉንም ህግ መጠበቅ እንደሚጠበቅባቸዉ ያስጠነቅቃቸዋል (ቁጥር 2-3) ፡፡ በህጉ ለመፅደቅ እየሞከራችሁ ከሆነ ከክርስቶስ የራቃችሁ ናችሁ (ቁጥር 4) ፤ ክርስቶስን ያለመቀነስ በክርስቶስ ላይ ምንም ነገር መጨመር አትችሉም ፡፡ ይህ “ ከፀጋ የመዉደቅ “ አካል (ቁጥር 4) ዘላለማዊ ህይወትን ማጣት ማለት አይደለም ከክርስቶስ ጋር መልካም ግንኙነትን የሚጠቅስ እንጂ ፡፡ በመንፈስ እና በእምነት በኩል ድነናል (ቁጥር 5) ፤ ነገሩ በፍቅር የሚሰራ እነምት ነው (ቁጥር 6) ፤ ይህ ፍቅር አጋፔ ነው ፡፡ ተስፋ (ቁጥር 5) የሆነ ነገር እንደሚሆን የማይቀር እንደ ሆነ ማረጋገጫ ነው ፡፡ በፍቅር የተነሳሳ እና በፍቅር የሚደረግ እምነት በክርስቶስ ስለተረጋገጠዉ ተስፋችን የሚመራን ነው ፡፡

ገላትያ (5፡ 7-12)፡ በሚገባ መሮጥ (ቁጥር 7) የማያቋርጥ ድርጊት እንጂ መሮጥ ባለፈዉ ጊዜ የተፈፀመ አልነበረም (ልክ ቅዳሜ 5ኪሜ እንደመሮጥ) ፡፡ መታዘዝም የሚቀጥል መታዘዝ የህይወት ስታይል ነው (ቁጥር 7) ፡፡ ጳዉሎስ መልሶ ወደኋላ ወደ መገረዝ የሚመልሳቸዉን ማንኛዉንም ትምህርት እንደማይቀበሉ እርግጠኝነቱን ተናገረ (ቁጥር 10) ፤ ጳዉሎስ እነዚያ አስተማሪዎች ከእዉነት አርቀዉ እየወሰዷቸዉ እንደ ነበር ተናገረ ፤ በክርስቶስ ያላቸዉን ነፃነት እንዳያጡ እነዚያን አስተማሪዎች እንዳይሰሙ አስጠነቀቃቸው ፡፡

ገላትያ (5፡ 13-15)፡ ቁጥር (1-12) ወደ ህጋዊነት እና በስራ ላይ ወደ ተደገፈ ፅድቅ ወደ ኋላ በምንትሸራተቱ ጊዜ ነፃነታችሁን ማጣት ቀላል ነዉ ይላሉ ፤ ቁጥር (13-15) ግን ጳዉሎስ ያን ነፃነት እንዳያጎሳቁሉት/እንዳያጡት አዘዛቸው ፡፡ ይልቁንም በፍቅር ሌሎችን በማገልገል የህይወት እስታይልን በሚያመለክተው “ ማገልገል “ እርስ በእርስ አለባቸው ፤ በሌላ ቋንቋ ወዳጃችሁን እንደ ራሳችሁ አድርጋችሁ ዉደዱ ማለት ነው ፡፡ እርግጠኝነት በሌለበት/በሚያጠራጥር ቃል ጳዉሎስ ወንጌል ከኃጢዓት ነፃ አያወጣችሁም አለ ፡፡ ከዚህ በፊት ካደረግነዉ በላይ እግዚአብሄርን የምወድበት ብዙ ምክንያቶች ስላሉን ፍቅር ወዳቻችንን እንድንወድ ምክንያት ይሆነናል ፡፡ መታዘዝ የልባችን የተፈጥሮ ገላጭ ይሆናል ፡፡ ጄይ.አይ. ፓከር፡ “ ክርስቶስ አገልጋዮቹ እንዲሰሩት ምን ስራን አስቀመጠ ? እርሱ የሚነግራቸው እርሱን የሚያገለግሉበት መንገድ የሚከተሏቸው አገልጋዮች አገልጋይ በመሆን እና ቃል በቃል ማንኛዉንም ነገር ለማድረግ ፍቃደኛ መሆን ነው ይሁን እንጂ እነርሱን ለመርዳት ውድ፣ የሚያሰለች ወይም የማያከብር አይደለም ፤ የባሪያን ድርሻ በመጫዎት የደቀ መዛሙርቱን እግር ባጠበ ጊዜ በመጨረሻዉ እራት ራሱ እንዳሳየው ፍቅር ማለት ይሄ ነው “ በማለት ፅፏል ፡፡ ጳዉሎስ “ እርስ በእርሳቸዉ ለመነካከስ እና ለመበላላት “ ፍቅርን ወደ ጎን ከተዉ “ እርስ በእርሳቸዉ እንደ ሚበላሉ “ አስጠነቀቃቸው (ቁጥር 15) ፡፡

