Paul's Letters 2 Corinthians

The Superior Convenant

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Treasure 2 Corinthians 7 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 525 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የ 2ቆሮንቶስን ስለ ጳዉሎስ ኃይለኛ ስለሆነዉ ግላዊ አገልግሎት ገለፃ የሆነዉን የዚህ ክፍል እየጨረስን ነው ፡፡ ዋይርስቤ ጳዉሎስ ስለ አንባቢዎቹ ስለ ፃፋቸዉ ነገሮች “በዚህ ሳምንት “ አስቀምጧል ፡፡

  • መከራ እያለ ጳዉሎስ ድል አድራጊ አገልግሎት ነበረው (ምዕራፍ 1-2-ሰኞ/ማክሰኞ) ፡፡
  • ጳዉሎስ የከበረ አገልግሎት ነበረው (ምዕራፍ 3 - ዕሮቡ) ፡፡
  • ጳዉሎስ በክስ ስር ሆኖም እንኳን ለማቆም በፍፁም አላሰበም (ምዕራፍ 4 - ሀሙስ) ፡፡
  • የጳዉሎስ አገልግሎት እግዚአብሄርን በማመን ላይ የተመሰረተ ነበር (ምዕራፍ 5 - አርብ) ፡፡

ጳዉሎስ የቆሮንቶስ አማኞች ልብን በመሞገት (ምዕራፍ 6) ለዚህ ክፍል ማጠቃለያዉን ሰጠ (ምዕራፍ 7 -ቅዳሜ) ፡፡

ትምህርት

2-ቆሮንቶስ (7፡ 1)፡ ይህ ለ2ቆሮ (6፡ 14-18) ግሉል የሆነ የጳዉሎስ መደምደሚያ ነበር ፡፡ ጳዉሎስ ከአለማዊ ተፅዕኖ መለየት እንዲሚያስፈልገን ፃፈ ይህ ከሆነ ከእግዚአብሄር ጋር የተቀራረበ ህይወት መኖር እንችላለን ፡፡ በመሰረቱ ይህን /አለማዊነትን ስናፀዳዉ እንደ ገና ህብረት አለን ፡፡ በቆሮንቶስ ባለች ቤተ ክርስቲያን ስላለዉ ችግር በማሰብ/በመናገር ብዙዉን ጊዜዉን በማሳለፍ ጳዉሎስ ለታመነ አገልግሎት ለማነሳሳት በቆሮንቶሳዊያን ሙሉ እምነት እና ደስታ እንዳለዉ መግለፅ ጀመረ ፡፡ ዋይርስቤ በዚህ ምዕራፍ ሰዎስት እጥፍ ማበረታታትን አጉልቶ ያሳያል፡፡

2-ቆሮንቶስ (7፡ 2-3)፡ ዋይርስቤ በቁጥር (2-4) ጳዉሎስ ቤተ ክርስቲያንን እንዳበረታታ ፅፏል ፡፡ ምናልባትም ይህ አብዛኛዉን ጊዜአችንን የምናሳልፍበት ስፍራ ነው ፡፡ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ስለ ጳዉሎስ ብዙ መጥፎ ነገሮችን አምነዋል እግዚአብሄር እንደማይጠቀምበት እና ሐዋሪያት ሊኖራቸዉ የሚገባዉ መልክ፣ ስልጣን እና ኃይል እንደሌለው ፡፡ ስለ ሰዎች ፍቅራችንን ማረጋገጥ ያልተቻለዉ ለምንድን ነው ?

ችግራቸዉ የመረጃ ችግር አልነበረም ለአለም ተከፍቶ የነበረ ነገር ግን ለጳዉልስ ያልተከፈተ የልባቸዉ ችግር ነበር ፡፡ “ ባልተመጣጠነ/ባልተመቸ አካሄድ መጠመድ “ በሚለዉ ፅሁፍ ጳዉሎስ ልባቸዉን ወደ አለም አቅርበዉ እንደ ነበር ነግሯቸዋል ፡፡ አሁን ልባቸዉን ለእርሱ የሚከፍቱበት ስዓት ነው ፡፡ ጳዉሎስ እንዲያምኑት ጠየቃቸው - እነርሱን ለማሳሳት በፍፁም አንዳች ነገር አድርጎ እንደ ነበር ፡፡ አስፈላጊ ከሆነ ጳዉሎስ ለእነርሱ ለመሞት ፍቃደኛ ነበር፣ በእርሱ ልብ ዉስጥ ነበሩ ፡፡

