Paul's Letters 2 Corinthians

Motivations For Giving

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Treasure 2 Corinthians 9 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 527 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ለዚህ የመፅሀፍ ቅዱስ መፅሀፍ አንድ ቃላችን በ 2ቆሮ (4፡ 7) መሰረት መዝገብ ነው ፤ ይህ መዝገብ በዉስጣችን ያለዉ ክርስቶስ ነው ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በኩል እግዚአብሄር በእኛ በኩል መናገር እና በእኛ ዉስጥ መንቀሳቀስ ይፈልጋል ፡፡ በ 2ቆሮንቶስ (8-9) እግዚአብሄር እምነት፣ የመናገር፣ የእዉቀት፣ የመለየት እና የመስጠት ስጦታ ሰጥቶናል ይላል ፡፡ ጳዉሎስ ቆሮንቶሳዊያን በኢየሩሳሌም ላሉት ክርስቲያኖች ቃላቸዉን በመፈፀም የታመኑ እንደሆኑ እርግጠኛ መሆን ፈለገ ፤ ለአይሁድ አማኞች መስጠት አስፈላጊ ነበር ምክንያቱም ይህን ሁሉንም ነገር ስለጀመሩ ፡፡ ድነት መጀመሪያ በአይሁዶች በኩል መጣ በእነርሱም ዉስጥ ለአሕዛብ መጣ ፡፡

ዋረን ዋይርስቤ በ 2ቆሮንቶስ “ እንደ ፀጋ ስጦታ “ የተጠቀሰዉን መስጠት ይገልፃል ፤ ቀጥሎም ዋይርስቤ ከመስጠት ጋር ከሚገናኙ አምስት መነሳሳቶች/መበረታታቶች በኩል ተጓዘ ፡፡ ጳዉሎስ የመስጠትን ጥቅም ለራሳቸዉ እና ስጦታቸዉን ለሚቀበሉት ለሁለቱም ያለዉን ጥቅም እንዲረዱ ፈለገ ፡፡

ትምህርት

2-ቆሮንቶስ (9፡ 1-5)፡ እንደ ዋይርስቤ አገላለፅ “ መስጠታችሁ ሌሎችን ያነሳሳል “ ይላል ፡፡ በምንሰጥ ጊዜ ሌሎች ደግሞ ይሰጣሉ ፡፡ በሚያስደንቅ እንቅስቃሴ ጳዉሎስ ከዚህ በኋላ ስለ መስጠት አላወራም በማለት ያን ወደ ማድረግ ቀጠለ ፡፡ ጳዉሎስ በምላሹ ለመስጠት ሜቄዶንያንም እንዲነሳሱ ስለ እነርሱ ከሜቄዶንያን ጋር ተከራከሩ ፤ ቀጥሎም ጳዉሎስ “ ወንድሞችን “ (ቁጥር 3) ስጦታቸዉን ለመሰብሰብ እና ለመስጠት ያልተዘጋጁትን ደግሞ በመፀለይ እንዲይዙ እየላካቸዉ እንደ ነበር ተናገረ (4) ፡፡ ጳዉሎስ ተስፋ ገብተዉ የነበሩትን የበረከት ስጦታቸዉን እንዲያዘጋጁ አበረታታቸው (ቁጥር 5) ፡፡

2-ቆሮንቶስ (9፡ 6-11)፡ እነዚህ ጥቅሶች እንደ ዋይርስቤ አገላለፅ “ መስጠታችሁ መባረካችሁን ያሳያል “ ፡፡ ጳዉሎስ ኃሳቡን ለመስራት/ለመናገር የእርሻ ቃል ተጠቀመ ፤ አንድ ገበሬ ብዙ ዘርን በተከለ/በዘራ ጊዜ ትልቅ ሰብልን ያገኛል ፤ ብዙ ዘርን ካልዘራ ግን ብዙ ሰብልን አያገኝም ፡፡ ዋይርስቤ “ እንደ ዘራነዉ በቁጥር የምንሰበስብበት የመጀመር መርህ እንዳለ “ ተንግሯል፤ በሉቃ (6፡ 38) ኢየሱስ የመከርን/የምርትን ህግ ገልፆታል፡ “ ስጡ ይሰጣችሁማል ፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ተመልሶ ይሰፈርላችኋል …..” ፤ ሰለሞንም በምሳ (11፡ 24-25) ተመሳሳይ ንግግርን አድርጓል ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ መስጠት ልክ እንደተዘራ ዘር ሲሆን ፤ የምርቱ መጠን በራሱ በዘሪ የሚወሰን ነው “ አለ ፡፡ ምሳሌ (19፡ 17) እግዚአብሄር ለድሆች ቸርነትን የሚያደርጉትን ይሸልማቸዋል ይላል ፤ በምትሰጡ ጊዜ እግዚአብሄር ይባርካችኋል ፡፡

