Paul's Letters Galatians

Sons And Heirs

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Liberator Galatians 4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 535 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ለገላትያ መፅሀፍ ጭብጣችን በገላ (5፡ 1) እንደተገለፀው “ በነፃነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን “ ክርስቶስ ነፃአዊጪ ነው ፡፡ ክርስቶስ ነፃ ስላወጣን ወደ ህግ የምንመለስበት ምንም ምክንያት የለም ፤ በገላ (4፡ 1-7) ጳዉሎስ አዲስን እና አሮጌን፣ ስጋን እና መንፈስን እንዲሁምአጋርን እና ሳር ያነፃፅራል ፡፡ ጳዉሎስ ለገላትያዊያን ጥሩ ልብ ስለ ነበረው ለምን ቀድሞ ነገሮችን ወደ ሚያደርጉበት መንገድ ለመመለስ እየሞከሩ እንደ ነበር ወይም ደግሞ ከአይሁድ የኃሰት ትምህርት እና አስመሳዮች ጋር ለምን ለመወዳጀት እየሞከሩ እንደ ነበር ለማወቅ ፈለገ ፡፡

ትምህርት

ገላትያ (4፡ 1-7)፡ በመጀመሪያዎቹ ሰባት ጥቅሶች ዉስጥ ዋይርስቤ ጳዉሎስ ልጆች የሆኑበትን ነገር ለመግለፅ እየሞከረ ነበር ይላል ፡፡ ጳዉሎስ ንፅፅርን አደረገ፡ በባርነት የነበሩ ልጆች ነበሩ ነገር ግን እግዚአብሄር በመምጣት ከባርነት አወጣቸው ፡፡ እንደ ማክአርቱር ገለፃ በቁጥር (1-2) ጳዉሎስ “ ለመናገር ያልጎለመሰ በጣም ልጅ፣ ትንሽ እንዲሁም በመንፈሳዊነት እና በአይምሮ ያልጠነከረ እና የልጅነት ኃላፊነትን ለመቀበል ያልተዘጋጀ “ እንደሆነ አመልክቷል ፡፡ ልክ እንደ ህፃናት ልጆች ስለ ነበሩ ቀኑ እስኪመጣ ድረስ በሌላ ሰዉ ጥበቃና ስልጣን ስር ነበሩ (ቁጥር 2)፡፡ በመጀመሪያ ትልቁን መልክ አልተረዱም ፡፡ ጳዉሎስ የሚጠቅሳቸዉ “ የመጀመሪያ/የአለማት ኃይሎች “ (ቁጥር 3) የክፉን አለም፣ ስጋን እና አለምን ማመልከት ይችላል ፡፡ አባላት ለሚለዉ ቃል የግሪክ ቃል “ ጥሬ ወይም ደረጃ…. ልክ እንደ አልፋ ቤት ፊደላት ዋና መሰረታዊ ነገሮች “ ማለት ነው ፡፡

እንደ ማክአርቱር ገለፃ “ በእግዚአብሄር የጊዜ ሰንጠረዥ/መርሀ ግብር ትክክለኛ ኃይማኖታዊ፣ ባህላዊ እና ፖለቲካዊ ሁኔታ በትክክል በሚያስፈልገዉ ስፍራ በተቀመጠ ጊዜ ኢየሱስ ወደ አለም መጣ “ ፡፡ ማክአርቱር በተጨማሪም “ አባቱ ልጁ ለሚመጣበት ቀን በዓል ጊዜዉን እንዳስቀመጠለት ከጠባቂዎች፣ ከባላደራቸዎቹ እና ከተቆጣጣሪዎች ነፃ የወጣ ስለሚሆን የሚያምኑትን ሁሉ ከህግ ባርነት እንዲያመጣቸው በትክከለኛዉ ክስተት ላይ ልጁን ላከው “ ፡፡ ጳዉሎስ ልጁን በጥቂት የተለያዩ መንገዶች ይገልፀዋል፡ ከሴት የተወለደ ስለ ነበር (የኢየሱስስን ሰዋዊነት አብሯርቷል) በህጉ ስር ተወለደ (ቁጥር 4) ፡፡ ኢየሱስ ህጉን ለመፈፀም ከህግ ስር መወለድ ነበረበት ፤ “ እንደ ሰው ኢየሱስ የእግዚአብሄርን ህግ የማክበር ግዴታ ነበረበት ፤ ከማንኛዉ ሰዉ በተለዬ ህጉን በፍፁም አከበረ ፤ ኃጢዓት አለማድረግ/ኃጢዓት የለለበት መሆኑ ስለ ኃጢዓት እንከን የሌለበት መስዋዕት እንዲሆን አደረገው … ያ ፍፁም ፅድቅ በእርሱ ለሚያምኑት የመጣበት ምክንያት ነው “ ፡፡

