Paul's Letters 2 Corinthians

Paul And The False Apostles

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Treasure 2 Corinthians 11 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 529 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በ 2ቆሮንቶስ 10 የትናትናዉ ትምህርት በጌታ ነፃነትን እንድናገኝ አበረታቶናል ምክንያቱም በዉስጣችን መዝገብ ስላለን - ያም በዉስጣችን ያለዉ ክርስቶስ ነው ፡፡ በድካማችንም እንኳን የእግዚአብሄርን ስራ እናያለን ፡፡ ጳዉሎስ ጠላት ተመስርቶ የነበረዉን ማንኛዉንም ነገር ማጥፋት ለመሞከር ይመጣል አለ ፤ በዚህ ጉዳይ የቆሮንቶሳዊያን ቤተ ክርስቲያን ነበር ፤ ጳዉሎስ በሰፈር ጠላትን በመለየት ያን ጠላት እንዴት እንዲዋጉት እንዲያወሩ አበረታታቸው፡፡ ጳዉሎስ የቆሮንቶሳዊያንን ቤተ ክርስቲያን ከመዉደዱ የተነሳ ከጠላት የሚከላከልላቸዉ እረኛ ሊሆናቸዉ ፈለገ ፡፡ ዛሬ በ 2ቆሮንቶስ 11 ጳዉሎስ የበግ ልብስ የለበሱ ተኩላዎች የነበሩ በሰፈር (በቤተ ክርስቲያን) ዉስጥ ሰዎች እንደ ነበሩ ተናገረ ፡፡ ጳዉሎስ ከመካከላቸዉ ሀሰተኛ ሐዋሪያትን ለመጥራት/ለማስወጣት ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ ወደደ ፡፡

ትምህርት

2-ቆሮንቶስ (11፡ 1-6, 13-15)፡ እንደ ዋረን ዋይርስቤ ገለፃ እነዚህ ጥቅሶች ስለ ቤተ ክርስቲያን የጳዉሎስን ቅንዓት ያሳያል ፡፡ ጳዉሎስ “ ከእርሱ ጋር እንዲታገሱ ፈለገ “ (ቁጥር 1) ምክንያቱም “ በእነርሱ ላይ እግዚአብሄራዊ በሆነ ቅንዓት ቀንቶ ስለ ነበር “ (ቁጥር 2) ፡፡ ጳዉሎስ ለአንድ ባል ሴት ልጁን ቃል ገብቶ የነበረን አፍቃሪ አባትን መልክ ስሏል ፤ ይህ ክርስቶስን ለማግባት የታጨች የአሁኗ ቤተ ክርስቲያን መልክ ነበር ፡፡ በኤፌ (5፡ 22-27) ጳዉሎስ በደንብ ይህን መልክ ገልፆታል ፡፡ በመሲሁ አንድ የመሆን ተመሳሳይ መልክ በሮሜ (7፡ 4) የሚገኝ ነው ፤ ይሁን እንጂ ይህ ጋብቻ ክርስቶስ ለሙሽራዉ እስኪመጣ ድረስ አይካሄድም (ራዕ 19፡ 1-9) ፤ ያ እስኪሆን ድረስ ቤተ ክርስቲያን የደፈረሰ ዉሃ ከሚያስመስል ማንኛዉም ነገር ባለመፍቀድ ንፁህ እንድትሆን ተመርጣለች ፡፡

ነገር ግን ቆሮንቶሳዊያን አደገኛ ሁኔታ ዉስጥ ነበሩ - ለክርስቶስ ባለመታመን ችግር ዉስጥ ፡፡ በአደገኛ ሁኔታዉ ኋላም ያለዉ ግለሰብ ሰይጣን ነበር ፡፡ ጳዉሎስ “ እባብ በተንኮሉ ሔዋንን አስቷት እንደ ነበር “ (ቁጥር 2) እና እነርሱም የተታለሉ ለመሆን አደጋ ላይ እንደ ነበሩ አሳሰባቸው ፡፡ በጠላት ድምፅ እና በእግዚአብሄር ድምፅ መካከል ልዩነት ማድረግ ካልቻሉ ምን ስህተት እንደ ነበር እንዴት ያዉቁታል ? በዘፍ (3፡ 1) እባብ “ ከሁሉም እንስሳ ተንኮለኛ “ እንደ ነበር ተገልፆአል ፤ ሰይጣንም የእግዚአብሄርን ቃል በመጠየቅ ሂዋንን አታለላት (ዘፍ 3፡ 1-6) ፡፡

