Paul's Letters 2 Corinthians

Visions And Revelations

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Treasure 2 Corinthians 12 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 530 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ጳዉሎስ በቆሮንቶስ የነበረችዉ ቤተ ክርስቲያኑ ለጌታ የታመነች ባለመሆኗ ያሰበ/የተጨነቀ ነበር ፤ ጳዉሎስ በመልዕክቱ ጥሩ አስተላልፎ ነበር ፡፡ ወደ ሰፈር በመግባት በማፋጨት ጳዉሎስን እና ሐዋሪያነቱን ዋጋ እያሳጡ የነበሩ ሰዎች ነበሩ ፡፡ ጳዉሎስ በጌታ ማን እንደ ሆነ በመመካት በቆሮንቶስ ካለችዉ ቤተ ክርስቲያን ጋር ለማገናኘት በመሞከር መለሰ ፡፡ በታሪክ ቆሮንቶሳዊያን በራዕይ እና በመገለጥ የተማረኩ ነበሩ ፤ ስለሆነም ጳዉሎስ በምዕራፍ 12 ይህን ይደርሳል ፡፡

ትምህርት

2-ቆሮንቶስ (12፡ 1)፡ ሰዉ እንደ ነቃ ራዕይ ይሆናል ፡፡ በሆነ ስፍራ ቆማችሁ ሊሆን ይችላል በሁሉም በድንገት የተለዬ ስፍራ እንዳላችሁ ይሰማችኋል ያ ራዕይ ነው ፤ በዚህ በተለዬ ስፍራ ጌታ የሖነ ነገር ያሳያችኋል ፡፡ ራዕይ ረጅም ጊዜ ሊወስድ የሚችል ወይም በጣም ፈጣን ሊሆን ይችላል ፡፡ ይህ ጳዉሎስ እያወራበት የነበረዉ አይነት ራዕይ ነበር ፡፡ ማክአርቱር ራዕይ በሐዋሪያት መፅሀፍ ዉስጥ ስድስት ጊዜ እንደተመዘገ ያስቀምጣል፡

  1. ራዕይ ለእናንተ በእግዚአብሄር እንድትመላለሱ መሰረትን ያስቀምጣል (ሐዋ 9፡ 12) ፡፡
  2. ራዕይ ሊሰማ እና ሊታይ ይቻላል (ሐዋ 16፡ 9-10) ፡፡
  3. ጌታም በራዕይ ሊታይ/ሊገለጥ ይችላል (ሐዋ 18፡ 9) ፡፡
  4. ራዕይ ማስጠንቀቂያ ሊሆን ይችላል (ሐዋ 22፡ 17-18) ፡፡
  5. ራዕይ አቅጣጫ ሊሰጥ ይችላል (ሐዋ 23፡ 11) ፡፡
  6. ራዕይ ማበረታታት እና ማረጋገጫ ሊሰጥ ይችላል (ሐዋ 27፡ 25-29) ፡፡

ጳዉሎስ ስለእነዚህ ራዕዮች ተመካ ምክንያቱም ከቆሮንቶስ አማኞች ጋር ለመገናኘት ይህ እንደሚያስፈልግ ስለሚያዉቅ ፡፡ ኢዮ (2፡ 28-32) ራዕይ እና ትንቢት መናገር እስከ ክርስቶስ መምጣት ድረስ እንደሚሆኑ ይገልፃል ፤ ይህ ማለት እግዚአብሄር ዛሬም ለሰዉ በህልም እና በራዕይ መናገሩን ይቀጥላል ማለት ነው ፡፡ እንዚህን ነገሮች በፍፁም ዝቅ አድርጋችሁ እንዳታዩ ! ጳዉሎስ ስለ መገለጡም ተናገረ ፡፡ መገለጥ ከክርስቶስ የሚመጣ ነው (ገላ 1፡ 12) ፤ አንዳንድ የጳዉሎስ ድርጊቶች በመገለጥ የተፈፀሙ ነበሩ (ገላ 2፡ 2) ፡፡ ሚስጥራት ለጳዉሎስ በራዕይ በኩል ተገልጦለታል (ኤፌ 3፡ 3) ፤ በግልፅ የሚመካበት ነገር ነበረው ፡፡

