Final Warnings And Exhortations
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Treasure 2 Corinthians 13 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ዛሬ በ 2ቆሮንቶስ የመጨረሻዉን ምዕራፍ እያጠናን ነው ፤ ለዚህ መፅሀፍ ቃላችን መዝገብ የሚል ነው ፡፡ መዝገቡ ክርስቶስ በእኛ ዉስጥ ነው ፤ በድካማችን እና በዝለታችን ዉስጥ ክርስቶስ የተገለጠ ነው ፡፡ አንዴ ለመጨረሻ ጊዜ ከቆሮንቶሳዊያን ጋር በጳዉሎስ መስተጋብር ላይ እንሂድ ፤ ሐዋሪያት ስራ 18 በቆሮንቶስ የቤተ ክርስቲያን መመስረት በግምት በጳዉሎስ በሁለተኛዉ የአገልግሎት ጉዞ ጊዜ ከክርስቶስ ሞት 50-52 በኋላ አካባቢ እንደሆነ ገልፆአል ፡፡ ጳዉሎስ 18 ወራት በመቀመጥ የእግዚአብሄርን ቃል እያስተማረ አገለገላቸው ፡፡ በዚህ ሂደት ዉስጥ ወሲባዉ ስነ ምግባር ከጎደላቸዉ ሰዎች ጋር እና ለጣዖት አምላኪዎች ከሆኑ ሰዎች ጋር ህብረት እንዳያደርጉ ባሳሰበበት በ 1ቆሮ (5፡ 9) ላይ የተጠቀሰዉን “ የጠፋዉን መልዕክት “ ጳዉሎስ ፅፏል ፡፡ 1ቆሮንቶስ ተብሎ የሚታወቀዉ መልዕክት ምናልባትም በዚያ ከነበረዉ አገልግሎቱ ከሁለት እስከ አምስት አመት በግምት ከክርስቶስ ሞት 55 በኋላ የተፃፈ ነበር ፡፡
ከቆሮንቶሳዊያን ጋር ንግግሩን በመቀጠል በሰዎስተኛዉ የአገልግሎት ጉዞዉ ላይ ጳዉሎስ ይህን መልዕክት ከኤፌሶን ፃፈ (1ቆሮ 16፡ 8) ፡፡ ጳዉሎስ ይቺን ቤተ ክርስቲያን አንድ ጊዜ ለእነርሱ “ የሚያም ጉብኝት “ እከማድረግ (2ቆሮ 2፡ 1) ይወዳታል ፡፡ በዚህ ጉብኝት ጊዜ በደህና አልሄደም ፤ አክብሮት የለም ለእርሱም ዋጋ አልሰጡትም ፡፡ በዚህ የሚያም ጉብኝት ምክንያት ኃይለኛ/ከባድ መልዕክትን ፃፈ (2ቆሮ 2፡ 3) ፡፡ ለማጠቃለል ያክል የጠፋ መልዕክት ስለ ነበር ስቃይ ያለበትን ጉብኝት በማስከተል 1ቆሮንቶስ ተፃፈ በመቀጠልም በግምት በግምት ከክርስቶስ ሞት 55-56 በኋላ ተፅፎ የነበረዉን 2ቆሮንቶስን በማስከተል ኃይለኛ መልዕክት ተፃፈ ፡፡ በ 2ቆሮ (12፡ 14) ጳዉሎስ እነርሱ ጋር ሰዎስተኛዉን ጉብኝት ለማድረግ በጣም እንደ ጓጓ ፅፏል ፤ ሐዋ (20፡ 1-4) ጳዉሎስ ለምን ይህን ሰዎስተኛዉን ጉብኝ እንዳላደረገ ገልፆአል ፡፡
ትምህርት