ሰይጣን እኛን ለማግኘት የእግዚአብሄርን ቃል በመጠየቅ የእግዚአብሄርን ቃል መካድን ይቀጥላል ፤ ሰይጣንም በራሱ ዉሸት ይቀይረዋል ፡፡ እንደ አማኝ ትዕግስት እናጣለን ፤ ትዕግስት በምናጣ ጊዜ እምነትን ያጣን በመሆን መሰጠታችንን እና ቅንነታችንን እናጣዋለን ፤ የቆሸሽን በመሆን ሰይጣንን እንዲሄድ እንፈቅዳለን ፡፡ ወደ ቀድሞዉ ህይወታቸዉ እየተመለሱ ስለ ነበሩ ጳዉሎስ በቆሮንቶሳዊያን በጣም ቅንዓት አድሮበት ነበር ፡፡

ጳዉሎስ ለሌላ ኢየሱስ እየተሰጡ እንደ ነበር፣ ለተለዬ መንፈስ እየተሰጡ እንደ ነበር እና ለተለዬ ወንጌልም እየተሰጡ እንደ ነበር አመለከተ (ቁጥር 4) ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ኢየሱስ አምላክ ሳይሆን አስደናቂ ሰዉ ነበር የሚሉ ? ወይም አዎ ኢየሱስ በመስቀል ሞቷል ነገር ግን አምላክ አልነበረም የሚሉ ? ወይም አዎ ኢየሱስ አዳኝ ነው ነገር ግን አምላክ አይደለም የሚሉ ምን ያክል ኃሰተኛ ኃይማኖቶች አሉ ? በአሁኑ ጊዜ ስራን እና እምነትን የሚያጣምር የተለዬ ወንጌል አለ - ይህ የማስመሰል ወንጌል ነው ፡፡ “ በዋና ሐዋሪያት “ ላይ ለመመልከት ሁለት መንገዶች አሉ (ቁጥር 5) ፤ ምናልባት ዘዴአቸዉ ማታለል የሆነ የሚያስመስሉ ሐሰተኛ ሐዋሪያት እንጂ ዋና ሐዋሪያት አይደሉም ፡፡ ሌለኛዉ መንገድ ይህን ለመመልከት ቃሉ ቀድሞ የመጣዉ የክርስቶስን ብቁ የሆኑ ሐዋሪያትን ያመለክታል ፤ ጳዉሎስ እንደ ተናጋሪ የትምዕርት ስልጠና ባይኖረዉም (ቁጥር 6) በጣም አዋቂ ነበር ፡፡

2-ቆሮንቶስ (11፡ 7-12)፡ በመቀጠልም ጳዉሎስ “ ለቤተ ክርስቲያን ስላደረገዉ ቸርነት “ አወራ ፤ ጳዉሎስ በፍፁም በማንኛዉም ነገር አስከፍሏቸው እንዳልነበር አመለከተ (ቁጥር 7) ፤ የኔልሰን ማብራሪያ “ በዚያን ጊዜ የተማሩ ፈላስፋዎች እና መምህሮች በግሪክ ማህበረሰብ ዉስጥ ስለ ትምህርት ሰዎችን ያስከፍላሉ “ አለ ፡፡ ጳዉሎስ እንደ ድንኳን ሰሪ በመሆን በመስራት ከሌሎች ቤተ ክርስቲያን ድጋፍን ተቀበለ ፤ ነገር ግን በቆሮንቶስ አዉድ ያለ ክፍያ በነፃ ወንጌልን ሰበከ ፡፡ ጳዉሎስ “ እናንተን ለማገልገል ደመወዝ እየተቀበልሁ ሌሎችን አብያተ ክርስቲያናት ዘረፍሁ “ (ቁጥር 8) በማለት ተናግሯል ፤ ሌሎች ሰዎች ስለደገፉኝ እናንተን ማገልገል እችላለሁ ይህስ እኔን እንዴት የምትመለከቱበት አይደለም ? ሀቀኝነቱን ለመጠበቅ እና በእርሱ ላይ ሰዎች ይህን ከመያዝ ለመከልከል ጳዉሎስ ማድረግ ቢችልም እንኳን ከእነርሱ ምንም አይነት ፋይናንሺያል ድጋፍ አልሰበሰበም (1ቆሮ 9፡ 1-12) ፤ በዚያ ፋንታም ጳዉሎስ የሚያስፈልገዉን እንዲያቀርበለት ከመቄዶኒያ በሆኑት ወንድሞቹ ላይ ስለተደገፈ በእነርሱ ላይ ሸክም አይሆንባቸው (ቁጥር 9) ፡፡ ዋይርስቤ ጳዉሎስ የአባትነት አስተሳሰብ ነበረዉ አለ ፤ ጳዉሎስ በእነርሱ ላይ ሸክም ሊሆንባቸዉ አልፈለገም ፡፡ ይህ የሸክምነት ስዕል እንደ “ ክስነት “ ሊተረጎም ይችላል ፡፡ እንደ ዋይርስቤ አገላለፅ “ በግሪክ ይህ በቀጥታ ድንዛዜ መጨመር ማለት ሲሆን ፤ ቃሉ በንዝረቱ የተጠቁትን ካደነዘዘ ከኤሌክትሪክ ስዕል የመጣ ነው ፤ የደነዘዘዉ የሰዉነት ክፍል ለተጠቂዉ ሸክም ይሆንበታል “ ፡፡ በመዝገቡ በክርስቶስ ከእርሱ የተነሳ ጳዉሎስ ስራዉን ለመቀጠል ወስኖ ነበር ፡፡ ጳዉሎስ ስለሚወዳቸው (ቁጥር 11) በእነርሱ ላይ ሸክምን ከሚያበዙት አንዱ ላለመሆን እምቢ ብሏል (ቁጥር 9) ፡፡ የጳዉሎስ አገልግሎት የፍቅር ስራ ነበር ፤ ጳዉሎስ ይህን ስላደረገ በእርሱ ላይ በኃሰት ለመናገር እድል የላቸዉም (ቁጥር 12) ፡፡