2-ቆሮንቶስ (7፡ 4-7)፡ ጳዉሎስ ስለ እነርሱ እየተመካ ነበር ፡፡ ይህ በተለይም በእኛ ጊዜ አሁን የሚተገበር ታላቅ የመልዕክት ስብስብ ነው ፡፡ በራሱ መፀኀፍ ዉስጥ የጳዉሎስ አስከፊ ቤተ ክርስቲያን፡ ምርጥ ሞደላችን ነው ? ፓስተር ቸርርች ዋርኖክ “ በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ለመከላከል የሆነ ሰዉ የሚመጣበት ጊዜ እንደሆነ አስባለሁ ፤ አዎ አሁን ሁሎም ሞተዋል ፤ ነገር ግን ለሚያያቸዉ ለሁሉም አለም በጳዉሎስ ሁለት መልዕክቶች ላይ ይኖራሉ ፤ በሚያከራክር ሁኔታ ቆሮንቶስ ለጳዉሎስ አስቸጋሪ ቤተ ክርስቲያን እንደ ነበረች ነገር ግን ለኛ ምርጥ ሞዴል እንደሆነች አስባለሁ “ በማለት ፅፏል ፡፡

ፍፁም አዲስ አማኞች ነበሩ ፤ ፎበን ከቆሮንቶስ የመጣች ነበረች (ሮሜ16፡ 1-2) ፡፡

ተሳትፈዋል ፡፡

ስህተት አድርገዋል ነገር ግን ያለጉጉት ነበር ፡፡

አዲሱ እምነታቸዉ ለቃላቸዉ አስፈላጊ ነበር ፤ ይህ ሁሉም ስፍራ ሀሰተኛ ፍቅር የነበረዉ ማህበረሰብ ነበር ፤ አንዴ እዉነተኛ ፍቅር ምን እንደ ነበር ሲረዱ በማህበረሰባቸዉ ዉስጥ ከሌሎች ጋር መነጋገር እና መግባባት ችለዉ ነበር ፡፡

እዉነተኛ ቤተ ክርስቲያን ነበረች ፡፡ በቤታችን ቆሻሻችንን ለመደበቅ ምን ያክል ጊዜ ጭንብልን ለብሰናል ? እዉነተኞች እና ትክክለኛ ለመሆን ተጠርተናል ፤ ያም እዉነተኛ ቤተ ክርስቲያን ስንሆን ነው ፡፡

2-ቆሮንቶስ (7፡ 5)፡ ዋይርስቤ በቁጥር (5-10) ቲቶ ጳዉሎስን እንዳበረታታዉ ፅፏል ፡፡ እነዚህ ፊልጲስዮስ፣ ተሶሎንቄ እና ቢራአ በሜቄዶንያ ያሉ ቤተ ክርስቲያኖች ናቸው ፡፡ በእግዚአብሄር የተሰጠዉን እረፍት እና ስራ የሚጎዳ ብጥብጥ ያጠቃኛል ፤ ይህ ጳዉሎስን አካላዊ፣ ስሜታዊ እና መንፈሳዉ ተፅዕኖ አድርጎበታል ፡፡

2-ቆሮንቶስ (7፡ 6-7)፡ ምን አይነት ታላቅ ብርታት ነው ! ይህ ለመናገር ወይም ለመጓዝ ለጳዉሎስ ቀላል አልነበረም፡፡ ከሌሎች ጋር በዙሪያችን በዚህ አለም ለመናገር የሚያቀልልን ነገር ለመዉሰድ እናዘነብላለን ፤ ጳዉሎስ ጳዉሎስ ቲቶ በቆሮንቶስ በማሳረፍ በሰጠዉ ሪፖርት ተበረታቷል ፡፡ ቆሮንቶሳዊያን የጳዉሎስን “ የሚያሳምም መልዕክት “ በማንበብ ከኃጢዓታቸዉ ንስኃ በመግባት ችግር የፈጠሩ አባላትን ቀጡ ፡፡ እዚህ ጋር ያለዉ በመዝሙር እና በምሳሌ በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ ያጠናነው ተጠያቂነት ሲሆን - ተፅዕኖም ሊኖረዉ ይችላል ፡፡

