Paul's Letters 2 Corinthians

The Motivation Of Giving

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Treasure 2 Corinthians 8 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 526 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

2 ቆሮንቶስ (8-9) በጳዉሎስ አጠቃላይ መልዕክት ዉስጥ የሆነ የሚቀጥሉ ጭብጦች ናቸው ፡፡ ለ 2ቆሮንቶስ አንድ ቃላችን መዝገብ ሲሆን፡ “ ነገር ግን የኃይሉ ታላቅነት ከእግዚአብሄር እንጂ ከእኛ እንዳይሆን ይህ መዝገብ በሸክላ ዕቃ ዉስጥ አለን “ (2ቆሮ 4፡ 7) ፡፡ የአማኞች መዝገብ ኢየሱስ በእኛ ዉስጥ ይኖራል ፡፡ በምዕራፍ (8-9) ጳዉሎስ ስለ እዉነተኛዉ መዝገብ አዉርቷል ፡፡ ጳዉሎስ እየተራቡ ለነበሩ በኢየሩሳሌም ለነበሩ ድሀ አማኞች መልሶ ለመዉሰድ ከቤተ ክርስቲያን የገንሰብ ሶጦታዎችን ወሰደ ፤ ጳዉሎስ ቤተክርስቲያን በያዘችዉ ከመዝገቡ ከኢየሱስ የተነሳ ይህን ምድራዊ መዝገብ ሰበሰበ ፡፡ “ ወደዋልና የእነርሱም ባለዕዳዎች ናቸው ፤ አሕዛብ በእነርሱ መንፈሳዊ ነገርን ተካፋዮች ከሆኑ በስጋዊ ነገር ደግሞ ያገለግሉአቸው ዘንድ ይገባቸዋልና “ (ሮሜ 15፡ 27) ፡፡ ይህ በጳዉሎስ አገልግሎት ሂደቱን ቀጠለው፡ “ እንዲሁ እየደከማችሁ ድዉዮችን ልትረዱና እርሱ ራሱ ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነዉ እንዳለ የጌታን የኢየሱስን ቃል ልታስቡ ይገባችሁ ዘንድ በሁሉ አሳየኋችሁ “ (ሐዋ 20፡ 35) ፡፡ ዋይርስቤ ጳዉሎስ ይህን መሰብሰብ ለኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን ለማድረግ ለምን እንደ ፈለገ አራት ምክንያቶችን አጉልቶ አሳይቷል፡

  1. የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ለማጠንከር ፡፡
  2. አሕዛቦች የአይሁዶች ባለ እዳዎች ስለ ነበሩ ፡፡
  3. ጳዉሎስ ለአይሁዶች ጠላት እንዳልነበር ለማሳየት ስለፈለገ ፡፡
  4. ጳዉሎስ ድሆችን ለመርዳት ቃል ስለገባ ፤ “ ድሆችን እናስብ ዘንድ ብቻ ለመኑን ይህንም ደግሞ ላደርግ ተጋሁ “ (ገላ 2፡ 10) ፡፡

ጳዉሎስ የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን እስከ መሰጠታቸዉ መጨረሻ ድረስ በዚህ እየኖሩበት ስላልነበር ቆሮንቶሳዊያንን ስለዚህ ስጦታ ሊያስታውሳቸዉ ነበር ፤ “ በዚህም ነገር ምክር እሰጣለሁ ፤ ከአምና ጀምራችሁ ለማድረግ ብቻ ያይደል ነገር ግን ለማሰብ ደግሞ አስቀድማችሁ የጀመራችሁት ይህ ይጠቅማችኋልና ፤ አሁንም ለማሰብ በጎ ፈቃድ እንደ ነበረ እንዲሁ እንዳላችሁ መጠን መፈጸም ደግሞ ይሆን ዘንድ ማድረጉን ደግሞ ፈጽሙ “ (2ቆሮ 8፡ 10-11) ፡፡