2-ቆሮንቶስ (13፡ 1-8)፡ እንደ ዋረን ዋይርስቤ ገለፃ ጳዉሎስ ቆሮንቶሳዊያንን አስጠነቀቃቸው ፤ እንደ ቶም ኮንስታብል ገለፃ የቁጥር 1 “ ሁለት ወይም ሰዎስት ምስክሮች “ የሚተረጎሙበት አራት እይታዎች አሉ ፤ “ መጀመሪያው… ማን ፃድቅ እንደ ነበር ለመወሰን በአዘዘዉ በኢየሱስ ክርስቶስ በምስክሮች ምስክርነት መሰረት ቤተ ክርስቲያን ፍርድን ታሳልፋለች “ ፤ በሌላ ቋንቋ ምስክሮቹ ጳዉሎስ ያለዉን ማንኛዉንም ያረጋግጣሉ (ማቴ 18፡ 15-20) ፡፡ “ ሁለተኛው ጳዉሎስ ወደ ቆሮንቶስ ያደረጋቸዉን ሰዎስት ጉብኝቶች ለንፁህነቱ እንደ ሰዎስት ምስክርነት ተመልክቷቸዋል ፤ ሰዎስተኛው ቆሮንቶሳዊያንን እንደማያድናቸው ምናልባትም ማስጠንቀቂያዎቹን እያመለከተ ይሆናል …. አራተኛው ጳዉሎስ ወደ ቆሮንቶስ በተመለሰ ጊዜ ምናልባትም የህብረቱ ሰራተኛ ምስክሮች ይሆናሉ “ ፡፡
ጳዉሎስ በኃጢዓታቸዉ ላይ በተናገረ ጊዜ ከቆሮንቶሳዊያን ጋር እንደ መፅሀፍ ቅዱስ ለመነጋገር አቀደ ፡፡ ዋይርስቤ “ በአካባቢ ቤተ ክርስቲያን ኃጢዓት ላይ በመንነጋገር ጊዜ ዉሸት ሳይሆን እዉነት ሊኖረን ይገባል “ ፡፡ ዘዳ (19፡ 15) ስህተት በአንድ ምስክር ብቻ ሊመሰረት እንደማይችል ነገር ግን የሁለት ወይም ከዚያ በላይ ምስክሮች ምስክርነትን እንደሚፈልግ ገልፆአል ፡፡ ጳዉሎስ በ 1ጢሞ (5፡ 19) ተመሳሳይ ንግግር አድርጓል ፡፡
የጳዉሎስ ማስጠንቀቂያ ኃጢዓት ማድረግን ለቀጠሉት ለዘብተኛ እንደማይሆን ንግግሩ ያካተተ ነው (ቁጥር 2) ፤ ቁጥር 3 ሀሰተኛ መምህራንን እና “ ሐዋሪያት ጳዉሎስ ሀቀኛ ሐዋሪያ እንደ ነበር ማረጋገጫን እየተናገሩ እንደ ነበር “ ያመለክታል ፡፡ ጳዉሎስን ደካማ ስለመሆኑ ከሰሱት ነገር ግን “ ጳዉሎስ በማንኛዉም ኃጢዓት እና አመፅ ላይ ለመናገር ሐዋሪያዉ ኃይሉን እና ስልጣኑን ይጠቀም ነበር “ ፡፡ ማክአርቱር በጳዉሎስ ላይ በማመፅ ቆሮንቶሳዊያን እና የአይሁድ አዋቂዎች በዚያ ቡድን ዉስጥ በክርስቶስ ላይ እያመፁ እንደ ነበሩ አመልክቷል ፡፡ ጳዉሎስ በእርሱ ዉስጥ ባለዉ በእግዚአብሄር ኃይል ያሸንፋቸዋል (ቁጥር 4) ፡፡ ማክአርቱር ጳዉሎስ “ ወደ ቆሮንቶስ በተነሳዉ በከበረዉ በክርስቶስ መቋቋም በማይቻለዉ ኃይል ይመጣል “ አለ ፡፡
በመቀጠልም ጳዉሎስ ቆሮንቶሳዊያንን ስለ እርሱ መጨነቃቸዉን በማቆም የራሳቸዉን እምነት እንዲፈትኑ አስጠነቀቃቸው ፤ ጳዉሎስ በቆሮንቶስ ላለች ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አባት ስለነበር እምነቱ ዉሸት ከነበር የእነርሱም እምነት ዉሸት ነበር ፡፡ ጳዉሎስ ዳግም ተወልደዉ እንደ ሆን ወይም ደግሞ እንዳልሆነ እንደሚያስተዉሉ ተስፋ አደረገ (ቁጥር 5-6) ፤ ስለዚህ ሰዎች ስለ እምነት ለማስረጃነት ራሳቸዉን እንዴት መመርመር ይችላሉ ? ማክአርቱር ብዙ መንገዶችን ዘርዝሯል ፡፡ በጽድቅ እና በቅድስና እየተመላለሳችሁ ነው (መዝሙር 