The Meeting
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Liberator Galatians 2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የአይሁድ አማኞች ጳዉሎስ ተጥለዉ እና ዉጪ ከነበሩ ሰዎች ጋር ወንጌልን ለመጋራት በነበረዉ የፍቃደኝነት እዉነት አስቸጋሪ ጊዜ ያላቸዉ እንደ ነበሩ ይመስላሉ ፤ በተጨማሪም ጳዉሎስ ህጉን ለመጠበቅ አይሁዶች ያልነበሩትን እነዚህን አዲሶች አልፈለገም ፡፡ አሕዛቦች አብዛኛዎቹ አይሁዶች ካደረጉት በላይ በተለዬ ወንጌልን አገኙ/ያዙ ፤ ይህ አሁንም በእምነት እና በስራ የመዳን መረዳት በሚሰሩት በአይሁድ አማኞች ላይ ጥቂት ችግሮችን ፈጥሯል ፡፡
ትምህርት
ገላትያ (2፡ 1-2)፡ ዋይርስቤ ጳዉሎስ “ ለብቻቸዉ አስታዉቃቸዋለሁ “ በማለት የገለፀዉን ጉባኤዉ በማለት ሰይሞታል ፡፡ ጳዉሎስ፣ በርናባስ እና ቲቶ በአሕዛብ መካከል ስለሰበከዉ ወንጌል የኢየሩሳሌም መሪዎችን ለመንገር ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ ፤ ይህ ጳዉሎስ ለቤተ ክርስቲያን መሪዎች አክብሮት ማሳየቱን እና ለመሪነታቸዉም መታዘዙን የሚያሳይ ነበር ፡፡ የኢየሩሳሌም መሪዎች የእርሱ ወንጌል ትክክለኛ እንደ ነበር እስኪወስኑ ድረስ የሚችለዉን መጠን ያክል ሄደ (ቁጥር 2) ፡፡
ጳዉሎስ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ ሲል (ቁጥር 1) ወደ ኢየሩሳሌም እየጠቀሰ የነበረዉ የትኛዉን ጉዞ እንደሆነ መጠየቅ አለብን ፡፡ ጳዉሎስ ወደ ኢየሩሳሌም ቢያንስ አምስት ጉዞን አድርጓል ፡፡
- ከኢየሱስ ጋር በደማስቆ መንገድ ከመገናኘቱ በኋላ - “ ሳዉልም ወደ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ይተባበር ዘንድ ሞከረ ፤ ሁሉም ደቀ መዝሙር እንደ ሆነ ስላላመኑ ፈሩት “ (ሐዋ 9፡ 26-30, ገላ 1፡ 18-20) ፡፡
- የርኃቡ ጉብኝት - “ ከእነርሱም አጋቦስ የሚሉት አንድ ሰው ተነስቶ በዓለም ሁሉ ታላቅ ራብ ሊሆን እንዳለዉ በመንፈስ አመለከተ ፤ ይህም በቀላዉዴዎስ ቄሳር ዘመን ሆነ ፡፡ ደቀ መዛሙርትም እያንዳንዳቸው እንደ ችሎታቸው መጠን አዋጥተዉ በይሁዳ ለሚኖሩት ወንድሞች እርዳታን ይልኩ ዘንድ ወሰኑ እንዲህም ደግሞ አደረጉ በበርናባስና በሳዉልም እጅ ወደ ሽማግሌዎች ሰደዱት “ (ሐዋ 11፡ 28-30, ገላ 2፡ 1-10) ፡፡
- የኢየሩሳሌምን ማህበር/ሽማግሌዎች/ሸንጎ - ምናልባትም ጉብኝቱ በደንብ ከገላትያ 2 ጋር ይገጣጠማል/ይመሳሰላል ፡፡ ገላትያ 2 በኢየሩሳሌም ማህበር/ሸንጎ ምን እንደተካሄደ በግልፅ ይናገራል (ሐዋ 15፡ 1-29) ፡፡
- የጳዉሎስ ሁለተኛ የአገልግሎት ጉዞ መጨረሻ ላይ (ሐዋ 18፡ 22) ፡፡
- በእስራት የሆዉ የመጨረሻ ጉብኝቱ (ሐዋ 21፡ 15 – 23፡ 35) ፡፡