ማክአርቱር ጉድፈቻ/መቀበል “ ከሌላ የተወለደን ሰዉን ወደ ራስ ቤተሰብ የማምጣት ድርጊት ነው ፤ የንስኃ ልብ የሌላቸዉ ሰዎች በተፈጥሮ የክፉ ልጆች ስለሆኑ የእግዚአብሄር ልጆች የሚሆኑበት ብቸኛዉ መንገድ መንፈሳዊ ጉድፈቻነት/ተቀባይነት ነው “ አለ ፡፡ እንደ አማኝ በዉስጣችን የኢየሱስ መንፈስ አለ (ቁጥር 6) ፡፡ እንደ እግዚአብሄር ልጆች ተቀባይነት ስላለን የእግዚአብሄር ወራሾች ነን (ቁጥር 7) ፡፡

ለዚህ አትሰሩም አታገኙትምም ፤ ቀድሞ እግዚአብሄርጠፍታችሁ ሳላችሁ እና ከቀድሞ ጓዛችሁ ስታመጡ መቼ እንደሚቀበላችሁ ያውቃል ፡፡ በገላትያ መፅሀፍት ዉስጥ የመንፈስ ቅዱስ ጭብጥ/ፍሬ ነገር አለ ፤ ገላ (3፡ 2) በእምነት መንፈስን እንደምንቀበል ይናገራል ፡፡ ጳዉሎስም ከመንፈስ ጋር እንድንሆን እና ወደ ስጋ ሀሳብ/ስራ እንዳንሄድ ይናገራል (ገላ 3፡ 3) ፡፡ እግዚአብሄር ተዓምራትን እንድንሰራ በሚፈቅድልን በመንፈስ ቅዱስ ይሰጠናል/ይሞላናል (ገላ 3፡ 5) ፡፡ በገላትያ 5 ጳዉሎስ በስጋ ሳይሆን በመንፈስ እንድንመላለስ ይነግረናል (ገላ 5፡ 16)፡፡ በስጋና በመንፈስ መካከል ያማያቆም ዉጊያ አለ ፤ ነገር ግን እንደ እግዚአብሄር ልጆች ተመልሰን ወደ ስጋ ሀሳብ/ስራ አንሄድም ፡፡

ገላትያ (4፡ 8-11)፡ በእነዚህ ጥቅሶች ዉስጥ ዋይርስቤ ጳዉሎስ ወደ ኋላ በመመለሳቸዉ አዘን ይላል ፡፡ ጳዉሎስ ወደ ቀድሞ መንገዳቸዉ እየተመለሱ ስለ ነበር ተጨነቀ ፡፡ የእሁድ ማለዳዎች /የሰንበት ቀኖች በጣም ቀላል ናቸው በእምነት እና በመንፈስ ቅዱስ መሰረት ላይ ግን ጠፍተዋል ፡፡ ጳዉሎስ በኃይማኖት ቅጠል ባርነት መመላለስ ለመንፈስ ፍሬ ስፍራ እንደሌለዉ አስጠነቀቀ ፤ ጳዉሎስ በነፃነት የሚያከብሯቸዉን የተለዬ ቀንን፣ ወራት፣ ወቅት እና አመታት በዓላት በመመልከት ከእነርሱ ጋር ወንጌልን ለማካፈል አድርጎት የነበረዉ ጥረቱ ባክኖ ከነበር ተደነቀ/ተገረመ (ቁጥር 11) ፡፡ ይህ ወደ ግብፅ መመለስ ከፈለጉት ከእስራኤላዊያን ጋር የሚመሳሰል ነበር ፡፡ ምን እንደሚያደርጉ ስለሚያዉቁት በዚያ ባሪያ መሆንን መረጡ ፡፡

