Faith In Christ
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Liberator Galatians 3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ገላትያ ስለምን እንደሚያወራ ለመረዳት በሙሉነቱ የሚጠና አይነት መፅሀፍ ነው ፤ እንዲሁም አንዴ የመፅሀፉን ጥናት ስትጨርሱ እንደ ገና በመመለስ ለማንበብ ወደ ምዕራፍ 1 መመለስ ያስፈልጋችኋል ፡፡ ጥናቱን ከመጀመራችን በፊት ምዕራፍ 3 ስለሚያደርገዉ “ የስጋ “ እና “ የመንፈስ “ ዉይይት ላይ ለመሸጋገር ለማዘጋጀት ጥቂት መነሻ መስጠት እፈልጋለሁ ፡፡ እስካሁን ስለ ግርዛት በስጋ ላይ እንደ ምልክት እና አዲስ ግርዛትን በልብ ላይ እንደ ምልክት አዉርተናል ፡፡ ሁላችንም ስለ እግዚአብሄር እና ስለ ክርስቶስ ያልተረዳናቸዉ ነገሮች በሚኖሩ ጊዜ ሞኝ ገላትያዊያን ነን፡፡
ትምህርት
ገላትያ (3፡ 1-5)፡ “ የማታስተዉሉ “ የሚለዉ ቃል (በቁጥር 1) “ አይናችሁን ወደ ሌላ አዞራችሁ “ በማለት ሊተረጎም ይችላል ፡፡ ምዕራፍ 2 የጳዉሎስን ግንኙነት ዋጋ አስከፍሎ የነበር በኃይለኛዉ የተነገረ የመልዕክቱ ከፋይ ክፍል ነበር ፤ በምዕራፍ 3 ዉስጥም በኃይል መናገሩን ቀጠለ ፡፡ ጳዉሎስ በሌሎች አንዳንድ መልዕክቶቹ ላይ የህጉን መልዕክት አጥፍቷል ፡፡ ሀሳቡ እምነት ለህጉ መልዕክት በመታዘዝ ላይ ሳይሆን በመንፈስ እንደሆነ ነው ፡፡
በአገልግሎቴ ዉስጥ አብሬአቸዉ ከተጓዝኳቸዉ ሰዎች ጋር ገላትያን እረዳለሁ ፤ የእዉነት ማሳመኛ የእዉነት ሰዎች እንደ ነበሩ በሚያስቡ ሰዎች መጥቶ ከነበር ኃሻባችሁን በእዉነታቸዉ ላይ ለማስቀመጥ ቀላል ነው ፡፡ ሊዎናርዶ ራቬንሂል “ ለእናንተ የተመቸ የሚመስል ቤተ ክርስቲያን ስታገኙ ሩጡ/አምልጡ ! “ ብሏል ፤ ወንጌል መመቸት/ምቾት ማግኘት ማለት አይደለም ፡፡ በምቾት ላይ ማተኮር ማለት ቤተ ክርስቲያን የምቾትን ወንጌል እየሰበከች ነዉ ማለት ነው ይህ የኢየሱስ ቃል በአለም ዉስጥ ጠልቆ በመግባት ለዉጥ እንዲያመጣ የሚራዳ ለአለም የሚሆን መልዕክት አይደለም ፡፡
ሁላችንም ያመነዉ እዉነት በመሆን እዉነታችን እንዲሆን መስማት እንችላለን ፤ ያንን እዉነት ስናጠናዉ እንደ አዳኝ እና እንደ ጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ እዉነት እንደ ሆነ እናዉቃለን ? ጳዉሎስ ስለ ሰዎስተኛ ሰማይ ልምምዱ አዉርቷል፡፡ በሰዎስተኛ ሰማይ ላይ ሳለ ለአዲስ ኪዳን እዉነት የአገልግሎት መገለጥ ተሰጥቶት ነበር ፤ ስለሆነም ጳዉሎስ ለማንኛዉም ምክንያት በሰዎች መካከል መገኘትንም አካትቶ ለእርሱ የተሰጠውን ማንኛዉንም ነገር ለማመቻመች ፍቃደኛ አልነበረም ፡፡ በቤተ ክርስቲያን ከሰዎች ጋር ተገናኘ ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን ምን ልትሆን እንደምትችል ያለዉን መገለጥ አልተቀበሉትም ነበር ፡፡ ጳዉሎስ ገላትያዊያንን ለማገልገል እና መላዉ አለምን ወደ እግዚአብሄር መንግስት ለማምጣት ዝግጁ ነበር ፡፡ ጳዉሎስ ገላትያዊያንን ያን መገለጥ እንዳይዙ እና በመገረዝ ድርጊት ላይ ማትኮራቸዉን እንዲቀጥሉ ሊፈቅድላቸዉ አልቻለም ፡፡ ትናትና ካይል እንዳስተማረው “ ግብዝነት ሰዎችን ከወንጌል እዉነት ይከለክላል “ ፡፡
ህጉ (ስርዓቱ፣ የኃይማኖታዊ አስተምሮን፣ ጳጳስነትን ወይም ሁልጊዜ ያላችሁበት መንገድ) የእዉነታችሁ ድንበር ከሆነ እና ከዚያም ዉጪ የመገለጥ መንፈስ ሲኖራችሁ በአይምሮአችሁ እና በኃሳባችሁ ምክንያት ከኢየሱስም እንኳን ወደ ኋላ ትመለሳላችሁ ፡፡ በእዉነተኛ መገለጥ ከተመላለሳችሁ ቃሉን ኮምፓሳችሁ ታደርጉታላችሁ ፡፡ ያለ ምክንያት እምነትን ያዙ ፡፡
ገላትያ (3፡ 6-9)፡ “ አብርኃም እግዚአብሄርን አመነ “ ምክንያቱም እግዚአብሄር ሲናገረዉ ሰምቶ ስለ ነበር (ቁጥር 6) ፡፡ እምነት የእግዚአብሄርን ቃል ከመስማት ይመጣል ፤ ያ ማለት አሕዛብ ሁሉ ሊሰሙት ይገባቸዋል ፡፡ ከእግዚአብሄር የሆነዉ “ ያ ቃል “ በግልፅ “ እግዚአብሄር ይናገራል “ ከሚለዉ ሬማ ከሚለዉ ቃል የሆነ ነው ፡፡ እምነት በመንፈስ የእግዚአብሄርን ቃል በመቀበል እንደሚያዝዘዉ የእግዚአብሄርን ቃል መታዘዝ ነው ፤ እምነት ወደ ማይታወቅ መጓዝ/መሄድ ማለት አይደለም ከእግዚአብሄር ለመጣዉ ቃል መታዘዝ ማለት እንጂ ፡፡ “ አሕዛብ ሁሉ “ በዚያ እምነት ይባረካሉ (ቁጥር 8) (ዘፍ 12፡ 3) ፡፡ አባታችን አብርሃም ለአብርሃም መንፈሳዊ ልጅን የሚያመጣን መንፈሳዊ ዘርን ሰጠ (ቁጥር 9) ፡፡
ገላትያ (3፡ 10-12)፡ ጳዉሎስ ሰዉ ህጉን መጠበቅን ከመረጠ ለማንኛዉም ሰዉ ለማድረግ የማይቻለዉን (ቁጥር 10) ሁሉንም ህግ መጠበቅ (ሁሉንም 613 ህግ) እንደነበረበት ለማመልከት ከዘዳ (27፡ 26) ይጠቅሳል ፤ ይሁን እንጂ ሰዉ ሁሉንም ህግ መጠበቅ ቢችል እንኳን በራሱ ድርጊት አይፀድቅም (ቁጥር 11) ፤ ይልቁንም ሰዉ በክርስቶስ ባለዉ እምነት የፀደቀ ሲሆን ህጉን መከተል በእምነት ላይ የተመሰረተ አይደለም (ሮሜ 3፡ 27-31፣ 4፡ 13-14) ፡፡ ህጉ ሰዎች በተቀበሉት በዚያን ጊዜ ለሰዎች እንደ እምነት አካል የተሰጠ ነበር ምክንያቱም የመገለጥ መንፈስ ተሰጥቷቸዉ ስላል ነበር ፡፡ በኃጢዓት እና በሞት ቁጥጥር ስር ባለዉ አለም ላይ ኢየሱስ በመስቀል ሞቱ በኩል የህይወትን ህግ አመጣ ፡፡