በርናባስ እና ቲቶ ወደ ኢየሩሳሌም በዚህ ጉዞ ላይ የጳዉሎስ አጋሮች ነበሩ ፡፡ የበርናባስ ስም “ የመበርታት ልጅ “ ማለት ነው ፡፡ በርናባስ በርኃቡ ጉብኝት እና በመጀመሪያዉ የአገልግሎት ጉዞ አብሮት ስለ ነበር ስለ ጳዉሎስ ትምህርት እና አገልግሎት ለመመስከር የተለዬ ስፍራ ላይ ነበር ፡፡ በተጨማሪም ጳዉሎስ ከጳዉሎስ አገልግሎት የተነሳ አማኝ የሆነዉን የአሕዛብ አማኙን ቲቶንም አመጣው፡ “ በኃይማኖት (በእምነት) ህብረት እዉነተኛ ልጄ ለሚሆን ለቲቶ “ (ቲቶ 1፡ 4) ፡፡
ከነማን ጋር ተገናኙ ? ገላት (2፡ 9) በተለዬ/በዝርዝር የሚጠቅሳቸው “ ያዕቆብን፣ ኬፉን (ጴጥሮስን) እና ዮሐንስን “ ፡፡ ጴጥሮስ እና ዮሐንስ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ነበሩ ፡፡ ኢየሱስ ጴጥሮስን የእምነትን በር እንዲከፍትና እንዲዘጋ “ ቁልፉን “ ሰጥቶት ነበር ፡፡ ዮሐንስ ከኢየሱስ ሰዎስት የቅርብ ደቀ መዛሙርት ዉስጥ አንዱ ነበር ፡፡ ያዕቆብ መጀመሪያ በኢየሱስ ያላመነ ነገር ግን በኋላ በኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን ላይ መሪ የሆነ የኢየሱስ ወንድም ነበር ፡፡
ገላትያ (2፡ 3-5)፡ ዋይርስቤ ይህን “ ሕዝባዊዉ ስብሰባ “ ፤ የአሕዛብ አማኙ ቲቶ ያልተገረዘ እና “ የተገረዘ እንዲሆን የመገደደ ስሜት “ አልተሰማዉም ነበር ፡፡ መገረዝ የአይሁድ ሰዎች ከእግዚአብሄር ጋር በኪዳን እንደ ነበራቸዉ የሚያሳይ ምልክት ነበር ፡፡ እዉነቱ ቲቶ ያልተገረዘ መሆኑ በስብሰባዉ ላይ ለመገኘት በሚያስተባብሩ አንዳንድ “ ሀሰተኛ ወንድሞች “ ትልቅ ጉዳይ ነበር ፡፡ አንዳንዶች በኢየሱስ ላይ እና ስራንእንደ መዳኛ መንገድ ሙጭጭ ሲሉ ጳዉሎስ በእምነት ብቻ ስለ ሆነዉ መልዕክት ሰብኮ ነበር ፤ ጳዉሎስኢየሱስ ነፃ አዉጪ እንደሚሆን ተረድቷል፡ “ በነፃነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን ፤ እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ “ (ገላ 5፡ 1) ፤ “ የወንጌልም እዉነት በእናንተ ዘንድ ጸንቶ እንዲኖር….. ተስፋ በመቁረጥ አልተገዛላቸዉም “ (ቁጥር 5) ፡፡
ገላትያ (2፡ 6-10)፡ ዋይርስቤ ይህን ክፍል “ ጋላዊ ማረጋገጫ “ በማለት ጠርቶታል ፤ ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ እና ዮሐንስ በቤተ ክርስቲያን ታዋቂ ስልጣን የነበራቸዉም ቢሆኑም ጳዉሎስ እግዚአብሄር ምንም አድሎ እንደማያደርግ ያውቃል ፡፡ በመጨረሻም ጳዉሎስየእነዚህን መሪዎች ማረጋገጫ ሳይሆን የእግዚአብሄርን ማረጋገጫ ተከታተለ ፡፡ ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ እና ዮሐንስ ጳዉሎስ የተለዬ ተልዕኮ እንደ ነበረዉ አዩ ፡፡ ጴጥሮስ ለተገረዙት ሲላክ ጳዉሎስ ላልተገረዙት የተለዬ ጥሪ እንደ ነበረዉ አስተዉለዋል ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ መሪዎቹ ጳዉሎስን “ የወዳጅነት እና የተቀባይነት የተለመደ ምልክት የነበረዉን የአጋርነታቸዉን ቀኝ እጃቸዉን ሰጡት ፤ ይህም በኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን ተወካዮች የጳዉሎስ ሙሉ እዉቅና ማግኘትን እንደሚያመለክት “ አመልክቷል ፡፡ ብቸኛዉ ልመናቸዉ ጳዉሎስ አድርጎት የነበረዉን እና ማድረጉን እንዲቀጥል ጳዉሎስ “ ድሆችን እንዲያስብ “ ብቻ ነበር (ቁጥር 10) ፡፡