ትምህርት

2-ቆሮንቶስ (8፡ 1-2)፡ ዋይርስቤ መስጠት በመንፈስ የተነሳሳ በሆነ ጊዜ በማንኛዉም ችግራችን ዉስጥ እንሰጣለን፡፡ ጳዉሎስ በሜቄዶንያ ያሉት ቤተ ክርስቲያኖች ከችግራቸዉ እንደ ሰጡ ጠቅሷቸዋል ፤ ጳዉሎስ በተለይ እነዚህን ቤተ ክርስቲያኖች ዋይርስቤ “ እንደ ጥልቅ አለት ሚስኪንነት “ በገለፀዉ “ በጥልቅ ድህነታቸዉ “ በማትረፍረፍ እንደሰጡ ጠቅሷቸዋል ፤ በመቆጨት ሳይሆን “ በተትረፈረፈ ደስታ “ (ቁጥር 2) ሰጥተዉ ነበር ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ የሜቄዶኒያ ቤተ ክርስቲያን መስጠት “ ከሚችሉት በላይ ነበር “ ፡፡

2-ቆሮንቶስ (8፡ 3-4)፡ የሜቄዶኒያ ቤተ ክርስቲያን በእዉነት ከልባቸዉ ሰጥተዋል ፡፡ በዉስጣቸዉ ካለዉ መዝገብ የተነሳ ለአይሁድ አማኞች ለመስጠት እድል እንዲኖራቸዉ “ ለመኑ “ (ቁጥር 4) ፡፡

2-ቆሮንቶስ (8፡ 5-9)፡ በዉስጣችን ካለዉ መዝገብ የተነሳ በሜቄዶኒያን ያሉ ቤተ ክርስትያን ኢየሱስ እንደሰጣቸዉ ሰጡ ፤ ጳዉሎስ የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን የያዙዓቸዉን የመንፈሳዊ ስጦታ እና ፀጋን መትረፍረፍን ተመለከተ፡ የእምነት፣ የቃል፣ የእዉቀት፣ የትጋት እና የፍቅር (ቁጥር 7) ፡፡ አሁንም ፍፁም ለሆነዉ ፍቅራቸዉ እንደ መፈተኛ ጳዉሎስ የኢየሩሳሌምን አማኞች እንዲረዱ በትጋታቸዉ ላይ እንዲከተሉ አበረታታቸው ፡፡ ለጋስነታቸው ለክርስቶስ ባላቸዉ ፍቅር የተነሳ የተትረፈረፈ ሆነ ፤ ጳዉሎስ ቆሮንቶሳዊያንን “ ሀብታም ሲሆን እናንተ በእርሱ ድህነት ባለ ጠጎች ትሆኑ ዘንድ ስለ እናንተ ድሀ ሆነ “ (ቁጥር 9) ፡፡

ጳዉሎስ ጠቅሶአቸዉ የነበሩ ባለጠጎች በምድራዊ ሁኔታ ባለጎች አልነበሩም ፤ ኢየሱስ ስላልሞተ ቦነስ እና የሀይቅ ቤት

ማግኘት እንችላለን ፡፡ ይልቁንም በኢየሱስ ባለን በእምነታችን የምንቀበለው ባለጠግነት ድነት የሚባሉ መንፈሳዊ ባለጠግነቶች ናቸው ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ፡ “ መዳን/መፅደቅ፣ ቁጥቋጦ/እንደ ገና ማደግን፣ ዘላለማዊ ህይወት፣ ክብር፣ ኢየሱስ ካጢዓት ባርነት በመግዛት የእግዚአብሄር ልጆች ያደርገናል “ በማለት ይዘረዝራል ፤ እንደ ባለፀጋ አማኞች ከክርስቶስ ይቀበላሉ ፡፡

2-ቆሮንቶስ (8፡ 10-12)፡ ዋይርስቤ በፍቃደኝነት በምንሰጥ ጊዜ መስጠት በመንፈስ ቅዱስ የተነሳሳ እንደሆነ እንደምናዉቅ ፅፏል ፡፡ የቆሮንቶሳዊያን መስጠት አንድ ኢንቨስትመንት ነበር ፤ ይህ የአካላዊ ስጦታ የኢየሩሳሌም አማኞችን እንደሚረዳቸው በተመሳሳይ መንገድ በእግዚአብሄር ፊት ይረዳቸዋል ፡፡