35) ? ፍትህን፣ ትህትናን እና ቸርነትን ታሳያላችሁ (ሚክ 6፡ 8) ? ማቴ (5፡ 3-12) መልካም/ብፁህ ባህሪያትን ይዘረዝራል ፡፡ በመንፈስ ድሆች ናችሁ ? አዝናችኋል ? በገርነት ትመላለሳላችሁ ? ፅድቅን ትራባላችሁ ትጠማላችሁስ ? ትምራላችሁ በልባችሁስ ንፁኅ ናችሁ ? አስታራቂዎች ናችሁ ? በ 1ቆሮ (13፡ 4-7) ላይ የተገለፀውን ፍቅር ታሳያላችሁ ? በህይወታችሁ ዉስጥ ያለዉ የመንፈስ ፍሬ ነው (ገላ 5፡ 22-23) ? አሳባችሁ ፊል (4፡ 8) ያንፀባርቃል ? በእምነት ከሆናችሁ በእነዚህ ነገሮች ላይ ታድጋላችሁ ፡፡ ህይወታችሁ በ 1ተሰ (5፡ 14-22) የተገለፁጽን መሰረታዊ ነገሮች/እዉነቶች ያንፀባርቃል ? በ 2ጴጥ (1፡ 5-9) እንደ ተገለፀዉ በጌታ እየተመላለሳችሁ ነው ? በእዉነት፣ በመታዘዝ እና በፍቅር ትመላለሳላችሁ (1 ዮሐንስ) ? በራዕ (1፡ 3) ባለዉ ሂደት ትኖራላችሁ ? ማንም ሰዉ መመርመርን አይወድም ፤ ምክንያቱም መፈተን/መመርመር ስለሚጎዳ እና ዉድቀትን ስልንፈራ ፡፡ ጳዉሎስ ግን ይህን ምርመራ እንዲያደርጉ ስለሞገታቸው ፈተናዉን አይወድቁም ፤ ጳዉሎስ ፈተናዉን እንዲያልፉ ፈለገ (ቁጥር 7) በተጨማሪም ሁሉንም ነገር በእዉነት መሰረት እንዲያደርጉት ፈለገ (ቁጥር 8) ፡፡
2-ቆሮንቶስ (13፡ 9-13)፡ በመቀጠልም ጳዉሎስ አበረታታቸው ፡፡ ጳዉሎስ ጠንክረዉ ስለ ነበር እና በሙገባ የበሰሉ እንዲሆኑ ስለሞፈልግ ተደሰተ (ቁጥር 9) ፤ ጳዉሎስ እንዲጎብዙ ፈለገ ፡፡ እንዲሞሉ፣ እንዲዘጋጁ እና የሰለጠኑ እንዲሆኑ ፈለገ ፡፡ ፍፁምነት ለማለት በቁጥር 9 ላይ ጳዉሎስ የተጠቀመበት ቃል “ የሚመጥን መሆን፣ የተዘጋጀ መሆን….. የተሰበረ አጥንትን ማስተካከል፣ የተንጋደደ እጅን/ወይም እግር ማስተካከል ….ለጉዞ መርከብንበሚገባ ማዘጋጀት… ለዉጊያ ሰራዊትን ማዘጋጀት… መረብን መጠገን “ በማለት ሊተረጎም ይችላል ፡፡ ጳዉሎስ ጠንካሮች እንዲሆኑ ፈለጋቸው ፡፡
ጳዉሎስ በቁጥር 11 በአምስት ምክሮች ዘጋ፡ “ ፍፁማን ሁኑ፣ ምክሬን ስሙ፣ በአንድ ልብ ሁኑ በሰላም ኑሩ የፍቅርና የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል “ ፡፡
መደምደሚያ
ዝግ በማለት እነዚህን ሁለት መልዕክቶች ስለምታጠኑ አመሰግናለሁ ፡፡ ምናልባትም በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ዉስጥ መዝገብ በሆነዉ ክርስቶስ በእናንተም ዉስጥ ስላለ በኃይለኛዉ ትበረታታላችሁ ፡፡
Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1989), p. 541.
