The Liberator
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Liberator Galatians 1 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ገላትያ ስለ መንፈስ ፍሬ በመግለፅ የታወቀ ነው ፤ በሁለተኛነት ገላትያ በክርስቶስ ስላለዉ ነፃነት በመግለፅም ይታወቃል ፤ በዚህ ማህበር ምክንያት ለገላቲያ ቃላችን ነፃ አዉጪ ነው ፡፡ ገላ (5፡ 1) “ በነፃነት ልንኖር ክርስቶስ ነፃነት አወጣን ፤ እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ “ ይላል ፡፡ በኢየሱስ እንደ ነፃ አዉጪ በሰራዉ ነገር ምክንያት በመንፈስ ለመኖር ነፃነት ስላለን የመንፈስን ፍሬ እናሳያለን ፡፡
ገላትያ ስሙን ያገኘዉ በትንሽ እስያ ስፍራ በአሁኑ ጊዜ ቱርክ ከሆነ ስፍራ አግኝቷል ፤ ብዙ ቤተ ክርስቲያንን ያካተተ ትልቅ ግዛት ነበር ፡፡ በገላ (1፡ 1) “ ሐዋሪያዉ ጳዉሎስ “ ብሎ እንዳስቀመጠው ጳዉሎስ ጥያቄ የሌለዉ የገላቲያ ፀሀፊዉ ነው ፡፡
መጀመሪያዉኑም ጳዉሎስ ለገላቲያ ቅርብ ከነበረች ከሲልሽያ ግዛት ከጢሮስ ነበር ፤ ከዚህም የተነሳ አካባቢዉን በደንብ ተረድቶታል /ያውቀዋል ፡፡ ጳዉሎስ በሐዋሪያት ስራ 22 እንደ ገለፀው በታዋቂዉ አስተማሪ/ህግ አዋቂ ገማሊያ ስር በመማሩ ከኢየሱስ ጋር በደማስቆዉ መንገድ ከገጠመዉ ነገር በፊት በይሁዳ ዉስጥ የተነሳ ኮኮብ ሆኗል ፤ ከዚህ ገጠመኝ በኋላ ማክአርቱር ጳዉሎስ “ የክርስቲያን አለቆችን ከማሳደድ ወደ ታላቅ አገልጋይነት “ ሆነ በማለት ፅፏል ፡፡
ገላትያ በአዲስ ኪዳን ዉስጥ የተካተተ ጳዉሎስ ከፃፋቸዉ 13 መልዕክቶች ዉስጥ አንዱ ነው ፤ ይህ መልዕክት ለቤተ ክርስቲያን ቡድኖች የተፃፈ ነበር - “ ወደ ገላትያ አብያተ ክርስቲያናት “ (ገላ 1፡ 2) ፡፡ በገላትያ 2 ጳዉሎስ ወደ ኢየሩሳሌም ሸንጎ/መማክርት የተደረገን ጉብኝት ይገልፃል ፤ ይህ አብዛኞች ምሁራን እስከነበሩበት ቀን ከክርስቶስ ሞት 49 በኋላ በሐዋሪያት ስራ 15 የነበረ የኢየሩሳሌም መማክርት ከነበር ገላቲያ ከጥቂት አመት ቆይታ በኋላ የተፃፈ እንደ ነበር ይመስላል ፡፡
ገላትያ በሮማዊያን ግዛት ክፍል /አዉራጃ ከመሆኗ በፊት ስያሜው የትንሽ ነገድ ክልል ያመለክታል ፤ ሮማዉያን ትልቅ ክፍለ ሀገርን በመፍጠር ገላትያ የሚለዉን ስም ሰጧት ፡፡ በብዙ ተቀባዮች ምክንያት ማክአርቱር ስለ ገላቲያ የጳዉሎስን ማጣቀሻ ስለ መረዳት የሁለት ትምህርት ቤቶች ትምህርትን አቅርቧል፡
- ገላትያ በነገድ ትርጉሙ ላይ የተጠቀመ ነበር - ገላትያ የአዉሮፓዉያን ነዋሪ የነበሩ ገላትያዊያን የሚኖሩበት በአነስተኛ በማዕከላዊ እስያ የሚገኝ ክልል ነበር ፡፡ ከክርስቶስ ልደት በፊት በሰዎስተኛዉ ክፍለ ዘመን ከጋዉል(ከቀድሞ ምዕራብ አዉሮፓ) ወደ ግዛቱ የፈለሱ ነበሩ ፤ ከዚያም ከክርስቶስ ሞት 25 አካባቢ በኋላ በነገድ ገላትያዊያን ባልነበሩ አንዳንድ ሰዎች ይኖርባት የነበረችን ገላትያ ክፍለ ሀገርን ፈጠሩ ፡፡
