Paul's Letters 2 Corinthians

The Spirit Life

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Treasure 2 Corinthians 6 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 524 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ምዕራፍ ስድስት ከመግባት በፊት በዚህ ምዕራፍ የምናጠናዉን ለማጥራት በምዕራፍ አምስት አጉልተን የምንመለከተዉ ጥቂት ፅሁፎች አሉ፡

“ በእዉነትም የሚሞተው በሕይወትም ይዋጥ ዘንድ ልንለብስ እንጂ ልንገፈፍ የማንወድ ስለ ሆነ በድንኳኑ ያለን እኛ ከብዶን እንቃትታለን “ (2ቆሮ 5፡ 4) ፡፡ ሸክማችን ወደ ዉጪ ሰብሮ መዉጣት የሚፈልገው በዉስጣችን ያለዉ ይህ መዝገቡ ነው ፤ ይህ መዝገብ በዉስጣችን የምንፈልገዉን ህይወት ይሰጠናል፣ ከእግዚአብሄር በሆነዉ ህይወት በስጋ ህይወታችንን ይወስደዋል /ይጨርሰዋል ፡፡

“ ስለዚህ እኛ ከአሁን ጀምሮ ማንንም በስጋ እንደሚሆን አናዉቅም ፤ ክርስቶስንም በስጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናዉቀዉም ፡፡ ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው ፤ አሮጌዉ ነገር አልፎአልና ፤ እነሆ ሁሉም አዲስ ሆኖአል ፡፡ ነገር ግን የሆነዉ ሁሉ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅንም አገልግሎት ከሰጠን ከእግዚአብሄር ነው “ (2ቆሮ 5፡ 16-18) ፡፡ በክርስቶስ በልባችበን አዲስ የሆነ ነገር ተፈጥሯል ፤ ለዚያ ነዉ “ ዳግም እንደተወለደ “ ሆነን የምንናገረው ፡፡ አሮጌዉ ህይወታችን አልፏል አዲሱ ህይወት ተሰጥቶናል ፡፡ እግዚአብሄር በእኛ እና ለእኛ ያደረገው አዲስ ማንነት እና አመለካከት ሰጥቶናል ፡፡

“ እንግዲህ እግዚአብሄር በእኛ የሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልዕክተኞች ነን ፤ ከእግዚአብሄር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን “ (2ቆሮ 5፡ 20) ፡፡ እግዚአብሄር በቀላሉ የቆሮንቶሳዊያንን ባህሪይ ለመቀየር ብቻ አልፈለገም ፤ ስራ እንዲሰሩ በሰጣቸዉ በክርስቶስ አዲስ ህዝብ እንዲሆኑ ፈለገ ፡፡

ትምህርት

2-ቆሮንቶስ (6፡ 1-2)፡ ጳዉሎስ በራሱ ጉዳይ ከጌታ ጋር አልሰራም ፤ ይልቁንም ጳዉሎስ “ ከእርሱ ጋር በአንድ ላይ እየሰራ እንደ ነበር “ አሳወቀ (ቁጥር 1) ፡፡ ጳዉሎስ ጌታ ስለ አገልግሎቱ አጀንዳዉን እንዲያስቀምጥለት በመፍቀድ ታዘዘ ፡፡ አማኞች ከእግዚአብሄር የተቀበሉት ፀጋ ሊያጠፉት ወይም ሊያስቀምጡት የሚቻል አልነበረም ፤ የት እንደ ነበሩ በክርስቶስ የለያል ፡፡ ጳዉሎስ ቆሮንቶሳዊያን በመንፈስ በአዲሱ ህይወት ልምምድ ዋና እንዲሆኑ ፈለገ ፡፡

2-ቆሮንቶስ (6፡ 3-10)፡ ጳዉሎስ በህይወቱ አብዛኛዉን በመንፈሳዊ ህይወት በመጓዝ ስለፈፀመ ማንም ግብዝ ወይም አስመሳይ እንደ ነበር ሊከሰዉ አልቻለም ፡፡ የጳዉሎስ የሚያደናቅፍ ትኩረት የአገልግሎቱ እርግጠኝነት ነበር ፤ በመንፈስ እስከ ሄደ ድረስ የአገልግሎቱ ኃይል እና ስልጣን ዋጋዉ ሊያጣ አይችልም ፤ ይህ መስፈርት እንደ አንድ አገልጋይ ለጳዉሎስ ብቻ አልነበረም ፡፡ ተመሳሳይ መስፈርት ለሁሉም አማኞች ይተገበራል ፡፡ በግል ነገር በየግል የተለዬ ይመስላል ነገር ግን ሁሉም አማኞች የመልዕክታቸዉ እርግጠኝነት መጥፋት በማይችልበት ይዘት በመንፈሳዊ ህይወት ይጓዛሉ ፡፡ ጳዉሎስ ከራሱ ልምምድ ተወልደዉ የነበሩ በመንፈሳዊ ህይወት የመጓዝ ብዙ መስፈርቶችን/ ማጣሪያዎችን ዘርዝሯል ፡፡