Thomas L. Constable, “Dr. Constable’s Notes on 2 Corinthians,” 2021 Edition, p. 175; available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/2corinthians.pdf.
Constable, p. 175.
Wiersbe, p. 541.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1652.
MacArthur, p. 1652.
MacArthur, p. 1652.
MacArthur, p. 1652.
Wiersbe, p. 542.
MacArthur, p. 1652.
Wiersbe, p. 542.
ጥያቄዎች
-
ፍርድን ከማስተላለፍ ወይም ቅጣትን ከማስተላለፍ በፊት ከሁለት በላይ ምስክር ለምን አስፈላጊ ነው (ዘኁ 35፡ 30, ዘዳ 19፡ 15) ? በ 2ቆሮ (13፡ 1) ጳዉሎስ ይህን ለቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ለምን ተናገረ ?
-
በ 2ቆሮ (13፡ 5) ቆሮንቶሳዊያን በእምነት ራሳቸዉን እንዲመረምሩና እንዲፈትኑ የተጠሩ ነበሩ ፤ ጳዉሎስ በዚህ ምን እያለ ነው (ዮሐ 14፡ 19-21, ሮሜ 8፡ 10, 1ቆሮ 9፡ 24-27) ? በእነዚህ ጥቅሶች መሰረት ራሳቸዉን ክርስቲያን ብለዉ የሚጠሩ ሁሉ ወደ ሰማይ ይሄዳሉ ብላችሁ ታስባላችሁ ?
-
በ 2ቆሮ (13፡ 10) ጳዉሎስ “ ስለዚህ ጌታ ለማፍረስ ያይደል ለማነጽ እንደ ሰጠኝ ስልጣን ከእናንተ ጋር ሳለሁ በቁርጥ እንዳልሰራ በሩቅ ሆኜ ይህን እጽፋለሁ “ አለ ፤ ጳዉሎስ እነዚህን ነገሮች ለማምጣት ከእነርሱ ጋር እስኪሆን ከመጠበቅ ይልቅ ይህን ለማድረግ ለምን እንደ መረጠ ምን ታስባላችሁ ?
-
የእግዚአብሄር አብ፣ የእግዚአብሄር ወልድን እና የእግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስን ፀጋ፣ ፍቅር እና ህብረት እንዴት ልናገኝ እንችላለን ? (ሮሜ 5፡ 5, ፊል 2፡ 1)
-
በ 2ቆሮንቶስ 13 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 2 Corinthians 13:5
“Test yourselves to see if you are in the faith. Examine yourselves. Or do you yourselves not recognize that Jesus Christ is in you?—unless you fail the test.”