- ገላቲያ በፖለቲካ ትርጉም ላይ ጥቅም ላይ የዋለ ነበር - ገላትያ መላዉን ክፍለ ሀገር የገለፀ እና በገላትያዊያን ነገድ ብቻ በሚኖሩበት ግዛት የተወሰነ አልነበረም ፡፡
ጳዉሎስ በደቡብ ገላትያ ከተሞች በአንፆኪያ፣ በልስጥራ፣ ደርቤ እና በኢቆንዮን ቤተ ክርስቲያንን መስርቷል ፤ ማክአርቱር እነዚህ ከተሞች በገላቲያ ነገድ ግዛት/ክልል የሚገኙ እንዳልነበሩ ይፅፋል ፡፡ በሰሜን ገላትያ ጳዉሎስ እንደ መሰረተው የተመዘገበ ቤተ ክርስቲያ የለም ፤ ይሁን እንጂ የዚህ መልዕክት የመጀመሪያ ተቀባይ ማን እንደ በር በእርግጠኝነት መናገር አስቸጋሪ ነው ፡፡ ጳዉሎስ በሰሜን ገላትያ ክፍል ዉስጥ ተጉዟል ነገር ግን በእነዚያ አካባቢዎች የተመዘገበ ያደረገዉ ምንም የወንጌል አገልግሎት የለም (ሐዋ 16፡ 6, 18፡ 23) ፡፡ በትንሹ ምናልባትም ጳዉሎስ የመሰረታቸዉ በደቡብ ገላትያ ቢያንስ አራቱ ቤተ ክርስቲያናት እንደ ተቀበሉ መደምደም ምክንያታዊ ነው ፡፡
ጳዉሎስ ለምን ገላትያን እንደ ፃፈ ማክአርቱር ሁለት ምክንያቶችን አጉልቶ ያሳያል፡
በእምነት መፅደቅን ለማብራራት - የአይሁድ ሰዎች ጳዉሎስ ከወንጌል ተቃራኒ እንደ ነበር ገልፆት የነበረዉን ሕግ ለእምነት ስለሚፈፅሙ ፡፡
አንዳንዶች የኢየሩሳሌም ማህበር/ሸንጎ ድንጋጌን/ስርዓትን እየጣሱ ስለ ነበር - እነዚህ ሐሰተኛ መምህራን በሙሴ ህግ ክርስቲያን ከመሆን በፊት መጀመሪያ አይሁድ መሆን ግዴታ እንደ ሆነ ስለተናገሩ ፡፡
ትምህርት
ገላትያ (1፡ 1-5)፡ ጳዉሎስ መልዕክቱን የሚጀምርበትን ሂደት ተከተለ ፡፡ ራሱን በማስተዋወቅ/በመለየት (ቁጥር 1) ተቀባዮቹን በመድረስ (ቁጥር 2) ሰላምታን አቀረበ (ቁጥር 3) ፡፡ ከዚያም በኋላ ጳዉሎስ በፍጥነት ወደ ወንጌል አጭር ቃለ ምልልስ ዉስጥ ገባ (ቁጥር 4-5) ፡፡
ገላትያ (1፡ 6-9)፡ አሁን ጳዉሎስ የፃፈበትን ምክንያት ማድረሱን ቀጠለ ፡፡ ገላትያዊያን ለእነርሱ ከሰበካቸዉ ወንጌል ዞር በማለት “ የተለዬ ወንጌል በመያዛቸው “ ተደነቀ (ቁጥር 6) ፤ ጳዉሎስ በእምነት ብቻ በሆነዉ የፅድቅ ወንጌል የፀና ስለ ነበር ያን ወንጌል በተናገረዉ ላይ መልዓክት እንኳን ቢሆን እርግማንን ተነገረባቸው (ቁጥር 8-9) ፡፡
ገላትያ (1፡ 10)፡ ጳዉሎስ ወደ ሌላ ሰዉ መልዕክት በማዳመጥ ደስተኛ እንዲሆኑ የማድረግ ፍላጎት አልነበረዉም ፤ በክርስቶስ ስለ ነበር ከኢየሱስ ወጪ ለሌ ማንንም ሰዉ ለመለማመጥ ትኩረት አልሰጠም (ቁጥር 10) ፡፡
ገላትያ (1፡ 11-12)፡ ጳዉሎስ የሰበከዉ ወንጌል “ ከኢየሱስ ክርስቶስ በመገለጥ የተሰጠ “ ነበር (ቁጥር 12) ፤ ከኢየሱስ ጋር የጳዉሎስ ፈጣን የሆነዉ መገናኘት ሙሉ በሙሉ ቀይሮት ነበር ፡፡ “ ሲሄድም ወደ ደማስቆ በቀረበ ጊዜ ድንገት በእርሱ ዙሪያ ከሰማይ ብርሃን አንጸባረቀ ፤ በምድርም ላይ ወድቆ ሳለ፡- ሳዉል ሳዉል ስለ ምን ታሳድደኛለህ? የሚለዉን ድምፅ ስማ ፡፡ ጌታ ሆይ ማን ነህ ? አለው ፡፡ እርሱም፡- አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ ፤ የመዉጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል አለው ፡፡ እየተንቀጠቀጠና እየተደነቀ፡- ጌታ ሆይ ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ ? አለው ፡፡ ጌታም ፡- ተነስተህ ወደ ከተማ ግባና ታደርገው ዘንድ የሚያስፈልግህን ይነግሩሃል አለው “ (ሐዋ 9፡ 3-6) ፡፡
ገላትያ (1፡ 13-17)፡ የኔልሰን ማብራሪያ ጳዉሎስ በቁጥር 13 የጠቀሰዉን “ የአባቶች ወግ “ የሚለዉን “ በከፊል በብሉይ ኪዳን እና በከፊል የአባቶቻቸዉን ልምድ ወይም ወግ በመጨመር ላይ የተመሰረተ የአይሁዶች የህይወት አኗኗር “ በማለት ገልፆታል ፡፡ ጳዉሎስ “ ለአባቶች ወግ ከመጥን በላይ እየቀና “ (ቁጥር 14) እግዚአብሄር ለህይወቱ የተለዬ እቅድ ነበረው ፡፡ ከደማስቆ መንገድ ገጠመኙ በኋላ በሌላ በማንም ሳይመከር ለሰዎስት አመት ወደ አረብ ሄደ፡፡
ገላትያ (1፡ 18-20)፡ በአረብ ከነበረዉ ጊዜ በኋላ ለ15 ቀን ከጴጥሮስ ጋር ወደ ተገናኘበት ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ ፡፡
ገላትያ (1፡ 21-24)፡ ጳዉሎስ እግዚአብሄር በህይወቱ ይህን ስራ በፀጋ እንዴት እንደሰራ አሳወቀ/ተናገረ ፡፡ የጳዉሎስ ቃለ ምልልስ እንደ ዜና በመሰራጨቱ ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሄር በጳዉሎስ ህይወት አድርጎት ስለ ነበረዉ ነገር እግዚአብሄርን አከበሩ ፡፡
መደምደሚያ
የጳዉሎስ የህይወት መስመር በእግዚአብሄር ተቀየረ ፡፡ ኢየሱስ ራሱን ለጳዉሎስ ገለጠለት ጳዉሎስም ነፃ አዉጪዉን በመቀበል እንደ ገና በባርነት ቀንበር መያዝን እምቢ አለ (ገላ 5፡ 1) ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville, Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 165.
MacArthur, p. 1654.
MacArthur, p. 1654..
MacArthur, p. 1654.
MacArthur, p. 1654.
MacArthur, p. 1654.
MacArthur, p. 1654.
Earl Radmacher, et. al., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary, (Nashville: Thomas Nelson, 1997), p. 1517.
ጥያቄዎች
-
ጳዉሎስ እንዴት ሐዋሪያ ሆነ (1ቆሮ 9፡ 1) ? እንደ አንድ ሐዋሪያ ጥሪዉ ምን ነበር (ሐዋ 9፡ 15) ? እንዲሰራ ተጠርቶበት የነበረዉን አሟልቷል/ፈፅሟል ? ጌታ እናንተን ምን እንድታደርጉ ጠርቷችኋል ? በዚህ ጥሪ እየኖራችሁ ነው ?
-
በገላትያ ቤተ ክርስቲያን ዋናዉ ጉዳይ ምን ነበር ? ከ 1ቆሮ (15፡ 1-11) ተመልሰዉ ለነበሩት ጳዉሎስ ያለዉ ወንጌል ምን ነበር ?
