Treasure In Clay Jars
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Treasure 2 Corinthians 4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ጳዉሎስ በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን የተሰማን ብዙ ግጭቶችን እና ሌላ ብዙ ነገሮች ደርሶታል ፤ በዚህ ምክንያት ጳዉሎስ ተስፋ የቆረጠ ለመሆን ብዙ ምክንያቶች ነበሩት ነገር ግን ተስፋ አልቆረጠም ፡፡ በምዕራፍ አራት መጀመሪያ እና መጨረሻ ላይ “ አንታክትም “ በማለት ፅፏል ፤ ለምን ? ምክንያቱም መዝገቡ ማን እንደ ነበር ስለሚያዉቅ ፡፡ መዝገብ በ 2ቆሮንቶስ ለኢየሱስ ማን እንደ ሆነ የሚገልፅ ቃላችን ነው ፤ ያ መዝገብ ጳዉሎስ በኢየሱስ ክርስቶስ የያዘዉ/ያገኘዉ ነበር ፡፡
ትምህርት
2-ቆሮንቶስ (4፡ 1)፡ ቁጥር 1 ከምዕራፍ 3 ላይ የተመሰረተ ነው ፤ ጳዉሎስ ይህ አገልግሎት ስለ ነበረው እና ምህረትን ስላዬ ተስፋ ለመቁረጥ/ለመታከት አልፈለገም ፡፡ የዚህ ምዕራፍ ጭብጥ ያ ነው ፡፡ ጳዉሎስ በምዕራፍ 3 እንደ ገለፀው “ ይህ አገልግሎት “ ምን ይመስላል ? “ የሞት አገልግሎት ነበር “ (2ቆሮ 3፡ 7)፣ “ የመንፈስ አገልግሎት ነበር “ (2ቆሮ 3፡ 8) እና “ የጽድቅ አገልግሎት ነበር “ (2ቆሮ 3፡ 9) ፡፡ ይህ አገልግሎት ጳዉሎስን ተስፋ የቆረጠ እንይሆን ጠበቀው ፡፡ ጳዉሎስ ቀድሞ በዚህ መልዕክት ላይ ለቆሮንቶሳዊያን እየተቀበለ የነበረዉ ሁሉም መልዕክት እና ሁሉም እየደረሰበት የነበረው ወደ ተስፋ መቁጥ አምጥቶት እንደ ነበር ነግሯቸዋል (2ቆሮ 1፡ 8) ፡፡
2-ቆሮንቶስ (4፡ 2-4)፡ ይህ አገልግሎት ጳዉሎስን አታላይ ከመሆን ጠበቀው ፡፡ ዋረን ዋይርስቤ “ መፅኃፍን ከአዉዱ ዉጪ በመጠምዘዝ የራሳችሁን ሀሳብ ምስክር አለመቀበልን በማቅረብ ማንኛዉንም ነገር በመፅኀፍ ቅዱስ ማረጋገጥ እንደሚቻል “ አመልክቷል ፡፡ በወንጌል ላይ ሰይጣን እንኳን ኢየሱስን ለመፈተን መፅኃፍትን እንደተጠቀመ እናስታውሳለን ፤ የሚበቃዉን እዉነት በመዉሰድ ብቻ ጠመዘዝው/አጣመመው ፡፡ ተመሳሳይ እናደርጋለን አንዳንድ ጊዜ በደንብ በማሰብ ፡፡ ሰዎች “ መያዝ ከምትችሉት በላይ ምንም ነገር እግዚአብሄር አይሰጣችሁም “ ሲሉ ምን ያክል ጊዜ ሰምታችሁ ታውቃላችሁ ? ነገር ግን መፅሀፍ ቅዱስ ያን አይልም ፡፡ በ 1ቆሮ (10፡ 13) “ ከምትችሉት በላይ አይፈትናችሁም “ የሚለዉን አንድ ቃል መጠምዘዝ ነው ፡፡ እግዚአብሄር መያዝ ከምትችሉት በላይ ምንም ነገር የማይሰጥ ከሆነ እግዚአብሄር አያስፈልጋችሁም ለማለት ነዉ ፤ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ እግዚአብሄር ያስፈልገናል ፡፡