ብዙ ሰዎች በየጊዜው በዶክተር ለሚደረግላቸው የጤና ምርመራ መሄድ አይፈልጉም ወይም ደግሞ በየጊዜው የመኪናቸውን ደህንነት ለማረጋገጥ ወደ ጋራጅ ይዘው አይሄዱም ፡፡ ምናልባት ፡- ይህ ገንዘብ ያስወጣኛል እኔ ደግሞ ገንዘብ ማውጣት አልፈልግም ፡፡ ብለው ያስቡ ይሆናል ፡፡ ደህና እንደሆንኩ ይሰማኛል ታድያ ስለምንድን ነው መሄድ የሚያስፈልገኝ ? የሆነ መጥፎ ነገር ቢፈጠርስ ? ከተፈጠረ ደግሞ ያንን መፍታት አለብኝ ! ሆኖም ግን ከሄዳችሁ በኋላ ታመሰግናላችሁ ደግሞም ከጭንቀታችሁ ታርፋላችሁ ! በተመሳሳይ በጌታ ላይ ያላችሁ እምነትም በየጊዜው ምርመራ ደግሞም እንዲሁ ክትትልን ይፈልጋል ፡፡
ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ቤተክርስቲያን የጻፈውን መልዕክቱን ሲጨርስ ራሳቸውን በኃይማኖት ይመረምሩ ይፈትኑ ዘንድ ይመክራቸዋል ፡፡ ኃይማኖታችሁን መፈተን ምናልባት በሳምንት አንድ ቀን ስለ ቃሉ ለመወያየት ከጓደኛችሁ ጋር መገናኘት ፤ ከጸሎት ጓዳችሁ ጋር ሳታቋርጡ መጸለይ ወይም ደግሞ በህይወታችሁ ስለምትፈተኑበት ክፍል ጓደኛችሁ እንድጠይቃችሁ መጠየቅ ሊሆን ይችላል ፡፡ ምናልባትም ደግሞ ራሳችሁን በእግዚአብሔር ፊት ዝም በማሰኘት እርሱ በልባችሁ ውስጥ ከእርሱ ጋር የማይስማማውን ነገር እንዲገልጠው መፍቀድም ሊሆን ይችላል ፡፡ ጌታ ለእናንተ የሚሻው ደስ እንድትሰኙ ፣ ፍጹማን እንድትሆኑ ፣ እንድትበረቱና ሰላም እንድሰማችሁ ነው ፡፡ በመንፈስ ለማደግ ደስ ቢላችሁም ባይላችሁም በትጋት ሳታቋርጡ እነዚህን “ ፈተናዎች ” በራሳችሁ ላይ አካሂዱ ፡፡ ከጓደኛችሁ ጋር ቀጠሮ ለመያዝ ጊዜ ውሰዱ ወይም ደግሞ ዛሬ ጌታ ልባችሁን ይመረምር ዘንድ ጸልዩ ፡፡ በቃ አድርጉት !
“ በኃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ ራሳችሁን ፈትኑ ወይስ ምናልባት የማትበቁ ባትሆኑ ኢየሱስ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ እንዳለ ስለ እናንተ አታውቁምን ? “ - 2ኛ ቆሮንቶስ 13፡5
ተጨማሪ ጥቅስ
- 1ኛ ቆሮንቶስ 11:28 — “ ሰው ግን ራሱን ይፈትን እንዲሁም ከእንጀራው ይብላ ከጽዋውም ይጠጣ ፡፡ “
- 2ኛ ቆሮንቶስ 13:11 — “ በቀረውስ ወንድሞች ሆይ ደኅና ሁኑ ፡፡ ፍጹማን ሁኑ ፣ ምክሬን ስሙ ፣ በአንድ ልብ ሁኑ ፣ በሰላም ኑሩ ፣ የፍቅርና የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል ፡፡ “
- ገላትያ 6:4 — “ ነገር ግን እያንዳንዱ የገዛ ራሱን ስራ ይፈትን ፣ ከዚያም በኋላ ስለ ሌላው ሰው ያልሆነ ስለ ራሱ ብቻ የሚመካበትን ያገኛል ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።