2-ቆሮንቶስ (12፡ 2-4)፡ ጳዉሎስ እዚህም ስለ ራሱ እያወራ ነበር ነገር ግን አሁንም ለመመካት ፍቃደኛ አልነበረም፡፡ በራሱ ጊዜ የአይሁድ ህግ አዋቂዎች በሰዎስተኛ ወገንነት አዉርተዋል ፡፡ ጳዉሎስ እንደ ባህሉ የቆሮንቶሳዊያንን ቋንቋ መናገር ይችላል ፡፡ ማክአርቱር የጳዉሎስ ልምምድ እስከ ሰዎስተኛ ሰማይ “ 2ቆሮንቶስ ከመፃፉ ከ14 አመት በፊት በመሆኑ በሐዋሪያት ስራ ዉስጥ ከተመዘገበዉ ማንኛዉም ክስተት የተለዬ ራዕይ ጳዉሎስ ጋር ግንኙነት ጋር ያለዉን መለየት አልቻለም “ በማለት ፅፏል ፡፡

ስለ ሰዎስተኛ ሰማዩ እናዉራ ፤ ጳዉሎስ በሰዎስተኛ ሰማይ እና በገነት መካከል ልዩነት እያደረገ አልነበረም ፤ ተመሳሳይ ስፍራዎች ናቸው ፡፡ ራዕ (2፡ 7) የህይወት ዛፍ በገነት ነዉ በማለት ሲናገር ራዕ (22፡ 14) የህይወት ዛፍ በሰማይ ነዉ በማለት ይገልፃል ፡፡ እንደ ማክአርቱር አገላለፅ “ የመጀመሪያዉ ሰማይ የምድር አየር /ህዋ ነው (ዘፍ 8፡ 2, ዘዳ 11፡ 11, 1ነገ 8፡ 35)፣ ሁለተኛዉ ደግሞ በአለማት እና በከዋክብት መካከል ያለ ስፍራ ነው (ዘፍ 15፡ 5, መዝ 8፡ 3, ኢሳ 13፡ 10) እና ሰዎስተኛው የእግዚአብሄር መኖሪያ ነው (1ነገ 8፡ 30, 2ዜና 30፡ 27, መዝ 123፡ 1) “ ፡፡

የሆነ ቦታ ላይ ጳዉሎስ በህይወቱ ጥሪን ተቀበለ ነገር ግን ሁሉንም ነገርያጋራ ነበር ፤ በአካል ወደ ሰማይ ሄዶ/ተወስዶ ይሁንም (በዘፍ (5፡ 24) ልክ እንደ ሄኖክ ወይም በ2ነገ (2፡ 11) ልክ እንደ ኤልያስ) ወይም ደግሞ ለጊዜ መንፈሱ ከሰዉነቱ ተለይታ ቢሆንም ይህ አስፈላጊ አይደለም ፤ በዚህ መፅሀፍ ጳዉሎስ የፃፈው የሚያስደንቅ መልክ ነው ፡፡

2-ቆሮንቶስ (12፡ 5-6)፡ ማክአርቱር ጳዉሎስ “ (ለየት ባለዉ ልምምደ) ከመመካት ተቆጠበ በራዕዩ ሳይሆን በአገልግሎቱ ላይ ባላቸዉ ምልከታ መሰረት ቆሮንቶሳዊያን እንዲዳኙት ፈለገ እንጂ “ በማለት ይገልፃል ፡፡ በራዕይ ላይ ወደ የተቆለላችሁ ብቻ አትሆኑም ፤ እንመላለስበታለንም እንጂ ፡፡ “ በስጋ ላይ ያለ እሾክ/መዉጊያ “ አካላዊ የታመመ ሰዉ ሳይሆን ሰይጣናዊ የነበረ ሰዉን እንደ “ ስጋዊ ችካል/መዉጊያ “ ሊተረጎም ይችላል ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ የስጋ እሾክ/መዉጊያ ምን ሊሆን እንደሚችል ሰዎስት ትርጓሜዎችን ገልፆአል ፡፡

አካላዊ ህመም - አንዳንድ አካለዊ ህመም አይነቶች ለምሳሌ እንደ ማያቋርጥ ራስ ምታት፣ በጆሮአችሁ ዉስጥ ያለ ጩኸት፣ አደገኛ የሖነ ማንከስ ወይም የልብ ድካም ማለት ነው ፡፡