ይልቁንም 1ቆሮ (10፡ 13) እግዚአብሄር ከገጠመን ከሁሉም ፈተና መዉጫ መንገዱን እንደሚሰጠን ተስፋ ይሰጣል፡፡ ማታለል እና ማጥፋት (ቁጥር 2) ለሚለዉ የግሪክ ቃል በአዲስ ኪዳን ዉስጥ በዚህ ጥቅስ ላይ ብቻ ይገኛል ፤ “ መበረዝ ወይም መደባለቅ “ ማለት ነው ፡፡ ስለዚህ ለምን ብዙ ሰዎች የጳዉሎስን መልዕክት አላዳመጡም ? ምክንያቱም “ ለእነርሱም የእግዚአብሄር ምሳሌ የሆነ የክርስቶስ የክብር ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው የዚህ ዓለም አምላክ የማያምኑትን አሳብ አሳወረ “ (ቁጥር 4) ፡፡ በተጨማሪም ጳዉሎስ ስለዚህ በሮሜ (11፡ 25) እና 2ቆሮንቶስ አዉርቷል ፡፡ ሰይጣን ሰዎች የመዳንን ክብር እንዲያዩ ስለማይፈልግ ሐሰተኛ መልዕክትን ለማሰራጨት ኃይማኖታዊ መምህራንን መጠቀም ይወዳል ፤ በዚህ ጊዜ ሰይጣን ከትርጓሜአቸዉ ጋር እንዲጣጣም መፅኃፍትን የጠመዘዙትን የአይሁድ አስተማሪዎች ተጠቀመ ፡፡
2-ቆሮንቶስ (4፡ 5-6)፡ ይህ አገልግሎት ጳዉሎስን ራሱን አስተዋዋቂ ከመሆን ጠብቆታል ፡፡ ጳዉሎስ ንፁህ የሆነ ትህትናን ከኢየሱስ የተነሳ ባሪያ እንደ ነበር በመናገር ተገበረ ፡፡ ጳዉሎስ ኃይለኛ የሆነ ማንነት ስለነበረዉ በቀላሉ ታዋቂ ቡድን መስራት ይችል ነበር ነገር ግን ያን አላደረገም ፡፡ ከክርስቶስ ይልቅ ፓስተርን ወይም ግለሰብን ማስተዋወቅ ቀላል ነው ነገር ግን ይህ የእኛ አይደለም - ይህ የአዳኛችን የክርስቶስ ተግባር ነው ፡፡ በምስክርነታችን ዉስጥ ኢየሱስን በምናስተዋዉቅ ጊዜ የእግዚአብሄር ብርኃን መብራት ይጀምራል (ቁጥር 6) ፡፡
2-ቆሮንቶስ (4፡ 7-12)፡ ለዚህ መፅሀፍ በሜንዲ በሚያስደንቅ ስዕል በተሰበረው መተላለፊያ ከሸክላ እንስራ ስንጥቅ ጀርባ ብርሃኑ ያበራል ፡፡ አብዛኛዉን ጊዜ በእንስራዉ ላይ እንመለከታለን - ማየት የምንችለዉን ብቻ ፡፡ ጥቂት በጣም አሪፍ የሆኑ የሸክላ እንስራዎችን በመስራት ማየት የምንችለዉ ላይ እናተኩር ፤ ፍፁም፣ ለስላሳ እና የሚያስደንቅ መሆናቸዉን እርግጠኞች መሆን አለብን ይሁን እንጂ ይህ በእንስራዎቹ ዉስጥ ካለዉ ነገር ዉጪ ምንም ነገር የለም ማለት ነው ፤ ጳዉሎስ በእንስራዎቹ ዉስጥ ስላለዉ ነገር ማተኮር እንዳለብን ያብራራል ፡፡ የሸክላ እንስራ ረጅም ጊዜ አይቆይም ምክንያቱም ከድንጋይ ወይም ከአርማታ ስላልተሰራ ፤ በጥቂት ጊዜ ይሰበራል ፡፡ ጥቅም/ዋጋ ያለዉ እንስራዉ አይደለም - ዋጋ ያለዉ የያዘዉ ነገር ነው ፤ ይህ በሸክላ እንስራ ዉስጥ ያለዉ ዋጋ ያለዉ ያ ነው ፡፡ በዉጨኛዉ ላይ ያለዉን በዉስጠኛዉ ላይ ካለዉ ጋር በቅርፅ፣ በመልክ እና በማንኛዉም መንገድ አይወዳደርም ፡፡