2-ቆሮንቶስ (8፡ 13-24)፡ ጸጋ መስጠት በእምነት የተፈፀመ እንዲሆን ያነሳሳል ፡፡ ጳዉሎስ ቆሮንቶሳዊያንን በቆሮንቶሳዊያን በድህነት ጊዜ ሌሎች ከሙላታቸዉ እንደሚዘሩባቸዉ በሚል አስተሳሰብ በሌሎች ላይ ከሙላታቸዉ እንዲሰጡ አበረታታቸው ፡፡ ቁጥር 15 እስራኤላዊያን በምድረበዳ መናን በሰበሰቡ ጊዜ የገጠማቸዉ ማጣቀሻ ነው፡ “ በጎሞርም በሰፈሩት ጊዜ እጅግ ለለቀመ አልተረፈዉም ጥቂትም ለለቀመ አልጎደለበትም ፤ ሁሉ እያንዳንዱ የሚበላዉን ያህል ለቀመ …… ነገር ግን ሙሴን አልሰሙትም ፤ አንዳንድ ሰዎችም ከእርሱ ለነገ አስቀሩ እርሱም ተላ ሸተተም ፤ ሙሴም ተቆጣቸው “ (16፡ 18, 20) ፡፡ የእግዚአብሄር ትዕዛዝ ለአንድ ቀን የሚበቃቸዉን ብቻ እንዲሰበስቡ ቢሆንም እስራኤላዊያን መናን አከማቹ ፤ ለቀጣዩ ቀን ለራሳቸዉ የሚሰጡበትን የተትረፈረፈ አስተሳሰብ ቀጠሉ ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ስለ ቀጣዩ ለመያዝ ካለማሰብ ለመንግስቱ ለመስጠት እናከማቻለን ፤ ሁልጊዜ ወደ እግዚአብሄር መንግስት መስጠትን እንደ ኢንቨስትመን አናየዉም ፡፡ ሁልጊዜ ለመያዝ በመረጥናቸዉ አካላዊ ብልፅግና ላይ የተሰጠን ከጌታ የምንቀበለዉን በረከት ዋጋ አንሰጥም ፡፡

ቲቶ ስሙ ካልተጠቀስ አንድ ወንድም ጋር ድጋፉን ለመሰብሰብ ሄደ ፤ ይህ ወንድም ጌታን ለማክበር ፍላጎት ነበረው፡፡ ይህ የህዝብ ቡድን ለሚቀበሉት ገንዘብ በቤተ ክርስቲያን ፊት እንደ ተጠያቂነት ተግባር ተጠያቂዎች ነበሩ ፤ እነርሱም በፍላጎታቸው የኢየሩሳሌምን ቤተ ክርስቲያን ለመጥቀም ሁሉም ቤተ ክርስቲያኖች በዚህ ድጋፍ ላይ እንደተደገፉ ለማየት “ በተባበረ መንፈስ “ ባህሪ ነበሩ ፡፡

መደምደሚያ

መዝገቡ ክርስቶስ በቆሮንቶሳዊያን ዉስጥ የነበረው በኢየሩሳሌም ለነበረች ቤተ ክርስቲያን የሚያስፈልጋትን እንዲያዋጡ የሚያነሳሳቸዉ ነበር ፡፡ ጳዉሎስ የመስጠትን በረከት በማሳሰብ ስጦታቸዉን ለመቀበል የመጡትን በቲቶና በወንድሙ ድርጊት እንዲሳተፉ አበረታታቸው ፡፡