  • ብዙ መፅናት/ታላቅ መታገስ (ቁጥር 4) - ጊዜ በሚወስዱ እና ምቾት በሌላቸዉ ነገሮች ዉስጥ እንጓዛለን ፡፡
  • መከራ (ቁጥር 4) - በእኛ ላይ የሚመጣ ያልተጠበቀ አስቸጋሪ ሁኔታ ፡፡
  • ችግር እና ጭንቀቶች (ቁጥር 4) - ልንታገሰዉ የሚገባን አስቸጋሪ ነገር ፡፡
  • ግርፋትና እስራት (ቁጥር 5) - አካላዊ ችግሮች ፡፡
  • ሁከት እና ድካም (ቁጥር 5) - ሰዎች በአካል በእናንተ ላይ ቢመጡባችሁ ሁኔታው አካላዊ ፅናት እና ጥረት ይፈልጋል ፡፡
  • እንቅልፍ በማጣትና በርሀብ ጊዜ (ቁጥር 5) - እንዳንተኛ ምክንያት የሚሆኑን ሸክሞች፣ የእግዚአብሄርን ተልዕኮ በምትከታተሉ ጊዜ ምግብ ወደ ማይገኝበት ስፍራ ይመራችኋል ፡፡
  • በንፅህና እና በእዉቀት (ቁጥር 6) - የሚያደርገዉ በእግዚአብሄር የታወቀ እንደሆነ ማረጋገጫ ፡፡
  • በትዕግስት እና በቸርነት (ቁጥር 6) - ዋጋ ያላቸዉ ነገሮች ነገር ግን በሚገባ የሚጠበቁ፣ በሞራል መጥበቅ አሪፍ የሆንን ብቻ አይደለም ፡፡
  • በመንፈስ ቅዱስ እና ግብዝነት በሌለዉ ፍቅር (ቁጥር 6) - በልብ ላይ ከእግዚአብሄር ስራ የተነሳ መታዬት የነበረበት እዉነተኛ ፍቅር ፡፡
  • የእዉነት መልዕክትበእዉነት መልዕክት፣ በእግዚአብሄር ቃል እና በጽድቅ ዕቃ ጦር (ቁጥር 7) - መንፈሳዊ መሳሪያ ለሁሉም አማኝ የተሰጠ ነው ፡፡
  • በክብርና በዉርደት፣ በሀሜት እና በመልካም ወሬ እዉነተኞች ሆነን እንደ አሳቾች መታዬት (ቁጥር 8) - የግል አስተያየቶች ይቀላቀላሉ፣ አንዳንዶች በመቋቋም የአገልግሎትን ስራ ዋጋ ለማሳጣት ይፈልጋሉ ፡፡
  • ያልታወቁ ስንባል የታወቅን፣ እየሞትን የምንኖር፣ የተቀጣን ስንሆን አንገደልም (ቁጥር 9) - ለሰዎች የማይታወቅ በእግዚአብሄር ግን በደንብ የታወቀ፣ የዉጨኛው ሰዉ ይጠፋል ነገር ግን ዉስጠኛው ሰዉ ግን ዕለት ዕለት የሚታደስ ነው ፡፡
  • ኃዘንተኞች ስንሆን ደስተኛች፣ ድሆች ስንሆን ብዙዎችን ባለጠጎች አድራጊ፣ አንዳች የሌለን ስንሆን ሁሉ የእኛ (ቁጥር 10) - አስቸጋሪ ነገሮች እየደረሱ ነገር ግን በዘላለማዊ እዉነታዎች ላይ ማትኮር፣ ሌሎች በመንፈሳዊ ተባርከዉ ለማየት ራስን ባዶ ማድረግ፣ ዘላለማዊነትን ለማግኘት የአንድን ሰዉ ህይወት ዝቅ ማድረግ ፡፡