ገላትያ (5፡ 16-26)፡ እነዚህ ቁጥሮች የስጋ ስራ ፍሬዎችን እና የመንፈስ ስራዎች ፍሬ መካከል ያለዉን ልዩነት ይገልፃሉ ፤ “ በመንፈስ ተመላለሱ “ (ቁጥር 16) የቀንን ወይም የወቅትን ህይወት ሳይሆን የአኗኗር ስታይልን ያመለክታል ፤ መንፈስ የክርስቲያንን ህይወት የቀን ለቀን፣ የማያቋርጥ፣ የሚያነሳሳ ኃይል ነው ፤ ለምን ? ምክንያቱም መንፈስ እና ስጋ እርስ በእርስ ስለሚቀዋወሙ (ቁጥር 17) ፡፡ እንደገና ይህ ጥቅስ እግዚአብሄር የሚፈልገዉን የህይወት አኗኗርን ለማድረግ ስለመፈለግ ይናገራል ፡፡ መንፈስ በሁሉም አማኝ ዉስጥ በማደር ከስጋ ጋር ተቃዉሞን እንዳለ ያረጋግጣል ፡፡ ጳዉሎስ በመንፈስ በመመላለስ በዚህ የህይወት እኗኗር እንድናድግ ያሳስበናል ፡፡ አማኞች በእነርሱ መንፈስ እንዲሰራ ሲፈቅዱ በአሸናፊነት ስሜት ብቅ ስለሚሉ በእርሱ መመላለስ ይችላሉ ፡፡ ጳዉሎስ በቁጥር (19-21) “ የስጋ ስራዎችን “ ይገልፃል - የወሲብ ስርዓት ጉድለት፣ የስነምግባር ጉድለት ናቸው ፤ ይህን ቀደም ብለን በመኃለይ መኃልዬ ሰለሞን ላይ ተመልክተናል ፡፡ ወሲብ እግዚአብሄር ባዘጋጀዉ መንገድ አዉድ በሚፈፀም ጊዜ የሚያምር እና የሚያስደንቅ ነው ፤ ነገር ግን ሰይጣን ያንን በመዉሰድ እና በዙሪያችን በመጠምዘዝ ስለ ስጋችን እና ስለፍላጎታችን ብቻ ያደርገዋል ፡፡ ገላትያዊያን የወሲብ ስነ ምግባራዊነት አለመኖር እንደ ኖርማል በሚታይበት አለም ኖሩ ነገር ግን ጳዉሎስ ያ እግዚአብሄር ያቀደዉ አይነት አይደለም አለ ፡፡ ሴሰኝነት ወይም ወራዳነት ከወሲብ ያለፈ/የሚበልጥ ነገር ነው፣ ለማንኛዉም አይነት ደስታ ለሚጠፋ ደስታ የተዘጋጀ የተዘጋጀ ነው ፡፡ ጣዖት አምላኪነት የእግዚአብሄርን ስፍራ የሚወስድ ማንኛዉም ነገር ነው ፤ አስማት ወይም ጥንቆላ ፋርማሲይ ከምናገኝበት የግሪክ ቃል የመጣ ነው ፤ በቀድሞዉ አለም አስማትን እና ጥንቆላን በመድኃኒትንት ብዙዎች ስለተጠቀሙ እንደ መድኃኒት የሚጠቅም ነው ፡፡ ከኃጢዓት ጋር ያለ ግንኙነት ማህበረሰብን ያጠፋል፡ ጥላቻን፣ ሁከትን፣ ቅናትን፣ በብስጭት ስሜት መገንፈልን (ወደ ምሬት የሚመራን)፣ የራስ ወዳድነት ፍላጎት (የመጀመሪያ ለመሆን መፈለግ)፣ ጠብን እና አንጃ ግራንጃን ( በቤተ ክርስቲያን ላይ ወደ ፉክክር ፍላጎት የሚመራን የቤድን መንፈስ)፣ ሀሜትን (መመኘትን)፣ ስካራምነትን፣ ርበሻን እና ማንኛዉንም የሚመሳሰል ነገር ፤ እነዚህን የምታደርጉ ከሆናችሁ የእግዚአብሄርን መንግስት አትወርሱም (ቁጥር 21) ፡፡

“ የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግስት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ እምነት፣ የዉሃትነት፣ ራስን መግዛት ነው “ (ቁጥር 22) ፡፡ የመንፈስ ፍሬዎች እንደ የጦር ልብስ የተጠቀሱ ናቸው ፤ ይህን መንፈሳዊ ዉጊያ በምንዋጋ ጊዜ ከዉስጣችን የሚወጣ ነው ፡፡ ይህ ንግግር ከፍራንሲስ ፍራንጊፓን ንግግር፡ “ ብዙ ኃይማኖታዊ መንጋዎች ይሁን እንጂ በቀላሉ ራሳቸዉ ክርስቶስን በማይመስሉበት እዉነት አለም ብዙ ክርስቲያን ለምን የለዉም በማለት እንደሚበሳጩ “ ከተናገረዉ ጋር ይመሳሰላል ፡፡ የመንፈስ ፍሬዎች በአንድ ላይ የሚመጡ እና በመንፈስ ቅዱስ የሚመነጩ ፍሬዎች ሲሆኑ፡ ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግስት፣ ርህራሄ፣ ቸርነት፣ እምነት፣ በጎነት እና ራስን መግዛት ናቸው ፤ ይህ እዉነት ሆኖ የሚገኝ የመንፈስ ፍሬ ነው ፤ በህይወታችሁ እዉን የሚሆንበት ብቸኛዉ መንገድ በመንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው ፡፡ በመንፈስ የምንመላለስ ከሆነ ጌታ እስኪመለስ ድረስ ከመንፈስ ጋር 24/7፣ የአመቱን 365 ቀን እንዲሁም በሁሉም አመታት እንዋሀዳለን ፡፡ ከእግዚአብሄር ግንኙነት ዉጪ በሆነ በራሳችን ለማድረግ በመሞከራችን ዉጤት የዉሸት ፍሬን እንፈፅማለን ፡፡ እግዚአብሄር በመንፈሱ እንድንመላለስ ስለ ጠራን ፍሬዉ ከእርሱ ይመጣል ፤ ሁሉም ፍሬ ከአንድ ስር ከአንድ ዛፍ ይመጣል ፡፡ በዚህ ዘመን አለም በመንፈስ ፍሬዎች መኖር ይጠበቅብናል ፡፡

  • ፍቅር - የሁሉም እዉነተኛ መንፈሳዊ እዉነት ስብስብ/ማጠቃለያ ፤ ፍቅር በአገልግሎት በ 1ቆሮንቶስ 13 የተገለፀ ነው ፡፡
  • ደስታ - ክርስቲያን በመሆናችን የሚያጠነክረን/የሚያበረታን ፤ ይህ መፍጠር አንችልም ፡፡
  • ሰላም - ስምምነት እና ደህንነት ፡፡
  • ትዕግስት -እግዚአብሄር በእኛ እንዴት የታገሰ እንደነበር ? በዚያ እንዴት መኖር እንችላለን ?
  • ቸርነት - ከዉስጠኛ ባህሪይ ጋር በመዋሀድ የህይወት ዉጫዊ ገለፃ ፡፡
  • ርህራሄ - ርህራሄ “ ለሆነ ነገር መልካም መሆነ “ ማለት ነው ፡፡
  • እምነት - መታመን እና ቃልን መጠበቅ ፡፡
  • በጎነት - ለእግዚአብሄር ፍቃድ መገዛት ፤ በልጓም ዉስጥ እንዳለ ፈረስ ጥንካሬ እንጂ ድክመት አይደለም፡፡
  • ራስን መግዛት - የራስ አለቃ መሆን/ራስን መቆጣጠር ፡፡

መደምደሚያ

በክርስቶስ ከሆናችሁ እና በመንፈስ የምትመላለሱ ከሆናችሁ ያልተጠበቀ ነገር ሲመጣ መንፈሱ በዉስጣችሁ በሚያደርገዉ ይሆናል ብላችሁ በማታስቡት መንገድ ምላሽ ትሰጣላችሁ ፡፡ በመንፈስ ፍሬዎች እያደጋችሁ ነው ? በየትኛዉ እየተፈተናችሁ ነው ? በመንፈስ ከኖርን መንፈሱንም መከተል አለብን ፡፡

  1. Mike Breen, Covenant and Kingdom (Pawleys Island, SC: 3DM, 2010), pp. 11–113.

  2. J. I. Packer, “Training for Christian Service,” in The Evangelical Christian (September 1961), Toronto, Ontario: Evangelical Publishers, 1961, pp. 10–11.