ገላትያ (3፡ 13-22)፡ ኢየሱስ እኛ አሕዛቦች የእግዚአብሄር ልጆች እንድንሆን የተረገመ ለመሆን ፍቃደኛ ነበር (ቁጥር13) (ዘዳ 21፡ 23) ፡፡ ቁጥር 14 በአንድ አረፍተ ነገር የመላዉ የወንጌል መልዕክት ነው “ የመንፈስን ተስፋ በእምነት እንድንቀበል የአብርሃምን በረከት ወደ አሕዛብ በኢየሱስ ክርስቶስ ይደርስላቸዉ ዘንድ “ ፡፡ ኢየሱስ ልባችንን የሚይዝ እና የሚማርክ አዲስ ህግን አመጣ ፤ በዉስጣችን ካለዉ መንፈሱ የተነሳ በኑሮአችን ላይ የሚይዘንን ኃጢዓት ማሸነፍ እንችላለን ፡፡
ቁጥር 16 ስለ መንግስቱ ባህል የእግዚአብሄርን እቅድ አስቀምጧል ፤ እግዚአብሄር ከመጀመሪያዉ የሰዉን ልጅ ሁሉ ወደ ራሱ ለማምጣት እቅድ ነበረው ፡፡ እግዚአብሄር በኃጢዓት ልምድ ዉስጥ አመጣን (በኖህ መርከብ)፣ በተመረጠዉ ህዝቡ በኩል (በአብርሃም በኩል)፣ በነፃ መዉጣታቸዉ ዉስጥ (በሙሴ) በምድር ላይ ማንም ያልነበረዉን አዲስ ህግ መቀበል ወደ ሚችሉበት ስፍራ አመጣን ፤ በዚህ ሁሉ ኢየሱስ ለላተካተቱት ሰዎች አዲሱን መርሁን ለመቀበል በመጣ ጊዜ በምድር ላይ ማንም ተቀብሎት እንዳልነበር በአዲስ ኪዳን ዉስጥ መረዳት ችለናል ፤ ይህን ለመግለፅ በእግዚአብሄር ቃል ዉስጥ የታሪክ ክፍሎች ስላሉን ይህን ሁሉ እናስተዉላለን ፡፡ እምነት በአጠቃላይ ስለመታዘዝ እና ከእኛ የሆነ ነገርን የሚፈልግ ነው (ቁጥር 16-17) ፡፡ በነፃነታችን ክርስቶስን እናገለግለዋለን፣ በእግዚአብሄር ፍቅር በኩል ለኢየሱስ ክርስቶስ በባርነት እናገለግላለን/እንቀመጣለን ፡፡
መደምደሚያ
ህጉ የሰዉ ልጅ በራሱ እንደፈለገዉ እንዳይኖር አስፈላጊ ነበር ፡፡ ይህ ህግ በሚገባ በኃጢዓት ይቅርታ በኩል አዲስ ኪዳንን አደረገ ፡፡
በኑሮአችን ማድረግ የምንችለዉ ታላቅ ነገር (በሪቫይቭ ት/ቤት እያደረግን ያለነው) የክርስቶስን መገለጥ ለመቀበል እና በኑሮአችን እንድንሰራዉ እግዚአብሄር የሚፈልገዉን ለማድረግ በጥቂት በመከፋፈል በቅደም ተከተሉ መፅሀፍ ቅዱስን ወደፊት እና ወደ ኋላ በአዲስ ኪዳን እና በብሉይ ኪዳን መካከል ማጥናት ነው ፡፡ በህይወታችሁ መገለጥ ከፈለጋችሁ ሌላ ኮንፈረንስ ላይ አትገኙ ብቻዉን በእግዚአብሄር ቃል ላይ ብቻ ሁኑ/ተገኙ ፡፡
ጥያቄዎች
-
ጳዉሎስ ገላትያዊያንን በምን ጠራቸው ? በዚያ እነርሱን መጥራቱ ምን እያለ ነበር (ሉቃ 24፡ 25, 1ጢሞ 6፡ 9, ቲቶ 3፡ 3) ?