  1. Warren Wiersbe, The Wiersbe Bible Exposition Commentary: New Testament (Nashville: David C Cook, 2007), p. 523.

  2. Wiersbe, p. 523.

  3. Wiersbe, p. 523.

  4. Earl Radmacher, et. al., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 1999), p. 1505

  5. Wiersbe, p. 524.

  6. Wiersbe, p. 524.

  7. Nelson’s Commentary, p. 1505.

  8. Wiersbe, p. 524.

  9. Wiersbe, p. 525.

  10. Wiersbe, p. 526.

ጥያቄዎች

  1. ጳዉሎስ ለቆሮንቶሳዊያን በኢየሩሳሌም ስለሚያስፈልጋቸው ስለ ሜቆዶንያ ቤተ ክርስቲያን ስጦታዎች ምን ነገራቸው ? (2ቆሮ 8፡ 1-8)
  2. ከምትችሉት በላይ ወይም የምትችሉትን ስጡ ማለት ምን ማለት ነው (2ቆሮ 8፡ 3) ? ልክ እንደዚህ ሰጥታችሁ ታዉቃላችሁ ? አይደለም ካላችሁ ምን ይይዛችኋል ?
  3. ጳዉሎስ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እኛ ድኃ ስለሆነ በእርሱ ድህነት ባለጠጎች ሆንን ሲል ምን ማለቱ ነበር? (2ቆሮ 8፡ 9)
  4. በ 2ቆሮ (8፡ 13-15) ጳዉሎስ ምን ዉጤት እንደተመኘ ምን ታስባላችሁ ? (ዘጸ 16፡ 18)
  5. በ 2ቆሮንቶስ 8 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 2 Corinthians 8:2

“During a severe testing by affliction, their abundance of joy and their deep poverty overflowed into the wealth of their generosity.”

ጳውሎስ በችግራቸውና በድህነታቸው እንኳ በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስለነበረው የልግስና መንፈስ መሰከረ ፡፡ በተመሳሳይ መንገድ እግዚአብሔር ልጁን ኢየሱስን መስዋዕት እንዲሆን ለዓለም ሰጠ ፡፡ እናንተም ከሞት ትድኑ ዘንድና የዘላለምን ህይወት እንድታገኙ ኢየሱስም እንድሁ ራሱን በመተው ያለ ስስት ራሱን ፍጹም ስጦታ በማድረግ አቀረበ ፡፡

ክርስቶስን እንደሚመስል ሰው እናንተም ልክ እንደ ክርስቶስ ያለ ስስት በልግስና እንዲትስጡ ተጠርታችኋል ፡፡ እንደ አማኝ ጌታ የህይወት ዘመናችሁን ሁሉ ለእርሱ እንድታቀርቡ ጥሪ ያቀርብላችኋል ፡፡ ገንዘብ በሌላችሁ ጊዜ እንኳ ሳይቀር ስጡ ፡፡ በስራ በምትወጠሩበት ጊዜም ጭምር ጊዜያችሁን ስጡ ፡፡ ሀልጊዜም ስለ ወንጌል ህይወታችሁን ስጡ ፡፡ በልግስና መስጠት በዙሪያችሁ ያሉ የሚያደርጉት ነገር ትርጉም በማይሰጣችሁ ጊዜ እንኳ ሳይቀር መንፈስ ወደ ሚመራችሁ በእምነት መታዘዝንም ጭምር ያካትታል ፡፡ ጌታ ዓለምን እንድትመስሉ ሳይሆን እርሱን እንድትከተሉ ይጠራችኋል ፡፡ ዛሬ እንዴት ይሆን ጌታ በመታዘዝ እንድትሰጡ የሚጠራችሁ ? በመታዘዝ ስትሰጡ በእግዚአብሔር ታማኝነት ላይ መደገፍን እንዳትዘነጉ !

“ በብዙ መከራ ተፈትነው ሳሉ የደስታቸው ብዛትና የድህነታቸው ጥልቅነት የልግስናቸውን ባለ ጠግነት አብዝቶአል ፡፡ “ - 2ኛ ቆሮንቶስ 8፡2

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ኤፌሶን 5:1–2 — “ እንግድህ እንደ ተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትከተሉ ሁኑ ፣ ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መስዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ በፍቅር ተመላለሱ ፡፡ “
  • ያዕቆብ 1:17 — “ በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው ፣ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ ፡፡ “
  • 1ኛ ዮሐንስ 3:16 — “ እርሱ ስለ እና ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶአልና በዚህ ፍቅርን አውቀናል ፤ እኛም ስለ ወንድሞቻችን ነፍሳችንን አሳልፈን እንድንሰጥ ይገባናል ፡፡ “