2-ቆሮንቶስ (7፡ 8)፡ ጳዉሎስ የጠቀሰዉ መልዕክት ምናልባትም በ 1 እና 2 ቆሮንቶስ መካከል የተፃፈ ነበር ፤ የክስተቶቹንም ቅደም ተከተል ለማስታወስ ይረዳል ፡፡ በቆሮንቶስ ባሉት ክርስቲያኖች መካከል ነገሮች በመጥፎ አየሄዱ ስለ ነበር ወደ መስመር መልሶ ለማስገባት በመሞከር ጳዉሎስ ነገሮች አስከፊ እንደሆኑ የሚመስል ፈጣን እና ያልታቀደ ጉብኝት አደረገ (2ቆሮ 2፡ 1) ፡፡ ከጉብኝቱ ዉድቀት በኋላ ጳዉሎስ ቆሮንቶስን እንደ ገና በአካል ላለመጎብኘት ወሰነ ነገር ግን በዚያ ፋንታ እንዲረዳቸዉ ከታላቅ የግሳፄ ደብዳቤ ጋር ቲቶን ላከው ፡፡ ጳዉሎስ ቆሮንቶሳዊያን መልዕክቱን እንዴት እንደሚቀበሉት ወደ እግዚአብሄር ይልሳቸዋል ወይስ ያበሳጫቸዋል በሚል ተጨንቆ ነበር ፡፡ በኤፌ (4፡ 14-16) ላይ ጳዉሎስ እየታገለ እንደ ነበር ታስባላችሁ ? እዉነትን በፍቅር ከመናገር በተጨማሪ ጳዉሎስ ማስተካከያ እና ማበረታቻ ሁለቱንም ሰጠ ፡፡

2-ቆሮንቶስ (7፡ 9-10)፡ መልዕክቱ ጥብቅ እና አላማዉን የመታ ነበር ፡፡ ቆሮንቶሳዊያን ንስሀ ገቡ ፤ ይህ ዝም ብሎ የማለፊያ ፀፀት አልነበረም ፡፡ በኃጢዓት እዉነተኛው እግዚአብሄራዊ ፀፀት ነበር ፤ ዋይርስቤ ልዩነቱን ይሁዳን እና ጴጥሮስን በማወዳደር ያሳያል፡ “ ይሁዳ በፀፀት በመሞላት ሄዶ ራሱን አጠፋ ፤ ጴጥሮስ በዉድቀቱ ንስኃ ገባ (ቁጥር 26፡ 75 – 27፡ 5) “ ፤ በቀላሉ ንስኃ መግባት ማለት ሀሳብን መቀየር ማለት ነው ፡፡ የማይታዘዙ ክርስቲያኖች ለመዳን ሳይሆን ከእግዚአብሄር ጋር ያላቸዉን ግንኙነት ለማደስ ንስኃ መግባት ያስፈልጋቸዋል ፡፡

2-ቆሮንቶስ (7፡ 11-16)፡ ጳዉሎስ በቁጥር 11-16 ቆሮንቶሳዊያን ቲቶን እንዳበረታቱት መዝግቧል ፡፡ በቆሮንቶስ ቲቶ የገጠመዉ እና ከዚያ የእርሱ ሪፖርት ቆሮንቶሳዊያን የተቀየረ ሀሳብ እንደ ነበራቸዉ እርግጠኛ ማስረጃ ነበር ፡፡ ዝግ ማለት እና ይህ አረፍተ ነገር ማጣጣም መልካም ነገር ነው ፤ ጳዉሎስ የስርዓት አያያዛቸዉን ተናገረ ፡፡ ጳዉሎስ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖችን አመሰገነ በድል ስፍራም እንዳሉ ይመስላሉ ፤ ነገር ግን በ 2ቆሮ (2፡ 1) በጠቀሳቸው “ በኃዘን መልዕክቶች ላይ “ ምስጋና አልነበረም ፡፡ ልዩነቱ ምን ነበር ? ልዩነቱ በዚህ ምዕራፍ ላይ በጳዉሎስ አስተያየት የተሰጠበት በቲቶ ሪፖርት ተደርጎ የነበረዉ ንስኃ መግባታቸዉ ነበር ፡፡