እግዚአብሄር ኢየሱስን ለጥቅል ለማድረግ አላስፈለገውም ፤ ጳዉሎስ ማንኛችንም ምርጥ የሚባል ፓኬጅ የለንም አለ ፡፡ ይህ ሁሉም ነገር “ ህይወት የሚሰጠዉ መንፈስ “ አካል ነው (ዮሐ 6፡ 63) “ ያ ህይወት የሰዉ ሁሉ መብራት ነው “ (ዮሐ 1፡ 4) ፤ ያ ህይወት በዉስጥ ስለሆነ በምነጎዳ ጊዜ - በማንኛዉም ምክንያት - ከዉስጥ ብርሃኑ ይበራል (ቁጥር 7) ፡፡ እንስራዉ /የሸክላ እቃዉ በኃይል ጫና የበዛበት እና የተጨነቀ ሊሆን ይችላል ነገር ግን አይሰበርም ፡፡ ግራ እንጋባለን እንጂ ተስፋ አንቆርጥም (ቁጥር 8) ፤ የሸክላ እቃዉ/እንስራው ይሰደዳል ነገር ግን በዉስጥ ያለዉ መዝገብ ብቻህን አይደለህም ይለዋል (ቁጥር 9) ፡፡
አብዛኛዉን ጊዜ በምድራዊ ስጋችን - በሸክላ እቃችን ዉስጥ - በምንሳደድ ጊዜ እግዚአብሄር ምንም ትኩረት እንዳልሰጠን እናስባለን ፡፡ ጳዉሎስ አንባቢዎቹ በእነርሱ ዉስጥ ካለዉ መዝገብ የተነሳ ብቻቸዉን እንዳልነበሩ እንዲያስተዉሉ ፈለገ ፡፡ ብንጣልም እንኳን አንጠፋም (ቁጥር 9) ፡፡ ኢዮብን ባጠናን ጊዜ “ ይህ ቁርበቴም ከጠፋ በኋላም እግዚአብሄርን አየዋለሁ “ (ኢዮ 19፡ 26) ያለዉን አይተናል ፡፡ በጌዲዎን ታሪክ ዉስጥ መብራት ወደፊት እንዲበራ በማድረግ ለእግዚአብሄር ህዝብ ድልን የሚያመጣ የተሰባበሩ መተላለፊያዎች ነበሩ (መሳ 7፡ 20) ፡፡ ጳዉሎስ አጥብቆ የተናገረው በዚህ አካል ላይ በዉጨኛዉ ያለዉ ይህን አያደርግም የሚለዉን ነው ፤ ነገር ግን በዉስጥ ያለዉ የከበረ እና የሚያስደንቀዉ - መዝገቡ ነው ፡፡ እንስራችሁ በዉስጥ የክርስቶስ መብራት ከሌለዉ ባዶ እንደሆነ ተረዱ ፡፡
2-ቆሮንቶስ (4፡ 13-18)፡ ኢየሱስ በትንሳኤዉ ሞትን አሸነፈው ፡፡ ጳዉሎስ ይህን ስለሚያምን “ ጌታን ኢየሱስን ያስነሳው እኛን ደግሞ ከኢየሱስ ጋር እንዲያስነሳን ከእናንተም ጋር እንዲያቀርበን እናውቃለን “ (ቁጥር 14) ለማለት ቻለ ፡፡ ይህ በዉስጥ ያለዉ መዝገብ ጳዉሎስን በእግዚአብሄር ክብር እርግጠኛ እንዲሆን አደረገው ፤ በተጨማሪም ጳውሎስ እነዚህ መከራዎች ለእርሱ እየሰሩ የነበሩ እንጂ በእርሱ ላይ የሚሰሩ እንዳልነበሩ እርግጠኛ ነበር ፡፡ ያለፈበት ሁሉም ነገር በኃይለኛዉ አስፈላጊ ነበር ፤ ስለሆነም ዉጨኛዉ ሰዉነቱ የተጎዳ/የተጎሳቆለ ቢሆንም እንኳን ተስፋ አልቆረጠም ፡፡ ጳዉሎስ ዉስጠኛዉ ሰዉ ሁል ጊዜ የታደሰ እንደሚሆን ያውቅ ነበር (ቁጥር 16) ፡፡
