Paul's Letters 2 Corinthians

Battling Spiritual Warfare

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Treasure 2 Corinthians 10 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 528 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ሁሉም ነገር ስለ መስጠት ብቻ ስለሆነው በ 2ቆሮንቶስ (8-9) ላይ ተመልክተናል ፡፡ ለ 2ቆሮንቶስ ቃላችን መዝገብ የሚል ነው (2ቆሮ 4፡ 7) ፤ በዉስጣችን መዝገብ አለን ፡፡ በ 2ቆሮንቶስ 10 ከዚህ በፊት ከነበሩት ጥቅሶች እና ምዕራፎች ጋር የማይገናኝ የሚመስል ትልቅ ለዉጥን/መቀየርን እናያለን ፡፡ ምዕራፍ 10 በመንፈሳዊ ዉጊያ ላይ ተቃራኒ ስለሆነዉ በእኛ ዉስጥ ስላለዉ የክርስቶስ ኃይል ነው ፡፡ እንዲሁም ጳዉሎስ በእርሱ ላይ ሀሰተኛ ንግግሮችን እያደረጉ የነበሩትን የአይሁድ አስተማሪዎችን ለመድረስ እድሉን ተጠቀመበት ፡፡

ትምህርት

2-ቆሮንቶስ (10፡ 1-6)፡ ዋይርስቤ ምዕራፍ 2 ወደ ሰዎስት ክፍል ይከፍለዋል፣ የመጀመሪያው “ እንዴት መንፈሳዊ ዉጊያን እንደምንዋጋ “ ያወራል ፤ ይህ ክፍል እነዚህን የመጀመሪያዎቹን ስድስቱን ጥቅሶችን አለማለፋችን በጣም ስለሚያስፈልግ በዚያም ደህና እሆናለሁ ፡፡ ጳዉሎስ “ በክርስቶስ ርህራሄ እና ገርነት “ (ቁጥር 1) ጀመረ ፤ በመቀጠልም በቅርብ ደካማ እንደ ነበር ነገር ግን በሩቅ ደፋር እንደሆነ በተናገሩት አዋቂዎች ላይ ተናገረ (ቁጥር 1) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ እለምናችኋለሁ በማለት ጳዉሎስ ቆሮንቶሳዊያንን ከመምጣቱ በፊት ስለ ትችቱ ለመፍታት በገርነት እየጠየቃቸዉ ስለ ነበር ከእነርሱ ጋር ነገሩ ጥብቅ እንደማይሆን “ ይገልፃል ፡፡ ጳዉሎስ በቁጥር 3 ራሱም እንኳን በስጋ እየኖረ እንዳለ በመግለፅበስጋ እንደሚኖሩ ገለፃቸው ፤ ነገር ግንጳዉሎስ “ መንፈሳዊ ባልሆነ መንገድ አልፈፀመም “ ምክንያቱም ጦርነቱ አለማዊ/ስጋዊ ሳይሆን ከእግዚአብሄር ኃይል ነበር እንጂ (ቁጥር 4) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ የሲዖል ኃይል አሁንም የእግዚአብሄርን ስራ ለማጥፋት እየሞከረ እንደ ሆነ (ማቴ 16፡ 18) “ ይገልፃል ፡፡ ጳዉሎስ ከእግዚአብሄር እዉቀት ያልመጡትን ከፍተኛ የስነ መለኮት አስተምሮዎች እና ክርክሮችን ማጥፋቱን ቀጠለ (ቁጥር 5) ፤ በመጨረሻም ጳዉሎስ ታዛዥ ያልነበረዉን ማንኛዉንም ሰዉ ለመቅጣት ዝግጁ ነበር (ቁጥር 6) ፡፡

ቁጥር 3 መንፈሳዊ ጦርነትን ጠቅሷል ፤ መንፈሳዊ ጦርነት ምንድን ነው ? መንፈሳዊ ጦርነት በብዙ የመገለጥ ደረጃዎች ላይ ያጠቃናል ፡፡

  1. የመጀመሪያዉ ደረጃ ስጋዊነት ነው - በስጋና በእግዚአብሄር ኃይል ጠላት (ሰይጣን) ወደ ስጋ ሊስበን እየሞከረ ነው ፤ ይህን እግዚአብሄር በሰጠን አንድ መሳሪያ መዋጋት አለብን - ከእርሱ ጋር በስጋዊ ዉጊያ አንገጥምም በማለት ፡፡

ሁለተኛዉ ደረጃ በእኛ ዉስጥ ግምት፣ ክርክር እና ዉሸት ያረፈብን ስንሆን - ሰይጣን በአንድ ጊዜ ከአንድ ስፍራ በላይ መገኘት ስለማይችል ፊታቸዉን ባዞሩት እንደ ወደቁት አይነት መለዓክት በብዛት ሰይጣናዊ የቤት ስራዎች ይገጥሙናል ፡፡ ስለ ራሳቸዉ በመዋሸት ያጠቁናል ፤ በብዙ ጉዳዮች ጠላት በጣም በአስቸጋሪ ክስተት ዉስጥ ልጅ በምንሆን ጊዜ ስለሚገባን ነገር እንድንጠይቅ በማድረግ ወደ ኑሮአችን ይናገራል ፡፡ ዝቅ የማለት እና ያለመተማመን ስለሚሰማን በዚያ እይታ ህይወትን እንተረጉማለን ፡፡