የማያቋርጥ የስጋ ፈተና - እንደ ትዕቢት፣ ገንዘብ፣ ብስጭት፣ ሰዉን ማስደሰት ወይም መፍራት አይነት ነው ፡፡

መሰደድ ወይም ተቃዉሞ ፡፡

የኔልሰን ማብራሪያ “ የጳዉሎስ መዉጊያ የሚያም ነበር የመዋረድ ልምምድ ትዕቢትን/ትምክህትን ለመከላከል እንደተሰጠ “ ይናገራል ፡፡

ማንኛዉም የነገሮች ቁጥር ትሁት ስለሚያደርጋችሁ በራሳችሁ ላይ ሳይሆን በጌታ ላይ ትደገፋላችሁ ፡፡ የሆነ ስፍራ ላይ በቆሮንቶስ ሰይጣናዊ የነበረ ሰዉ ነበር ፤ ምናልባትም ይህ ሰዉ የጳዉሎስን ዋጋ ለማጥፋት እየሞከረ የነበረ በስጋ የጳዉሎስ መዉጊያ ነበር ፡፡

2-ቆሮንቶስ (12፡ 9-10)፡ የስጋ መዉጊያ እሾክ በመጨረሻ በእግዚአብሄር ላይ የምንደገፍ ያደርገናል ፡፡

መደምደሚያ

በዚህ ምዕራፍ በቀረዉ ጥቅስ ዉስጥ በደንብ መግባታችሁን እንድትቀጥሉ አበረታታችኋለሁ ፡፡ ነገ ቃለ ምልልሱን እንቀጥላለን ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1649.

  2. MacArthur, p. 1649.

  3. MacArthur, p. 1649.

  4. MacArthur, p. 1649.

  5. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1511.

ጥያቄዎች

  1. በ 2ቆሮ (12፡ 1) ጳዉሎስ ስለ ምን አይነት መመካት እያወራ ነበር (2ቆሮ 11፡ 30, ገላ 1፡ 12) ? ትምክት ለምን አትራፊ እንደ ነበር ተናገረ ?
  2. በ 2ቆሮ (12፡ 2) ጳዉሎስ ስለ ነበረዉ መገለጥ ከማን እንደ ነበር ተናገረ ? (ሐዋ 14፡ 19-20) “ ሰዎስተኛ ሰማይ “ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ምን ታስባላችሁ (ዘፍ 28፡ 12, ራዕ 4፡ 2, 5፡ 13) ? በሆነ ነገር ላይ አጥብቆ በማሰላሰል እንደ መፀኃፍ አገላለፅ ሰዎስተኛ ሰማይ ካላ የመጀመሪያዉ እና ሁለተኛዉ ሰማይ ምንድን ናቸው ? (ዘፍ 1፡ 1, ዘዳ 10፡ 14, መዝ 148፡ 4)
  3. በ 2ቆሮንቶስ 12 መሰረት ጳዉሎስ “ የስጋ መዉጊያ “ የተሰጠዉ ለምን ነበር ? በህይወታችሁ በስጋችሁ/በህይወታችሁ “ እንደ መዉጊያ “ የምታዩት ነገር አላችሁ ? አዎ ከሆነ ትሁት ያደርጋችኋል ወይስ ያበሳጫችኋል ?
  4. በ 2ቆሮ (12፡ 20-21) ጳዉሎስ በዚያ በሚደርስ ጊዜ ቆሮንቶሳዊያን እያደረጓቸዉ እንደሚያገኛቸዉ የፈራቸዉን አንዳንድ ኃጢዓቶች ጠቅሷል ፤ ከእነዚህ ነገሮች ዉስጥ በአሁኑ ጊዜ ለክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን ትክክለኛ ድምፅ ነው ? እነዚህን ነገሮች እንድንቋቋም ምን ሊረዳን ይችላል ? (ኤፌ 4፡ 2-3, ፊል 2፡ 3, 1ጴጥ 5፡ 5)
  5. በ 2ቆሮንቶስ 12 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 2 Corinthians 12:9–10

“But He said to me, ‘My grace is sufficient for you, for power is perfected in weakness.’ Therefore, I will most gladly boast all the more about my weaknesses, so that Christ’s power may reside in me. So I take pleasure in weaknesses, insults, catastrophes, persecutions, and in pressures, because of Christ. For when I am weak, then I am strong.”