በተጨማሪም ዋይርስቤ “ የፍላጎት መርህ “ እንዳለ ተናግሯል ፤ እግዚአብሄር በመንፈስ ቅዱስ በተነሳሱ ጊዜ በእዉነት እና በደስታ የሚሰጡትን በልግስና የሚሰጡትን ይወደል (ቁጥር 7) ፡፡ በመቀጠልም ዋይርስቤ ሰዎስተኛዉን “ የአንገብጋቢ ጉዳይ መርህ “ የሚለዉን መርህ ገልፆአል ፡፡ ከጌታ በምንሰማ ጊዜ ወዲያዉኑ መስጠት ያስፈልጋችኋል ፤ ለማሰላሰል ወይም ላለማትኮር ጊዜን አትዉሰዱ ፤ እግዚአብሄር እንዳዘዛችሁ ስጡ ፡፡ በቁጥር 9 ጳዉሎስ በንግግሩ መዝ (112፡ 9) ጠቅሷል ፤ በመሰረቱ የመልካም ሰው የለጋስነት ድርጊት ለዘላለም የሚቆይ እና ለሚቀበሉአቸዉም ዘላለማዊ በረከትን ያመጣል ፤ ምክንያቱም እግዚአብሄር “ ለዘሪ ዘርን እና ለምግብነት እንጀራን “ ሰጥቶ ስለ ነበር (ቁጥር 10)፣ እንዲሁም ምግብን/የሚያስፈልግን ነገር የመስጠት እና የወደፊት እድገትን ማምጣት ችሎታም አለው፡፡

በአሜሪካ የብልፅግና ወንጌል/ስነ መለኮት ከሰጣችሁ በሁሉም ነገር ባለፀጋ ትሆናላችሁ ለማለት ቁጥር (10-11) ይጠቀማሉ ፡፡ ማህበረሰባችን ስለ መስጠት ግራ የተጋባ ከሆነ የወንጌል ህብረት ስለ ብልፅግና ወንጌል አምስት ስህተቶችን ይገልፃል ፡፡

  1. የአብራሐም ኪዳን የቁስ አካል እንደሆነ ማሰብ ነው ፤ በዘፍ (12፡ 3) እግዚአብሄር አብርኃምን የሚባርኩትን እንደሚባርካቸዉ ቃል ገብቷል ፤ ይህ ማለት ሌሎች በእስራኤል ላይ ፊታቸዉን ያዞሩ ሲረገሙ እስራኤልን የሚባርኩ የእግዚአብሄርን በረከት ይቀበላሉ ፡፡ የብልፅግና ወንጌል ሁሉንም ገንዘቤን ወደ እስራኤል ሳፈስ ሁሉንም አይነት ገንዘብ መልሰን እናገኛለን ይላል ፤ ያ የተሳሳተ ፍላጎት ነው ፡፡ ነገር ግን በቀላሉ እስራኤልን መባረክ አለብን ምክንያቱም መፅሀፍ እንድናደርግ ስለሚያዘን ፡፡
  2. የኢየሱስ ማስተሰርየት “ የቁሳዊ ድህነትን “ እስከማስወገድ እንደተዘረጋ ማሰብ ነው ፤ የብልፅግና ወንጌል የኢየሱስ ድርጊት በመስቀል ላይ ሙሉዉን የድህነት አስተሳሰብ (በ 2ቆሮ 8፡ 9 መሰረት) እንዳጠፋ ይናገራል ፤ በኢየሱስ ሞትና መቀበር ከዚህ በኋላ ድሆች እንደማትሆኑ ይናገራሉ ፡፡
  3. ክርስቲያኖች ከእግዚአብሄር ቁሳዊ የሖነ ካሳን ለማግኘት ይሰጣሉ ፤ በማር (10፡ 30) መሰረት የብልፅግና ወንጌል መስጠት 100 እጥፍ እንደሚያመጣ ይናገራል ፡፡
  4. እምነት ወደ ብልፅግና የሚመራ በራሱ የሚያመነጭ መንፈሳዊ ኃይል ነው ፤ የብልፅግና ወንጌል እምነት ካላችሁ ይህ ሊሆን ስለሚችል ትበለፅጋላችሁ ፡፡ በዚያ ፋንታ ለሌሎች እንድንሰጥ የሰጠንን አማኞች በእግዚአብሄር ፀጋ ይሰጣሉ ፡፡
  5. ፀሎት ብልፅግናን ለማምጣት እግዚአብሄርን ለማስገደድ መሳሪያ ነው ፤ የብልፅግና ወንጌል ስለዚህ ነገር ስትፀልዩ ሁሉም ነገር ሊሆን ይችላል በማለት ይናገራል ፡፡