መደምደሚያ

ይህ ጳዉሎስ ከቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ጋር ያለዉ ግንኙነት ምን ያክል አሳስቦት እንደ ነበር እና ያ ህዝብ ለአገልግሎቱ በጣም አስፈላጊ እንደ ነበር ያሳያል ፡፡ አገልግሎትን ከህዝብ ጋር ባለዉ ወጪ ማድረግ አልፈለገም ፡፡

ለማድረግ ከሚያስቸግሩ አንዱ የተበታተነ ግንኙነትንመልሶ መገንባት ነው ፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ በአሁኑ ጊዜ በቤት፣ በቤተ ክርስቲያን እና በአገልግሎት ብዙ የተበታተኑ ግንኙነቶች አሉ - ሰዎች ችግርን በትህትና በመጋፈጥ መፅሀፍ ቅዱሳዊ እና በፍቅር በማድረግ በእግዚአብሄር ትክክለኛዉን የሚፈልጉ ብቻ መልሰዉ መገንባት እና ማጠንከር ይችላሉ ፡፡ የራሳችንን ኑሮ ስንፈትን የመልሱ አካል እንጂ የችግሩ አካል መሆን እንደሌለብን መወሰን አለብን ፡፡ ከጳዉሎስ እና በቆሮንቶስ ከነበረችዉ ቤተ ክርስቲያን በመማር የተሰበረን ግንኙነት ለመጠገን እግዚአብሄርን እንጠይቅ ፡፡

  1. Warren Wiersbe, The Wiersbe Bible Exposition Commentary: New Testament (Nashville: David C Cook, 2007), p. 519.

  2. Wiersbe, p. 522.

  3. Wiersbe, p. 522.

  4. Chuck Warnock, Paul’s Worst Church: Our Best Model?; available online at chuckwarnockblog.wordpress.com/2007/12/02/corinth-why-pauls-worst-church-may-be-our-best-model/.

  5. Wiersbe, p. 522.

  6. Wiersbe, p. 522.

ጥያቄዎች

  1. 2 ቆሮ (7፡ 1) ራሳችንን መንፈስን እና ስጋር ከሚያረክስ ነገር እንድናነፃ ጥሪ ነው ፤ ይህን እንዴት ታደርጉታላችሁ ?
  2. በ 2ቆሮ (7፡ 5) መሰረት ጳዉሎስ እና ባልደረቦቹ በዉስጣዊ ፍርሃት ተቸግረዉ ነበረ ፤ ጳዉሎስ መፍራቱ ያስገርማችኋል ? ለፍራታቸዉ ምክንያቱ ምን ሊሆን ይችላል ? (2ቆሮ 1፡ 8-10, 6፡ 4-10)
  3. ጳዉሎስ ቆሮንቶሳዊያንንእግዚአብሄር ከጭንቀታቸዉ እንደሚያስናናቸዉ ነገራቸው ፤ ያን መፅናናት እንዴት ልንቀበለዉ እንችላለን ? (2ቆሮ 7፡ 6)
  4. በ 2ቆሮ (7፡ 10) የተጠቀሱ ሁለት አይነት ኃዘኖች አሉ ፤ እያንዳንዳቸዉን ይገልፃል ፤ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች በክርስቶስ ሳያምኑ አለማዉ በሆነ ማዘን “ ንስኃ ይገባሉ “ ብላችሁ ታስባላችሁ ? አዎ በእዉነት የዳኑ ናቸው?
  5. በ 2ቆሮንቶስ 7 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 2 Corinthians 7:4

“I have great confidence in you; I have great pride in you. I am filled with encouragement; I am overcome with joy in all our afflictions.”