ገላትያ (4፡ 12-18)፡ በእነዚህ ቁጥሮች ዋይርስቤ ጳዉሎስ ፍቅራቸዉን/መዉደዳቸዉን ይፈልጋል ይላል ፡፡ ይህ የጳዉሎስ የእረኝነት ስራዉ የታየበት ስፍራ ነበር ፤ ጳዉሎስ እሱን እንዲመስሉ ለመናቸው (ቁጥር 12) ፡፡ በ 1ቆሮ (11፡ 1) ጳዉሎስ ቆሮንቶሳዊያንን “ እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ “ በማለት ነግሯቸዋል ፡፡ ጳዉሎስ ማክአርቱር እንዳለው ከአምፊሊያ የባህር ዳርቻ አካባቢ በወባ በሽታ በመያዙ በስጋ ድካሙ ጊዜ አገልግሏቸዉ ነበር (ቁጥር 13) ፡፡ ጳዉሎስ ለምን በጉጉት ተቀብለዉት እንደ ነበር ከዚያም በመመለስ አሁን እርሱን ለመቀበል ባለመፈለጋቸው ተገረመ (ቁጥር 14-15) ፡፡ የጳዉሎስ ህመም ቁጥር 15 እንደሚመሰክረው አይኖቹ በሆነ መጠን ያክል ጉዳት ደርሶባቸው ነበር “ ቢቻልስ ዓይኖቻችሁን አዉጥታችሁበሰጣችሁኝ ብዬ እመሰክርላችኋለሁ “ የሚለዉ ገላትያዉያን በእዉነት ለጳዉሎስ ይጠነቀቁ/ያስቡ እንደ ነበር ያሳያል ፡፡ ጳዉሎስ “ በብርቱ ይፈልጉአችኋል ነገር ግን ለመልካም አይደለም “ (ቁጥር 17) ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ወደ ጉባኤ የሚመጡ ፍላጎታቸዉ መልካም ያልሆነ ሰዎች አሉ ፤ ለራሳቸዉ የሆነ ነገርን በመፈለግ እንጂ የክርስቶስን አካል ማበረታታት እና ሌላ ተጨማሪ ፍላጎት የላቸውም ፡፡

ገላትያ (4፡ 19-20)፡ ጳዉሎስ የንግግሩ መጨረሻ ላይ እንደነበር እና በገላትያ ምን እንደሚያደርእንደማያዉቅ እያመለከተ ነበር ፡፡