ይህን በማጋራት የካይልስ ልብ ይህ ነው፡ በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ በበግ ለምድ የተደበቁትን ተኩላዎች እንድናዉቃቸዉ ይፈልጋል ፤ ይህ በአሜሪካ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን በመላዉ አለም ቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ነው ፤ መፅሀፍን በመጠምዘዝ ፍላጎታችንን በማሟላት ላይ ሳይሆን ትኩረቱ በቁሳዊ ነገር ላይ ነው ፡፡

2-ቆሮንቶስ (9፡ 12)፡ ዋይርስቤ “ ስጦታችሁ/መስጠታችሁ የሚያስፈልግ ነገርን እንደሚያሟላ “ አመልክቷል ፡፡ በዚህ ጥቅስ ላይ ጳዉሎስ እንደተናገረው በምንሰጥ ጊዜ ሰዎችን እንረዳለን ፡፡

2-ቆሮንቶስ (9፡ 13)፡ በተጨማሪም ዋይርስቤ “ መስጠታችሁ እግዚአብሄርን ያከብራል “ አለ ፡፡ በልግስና መስጠት ለሚለዉ ለእግዚአብሄር ትዕዛዝ መታዘዛችሁ ለእግዚአብሄር ክብር ያመጣል ፡፡

2-ቆሮንቶስ (9፡ 14-15)፡ በመጨረሻም ዋይርስቤ “ መስጠታችሁ የእግዚአብሄርን ሰዎች እንደሚያደርግ “ ተመልክቷል ፡፡ ከሌላ ሰዉ ገንዘብ በምትቀበሉ ጊዜ ስለ እነርሱ መፀለይ ትጀምራላችሁ ምክንያቱም ልባችሁ ለእነርሱ ስለሆነ (ምክንያቱም ለእናንተ የሖነ ነገር ስለሰጧችሁ) ፡፡ በዚያ ስጦታ ምክንያት ሌሎች ሰዎችም እግዚአብሄርን መቅመስ ይጀምራሉ ፡፡

መደምደሚያ

ከክርስቶስ የተነሳ በዚያ መዝገብ፣ በዚያ ስጦታ ክርስቶስን የማንፀባረቅ እድል አለን ፡፡

  1. Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1989), p. 527.

  2. Wiersbe, p. 527.

  3. Wiersbe, p. 527.

  4. Wiersbe, p. 527.

  5. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1505.

  6. Wiersbe, p. 527.

  7. Wiersbe, p. 527.

  8. David D. Jones, “5 Errors of the Prosperity Gospel”; available on-line at https://www.thegospelcoalition.org/article/5-errors-of-the-prosperity-gospel/.

  9. Wiersbe, p. 529.

  10. Wiersbe, p. 529.

  11. Wiersbe, p. 529.

ጥያቄዎች

  1. ጳዉሎስ ቆሮንቶሳዊያንን እና ሜቄዶንያዋንን አንዱ በሌላዉ ላይ በልግስና ለመስጠት እንዲቀናኑ እንዴት ተጠቀመባቸው ? (2ቆሮ 8፡ 1-2, 9፡ 2-4፣ ዕብ 10፡ 24)
  2. በ 2ቆሮ (9፡ 3-5) የጳዉሎስ ትኩረት ምን ይመስላል?ስለ አንድ ሰዉ ወይም ስለ አንድ ቡድን ስትመኩ ዝቅ አድርገዋችሁ ያውቃሉ ?
  3. በ 2ቆሮ (9፡ 8-10) ጳዉሎስ ምን መርህን እያስተማረ ነበር ? በልግስና በመሰጠታችሁ ይህን መርህ እዉነተኛነቱ ሲረጋገጥ አይታችኋል ?
  4. በ 2ቆሮ (9፡ 15) ከእግዚአብሄር ለተሰጠዉ “ ለየትኛዉ ስጦታ “ ጳዉሎስ አመሰገነ ? (2ቆሮ 9፡ 8, 14)
  5. በ 2ቆሮንቶስ 9 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 2 Corinthians 9:7–8

