Walk By Faith
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Treasure 2 Corinthians 5 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ዛሬ ትናትና በሸክላ እቃ ዉስጥ ስላለዉ መዝገብ በተካፈልነዉ መልዕክት ላይ እንገነባለን/እንቀጥላለን ፡፡ በ 2ቆሮ (4፡ 1) ጳዉሎስ ለዚህ አገልግሎት እንደተጠራና ላለመታከትም እንደወሰነ ተናገረ ፡፡ በ 2ቆሮ (4፡ 7) ጳዉሎስ ተሰጥቶት ስለ ነበረዉ መዝገብ (የሸክላ እንስራዎች እንደ ሆንን ኢየሱስ ደግሞ መዝገቡ) ገልጾአል ፡፡ በ 2ቆሮ (4፡ 13) ጳዉሎስ ለመናገር የሚመራን ተመሳሳይ የእምነት መንፈስ አለን አለ ፡፡ ወደ 2ቆሮንቶስ ስንሻገር ቁጥር 1 በሰዉ እጅ ያልተሰራ ዘላለማዊ መኖሪያ ከእግዚአብሄር የሆነ ሕንፃ እንዳለን ይነግረናል ፡፡
ትምህርት
2-ቆሮንቶስ (5፡ 1-5)፡ ሐዋ (18፡ 1-3) ጳዉሎስ በቆሮንቶስ ሲያገለግል ድንኳን በመስራት ራሱን እንደደገፉ ይነግረናል ፡፡ ድንኳን የተለመደ አንድ ነገር አለው - በመቆየት እንዲፀልዩ ተስፋ ታደርጋላችሁ ምክንያቱም አንድ ኃይለኛ ንፋስ ስለሚጥላቸው ፡፡ ድንኳን ጠንካራ አይደለም፣ ቋሚ ስትራክቸር አይደለም ፡፡ “ ጊዜያዊዉ ምድራዊዉ መኖሪያችን ቢፈርስም እንኳን “ በሚል ጊዜ ጳዉሎስ በአካል ስንሞት ስለሚጠፋዉ አካላችን እያወራ ነበር ፤ እግዚአብሄር ይመስገን ሌላ ነገር አለን - “ በእጅ ያልተሰራ በሰማያ የዘላለም መኖሪያ አለን “ ፡፡ ጳዉሎስ በሰማይ ስለ ግንብ እያወራ አልነበረም - ስለሌላ የከበረ ሰዉነት እያወራ ነበር እንጂ ፤ በፍፁም ደካማነትን የማያሳይ ይህ አዲስ የሚያምር ዘላለማዊ ሰዉነት አለን ፡፡ ያ ዉጋት፣ ህመም፣ ራስ ምታት፣ መጥፎ እግር ወይም መጥፎ ጭን ካለዉ ደካማና ጊዜያዊ ሰዉነት ሙሉ በሙሉ ተቃራኒ ነው ፡፡ የከበረዉ ሰዉነት 100 ፐርሰንት ጊዜያዊዉን ድንኳን ይበልጣል ፡፡
ይህ አዲስ ህንፃ በክርስቶስ ትንሳኤ ምክንያት ይመጣል (1ቆሮንቶስ 15) ፡፡ ከክርስቶስ ትንሳኤ የተነሳ በሙሉ ራስ መተማመን የከበረ ሰዉነት አለን ማለት እንችላለን ፡፡ ሞት ከዚህ በኋላ ሊቀጣን ወይም በኛ ላይ ድል ሊቀዳጅ አይችልም ፤ ምክንያቱም በዉስጣችን ይህ መዝገብ አለን “ በዚህ ዉስጥ በእዉነት እንቃትታለንና ከሰማይ የሚሆነዉን መኖሪያችንን እንድንለብስ “ (ቁጥር 2) ፡፡ ዋረን ዋይርስቤ ይህን በሌላ መንገድ አስቀምጦታል፡ የኢየሱስን ተመልሶ መምጣት በእዉነት እንጠብቃለን በማለት እግዚአብሄር ለዚህ አላማ በማዘጋጀት (ለከበረዉ ሰዉነት) መንፈሱን እንደ መያዣነት ሰጠን (ቁጥር 5) ፡፡ ጳዉሎስ ወደፊት የተሸለ ነገር ስላለን ይህን ሂደት እንድንታገስ አሳስቦናል ፤ በዚህ ሂደት ዉስጥ እንዲረዳን እግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስን ሰጥቶናል ፤ በሚያስደንቅ ሁኔታ “ በቅንነት “ የሚለዉ የግሪክ ቃል “ የእጮኝነት ቀለበት “ ማለት ነው ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ለኢየሱስ ክርስቶስ በመታጨቷ ወደ ሰርጉ መጥቶ እስኪወስዳት ሙሽራዉን እየጠበቀች ነው ፡፡