2-ቆሮንቶስ (11፡ 16-33)፡ ጳዉሎስ “ ስለ ቤተ ክርስቲያን ጭንቀቱን “ ገለፀ ፡፡ ጳዉሎስ አልፎባቸዉ የነበራቸዉን ሁሉንም ነገሮች ዘረዘረ፡ አምስት ጊዜ 39 ግርፋትን ተቀብሎ ነበር (ቁጥር 24)፣ ሰዎስት ጊዜ በሮማዉያን በበትር ተመቶ ነበር፣ ተወግሯል፣ የመርከብ አደጋ ደርሶበታል (ቁጥር 25) ፡፡ ጳዉሎስ ገጥመዉት የነበሩትን መንፈሳዊ አካል እና አካላዊ ችግሮች/መከራዎች ዘርዝሯል፡ በወንዝ ፍርኃት፣ በወንበዴዎች ፍርኃት፣ በአሕዛብ ፍርኃት፣ በከተማ ፍርኃት፣ በምድረበዳ ፍርኃት፣ በባህር ፍርኃት እና በዉሸጻም ወንድሞች ፍርኃት በረበት (ቁጥር 26) ፡፡ ነገር ግን ጳዉሎስ “ ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው “ በማለት ጠቀሰ (ቁጥር 28) ፡፡ ጳዉሎስ ስለ ቤተ ክርስቲያን ስጋት ተሰማዉ ምክንያቱም ስለሚያስብ - እንዲሸሸጉ ወይም እንደሰጡ አልፈለገም ፤ በዚህ ሁሉ ዉስጥ ለመሄድ ፍቃደኛ ነበር ምክንያቱም ስለ እነርሱ ስለሚያስብ ፡፡ ጳዉሎስ በማንኛዉም ወይም ደግሞ በሁሉም ነገር ዉስጥ ለማለፍ ፍቃደኛ ስለ ነበር በትምህርቱ ላይ ይቆያሉ ፡፡

መደምደሚያ

ጳዉሎስ ለቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን የእዉነት የአባት መልክ/ስዕል ነው ፡፡ ሁሉም ሊያዉቋቸዉ የሚያስፈልገዉ ሐሰተኛ ሐዋሪያት የነበሩ በሰፈሩ ዉስጥ እየተንቀሳቀሱ የነበሩ ሰዎች እንደ ነበሩ ጳዉሎስ እያስጠነቀቃቸዉ ነበር ፡፡ በሐዋ (20፡ 24) ጳዉሎስ “ ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሄርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ “ ፡፡

  1. Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1989), p. 534.

  2. Wiersbe, p. 534.

  3. Wiersbe, p. 534.

  4. Wiersbe, p. 534.

  5. Wiersbe, p. 535.

  6. Wiersbe, p. 535.

  7. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 1999).

  8. Wiersbe, p. 535.

    Wiersbe, p. 535.

  9. Wiersbe, p. 536.

  10. Wiersbe, p. 536.

ጥያቄዎች

  1. በ 2ቆሮ (11፡ 1-4) ጳዉሎስ ስለ ሀሰተኛ አስተማሪዎች እና በተመሳሳይ መምህራንም ቆሮንቶሳዊያን እንደ ተማረኩ/እንደ ተጣመሙ ተናገረ ፤ በአሁኑ ጊዜ አለምን ስትመለከቱ ይህ በእኛ ዘመንም እዉነት ሊሆን ይችላል ? በምን መንገድ ?
  2. በ 2ቆሮ (11፡ 2) እንዳለዉ “ ሙሽራዋ “ ለክርስቶስ እንደ ሆነች በተመለከተ በመፀሀፍ ሌላ የት ስፍራ ላይ ተጠቅሷል ? (ኤፌ 5፡ 25-27፣ ራዕ 19፡ 7-9, 21፡ 1-2)
  3. በ 2ቆሮ (11፡ 23-27) ጳዉሎስ የእግዚአብሄርን ቃል ሲያሰራጭ የታገሳቸዉን መከራዎች ገልፆአል ፤ በዩናይትድ ስቴት በዚህ ቀን እና በዚህ ዘመን ለእንደዚህ አይነት መከራ ለመታገስ የቀረበ ክርስቲያን አለ ? በግል አስተያየታችሁ እንደ ክርስቲያን ይህ አይነቱን መከራ መሸከም እንችላለን ?
  4. በ 2ቆሮንቶስ 11 በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 2 Corinthians 11:10–11