ሰዎስተኛዉ ደረጃ ስለ እግዚአብሄር በልባችን ዉስጥ የሚገባዉ ዉሸት ነው ፤ እነዚህ ዉሸቶች በልባችን ዉስጥ የተሳሳተ መረዳትን እና የዉሸት ሰንሰለትን ለመፍጠር በሁለተኛ ደረጃ ላይ ባሉ ዉሸቶች ይሰራሉ ፡፡ ይህ የዉሸት ትብትብ እኛ መንፈስ ቅዱስ እዉነት ነው፣ ኢየሱስስ ይከዳናል በእዉነትስ እግዚአብሄር ያስብልናል ብለን እንድንጠይቅ ምክንያት ይሆናል ፤ ይህ ስለ ኑሮአችን እና ስለ እምነታችን ተስፋ ቢሶች እና ተስፋ የቆረጥን እንድንሆን ምክንያት ይሆናል ፡፡ እነዚህ ሁሉ በኑሮአችን ዉስጥ ጠላት ሊያሸንፈን ለመሞከር ሊጠቀምባቸዉ የሚችል ምሽጎችን ይፈጥሯሉ ፡፡ አማኞች ከመሆናችን በፊት ስለሆኑ ከክርስቶስ ጋር ወዳለን ግንኙነት እናመጣቸዋለን ፤ ልባችንን ለኢየሱስ በከፈትን ጊዜ እነዚያን ሁሉ ስፍራዎችም እንከፍታለን ፡፡

አራተኛዉ ደረጃ ትልቅ ምሽግ/ኃይለኛ ምሽግን ይይዛል ፤ ዝቅ እንዳልን ተሰምቶን በመዘለፋችን ስንበሳጭ ብስጭቱ የሚኖርበትን ስፍራ ፈጥረናል ፡፡ የተከለከለ ስፍራዉን ምክንያት ስሩን/መነሻዉን ካላገኘነው በክርስቶስ ነፃነትን ማግኘት አንችልም ፤ ኢየሱስ ነፃ መሆን ከመቻላችን በፊት የኃይለኛዉን ምሽግ ስር ይቆርጠዋል ፡፡

በእኛ ዉስጥ የእግዚአብሄር መዝገብ አለን ፡፡ እነዚህን ደረጃዎች ማሸነፍ ለመቻል በእነዚህ ደረጃዎች ዉስጥ እንዴት እንመላለስ ?

ከእግዚአብሄር ድምፅ ለይተን የጠላትን ድምፅ ማወቅ አለብን ፤ የጠላት ድምፅ ልክ እንደኛ ሲመስል የእግዚአብሄር ድምፅ ግን በዚህ ያላስቀመጥነዉ ሀሳብ ወይም ራዕይ ነው ፤ የእግዚአብሄር ድምፅ የራሱን ባህሪይ ነዉ የሚመስለዉ ፡፡ ጠላት ራሱን መልካም እንደሚናገር በማስመሰል ነገር ግን ቃሉ ፍሬ የለዉም ፡፡

የእግዚአብሄር ድምፅ ነፃ ያወጣናል ወይስ የጠላት ድምፅ በባርነት ዉስጥ ያስቀምጠናል ? ከእግዚአብሄር ተፈጥሮ ተቃራኒ የሆነ ድምፅ ስትሰሙ መንፈስ ቅዱስ እንደመራችሁ በተቃራኒ ፀልዩ ፡፡ በኢየሱስ በኩል ህይወት እና እዉነት ሲነገር የጠላት ድምፅ ከዚህ ርቆ ይሄዳል ፡፡

መደምደሚያ

ከምርኮ ነፃ ለማዉጣት እና ከእስራት ለመምጣት ስለመጣ ኢየሱስ እናመሰግንኃለን ፤ ነፃነትን ለመቀበል ለማረከ ከፍተኛ ገንዘብ ከፍላችኋል ፡፡ ይህ የሚያጠኑ እና የሚሰሙ በአዲስ እና በጥልቅ መንገድ እንዲያገኙት እፀልያለሁ ፤ እነዚህ በጠላት ድምፅ ላይ በመብለጥ የእርሱን ድምፅ ለማወቅ እን በግል መስማት ለመቻል እንዲቀመጡ እፀልያለሁ ፡፡ ነፃ ሊያወጣን ኢየሱስ ይመጣል ፤ አሜን ፡፡

  1. Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1989), p. 664.

  2. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Pubishers,1999), p. 1507.