2-ቆሮንቶስ (5፡ 6-7)፡ ድነታችንን ስለ ማጣት በፍፁም መጨነቅ የለብንም ፤ ከጌታ የራቅን ብንሆንም እንኳን በእኛ ዉስጥ ባለዉ ክርስቶስ ምክንያት ሙሉ መተማመን ሊኖረን እንደሚችል እናውቃለን ፡፡ በሚገባ “ በእይታ ሳይሆን በእምነት “ መጓዝ እንችላለን (ቁጥር 7) ፤ ይህ በጠቅላላ ምዕራፉ እንዴት በእምነት መጓዝ እንዳለብን ለመረዳት ቁልፍ/ዋና ነው ፡፡ ይህን ለማድረግ እንዴት እንማራለን ? ዊክሀዉ በቦልድ ህትመት የተዘረዘሩት አንዳንድ ምክሮችን አቅርቧል፡
- ዘላለማዊ አስፈላጊነት ባላቸዉ ነገሮች ላይ ማትኮር ፡፡ ማየት ከምትችሉት ነገር ላይ ብቻ ትኩረታችሁን አሳልፋችሁ አትኩሩ ፡፡
- መፅሀፍ ቅዱስን እና የእግዚአብሄር ትዕዛዝን ማክበር ፡፡
- ሞኝነት የሚመስል ነገርን ለመመልከት መዘጋጀት ፡፡ ለእግዚአብሄር ሞኝ መሆን መልካም ነው ፤ ቤተ ክርስቲያን በአለም አይን ሞኝ ለመሆን ትፈራለች ፡፡ ሰዎች በባለቤታቸዉ ወይም በልጆች ፊት ሞኝ መሆን ይፈራሉ ፡፡
- በመንገድ/በጉዞ ላይ መከራ እንደሚገጥም ማሰብ ፡፡ በእምነት መጓዝ ቀላል አይደለም ነገር ግን ሁል ጊዜ እግዚአብሄር ከእናንተ ጋር ነው ፡፡
- አንድ ጥምቀትን መጠበቅ ማቆም ፡፡ ስንፀልይ “ እግዚአብሄር ምልክት ይሰጠኛል እሄዳለሁም “ ማለትን አሁንም ያ በእይታ መሄድ ስለሆነ ፡፡
- በምታደርጉት ሁሉ እግዚአብሄርን ማክበር ፡፡ ጳዉሎስ ይህን በ 1ቆሮ (10፡ 31) ብሏል ፡፡
በእምነት ለመጓዝ የእምነት መንፈሳዊ ስጦታ ካልተሰጣችሁ ፤ ዮሐንስ ፒፐር ይህን ዝርዝር አቅርቧል፡
ከእግዚአብሄር ዉጪ ምንም ነገር ማድረግ እንደማትችሉ እመኑ (ዮሐ 15፡ 5) ፡፡
ስለ እርዳታ መፀለይ (መዝ 50፡ 15) ፡፡
የተለዩ ተስፋዎችን ማመን (2ዜና 20፡ 20) ፡፡
መተግበር/መስራት (ፊል 2፡ 12-13) ፡፡
ስለ ስጦታዉ እና ርህራሄዉ/ቸርነቱ እግዚአብሄርን ማመስገን (መዝ 106፡ 1) ፡፡
በሮሜ (10፡ 17) ጳዉሎስ “ እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሄር ቃል ነው “ በማለት ፅፏል ፤ ስለዚህ በእግዚአብሄር ቃል መሰረት እነዚህን ነገሮች ስንሰማ በዚህ እምነት እንሄዳለን ፡፡ የዚህ ሁሉ ጥቅም ምንድን ነው ? በኤፌ (3፡ 20) እግዚአብሄር “ እንግዲህ በእኛ እንደሚሰራው ኃይል መጠን ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ ይልቅ እጅግ አብልጦ በእኛ እንደሚሰራ “ እናነባለን ፡፡ በዮሐ (14፡ 12) ኢየሱስ “ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገዉን ስራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል ፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል “ አለ ፡፡ እንዴት በእምነት እንደምትጓዙ ማወቅ ትፈልጋላችሁ ? እምነት ሲኖራችሁ ኢየሱስ ከሰራዉ የሚበልጥ ነገር ማድረግ ትችላላችሁ ፤ ስለዚህ ከእርሱ ዉጪ ይህን ማድረግ እንደማትችሉ እመኑ፣ በመፀለይ እንዲረዳችሁ ጠይቁት፣ በዚህ በተለዬ ተስፋ በማመን በዚህ ለመስራት በመጀመር እግዚአብሄር ስለሚታይላችሁ/ስለሚገለጥላችሁ አመስግኑ ፡፡
መደምደሚያ
ይህ ምዕራፍ የክርስቶስ አምባሳደር ስለመሆን የሚያወራ ቢሆንም ዛሬም በእምነት እንድትጓዙ እንዳበረታታችሁ እግዚአብሄር እንደነገረኝ ተሰምቶኛል ፡፡
Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1989), p. 515.
Wiersbe, p. 515.