ገላትያ (4፡ 21-31)፡ ጳዉሎስም ስለ አብርኃም የብሉይ ኪዳንን ታሪክ በመጠቀም ንፅፅርን ማድረግ ጀመረ ፡፡ የኃሳብ ባርነትን ከነፃነት ጋር አወዳደረ ፤ ከደብረ ሲና የሆነችዉ አጋር ልጆቿንለባርነት ትወልዳለች (ቁጥር 24)፣ ስጋንና ባርነትን ትወክላለች ፡፡ በሌላ በኩል ሳራ ነፃነትን ትወክላለች “ ላይኛይቱ ኢየሩሳሌም ግን በነጻነት የምትኖር ናት እርስዋም እናታችን ናት “ (ቁጥር 26) ፤ ከኢሳያስ እና ከዘፍጥረት ጳዉሎስንግግሩን ያጠቃልላል ፡፡ “ ስለዚህ ወንድሞች ሆይ የጨዋይቱ ልጆች ነን እንጂ የባሪያይቱ አይደለም “ (ቁጥር 31) ፤ ጳዉሎስ በመቀበላቸዉ ሂደት ዉስጥ በመሄድ ከጌታ እየዞሩ ስለነበርና ቀድሞ ነገሮችን ወደሚያደርጉበት መንገዳቸዉ በመመለሳቸው የተበሳጨ ነበር ፡፡ ምን መሆን እንደሚፈልጉ ጠየቃቸው - የባሪያ ልጅ ወይስ በዉስጣቸዉ ባለዉ በእግዚአብሄር መንፈስ መሮጥ የሚችሉ የነፃነት ልጆች ፡፡ አብርሃም በእግዚአብሄር ተስፋ ላይ ባለመደገፉ በእስላማዊይ እምነት የመጣው እስማኤል አለን ፤ በእስላማዊ እምነት ምክንያት በይስሐቅ እና በእስማኤል ትዉልድ መካከል ትልቅ ጉዳዮች አሉን ፤ ነገር ግን በሚገባ የባርነት እና የነፃነትን መልክ ነው ፡፡ ያ ነፃነት መምጣት የሚችለዉ በነፃ አዉጪዉ ብቻ ነው - በአይሁድነት፣ በእስልማና እና በክርስትናም አይደለም ፤ ያ ነፃነት በክርስቶስ በኩል ብቻ ይመጣል ፡፡ ክርስቶስ “ ከእኔ የተነሳ የእግዚአብሄር ልጆች ናችሁ “ ያለ ነው ፡፡

መደምደሚያ

በአሁኑ ጊዜ ስለምትሰሙት በመፀለይ አብላሉት ፤ ተመልሶ በመሄድ ገላትያ 4 እንደገና አንብቡ ፡፡ ነገ ስለ መንፈስ ፍሬዎች ስናወራ ብዙ የማይረቡ ልቦች ይኖራሉ ፡፡

  1. Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 1989), p. 564.

  2. John MacArthur, The MacArthur Study Bible (Nashville: Thomas Nelson, 1997), p. 1794, footnote for verse 1.

  3. MacArthur, p. 1794, footnote for verse 3.

  4. MacArthur, p. 1795, footnote for verse 4.

  5. MacArthur, p. 1795, footnote for verse 4.

  6. MacArthur, p. 1795, footnote for verse 4.

  7. MacArthur, p. 1795, footnote for verse 5.

  8. Wiersbe, p. 566.

  9. Wiersbe, p. 566.

  10. MacArthur, p. 1795, footnote for verse 13.

ጥያቄዎች

  1. በገላትያ 4ስለ ገላትያዊያን የጳዉሎስ ፍራት ስለ ምን ነበር ?ጳዉሎስ ስለዚህ የተጨነቀዉ ለምን ነበር (ገላ 4፡ 8-9) ? ወደ ደካማና ዋጋ ወደሌለዉ ነገር ተመልሳችሁ ታውቃላችሁ ? እንደ እግዚአብሄር ልጅ ይህን ለምን እንደምናደርግ ምን ታስባላችሁ ?
  2. በገላ (4፡ 14) ጳዉሎስ ገላትያዊያንን ለምን አዘዛቸው ? አሳዛኝ በሚመስል ሁኔታ ዉስጥ የሚሄዱ አይነት ሰዎችን ስታስወግዱ ራሳችሁን አግኝታችሁታል ወይስ መጀመሪያ ወደ እነርሱ ሲመጣ ገላትያዊያን ለጳዉሎስ እንዳደረጉት ትይዙአቸዋላችሁ ? ለመልሳችሁ ምክንያቱን ስጡ
  3. በገላ (4፡ 16) ጳዉሎስ “ እንኪያስ እዉነቱን ስለ ነገርኋችሁ ጠላት ሆንሁባችሁን ? “ አለ በፍቅር እዉነቱን በመናገር የሆነ ሰዉ ጠላት ሆናችሁ ታውቃላችሁ ? ስለዚህ መፅሀፍ ምን ይላል (ማቴ 18፡ 15-18, ኤፌ 4፡ 14-15, 2ጢሞ 4፡ 3-4) ?
  4. በገላ (4፡ 21-31) የሳራን እና የአጋርን ታሪክ በመናገርጳዉሎስ ምን ስዕልን ለመሳል እየሞከረ ነበር (ሮሜ 4፡ 16, ገላ 3፡ 8, 29) ?
  5. በገላትያ 4 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Galatians 4:6–7