ጥያቄዎች

  1. በኢየሱስ ከማመን ዉጪ ምናልባት ልንድንበት የምንችልበት ሌላ መንገድ አለ (ማቴ 7፡ 13-14, ሉቃ 13፡ 23-24, ዮሐ 14፡ 6, ሐዋ 4፡ 12) ? ክርስቲያን እንደ ሆነ የሚናገር ሁሉ ወደ መንግስተ ሰማይ ይገባል/ይሄዳል ብላችሁ ታስባላችሁ (ማቴ 7፡ 21-23) ?
  2. ክርስቲያን በክርስቶስ ያለዉን ነፃነቱን እንዴት መጠቀም አለበት (ገላ 5፡ 13) ? ነፃነታችሁን እንዴት ትጠቀሙበታላችሁ ?
  3. በመንፈስ እንዴት ትመላለሳላችሁ (ሮሜ 6፡ 12, 8፡ 4-6) ?
  4. በገላትያ 5 መሰረት የስጋ ስራዎች ምንድን ናቸው ? ከእነዚህ ዉስጥ በየትኛዉ ትፈተናላችሁ/ትቸገራላችሁ? በተቃራኒው የመንፈስ ፍሬ ምንድን ነው ? እነዚህን በራሳችሁ ላይ ታዩአቸዋላችሁ ? ሌሎች በእናንተ ላይ ያዩአቸዋል ?
  5. በገላትያ 5 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Galatians 5:22–25

“But the fruit of the Spirit is love, joy, peace, patience, kindness, goodness, faith, gentleness, self-control. Against such things there is no law. Now those who belong to Christ Jesus have crucified the flesh with its passions and desires. Since we live by the Spirit, we must also follow the Spirit.”

ክርስቶስ ነጻ ሊያወጣችሁ የመጣው በስጋ ሳይሆን በመንፈስ መኖር እንድትችሉ ነው ፡፡ የስጋ ስራዎች ጣዖትን ማምለክ ፣ አድመኝነት ፣ ቅናት ፣ ቁጣ ፣ መለያየት ፣ ቅናት እናም ስካር ናቸው ፡፡ ህይወታችሁ ከእነዚህ ውስጥ የትኛውንም የሚያሳይ ከሆነ ጳውሎስ በስጋ እየኖራችሁ እንደሆነ ይናገራል ፡፡ በመንፈስም በስጋም ልትመላለሱ አትችሉም ፡፡

በመንፈስ መመላለስን ልክ የበምፐር መኪና ላይ እንደመሳፈር አድርጋችሁ አስቡት ፡፡ የበምፐር መኪናችሁ ኃይል ከሚያመነጨው ጣሪያ ጋር በብረት ቁራጭ ይገናኛል ፡፡ የበምፐር መኪናችሁን ስትነዱት መኪናችሁ ኃይልን የሚያገኘው ከላይ ከጣሪያው ነው ፡፡ የሃይል ምንጩ ማለትም ጣሪያውና ብረቱ ካልተገናኘ መኪናው አይንቀሳቀስም ፡፡ በተመሳሳይ መንገድ የመንፈስን ፍሬ ለማፍራት የሚያስችላችሁን ኃይል የምታገኙት ከመንፈስ ቅዱስ ነው ፡፡ ከእርሱ ጋር ስትራመዱ የፍቅርን ፥ የደስታን ፥ የሰላምን ፥ የትዕግሥትን ፥ የቸርነትን ፥ የበጎነትን ፥ የእምነትን ፥ የየውሃትን ፥ ራስን የመግዛትን ፍሬ ታፈሩ ዘንድ ኃይሉ በእናንተ ላይ ይፈሳል ፡፡ እስኪ ራሳችሁን እንዲህ ጠይቁ ፡- ከኃይል ምንጩ ጋር ተገናኝቻላሁ ደግሞስ ፍሬን እያፈራሁ ነው ? ወይስ በራሴ እየታገልኩ ነው እንዲሁም የስጋ ስራዎችን መስራቴን ቀጥያለሁ ? ዛሬ ከመንፈስ ቅዱስ ኃይል ጋር ግንኙነታችሁን አጽኑ እና ስጋንና በህይወታችሁ ውስጥ ያለውን ፍሬውን ሲጠፋ ሲደበዝዝ ማየት ትጀምራላችሁ ፡፡

“ የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው ። እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም ። የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ ። በመንፈስ ብንኖር በመንፈስ ደግሞ እንመላለስ ። “

  • ገላትያ 5፡22-25

ተጨማሪ ጥቅስ

ዮሐንስ 15:4–5 — “ በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው፥ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም ። እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል ። “

ገላትያ 5:1 — “ በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን፤ እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ ። “

ኤፌሶን 5:18–20 — “መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና ፤ በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ፤ ለጌታ በልባችሁ ተቀኙና ዘምሩ ፤ ሁልጊዜ ስለ ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አምላካችንንና አባታችንን ስለ ሁሉ አመስግኑ ። “