የጳዉሎስ ማጥሪያ እንደ ገና በ 2ቆሮ (11፡ 23-27) ይመጣል፡ “ የክርስቶስ አገልጋዮች ናቸዉን ? እንደ እብድ ሰው እላለሁ ፤ እኔ እበልጣለሁ ፤ በድካም አብዝቼ በመገረፍ አብዝቼበመታሰር አትርፌ በመሞት ብዙ ጊዜ ሆንሁ ፡፡ አይሁድ አንድ ሲጎድል አርባ ግርፋት አምስት ጊዜ ገረፉኝ ፡፡ ሶስት ጊዜ በበትር ተመታሁ ፤ አንድ ጊዜ በድንጋይ ተወገርሁ ፤ መርከቤ ሶስት ጊዜ ተሰበረ ፤ ሌሊትና ቀን በባህር ዉስጥ ኖርሁ ፡፡ ብዙ ጊዜ በመንገድ ሄድሁ ፤ በወንዝ ፍርሃት በወንበዴዎች ፍርሃት በወገኔ በኩል ፍርሃት በአሕዛብ በኩል ፍርሃት በከተማ ፍርሃት በምድረ በዳ ፍርሃት በባህር ፍርሃት በዉሸተኞች ወንድሞች በኩል ፍርሃት ነበረብኝ ፤ በድካምና በጥረት ብዙ ጊዜም በመጦም በብርድና በራቁትነት ነበርሁ “ ፡፡

2-ቆሮንቶስ (6፡ 11-13)፡ ጳዉሎስ ቆሮንቶሳዊያንን በመዉደድ ነግሯቸዉ የነበረዉን የክርስቶስን ነፃነት እንዲያዉቁና እንዲደሰቱበት ፈለገ ፡፡ ጳዉሎስ ቀድሞ ጠቅሷቸዉ የነበሩትን ሁሉንም ነገር ለቤተ ክርስቲያን ካለዉ ፍቅር እና ጉጉት የተነሳ ታገሰ ነገር ግን ቆሮንቶሳዊያን “ በራሳቸዉ ችግር ጠብበው /ተወስነዉ ነበር “ (ቁጥር 12) ፡፡ ጳዉሎስ ቆሮንቶሳዊያንን ለእነርሱ እያለ የነበረዉን ለመስማት ልባቸዉን እንዲከፍቱ አበረታታቸዉ ፡፡

2-ቆሮንቶስ (6፡ 14-18)፡ ጳዉሎስ አማኞችን “ ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ እንዳይጠመዱ “ (ቁጥር 14) አበረታታቸው ፡፡ አማኞች የማያምኑት በቀላሉ ሊረዱት የማይችሉት በዉስጣቸዉ መዝገብ አላቸው ፡፡ በመቀጠል ጳዉሎስ አማኞች ከማያምኑት እንዴት እንደሚለዩ ብዙ ምሳሌዎችን ሰጠ (ቁጥር 14-16) ፡፡ ሀሳቡ በዉስጥ ያለዉ ከዉጪ ካለዉ በጣም ጠቃሚ ነበር የሚል ነው ፡፡

መደምደሚያ

በእኛ ዉስጥ መዝገብ እንዳለ በእዉነት የምናምን ከሆነ እኛን በመጠበቅ፣ መዝገብ በመሆን፣ በከፍተኛ ስለ ምግባር ሀቀኝነት በመጠበቅ እና ወደ እግዚአብሄር እኛን በማስገደድ ይጠቅማል ምክንያቱም በልባችን ዉስጥ ያደረገዉን ስለምንወድ ፡፡

ጥያቄዎች

  1. በከንቱነት የእግዚአብሄርን ፀጋ መቀበል ምን ይመስላል ? (2ቆሮ (6፡ 1)
  2. 2 ቆሮ (6፡ 3) አንብቡ ፤ ወደ ክርስቶስ ከመጣችሁ “ የማሰናከያ ምክንያት ትሰጣላችሁ “ ? እንደ አማኝ የተጠራንበትን የማስታረቅ አገልግሎት ዋጋ የሚያሳጣ ማሰናከያን አይትችኋል ? (2ቆሮ 5፡ 18)
  3. በ 2ቆሮ (1፡ 4-8) ጳዉሎስ መከራዎችን እና ችግሮችን በመጥቀስ በ 2ቆሮ (6፡ 4-8) የአንዳንዶቹን ዝርዝር አካፈለ ፤ ከችግር እና ከመከራ በተጨማሪ ሌላ ምንን አካተተ ? በዚህ ዝርዝር በየትኛዉ ጥልቅ ዝርዝር በግል ልትለዩ ትችላላችሁ ?
  4. በ 2ቆሮ (6፡ 7) ለቀኝ እጅ እና ለግራ የፅድቅ መሳሪያዎችን የተጠቀሱ ናቸው (ነህ 4፡ 16-18) ፤ እነዚህ ምን እንደሆኑ ምን ታስባላችሁ ? (2ቆሮ 10፡ 3-4, ኤፌ 6፡ 17-18, ያዕ 5፡ 16)
  5. ከማያምኑት ጋር ራሳችንን የምናጣምርባቸዉ ምን አይነት መንገዶች ናቸው ? (1ቆሮ 15፡ 33)
  6. በ 2ቆሮንቶስ 6 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 2 Corinthians 6:3–4a

“We give no opportunity for stumbling to anyone, so that the ministry will not be blamed. But as God’s ministers, we commend ourselves in everything.”