“And because you are sons, God has sent the Spirit of His Son into our hearts, crying, ‘Abba, Father!’ So you are no longer a slave but a son,and if a son, then an heir through God.”

እናንተ የእግዚአብሔር አብ ወራሾች ናችሁ ፡፡ እግዚአብሔር አባታችሁ ነው ፣ የሰማዩ አባታችሁ ነው ፡፡ ከእንግዲህ ለህግ ፣ ለዚህ አለም ፣ ለፍርኃት ደግሞም ለስራ ባሪያ አይደላችሁም ፡፡ ወዳጆች ሆይ ከክርስቶስ በፊት ህይወታችሁ ምንም ይምሰል ነገር ግን በእርሱ ስላመናችሁ የእርሱ ልጆች ናችሁ ደግሞም ከእርሱ ከሰማዩ አባታችሁ ወራሽነትን አግኝታችኋል ፡፡

ምናልባት “ ይህ አይገባኝም “ ብላችሁ ታስቡ ይሆናል ፡፡ ይህ ከሰይጣን የሆነ ውሸት ነው ፡፡ ከሰማዩ አባታችሁ የሆኑ ሁሉም የከበሩ ሀብቶች ይገቡዋችኋል ፡፡ እርሱ ለእናንተ ታላቅ የሆነ የአባት ፍቅር አለው ፡፡ እናንተ ወደ ቤተሰቡ የተቀላቀላችሁ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ ፡፡ ትፈለጋላችሁ ፡፡ ተመርጣችኋል ፡፡ ዋጋ አላችሁ ፡፡ በክርስቶስ ወራሾች ናችሁ ፡፡ ስለዚህ በቂ እንዳልሆናችሁ ፣ ቤተሰብ እንደሌላችሁና ብቸኛ እንደሆናችሁ በሚሰማችሁ ጊዜ የእግዚአብሔር አብ ወራሾች እንደሆናችሁና በዚህ እውነት ላይ መቆም እንዳለባችሁ አስታውሱ ፡፡

“ ልጆችም ስለ ሆናችሁ እግዚአብሔር አባ አባት ብሎ የሚጮኽ የልጁን መንፈስ በልባችሁ ውስጥ ላከ ። ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባሪያ አይደለህም፤ ልጅም ከሆንህ ደግሞ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ወራሽ ነህ ። “

  • ገላትያ 4፡6-7

ተጨማሪ ጥቅስ

2ኛ ወደ ቆሮንቶስ6:18 — “ ለእናንተም አባት እሆናለሁ እናንተም ለእኔ ወንድ ልጆችና ሴት ልጆች ትሆናላችሁ ይላል ። “

ገላትያ 4:1 — “ ነገር ግን እላለሁ፥ ወራሹ ሕፃን ሆኖ ባለበት ዘመን ሁሉ፥ ምንም የሁሉ ጌታ ቢሆን ከቶ ከባሪያ አይለይም ፡፡ “

1ኛ ዮሐንስ 3:1–2 – “ የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። ስለዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን ስላላወቀው እኛን አያውቀንም ። ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን ። “