Paul's Ministry
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Treasure 2 Corinthians 3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የ 2ቆሮንቶስ የመጀመሪያዎቹ ሰባት ምዕራፎች እንደ ሐዋሪያ በቆሮንቶስ ወደ ቤተ ክርስቲያን ማፍሰስ/ማስተማርን የጳዉሎስን ሚና/ተግባር በመግለጥ ያረጋግጣሉ ፡፡ በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ችግሮች እያሉ ቢሆንም አሁንም ጳዉሎስ በእነርሱ ቤተሰብ በልጁ እንደሚያምነዉ ያምናል ፡፡
ትምህርት
2-ቆሮንቶስ (3፡ 1-3)፡ ጳዉሎስ ቆሮንቶሳዊያን አገልግሎቱን ለማረጋገጥ ከሌላ ቤተ ክርስቲያን ወይም ግለሰብ የማረጋገጫ ደብዳቤ ያስፈልጋቸዉ እንደሆን ጠየቃቸው ፡፡ ቆሮንቶሳዊያን በራሳቸው የጳዉሎስ የማረጋገጫ ደብዳቤዎች ነበሩ ፡፡ ወደ ሌሎች ሐዋሪያቶች ተመልሰዉ ስለነበር በባህል ተግባራት ተወሰዱ ምክንያቱም ጳዉሎስ የሰጣቸዉን ትዕዛዝ ስላልወደዱ ፡፡ የጳዉሎስ አገልግሎት ማረጋገጫ በሚያዉቃቸዉ ነገሮች አልነበረም ፤ ልክ በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን በሰዎች ላይ አምጥቶት በነበረዉ አይነት ተፅዕኖ ነበር ፡፡
ለ 2ቆሮንቶስ ቃላችን መዝገብ ነው ፡፡ በእነርሱ ባለዉ መዝገብ ምክንያት የቆሮንቶሳዊያን ቤተ ክርስቲያ ክርስቶስን ታንፀባርቅ ነበር ፤ ለአለም የክርስቶስ መልዕክት ነበሩ ፡፡ ወደ እነርሱ ዉስጥ ስለ ተጠያቂነት እና መንፈሳዊ እድገት የሚያስተምር ሰዉ አስፈልጓቸዋል ፤ ቆሮንቶስ በእዉቀት ሳይሆን በመንፈስ የተፃፈ ልዕክት ነበር “ ፊተኛው ሰዉ አዳም ሕያው ነፍስ ሆነ ተብሎ ተጽፎአል ፤ ኋለኛዉ አዳም ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ “ (1ቆሮ 15፡ 45) ፡፡ ቆሮንቶሳዊያን በእግዚአብሄር መንፈስ ህይወት የተሰጣቸዉ እንጂ በድንጋይ ፅላት ላይ በተፃፈ ማንኛዉም ዉጫዊ ኮድ አልነበረም ፡፡
2-ቆሮንቶስ (3፡ 4-6)፡ ጳዉሎስ ቆሮንቶሳዊያን የእርሱ አገልግሎት ማረጋገጫዎች እንደ ነበሩ ሲገልፅ ብስጩ አልነበረም ፤ ይልቁንም ሙሉነቱን በክርስቶስ አግኝቶ ነበር ፡፡ ጳዉሎስ በአገልግሎቱ ብቁነቱ ከእግዚአብሄር የመጣ እንደ ሆነ እዉቅና ሰጠ ፤ እግዚአብሄር ህይወት የሚሰጠዉ የአዲሱ የመንፈስ ኪዳን አገልጋይ አደረገው ፡፡
ሁለተኛ ቆሮንቶስ ከክርስቶስ ሞት በኋላ ከ70 በፊት አካባቢ የተፃፈ ነበር ፤ ሁለተኛ ቆሮንቶስ ከክርስቶስ ሞት በኋል ከ70 በፊት የተፃፈ ከነበር ቤተ መቅደሱ በሰዓቱ ነበር ማለት ነው ፡፡ ቆሮንቶሳዊያን በኢየሱስ የእምነትን አለም ከሙሴ ህግ ጋር ለመቀላቀል የታገሉ እንደሆኑ ማሰብ ቀላል/የሚቻል ነው ፡፡