ጳውሎስ ስለ ቆሮንቶስ ሰዎች አኗኗር እውነታውን እናም በቆሮንቶስ የነበረው ጉብኝት እንዴት የሚያሳዝን እንደነበረ ጽፏል ፡፡ በተጨማሪ ጳውሎስ ምስጋናውንም ገልጧል ፡፡ ምንም እንኳ በጊዜው የቆሮንቶስ ሰዎችን መመልከት የሚያሳዝን ቢሆንም ፣ የጳውሎስ አገልግሎት ግን አልጠፋም ነበር ፡፡ የቆሮንቶስ ሰዎች ልክ እንደ ዛሬዋ ቤተክርስቲያን በጸጋ የዳኑ ኃጢአተኞች እናም እንዴት በመንፈስ መኖር እንደሚገባቸው በስራ ሳይሆን በእምነት የተማሩ ነበሩ ፡፡ የቆሮንቶስ ሰዎች በጣም ውድ የሆነ ሀብት በውስጣቸው ይዘው ከእግዚአብሔር ጋር እንደተለያየ እንደተቆረጠ ቧንቧ ወይም መስተላለፊያ መኖርን እየተለማመዱ ነበር ፡፡ ስለዚህም ነው ጳውሎስ ያ ኀዘን ወደ ንስሃ ስለመራቸው የጻፈላቸው መልዕክት ውጤት ማምጣቱን ጊዜ ወስዶ የሚያረጋግጥላቸው ፡፡

በህይወትህ ከጌታ ጋር እንዴት ሊመላለሱ እንደሚገባቸው ምክርን እንድሁም ደግሞ ተግሳፅን የሚፈልጉ ሰዎች ይኖሩ ይሆናል ፡፡ እነዚህ ሰዎች አቻዎችህ ፣ የስራ ባልደረቦችህ ፣ ጎረቤቶችህ ልጆችህም ጭምር ሊሆኑ ይችላል ፡፡ ለቤተክርስቲያን የተነገረው የጳውሎስ የማረጋገጫና የምክር ቃል አንተ ደግሞ ለሌሎች ፍቅርህን እንድታረጋግጥ እንድያስችልህ ፍቀድ ፡፡ ምናልባትም ዛሬ በህይወትህ የሆነን ሰው መምከር ይገባህ ይሆናል ምናልባትም የሆነ የቤተስብህን አካል ሊሆን ይችላል ፡፡ በውድቀት በመሸማቀቅ ጊዜ አንኳ ሳይቀር በመጥፎ ነገር ውስጥ ከመኖር ስለ ድክመት ከማውራት ይልቅ የሆነ ጡሩ መልካም የሆነን ነገር አንሳ ፡፡ ሌሎችን ገንባ አበረታታ ፡፡ ዛሬ ከምንም ጋር ሳታያይዝ በህይወትህ ውስጥ ያሉትን ሰዎች በደንብ አድርገህ የምር ለመውደድ ጊዜን ውሰድ ፡፡ እንተ ምንም አይነት ፍሬ ብታይም ባታይም እግዚአብሔር ግን በስራ ላይ ነው ፡፡ ጌታ ነገርን ሁሉ ለአለማው ለአሳቡ ይሰራዋል ፡፡

“ ስለ እናንተ እምነቴ ታላቅ ነው ፣ በእናንተ ምክንያት ትምክህቴ ታላቅ ነው ፤ መጽናናት ሞልቶብኛል ፤ በመከራችን ሁሉ ደስታዬ ከመጠን ይልቅ ይበዛል ፡፡ “ - 2ኛ ቆሮንቶስ 7፡4

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ሮሜ 1:8 — “ እምነታችሁ በዓለም ሁሉ ስለ ተሰማች አስቀድሜ ስለ ሁላችሁ አምላኬን በኢየሱስ ክርስቶስ አመሰግናለሁ ፡፡ “
  • 2ኛ ቆሮንቶስ 7:9–10 — “ በምንም ከእኛ የተነሳ እንዳትጎዱ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ አዝናችኋልና ፡፡ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ኀዘን ጸጸት የሌለበትን ወደ መዳንም የሚያደርሰውን ንስሐ ያደርጋልና ፤ የዓለም ኀዘን ግን ሞትን ያመጣል ፡፡ “
  • 3ኛ ዮሐንስ 1:4 — “ ልጆቼ በእውነት እንድሄዱ ከመስማት ይልቅ የሚበልጥ ደስታ የለኝም ፡፡ “