“As the truth of Christ is in me, this boasting of mine will not be stopped in the regions of Achaia. Why? Because I don’t love you? God knows I do!”

ጳውሎስ ለሚያገለግላቻውም ጭምር ይጨነቅና ያስብ ነበር ለእነርሱም የነበረው ይህ ጥልቅ ፍቅር በከባዶቹ ጊዜያት ውስጥ ይጸና ዘንድ አበረታው ፡፡ እርሱም በቆሮንቶስ ላለችው ቤተክርስቲያን ይናገራል ፡- ልክ እግዚአብሔር እንደሚወዳችሁ ሁሉ እኔም እወዳችኋለሁ ፡፡ ዳካማ ነኝ ፡፡ ተደብድቤለሁ ደግሞም ስለ እናንተ ስለ ወንጌል እናም ህይወትን ስለሚለውጠው እውነት ብዙ መከራን ተቀብያለሁ ፡፡ ሆኖም ግን ይህ ሁሉ ይገባዋል ፡፡ ነገር ግን ጳውሎስን ያስተናገደው መገፋትና መገለል አላስቆመውም ፡፡ አማኞች እውነቱን ይከተሉ ዘንድ እናም አስቸጋሪዎች እንዳይሆኑ ጳውሎስ ስለ ወንጌል ጸና ፡፡ ጳውሎስ በጌታና ጉዞውን እንዲቀጥል በረዳው ለሌሎች ባለው ፍቅር ላይ ብቻ ተመካ ፡፡

በአገልግሎት ከባድ ጊዜያት ውስጥ ስለመጽናት ጳውሎስ ምሳሌ ነው ፡፡ ምናልባት የምታገለግለው በቤትህ ውስጥ ልጆችህን ፣ የሰንበት ትምህርት በማስተማር ፣ ትንስ የሆነ ቡድንን በመምራት ፣ ቤት የሌላቸውን በማገልገል ፣ በትልልቅ መድረኮች ላይ በማስተማር ወይም በጓዳህ ስለሌሎች በመጸለይ ሊሆን ይችላል ፡፡ ክርስቶስን ስትከተል ጌታ በጥልቀት ትወዳቸው ዘንድ ሰዎችን በዙሪያህ ያስቀምጣል ፡፡ ይህ ታላቅ ፍቅር ልክ ለጳውሎስ እንዳደረገው ሁሉ ለአንተም በድካምህ እንድትጸና ፤ በመገፋትህ እንድትጸና ደግሞም ስለ ወንጌል በምትደክመው ድካም እንድትጸና ያበረታሃል ፡፡ ጌታ በዓላማ መገኘት ባለብህ ቦታ ሁሉ አለልህ ፡፡ አስታውስ ብቻህን አይደለህም ፡፡ በዙሪያህ ላሉት ያለህን ታላቅ ፍቅርና እነርሱ ኢየሱስን እንዲያውቁ ያለህን ፍላጎት አስታውስ ፡፡ ጌታ በታላቅ ፍቅሩ እንድትጸና ብርታትን ይሰጥሃል ፡፡

“ የክርስቶስ እውነት በእኔ እንዳለ ይህ ትምክህት በእኔ ዘንድ በአካይያ አገር አይከለከልም ፡፡ ስለ ምን ? ስለማልወዳችሁ ነውን ? እግዚአብሔር ያውቃል ፡፡ “ - 2ኛ ቆሮንቶስ 11፡10-11

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ሐዋርያት ሥራ 20:24 — “ ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ ፡፡ “
  • 2ኛ ቆሮንቶስ 11:27–30 — “ በድካምና በጥረት ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት በራብና በጥም ብዙ ጊዜም በመጦም በብርድና በራቁትነት ነበርሁ ፡፡ የቀረውንም ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው ፡፡ የሚደክም ማን ነው እኔም አልደክምምን ? የሚሰናከል ማን ነው እኔም አልናደድምን ? ትምክህት የሚያስፈልግ ከሆነ ከድካሜ በሚሆነው ነገር እመካለሁ ፡፡ “
  • ገላትያ 6:9 — “ ባንዝልም በጊዜው እናጭዳለንና መልካም ስራን ለመስራት አንታክት ፡፡ “