-
ጳዉሎስ ቤተ ክርስቲያንን በሚያሳድድበት መካከል ላይ ወንጌልን እንዴት ተቀበለ (ሐዋ 9፡ 3-9) ? የአይሁድ ማህበር/አዋቂዎች የኃይማኖትን ትዕዛዝ ከተቀበሉት ጋር የዚህ ንፅፅሩ እንዴት ነበር ? ወንጌልን እንዴት ተቀበላችሁ ?
-
ከተቀየረ በኋላ ከሌሎች አማኞች ጋር የጳዉሎስ ግንኙነት ምን ይመስል ነበር ? ወዲያዉኑ ወደ ኢየሩሳሌም ካልሄደ ጳዉሎስ ወዴት ሄደ ? ጌታ ለአገልግሎት ለምን ያክል ጊዜ አዘጋጀው ?
-
ጴጥሮስ እና ሌሎች ደቀ መዛሙርት በጎበኛቸዉ ጊዜ ጳዉሎስን ተቀብለዉታል (ሐዋ 9፡ 26-28) ? በእርሱ ለምን ነበር የተጠራጠሩት ? በመጨረሻ ጳዉሎስ ስለ ማን ማረጋገጫ አሰበ/ተጠነቀቀ ?
-
በገላትያ 1 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Galatians 1:6–7
“I am amazed that you are so quickly turning away from Him who called you by the grace of Christ and are turning to a different gospel—not that there is another gospel, but there are some who are troubling you and want to change the good news about the Messiah.”
ለሰዎች ወንጌሉን ስትነግሯቸው ለክርስቶስ ወንጌል እርግጠኞች ፣ ልበ ሙሉ እናም ደፋር ሆነው ማየት ደስ አይልም ? ሆኖም ግን አንዳንዴ ያንን እርግጠኛ እና ደፋር ሰው ከወንጌሉ እውነት ፈጥኖ ዘወር ሲል ታገኙታላችሁ ፡፡ ይህም የወንጌሉ ዘር ከውስጣቸው ስለተወሰደ ነው ! ጳውሎስም እንዲሁ ሌሎችን ሲያገለግል እንዲህ አይነት ነገር ገጥሞታል ፡፡ እርሱም እንዴት ፈጥነው ከተቀበሉት እውነት ዘወር ሊሉ እንደቻሉ ለመረዳት ከበደው ፡፡
ጌታ የወንጌሉን ዘር እንድትዘሩ እንዳዘዛችሁ አስታውሱ ፡፡ እውነቱ አንዳንድ ዘሮች ጠንካራ ሆነው ይበቅላሉ ፤ አንዳንዶች ደግሞ ለማደግ ይቸገራሉ ፤ አንዳንድ ዘሮች ደግሞ በጠላት ተንኮል ምክንያት ይነቀላሉ ፡፡ ጠላት ፣ አሳቹ እያደባ ነው ፡፡ መንፈሳችሁ ዝግጁ ቢሆንም እንኳ ስጋችሁ ግን ዳካማ ነው ፡፡ እንደ አማኝ በጌታ በርቱ ፡፡ አይኖቻችሁን በእምነታችሁ ጀማሪ ላይ ከማድረግ አታቋርጡ ፡፡ በእርሱ ጽኑ ፡፡ ምልከታችሁን በአንዱ እና በእውነተኛው በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ስታደርጉ ትበረታላችሁ ፡፡
“ በክርስቶስ ጸጋ እናንተን ከጠራችሁ ከእርሱ ወደ ልዩ ወንጌል እንዲህ ፈጥናችሁ እንዴት እንዳለፋችሁ እደነቃለሁ ፤ እርሱ ግን ሌላ ወንጌል አይደለም ፤ የሚያናውጡአችሁ የክርስቶስንም ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ አንዳመንዶች አሉ እንጂ ፡፡ “
- ገላትያ 1፡6-7
ተጨማሪ ጥቅስ
ማቴዎስ 13፡19 –“ የመንግስትን ቃል ሰምቶ በማያስተውል ሁሉ ፣ ክፉው ይመጣል ፣ በልቡ የተዘራውንም ይነጥቃል ፤ በመንገድ ዳር የተዘራው ይህ ነው ፡፡ “
ዮሐንስ 10፡10 –“ ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም ፤ እኔ ህይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ ፡፡ “
2ኛ ጴጥሮስ 3፡17-18 –“ እንግዲህ እናንተ ወዳጆች ሆይ ይህን አስቀድማችሁ ስለምታውቁ ፣ በዓመጸኞች ስህተት ተስባችሁ ከራሳችሁ ጽናት እንዳትወድቁ ተጠንቀቁ ፤ ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ ፡፡ ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን ፤ አሜን ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።