-
በህግ ስራ መዳን ለምን የሚቻል አልሆነም (ኤፌ 2፡ 8-9, ቲቶ 3፡ 5) ?
-
የአብርኃም እምነት በአሕዛብ አማኞች ላይ ምን ይሰራል (ሮሜ 4፡ 11, 16) ?
-
ለእናንተ ኢየሱስ እንዴት እርግማን እና በረከት ሆኗል (ዘዳ 21፡ 23, ኢሳ 32፡ 15, ሕዝ 36፡ 26, ዮሐ 7፡ 37-39, 2ቆሮ 5፡ 21, ዕብ 9፡ 28, 1ጴጥ 2፡ 24) ?
-
በህጉ የማትድነ ከሆናችሁ ህጉ ለምን ተሰጠ (ሮሜ 7፡ 1-13) ? ህጉን በመስጠት የተሳተፈዉ ማን ነበር (ሐዋ 7፡ 53, ዕብ 2፡ 2) ?
-
በገላትያ 3 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Galatians 3:27–29
“For as many of you as have been baptized into Christ have put on Christ like a garment. There is no Jew or Greek, slave or free, male or female; for you are all one in Christ Jesus. And if you belong to Christ, then you are Abraham’s seed, heirs according to the promise.”
ጳውሎስ ለገላትያ ሰዎች አማኞች የሚድኑት በእምነት ብቻ እንደሆነና ጻድቅ የሚኖረው በእምነት እንደሆነ ማብራራቱን ቀጠለ ፡፡ ይህ እምነትም የሚገኘው የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ነው ፡፡ ከእንግዲህ የኃጢአትና የሞት ህግ አያስፈልግም ፡፡ ከእንግዲህ በአይሁድና በግሪክ ፣ በባሪያና በጌታ ፣ በወንድና በሴት መካከል ልዩነት የለም ፡፡ የመንፈስ ህግ የሚገኘው በክርስቶስ ዘንድ ነው ፡፡ የክርስቶስ ናችሁ ፡፡ ስለዚህም በየቀኑ ክርስቶስን ልክ እንደ ልብስ ልበሱት በመንፈሱም ተመላለሱ ፡፡ በህይወታችሁ ታአምራትን የሚሰራው መንፈስ ነው ፡፡
በቃሉ ላይ ጊዜን አሳልፉ ምክንያቱም እምነት የሚገኘው የእግዚእብሔርን ቃል በመስማት ስለሆነ ፡፡ የእግዚእብሔር ኃይል በእናንተ ውስጥ ታላቅ ይሆናል ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኢየሱስ ይመራችኋል ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ወደ መንፈስ ይመራችኋል ፡፡ በክርስቶስ ላይ በላችሁ እምነት አማካኝነት የታላቁ ንጉሥ ወንዶችና ሴቶች ልጆች እንደሆናችሁ አስታውሱ ፡፡ የክርስቶስ ናችሁ ፤ በክርስቶስ ነጻ ወጥታችኋል ደግሞም በክርስቶስ አንድ ናችሁ ፡፡
“ ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና ። አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና ።
እናንተም የክርስቶስ ከሆናችሁ እንኪያስ የአብርሃም ዘር እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ ። “ ገላትያ 3፡27-29 ተጨማሪ ጥቅስ ሮሜ 10:17 — “እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ገላትያ 3:11 — “ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎአልና ማንም በእግዚአብሔር ፊት በሕግ እንዳይጸድቅ ግልጥ ነው። ገላትያ 3:26 — “በእምነት በኩል ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁና፤ |
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።