“Each person should do as he has decided in his heart—not reluctantly or out of necessity, for God loves a cheerful giver. And God is able to make every grace overflow to you, so that in every way, always having everything you need, you may excel in every good work.”

መንፈስ ቅዱስ እንድትሰጡ በሚያሳስባችሁ ጊዜ ድምጹን አክብሩ ፡፡ ጌታ በጥቂት የሚዘራ በጥቂት ፤ በበረከትም የሚዘራ በበረከት እንደሚያጭድ ተናግሯል :: ጌታ የሆነ ያክል እንድትሰጡ ልባችሁን ካሳሰበው ባሳሰባችሁ መሰረት ስጡ ፡፡ ጌታ ልባችሁን ለሆነ ቤተሰብ ምግብ እንድታቀርቡ ፣ በጓዳ ውስጥ ምግብ በመስራት ጊዜን እንዲታሳልፉ ፣ ወይም የደቀ መዛሙርት ቡድንን እንዲትመሩ አሳስቧችሁ ነገር ግን አንተ ይህንን ነገር ለማድረግ ጉልበቱ ፣ ጥበቡ ፣ ጊዜው እናም ተሰጦው እንደሌላችሁ ቢሰማችሁ ፣ ማመዛዘኑን ትታችሁ በመታዘዝ አድርገት ፡፡ አስታውሱ ጌታ እያንዳንዱ ጸጋ በአንተ ላይ እንዲፈስ ማድረግ እንደሚችል ስለዚህም ደግሞ አናንተ በሁሉም መንገድ ሁልጊዜም የሚያስፈልጋችሁ ነገር ሁሉ ይኖራችኋል እናም በበጎ ስራ ሁሉ ትከናወናላችሁ ፡፡

የመስጠት አገልግሎት በእምነት እርምጃ መውሰድን ይፈልጋል ፡፡ የመስጠት አገልግሎት መስዋዕትነትን ይጠይቃል ፡፡ የመስጠት አገልግሎት መታዘዝን ይጠይቃል ፡፡ የመስጠት አገልግሎት ከመንፈስ ቅዱስ የተለየ ጸጋንና ኃይልን ይጠይቃል ፡፡ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር በመታዘዝ ስትራመዱ እርሱ መንገድን እንደሚያዘጋጅ ተናግሯል ፡፡ ስለዚህ በታዛዥነት በመስጠት መመላለስ ጀምሩ ፡፡ ረሳችሁንና የእናንተ የሆነውን ነገር አብዝታችሁ በሰጣችሁ ቁጥር ከምታስቡት በላይ ጌታ በህይወታችሁ ውስጥ ለመስራት ብዙ ቦታን ያገኛል ! እግዚአብሔርን ፈጽሞ መተው አትችሉም ፡፡ በህይወታችሁ ውስጥ ፍቅሩ ፣ ጸጋውና ኃይሉ መፍሰሱን ይቀጥላል ፡፡

“ እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ ፣ በኀዘን ወይም በግድ አይደለም ፡፡ እግዚአብሔር ሁልጊዜ በነገር ሁሉ ብቃትን ሁሉ አግኝታችሁ ለበጎ ስራ ሁሉ ትበዙ ዘንድ ፣ ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል ፡፡ “ - 2ኛ ቆሮንቶስ 9፡7-8

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ሮሜ 15:13 — “ የተስፋ አምላክም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በተስፋ እንድትበዙ በማመናችሁ ደስታንና ሰላምን ሁሉ ይሙላባችሁ ፡፡ “
  • ፊልጽስዩስ 4:13 — “ ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ ፡፡ “
  • 1ኛ ጢሞቴዎስ 1:14 — “ የጌታችንም ጸጋ በክርስቶስ ኢየሱስ ካሉ ከእምነትና ከፍቅር ጋር አብልጦ በዛ ፡፡ “