እዚህ ስፍራ ላይ ሁሉም በተመሳሳይ ገፅ ላይ ነበሩ ፡፡ ጳዉሎስ እና ጴጥሮስ ስለ ተልዕኮአቸዉ መረዳት ላይ ደርስዉ ስለ ነበር አንዱ የሌላዉን አስተምሮ እና ተልዕኮ ተረድቷል ፡፡
ገላትያ (2፡ 11-14)፡ ጳዉሎስ ጴጥሮስ በማስመሰል ያደረገዉን ገጠመኙን እንደ ገና ተናገረ ፡፡ ጴጥሮስ ወደ አንጾኪያ በመምጣት “ ጥቂት ሰዎች ከያዕቆብ እስከሚመጡ ድረስ “ (ቁጥር 12) ከአሕዛብ ጋር በላ ፤ እነዚህ ሰዎች አሁንም ስለ መገረዝ የሚያስቡ የአይሁድ አማኞች ይሆናሉ ፡፡ ከደረሱም በኋላ ጴጥሮስ ራሱን ከአሕዛቦቹ እና ከሚያምኑት አይሁዶች ራሱን አገለለ፣ በርናባስም የእርሱን ምሳሌ ተከተለ (ቁጥር 13) ፡፡ “ ከተገረዙት ወገን ያሉትን ፈርቶ ያፈገፍግ ነበርና “ (ቁጥር 12) ፡፡ ጳዉሎስ በሕዝብ ፊት በቀድሞዉ የግል ቃለ ምልልሳቸዉ የተነሳ ጴጥሮስን ተጋፈጠው (ቁጥር 14) ፡፡
ገላትያ (2፡ 15-21)፡ ጳዉሎስ በኢየሱስ የሆነ እምነት ብቻዉን አማኞችን እንደሚያፀድቅ ደግሞ ተናገረ ፡፡ ህግን መጠበቅ በፍፁም በእግዚአብሄር ፊት አንዴ እንደሚያጸድቅ ያውቃል ፤ በእግዚአብሄር ፊት በህግ በኩል ሰዉ ፅድቅን ማግኘት የሚችል ከነበር ኢየሱስ በከንቱ ሞቷል ማለት ነው (ቁጥር 21) ፡፡
መደምደሚያ
ብቻዉን የእምነት ወንጌል ለአሕዛብም ለአይሁዶችም ነበር ፡፡
Warren Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: New Testament, (Colorado Springs: David C Cook, 2007), p. 690.
Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Galatians, p. 34; available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/galatians.pdf.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), pp. 1660–1661.
MacArthur, p. 1662.
Wiersbe, p. 691.
Wiersbe, p. 692.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1520.
ጥያቄዎች
-
ቲቶ ማን ነበር ? ከጳዉሎስ ጋር እንዴት የተገናኜ/ህብረት ያለው ሆነ ( 2ቆሮ 2፡ 13, 7፡ 5-6, ቲቶ 1፡ 4-5)
-
ከኢየሩሳሌም መሪዎች ጋር በግል ለመወያዬት ጳዉሎስ ለምን አስፈለገው (ሐዋ 15፡ 1-2) ? ጳዉሎስን ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሄድ ማን ነገረው ? የስብሰባዉ ዉጤት ምንድን ነበር (ገላ 2፡ 6) ?
-
የጳዉሎስ ጉዳይ ከጴጥሮስ ጋር ምን ነበር ? ጳዉሎስ ግጭቱን እንዴት ያዘዉ/አስተካከለው?ሌላ አማኝን በኃጢዓት ዉስጥ በምታዩ ጊዜ ግጭቱን እንዴት ትይዙታላችሁ/ትፈቱታላችሁ ?