አዎ ህይወት አስቸጋሪ ነው ነገር ግን በዚህ መካከል ላይ አይናችሁን፣ ልባችሁን፣ ነፍሳችሁን እና ሀሳባችሁን በማይታየዉ ላይ በማድረግ አትኩሩ (ቁጥር 18) ፡፡ ዋይርስቤ እዚህ ንፅፅሩን አመልክቷል፡ ቀላል የሆነዉ መከራን ከክብሩ ክብደት ጋር፣ ጊዜያዊዉን ከዘላለማዊዉ ጋር፣ የጠፋዉን እለት እለት ከሚታደሰዉ ጋር ፡፡ በዚህ ህይወት ቀላል የሆነ መቅሰፍ አለን - ይህ ህይወት አስቸጋሪ ነው - ከክብሩ መጠን/ክብደት ጋር ሲወዳደር ምንም አደል የክብሩ ደስታ ይጨምራል ምክንያቱም ይህ የሚያልፍ ነዉ ያ ደግሞ ዘላለማዊ ነው ፡፡ ጳዉሎስ በአንድ ተጨማሪ ነገር እርግጠኛ ነበር፣ የማይታየዉ አለም እዉነት እንደ ሆነ እርግጠኛ ነበር ፤ በሚታየዉ ላይ ከማተኮር ይልቅ ጳዉሎስ በማይታየዉ ላይ አተኮረ (ቁጥር 18) ፡፡ የሚታየዉ ይህ የተሰበረዉ የሸክላ እቃ ሰዉነት ሲሆን - ጊዜያዊም ነው ፤ የማይታየዉ ደግሞ በዉስጥ ያለዉ ብርኃን ዘላለማዊ ነው ፤ እምነትን ይወስዳል ፡፡ ዋይርስቤ “ የዚህ አለም ነገር ስለምናየዉ እና ስለምንዳስሰው በጣም እዉነት ይመስላል ነገር ግን ሁሉም ጊዜያዊና መጨረሻቸዉ ማለፍ የሆኑ ናቸው ፤ የመንፈሳዊ ህይወት ዘላለማዊ ነገር ብቻ ለዘላለም ይቆያል “ አለ ፡፡
መደምደሚያ
በምዕራፍ 5 ይህ ሁሉ እንዴት እንደሚተገብር እናያለን ፡፡ ወፈፌ ብላችሁ ጥሩኝ በዚህ ከጳዉሎስ ጋር እቀላቀላለሁ ፡፡ በዉስጤ ባለዉ ክርስቶስ ምክንያት ይህ ምስጋና ነው ፡፡
Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1989), p. 512.
Wiersbe, p. 513.
Wiersbe, p. 513.
Wiersbe, p. 513.
Wiersbe, p. 514.
Wiersbe, p. 514.
Wiersbe, p. 515.
Wiersbe, p. 515.
ጥያቄዎች
-
በ 2ቆሮ (4፡ 1) ጳዉሎስ ምን አይነት አገልግሎት አለን አለ ? (2ቆሮ 3፡ 4-18)
-
እንደ ወንጌል የክርስትና ህይወት እንዴት መኖር እንዳለበት ጳዉሎስ እንዴት ገለፀ ? ራሳችሁን የእግዚአብሄርን ቃል ከመቀላቀል ራሳችሁንእንዴት መጠበቅ ትችላላችሁ ?
-
አንዳንድ ሰዎች የወንጌልን ብርሃን ለምን ይቀላቅሉታል ? “ የዚህ ዘመን አማልዕክት “ ማነው ? (ዮሐ 12፡ 31, 14፡ 30, 16፡ 11)
-
በ 2ቆሮ (4፡ 8-12) ጳዉሎስ በአገልግሎቱ ታግሶባቸዉ የነበሩትን ነገሮች ገለፀ ፤ ከባድ መከራ በመንገዳችሁ በሚመጣ ጊዜ በጌታ ይህ ልበ ሙሉነት ይኖራችኋል ?
-
ጳዉሎስ ምንም እንኳን በአንዳንድ አስቸጋሪ ነገሮች ዉስጥ ቢያልፍም አማኞች ምን ማድረግ የለባቸዉም አለ ? ትኩረታቸዉን ምን ላይ ማድረግ አለባቸው ? በማይታዩ ነገሮች ላይ እንዴት ትኩረት እናደርጋለን ? (2ቆሮ 5፡ 7, ዕብ 11፡ 27)
-
በ 2ቆሮንቶስ 4 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 2 Corinthians 4:16
“Therefore, we do not give up! Even though our outer person is being destroyed, our inner person is being renewed day by day.”