ጳውሎስ ብርቱ ሆኖ በራሱ እንዳይመካ እግዚአብሔር ስለሰጠው በስጋው ስለተሸከመው መውጊያ ያብራራል ፡፡ ጳውሎስ ይህ ነገር ከእርሱ እንድወሰድ ሶስት ጊዜ በጸሎት ቢጠይቅም ነገር ግን አልተወሰደም ፡፡ ምናልባት ይህ አካላዊ ህመም ፣ ፈተና ፣ ያማያቋርጥ ፍላጎት ወይም ደግሞ ስለ ኃይማኖት መሰደድ ሊሆን ይችላል ፡፡ ጳውሎስ በድካሙ ውስጥ ነበር ብርታት የሚገኘው ከጌታ ዘንድ እንደሆነና የእግዚአብሔር ጸጋ በቂ እንደሆነ ያወቀውና የተረዳው ፡፡

አለም እንድህ ይላል “ ጠንካራ መሆን አለብህ እናም ደግሞ ሁሉም ነገር ሊኖርህ ይገባል ፡፡ “ ነገር ግን ጌታ “ አንተ ስትደክም እኔ ብርቱ ነኝ “ ይላል ፡፡ ሁሉንም ነገር ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት አቁም ፡፡ በራስህ በቂ ፣ ጠንካራ ደግሞም ብቻውን የቆመ ለመሆን የሚደረግ ፈተናን ተቃወም ፡፡ ድክመቶችህን መደበቅ አያስፈልግህም ፡፡ አንተ ስትደክም ክርስቶስ በውስጥህ ብርቱ መሆን ይችላል ፡፡ በድካምህ መገኘቱን ፣ ኃይሉንና ጸጋውን በህይወትህ ውስጥ እንዲሰራ ታስችላለህ ፡፡ በድካምህ የእርሱ ኃይል ይፈጸማል ምክንያቱም ለመስራት ቦታ ይኖራልና ፡፡ ከራስህ ጥንካሬ ይልቅ ሰዎች በህይወትህ ውስጥ የክርስቶስን ኃይል ያያሉ ፡፡ ስለዚህም በራስህ ሳይሆን በጌታ ትመካለህ ፡፡ ወንጌል ማለት በጠቅላላው ስለ ኢየሱስና በአንተ ውስጥ ስለሚሰራው ስለ እርሱ ጸጋ ነው ፡፡ በድካምህ ደስ ይበልህ ፡፡ በቃ ዝም ብለህ በረጅሙ ተንፍስና ለህይወትህ ጥቂት የእግዚአብሔር ጸጋን ወደ ውስጥ አስገባ ፡፡ ከዚያም የእግዚአብሔር ኃይል በአንተ ይታይ ዘንድ ጠብቅ ፡፡

“ እርሱም ጸጋዬ ይበቃሃል ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ ፡፡ እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ድስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ ፡፡ ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካሜ በመንገላታትም በችግርም በስደትም በጭንቀትም ደስ ይለኛል ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና ፡፡ “

  • 2ኛ ቆሮንቶስ 12፡9-10

ተጨማሪ ጥቅስ

ሮሜ 11:6 — “ በጸጋ ከሆነ ግን ከሥራ መሆኑ ቀርቶአል ጸጋ ያለዚያ ጸጋ መሆኑ ቀርቶአል ፡፡ “

2ኛ ቆሮንቶስ 4:7 — “ ነገር ግን የኃይሉ ታላቅነት ከእግዚአብሔር እንጂ ከእኛ እንዳይሆን ይህ መዝገብ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን ፡፡ “

2ኛ ቆሮንቶስ 12:7–8 — “ ስለዚህም በመገለጥ ታላቅነት እንዳልታበይ የስጋዬ መውጊያ እርሱም የሚጎስመኝ የሰይጣን መልዕክተኛ ተሰጠኝ ይኸውም እንዳልታበይ ነው ፡፡ ስለዚህ ነገር ከእኔ እንዲለይ ሶስት ጊዜ ጌታን ለመንሁ ፡፡