ጳዉሎስ ግን ጳዉሎስ ህይወትን እንደሚሰጥ የተከራከረበት የአዲሱ ኪዳን አገልጋይ ነበር ፤ በተቃራኒው ፅኁፉ(ህጉ) ገድሏል፡ “ እንግድህ ሕግ የእግዚአብሄርን የተስፋ ቃል የሚቃወም ነውን ? አይደለም ፡፡ ሕያዉ ሊያደርግ የሚቻለው ሕግ ተሰጥቶ ቢሆንስ በእዉነት ጽድቅ ከሕግ በሆነ ነበር (ገላ 3፡ 21) ፤ በአጭሩ ህጉ ህይወት ሊሰጥ አይችልም መንፈስ ግን ይችላል ፡፡
- “ የእስራኤልን ቤትና የይሁዳን ቤት በሰዉ ዘርና በእንስሳ ዘር የምንዘራበት ዘመን እነሆ ይመጣል ይላል እግዚአብሄር ፡፡ እንዲህም ይሆናል ፤ አፈርሳቸዉና ክፉ አደርግባቸዉ ዘንድ እንደ ተጋሁባቸው እንዲሁ እሰራቸዉና እተክላቸዉ ዘንድ እተጋለሁ ይላል እግዚአብሄር ፡፡ በዚያ ዘመን ሰዉ ዳግመኛ እንዲህ አይልም አባቶች ጨርቋ የወይን ፍሬ በሉ የልጆችም ጥርሶች ጠረሱ ፤ ነገር ግን ሰዉ ሁሉ በገዛ በደሉ ይሞታል ፤ መራራዉን የወይን ፍሬ የሚበላ ሁሉ ጥርሶቹ ይጠርሳሉ ፡፡ እነሆ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የምገባበት ወራት ይመጣል ይላል እግዚአብሄር ከግብፅ አገር አወጣቸዉ ዘንድ እጃቸዉን በያዝሁበት ቀን ከአባቶቻቸዉ ጋር እንደ ገባሁት ያለ ቃል ኪዳን አይደለም ፤ እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑምና እኔም ቸል አልኋቸው ይላል እግዚአብሄር ፡፡ ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና ይላል እግዚአብሄር ፤ ሕጌን በልቡናቸዉ አኖራለሁ በልባቸዉም እጽፈዋለሁ ፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል ፡፡ እያንዳንዱ ሰው ባልንጀራውን እያንዳንዱም ወንድሙን እግዚአብሄርን እወቅ ብሎ አያስተምርም ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያዉቁኛልና ይላል እግዚአብሄር ፡፡ በደላቸዉን እምራቸዋለሁና ኃጢዓታቸዉንም ከእንግዲህ ወዲህ አላስብምና “ (ኤር 31፡ 27-34) ፡፡
ጳዉሎስ ቆሮንቶሳዊያንን አሮጌዉን ከአዲሱ ጋር እንዳይቀለቅሉ አዘዛቸው ፡፡
2-ቆሮንቶስ (3፡ 7-11)፡ ህጉ “ እንደ ሞት አገልግሎት “ የሆነ ቢሆንም እንኳን ጳዉሎስ አሁንም በክብር እንደ መጣ ተናገረ ፡፡ የሙሴ ፊት ህጉን በተቀበለ ጊዜ በእግዚአብሄር ክብር አበራ/አንፀባረቀ ፤ ይሁን እንጂ ሙሴ እዉነቱን ለመደበቅ ፊቱን ሸፈነ የእግዚአብሄር ክብርም ከጥቂት ጊዜ በኋላ ከፊቱ ላይ ደበዘዘ ፡፡ ዋይርስቤ የህጉን ስድስት እጥረቶች ፅፏል፡
ህጉ የጠፉትን ኃጢዓተኞች ማዳን/ማፅደቅ አይችልም - “ ነገር ግን ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንዲጸድቅ እንጂ በሕግ ስራ እንዳይሆን አዉቀን “ (ገላ 2፡ 16) ፡፡
ህጉ ኃጢዓተኞችን ጽድቅን መስጠት አይችልም - “ የእግዚአብሄርን ጸጋ አልጥልም ፤ ጽድቅስ በሕግ በኩል ከሆነ እንኪያስ ክርስቶስ በከንቱ ሞተ “ (ገላ 2፡ 21) ፡፡