ጳውሎስ የቆሮንቶስ ቤተክርስቲያን ሰዎችን ተስፋ እንዳይቆርጡ ያበረታቸዋል ፡፡ ጳውሎስ እነርሱ ባይወድቁም እንኳ ከውጭ በሁሉም መንገድ ተገፍተው እንደነበር ተረድቷል ፡፡ ግራ ተጋብተው ፣ ተሰደው እናም ተጠቅተውም ነበር ፡፡ ነገር ግን ተስፋ አልቆረጡም ፣ አልተበተኑም ደግሞም አልጠፉም ፡፡ አዎን ከውጪ የሚገጥማቸው ጊዜያዊ መከራ የሚያጠፋ ቢሆንም ነገር ግን ጌታ ያየው በውስጥ የነበረውን የማይታየውን የመንፈስ ቅዱስ ስራ ነበር ፡፡ እግዚአብሔር በፍጹም ሊወዳደር የማይችል ዘላለማዊ ክብርን እያስገኘ ነበር ፡፡
ምናልባት ዛሬ ተስፋ መቁረጥ ተሰምቷችሁ ይሆናል ፡፡ ዕዳ ተጭኗችሁ ፣ የጤና ሁኔታችሁ የማያገግም መስሏችሁ ፣ በትዳራችሁ ጥፋት ተጋርጦባችሁ ወይም አንገታችሁን ከአልጋችሁ ቀና ማድረግ እንዳትፈልጉ የሚያደርግ ብስጭትና ኀዘን ተሰምቷችሁ ፡፡ ተስፋ እንዳትቆርጡ ጓደኞቼ ፡፡ ጽኑ ፡፡ ቀጥሉ ፡፡ ተነሱ ፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጣችሁ በስራ ላይ ነው ፡፡ መጠቀሚያዎቹ ናችሁ ፡፡ አዎን ድክመት አለባችሁ ፣ ስህተት ደግሞም መከራ ነገር ግን ይህን መንገድ በማረና በተዋበ መልኩ ተወጥታችሁታል ! እነዚህ ድክመቶች የእግዚአብሔርን ኃይል ፣ ብርታትና ጥንካሬ በእናንተ ለሌሎች እንድያበራ የስችሉታል ፡፡ በክርስቶስ ላይ ባላችሁ ተስፋ ጽኑ ፡፡ የእግዚአብሔር ኃይል በእናንተ ውስጥ በስራ ላይ ነው ! ተስፋ እንዳትቆርጡ ! ታልፉታላችሁ !
" እንግዲህ እኔን የምትመስሉ ሁኑ ብዬ እለምናችኋለሁ።"
-1ኛ ቆሮንቶስ 4:16
ተጨማሪ ጥቅስ
- 1ኛ ቆሮንቶስ 4:7-9 -“ አንተ እንድትበልጥ ማን አድርጎሃል? ያልተቀበልኸውስ ምን አለህ? የተቀበልህ ከሆንህ ግን እንዳልተቀበልህ የምትመካ ስለ ምንድር ነው? አሁን ጠግባችኋል፤ አሁንስ ባለ ጠጎች ሆናችኋል፤ ያለ እኛ ነግሣችኋል፤ እኛ ደግሞ ከእናንተ ጋር እንድንነግሥ ብትነግሡ መልካም ይሆን ነበር። ለዓለም ለመላእክትም ለሰዎችም መጫወቻ ሆነናልና፤ እግዚአብሔር እኛን ሐዋርያቱን ሞት እንደ ተፈረደባቸው ሰዎች ከሁሉ ይልቅ የኋለኞች እንዳደረገን ይመስለኛልና።
- 1ኛ ቆሮንቶስ 4:17-18 –“ ስለዚህ የምወደውንና የታመነውን በጌታ ልጄ የሆነውን ጢሞቴዎስን ልኬላችኋለሁ፥ እኔም በየስፍራው በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እንደማስተምር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚሆነውን መንገዴን እርሱ ያሳስባችኋል። አንዳንዱ ግን ወደ እናንተ የማልመጣ እየመሰላቸው የታበዩ አሉ :: "
- ገላትያ 6:9-" ባንዝልም በጊዜው እናጭዳለንና መልካም ሥራን ለመሥራት አንታክት። "
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።