“How to Walk by Faith: Part 2, Delve Deeper”; available from https://www.wikihow.com/Walk-by-Faith.
John Piper, “Practical Steps to Walk by Faith”; available from https://www.wikihow.com/Walk-by-Faith.
ጥያቄዎች
-
2 ቆሮ (5፡ 1) ካነበባችሁ በኋላ እንዴት ተሰማችሁ ? በሰማይ ስላለዉ “ ቤታችሁ “ እና ዘላለማዉ ሰዉነታችሁ ትንሽ ደቂቃ በመዉሰድ አስቡ ፤ ስለሰጣችሁ ስለ ነዚህ ስጦታዎች እግዚአብሄር ይመስገን ፡፡
-
በ 2ቆሮ (5፡ 7) መሰረት “ በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስም “ ፤ ለእናንተ ይህ ምን ማለት ነው ? ስለዚህ በህይወታችሁ አንዳንድ ምሳሌዎችን ስጡ
-
2ቆሮ (5፡ 10) ስታነቡ በልባችሁ ላይ ፍርሃትን አስቀምጧችኋል ? በዚያ ቀን ስለምትቀበሉት መልካም ወይም መጥፎ ነገር ምን ታስባላችሁ ?
-
2 ቆሮ (5፡ 17) ለአንድ ለማያምን ሰዉ በተግባር እንዴት ትገልፁለታላችሁ ? ይህን ጥቅስ በማመን በእርሱ ትመላለሳላችሁ ? አዎ ከሆነ እንዴት ?
-
ሙሉ በሙሉ 2ቆሮ (5፡ 21) ታምኑበታላችሁ ? ያን ከሌሎች ጋር ትጋሩታላችሁ ? “ ኃጢዓት ያላወቀዉን እርሱን ስለ እኛ ኃጢዓት አደረገው “ የሚለዉን ለሌሎች እንዴት አድርጋችሁ ማጋራት ትችላላችሁ ?
-
በ 2ቆሮንቶስ 5 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 2 Corinthians 5:7
“For we walk by faith, not by sight.”
ጳውሎስ የቆሮንቶስ አማኞችን በማየት ሳይሆን በእምነት ይመላለሱ ዘንድ መከራቸው ፡፡ እምነት ማለት በሆነ አካል ወይም በሆነ ነገር ላይ ሙሉ እምነት ማሳደር ማለት ነው ፡፡ እንደ አማኝ በእግዚአብሔር ላይ ፍጹም የሆነ መተማመንና 100% እምነት ሊኖራችሁ ይችላል ፡፡ ይህ በራስህ እጅ ነገሮችን መቆጣጠርን መተውና አንተ ሁሉንም እንደማታውቅ ማመንን ይጠይቃል ፡፡ እስኪ አስብ አይኖችህ በጨርቅ ተሸፍነው መሬቱ እንደሚኖር በማመን እያንዳንዷን እርምጃ ወደፊት ስትራመድ ፡፡ ሆኖም ግን በምትረገጠው መሬት መካከል ጉድጓድ ቢኖርም እምነት ማለት ግን ጉድጓድ እያለም የምትፈልገውን ድጋፍ ከመሬቱ እንደምታገኝ ማመን ማለት ነው ፡፡ ጉዞህን ለመቀጠል የሚያስፈልግህን ድጋፍ ታገኛለህ ፡፡
የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ ይህ ጊዜ በማየት ሳይሆን በማመን የምትመላለስበት ጊዜ ነው ፡፡ እግዚአብሔር በዚያ ከአንተ ጋር እንደሚሆን ተናግሯል ፡፡ እርሱ ፈጽሞ አይተውህም ፡፡ ከእርሱ ርቀህ ምንም ማድረግ ስለማትችል ኢየሱስ በእርሱ እንድትኖር ይነግርሃል ፡፡ እግዚአብሔር በእምነት ኢየሱስ ከደረጋቸው ነገሮች የሚበልጡ እንድሁም ከምታስበው በላይ የሆነ ነገሮችን ማድረግ እንደምትችል ተናግሯል ፡፡ ስለዚህ ዛሬ አንድኛው ወደፊት ለመራመድ የምትወስደው የእምነት እርምጃ ምንድን ነው ? ምናልባት የሚያስፈራ እና የማይመች ሊሆን ይችላል ነገር ግን ይህ ዛሬ ልትወስደው የሚገባ የእምነት እርምጃ ነው ፡፡ ጌታ በፊትህ ያለውን የማይታወቀውን እንድትዳስስ እንድትረዳ እንደሚረዳህ እመን ፡፡ በል ተራመድ እና እግዚአብሔር እንዲሰራ አድርግው ፡፡
" በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና :: "
- 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5 :7
ተጨማሪ ጥቅስ
- ዮሐንስ ወንጌል 14 : 12 – " እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል :: "
- ዮሐንስ ወንጌል 15 : 5 – “እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል ። “
- ዕብራውያን 11:1- " እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው ። "
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።