  3. Wiersbe, p. 665.

ጥያቄዎች

  1. በ 2ቆሮ (10፡ 1-2) ጳዉሎስ በክርስቶስ ስላለ ድፍረት ተናገረ ፤ በዚህ አይነት ድፍረት እየተመላለሳችሁ እንደ ሆነ ታስባላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አታስቡም ?
  2. 2 ቆሮ (10፡ 5) ለሰዉ እንዴት ትገልፁታላችሁ ? “ ለክርስቶስም ለመታዘዝ አዕምሮን ሁሉ እንማርካለን “ ማለት ምን ማለት ነው ? ይህ ለማድረግ ቀላል ነዉ ወይስ ለእናንተ ፈታኝ ነው ?
  3. በ 2ቆሮ (10፡ 15-16) መሰረት በምን ምክንያት ጳዉሎስ የቆሮንቶሳዊያንን እምነት መጨመር ፈለገ ? የቆሮንቶሳዊያን እምነት ለጳዉሎስ ወደ አባቱ እንዲጓዝ/እንዴት እንዴት ይፈቅድለታል ?
  4. በ 2ቆሮንቶስ 10 በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 2 Corinthians 10:4–5

“Since the weapons of our warfare are not worldly, but are powerful through God for the demolition of strongholds. We demolish arguments and every high-minded thing that is raised up against the knowledge of God, taking every thought captive to obey Christ.”

እንደ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ልክ እንደ ቆሮንቶስ ቤተክርስቲያን በመንፈሳዊ ውጊያ ውስጥ እንደሆናችሁ መረዳት ይገባችኋል ፡፡ ከደምና ከስጋ ጋር አይደለም ነገር ግን ከአለቆች ፣ ከስልጣናት ፣ ከጨለማው ዓለም ገዦች እና ከመንፈሳዊ ሰራዊት ጋር እንጂ ፡፡ እግዚአብሔር የሚሻው በጎ ነው ይህም ጠላት እንድሸነፍ ነው ፡፡

ውጊያውን ለመዋጋት በእናንተ ላይ ስለተነሳው ጦር ማወቅ አለባችሁ ፡፡ ጌታ አዕምሯችሁን በየቀኑ ማደስ እንደሚያስፈልጋችሁ ይናገራል ምክንያቱም ጸንታችሁ ለመቆም ፣ ጠላትን ለመዋጋት እናም የጌታን ድምጽ ለመስማት እውነቱ ያስፈልጋችኋልና ነው ፡፡ የጌታ ድምጽ እውነትንና ህይወትን ይናገራል ፡፡ ቃሉን አብዝታችሁ ስታነቡ በውጊያ ውስጥ ያለውን ድምጹን በደንብ አድርጋችሁ ታውቃላችሁ ፡፡ ጠላት ውሸትን ነው ሚነግራችሁ ፡- በቂ አይደላችሁም ፤ ዋጋ የላችሁም ፤ አትፈለጉም ፤ አትከናወኑም ፡፡ “ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ አማኞች አሳብን ሁሉ ለክርስቶስ እንድማርኩ ያዛቸዋል ፡፡ ይህም ማለት እነዚህ ውሸቶች ሲሰሙ ፣ ሲጸኑና ሲታወጁ በሌላ በኩል የእግዚአብሔር ቃል እውነት ደግሞ እንድህ ይላል ፡- “ እናንተ ውብና ድንቅ ሆናችሁ ተፈጥራችኋል ፤ ጽድቅን ለብሳችኋል ፤ ውድ ናችሁ ፤ ኃይልን በሚሰጣችሁ በክርስቶስ ሁሉን ትችላላችሁ ፡፡ “ እውነት ነጻ እንደሚያወጣችሁ እመኑ እናም የጠላት ድምጽ ይሸሻል ፡፡ እናም በውጊያ ድልን ትቀዳጃላችሁ ፡፡ ዛሬ በውጊያችሁ መካከል እያንዳንዱን አሳብ መማረክንና ኢየሱስን እንድያውጅ ማድረግን ተለማመዱ ፡፡ ኢየሱስ ከእናንተ ጋር ነው ደግሞም እርሱ ነጻነት ነው !

“ የጦር ዕቃችን ስጋዊ አይደለምና ፣ ምሽግን ለመስበር ግን በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ ነው ፤ የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ የሚነሳውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን ሁሉ እንማርካለን ፡፡ “

  • 2ኛ ቆሮንቶስ 10፡4-5

ተጨማሪ ጥቅስ

ዮሐንስ 8:32 — “ እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው ፡፡ “

ዮሐንስ 10:10 — “ ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም ፤ እኔ ህይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ ፡፡ “

ኤፌሶን 6:12 — “ መጋደላችን ከደምና ከስጋ ጋር አይደለምና ፣ ከአለቆችና ከስልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር ከሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳዊያን ሰራዊት ጋር ነው እንጂ ፡፡