እንደ ክርስቶስ አማኞች እናንተ አድስ ፍጥረት ናችሁ ፣ የቀድሞ መንገዳችሁም አልፏል ፡፡ የእግዚአብሔር ጸጋ በእናንተ ላይ ነው ፤ በአድስ ህይወትም መመላለስ ትችሉ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ አላችሁ ፡፡ ይህንንም ስታደርጉ እንደ ክርስቶስ አምባሳደሮች ክርስቶስን ለሌሎች በመወከል ታገለግላላችሁ ፡፡ እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች መከራና ችግር ቢኖርም ክርስቶስን የማንጸባረቅ ሃላፊነት አለባችሁ ፡፡ አዎን ልክ በጳውሎስ ላይ እንደሆነው አይነት መከራ እንደሚመጣ ጌታ ተናግሯል ፡፡ ነገር ግን በመከራም ውስጥ ቢሆን እንኳ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል በውስጣችሁ ስለሚሰራ በትዕግስት ፣ በቸርነት ፣ በንጽህና ፣ በእውቀት እና በጥበብ ክርስቶስን አንጸባርቁ ፡፡ በቅንነት የተሞላ ፍቅርን በማሳየት የእውነቱን መልዕክት አስተላልፉ ፡፡

ምናልባት ይህ ማድረግ ያለባችሁ ነገሮች ዝርዝር ሊመስል ይችላል ነገር ግን ክርስቶስ እነዚህን በመቆጣጢያ ደብተር ላይ ጽፋችሁ እንድትይዟቸው አይፈልግም ፡፡ ይልቁንም በማመስገንና በጌታ ደስ በመሰኘት እንድታደርጓቸው እንጂ ፡፡ ለምን ? እናንተ አዲስ ፍጥረት ስለሆናችሁ ! ሂዱ ደግሞም ከሞት በተነሳው አዳኝ ደስ ይበላችሁ ፡፡ በሚያድን ጸጋው ተመላለሱ ፡፡ ህይወት ምንም ያህል ከባድ ይሁን ጌታ የሚነግራችሁ ትታገሱ ዘንድ ነው ደግሞም እግዚአብሔር ኃይሉን በመንፈስ ቅዱስ እንደሚሰጣችሁ አስታውሱ ፡፡ እንደ እግዚአብሔር አምባሳደሮች በእያንዳንዷ እርምጃችሁ ጸጋው እንደሚሸከማችሁ በማመን ፣ በእምነት ተመላለሱ ፡፡

“ አገልግሎታችንም እንዳይነቀፍ በአንዳች ነገር ማሰናከያ ከቶ አንሰጥም። ነገር ግን በሁሉ እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ራሳችንን እናማጥናለን :: "

- 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6 : 4 -

ተጨማሪ ጥቅስ

  • 2ኛ ቆሮንቶስ 5:17 ፤ 5፡20-" ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።..... እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን ። “
  • 2ኛ ቆሮንቶስ 6:5-7–“ በብዙ መጽናት፥ በመከራ፥ በችግር፥ በጭንቀት፥ በመገረፍ፥ በወኅኒ፥ በሁከት፥ በድካም፥ እንቅልፍ በማጣት፥ በመጦም፥ በንጽህና፥ በእውቀት፥ በትዕግሥት፥ በቸርነት፥ በመንፈስ ቅዱስ፥ ግብዝነት በሌለው ፍቅር፥ በእውነት ቃል፥ በእግዚአብሔር ኃይል :: "
  • 1ኛ ዮሐንስ 2:4-5-" አውቄዋለሁ የሚል ትእዛዛቱንም የማይጠብቅ ውሸተኛ ነው እውነትም በእርሱ ውስጥ የለም። ቃሉን ግን የሚጠብቅ ሁሉ በእርሱ የእግዚአብሔር ፍቅር በእውነት ተፈጽሞአል። በእርሱ እንዳለን በዚህ እናውቃለን ፡፡ “