-
ጴጥሮስ እምነቱን ለምን አመቻመቸ ? በአሁኑ ጊዜ ላይ ቤተ ክርስቲያን በምን ታመቻምቻለች ? በምን ላይ ታመቻምቻላችሁ ? ራሳችሁን በመመርመር እነዚህን ነገሮች መንፈስ ቅዱስ ለእናንተ እንዲገልጥላችሁ ጠይቁ (2ቆሮ 13፡ 5) ፡፡
-
የጳዉሎስ ህይወት ገላ (2፡ 20) እንዴት አንፀባርቆታል (ሮሜ 6፡ 2-6, ኤፌ 4፡ 22) ? ያን ጥቅስ ህይወታችሁ እንዴት ያንፀባርቀዋል ?
-
በገላትያ 2 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Galatians 2:19–20
“For through the law I have died to the law, so that I might live for God. I have been crucified with Christ and I no longer live, but Christ lives in me. The life I now live in the body, I live by faith in the Son of God, who loved me and gave Himself for me.”
ክርስቶስ ሞቶ ከባርነት ፣ ከህግ ፣ ከስራ ደግሞም እግዚአብሔርን በራሳችሁ ደስ ለማሰኘት ከመጣር ነጻ አውጥቷችኋል ፡፡ ክርስቶስ ለእናንተ ራሱን ሰጠ ፡፡ ክርስቶስ ሞቶ እናንተ ግን አሁንም ጽድቅን ለማግኘት ህጉን መጠበቅና በህጉ መኖር ካስፈለጋችሁ ክርስቶስ በከንቱ ሞቷል ማለት ነው ፡፡ ነገር ግን ክርስቶስ የሞተው ስለ እናንተ ነጻነት ነው ፡፡ ጽድቃችሁ በክርስቶስ ብቻ ነው ፡፡ ለራሳችሁ ያላችሁ ከፍተኛ አመለካከት ፣ ህግን መጠበቃችሁ እንድሁም ፍጹም ለመሆን የምታደርጉት ጥረት ጭምር ከክርስቶስ ጋር አብሮ ሞቷል ፡፡ ከእንግዲህ ህይወታችሁ ስለእናንተ አይደለም ፡፡ ነገሮችን የእግዚአብሔርን ይሁንታ ለማግኘት ብሎ ማድረግ ከክርስቶስ ጋር ሞቷል ፡፡ አሁን ክርስቶስ በእናንተ ይኖራል በእርሱም ጸድቃችኋል ፡፡
አስታውሱ ኢየሱስ የሞተው ስለሚወዳችሁና ለእናንተ ነፍሱን አሳልፎ ለመስጠት ስለወሰነ ነው ፡፡ የእርሱ ፍቅር እንደሚገባችሁ እመኑ ፡፡ ልክ እየወደቃችሁ እንደሆነ መቆም እንደማትችሉ ሲሰማችሁ መታገሉን አቁሙ ፡፡ ኢየሱስ ወደ ምድር መጥቶ የሞተው በራሳችሁ ለመቆም የምታደርጉትን ጥረት ትቀጥሉ ዘንድ አይደለም ፡፡ ፍጹም ለመሆን ጥረታችሁን እንድትቀጥሉ አይደለም ፡፡ በክርስቶስ ውስጥ ያለ ህይወት በእርሱ ብቻ መኖር ነው ፡፡ ክርስቶስ ያለ ገደብ በሰጣችሁ ጸጋ በነጻነት መመላለስ ነው ፡፡ ከህግ ነጻ ናችሁ ፡፡ በዚያ ነጻነት ተመላለሱ ፡፡ እግዚአብሔር አክብሩ !
“ እኔ ለእግዚአብሔር ህያው ሁኜ እኖር ዘንድ በህግ በኩል ለህግ ሞቼ ነበርና ፡፡ ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ ፤ እኔም አሁን ህያው ሁኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል ፤ አሁንም በስጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው ፡፡ “
- ገላትያ 2፡19-20
ተጨማሪ ጥቅስ
- ገላትያ 2፡21 –“ የእግዚአብሔርን ጸጋ አልጥልም ፤ ጽድቅስ በኩል በኩል ከሆነ እንኪያስ ክርስቶስ በከንቱ ሞተ ፡፡ “
- ኤፌሶን 3፡12 –“ በእርሱም ዘንድ ባለ እምነታችን በኩል በመታመን ድፍረትና መግባት በእርሱ አለን ፡፡ “
- 1ኛ ጴጥሮስ 2፡16 –“ አርነት ወጥታችሁ እንደ እግዚአብሔር ባሪያዎች ሁኑ እንጂ ያ አርነት ለክፋት መሸፈኛ እንዲሆን አታድርጉ ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።