ህጉ መንፈስ ቅዱስን መስጠት አይችልም - “ ይህን ብቻ ከእናንተ እንድማር እወዳለሁ ፤ በሕግ ስራ ወይም ከእምነት ጋር በሆነ መስማት መንፈስን ትቀበላላችሁን (ገላ 3፡ 2) ? “
ህጉ ርስትን/ዉርስን መስጠት አይችልም - “ ርስት በሕግ ቢሆንስ እንግዲያስ በተስፋ ቃል አይሆንም ፤ በተስፋ ቃል ግንእግዚአብሄር ለአብርሃም ሰጥቶአል “ (ገላ 3፡ 18) ፡፡
ህጉ ህይወት መስጠት አይችልም - “ እንግዲህ ሕግ የእግዚአብሄርን የተስፋ ቃል የሚቃወም ነዉን ? አይደለም ፡፡ ሕያዉ ሊያደርግ የሚቻለው ሕግ ተሰጥቶ ቢሆንስ በእዉነት ጽድቅ ከሕግ በሆነ ነበር “ (ገላ 3፡ 18) ፡፡
ህጉ ነፃነትን መስጠት አይችልም - “ ነገር ግን በዚያን ጊዜ እግዚአብሄርን ሳታውቁ በባሕሪያቸው አማልክት ለማይሆኑ ባሪያዎች ሆናችሁ ተገዛችሁ ፤ አሁን ግን እግዚአብሄርን ስታዉቁ ይልቅስ በእግዚአብሄር ስትታወቁ እንደ ገና ወደ ደካማ ወደሚናቅም ወደ መጀመሪያ ትምህርት እንዴት ትመለሳላችሁ ? እንደ ገና ባሪያዎች ሆናችሁ ዳግመኛ ለዚያ ልትገዙ ትወዳላችሁን ? ቀንንና ወርን ዘመንንም ዓመትንም በጥንቃቄ ትጠብቃላችሁ “ (ገላ 4፡ 8-10) ፡፡
የአዲሱ ኪዳን ክብር ከአሮጌዉ በጣም ይበልጣል ፡፡
2-ቆሮንቶስ (3፡ 12-18)፡ በህጉ ስር የነበሩ ህጉን ሲያነቡ በፊታቸዉ መጋረጃዉ እንደ ነበር ያነባሉ ፤ መረዳታቸዉም በመጨለሙ በክርስቶስ በማመን ብቻ ሊወገድ የሚችል ነው ፡፡ ጳዉሎስ እነዚህን ሀሳቦች በአገሩ ሰዎ ልቡ የተሰበረ ሰዉን በማድረግ “ ብዙ ኃዘን የማያቋርጥም ጭንቀት በልቤ አለብኝ ስል በክርስቶስ ሆኜ እዉነትን እናገራለሁ ፤ አልዋሽም ሕሊናዬም በመንፈስ ቅዱስ ይመሰክርልኛል ፡፡ በስጋ ዘመዶቼ ስለሆኑ ስለ ወንድሞቼ ከክርስቶስ ተለይቼ እኔ ራሴ የተረገምሁ እንድሆን እጸልይ ነበር “ (ሮሜ 9፡ 1-3) ፡፡ ጳዉሎስ ህጉ ሞትን እንዳመጣ ብዙ እዉነታዎችን በተሸለ ተረድቷል ፤ በካስማዉ ላይ ምን እንደ ነበር ያውቃል እንዲሁም የአይሁድ እህቶቹና ወንድሞቹ በኢየሱስ ወደ ማመን ሲመጡ ለማየት ማንኛዉንም ያክል ርቀት ለመሄድ ፍቃኛ ነበር ፡፡
ጳዉሎስ ምዕራፉን አማኞች በመንፈስ ቅዱስ በኩል የእግዚአብሄርን መገኘት ማግኘት ይችሉ እንደ ነበር በማመልከት አጠቃለለው ፡፡ ሙሴ የእግዚአብሄርን መገኘት ለማግኘት ወደ ተራራው መዉጣት ነበረበት ነገር ግን የክርስቶስ ተከታዮች የእግዚአብሄርን መገኘት የትኛዉም ስፍራ እና በማንኛዉም ጊዜ ማግኘት ይችላሉ ፡፡ ጳዉሎስ የጠቀሰው “ መስታወት “ የእግዚአብሄር ቃል ነበር ፡፡ እንደ አማኝ ወደ እግዚአብሄር ቃል ስንመለከት በዉስጣችን በሚኖረው በክርስቶስ ወደ እግዚአብሄር መልክ ተቀይረናል ፡፡
መደምደሚያ
የአሮጌዉ ኪዳን ዉጤት ሞት እና የኃጢዓት ባርያ መሆን ነበር ፡፡ የአዲሱ ኪዳን ዉጤት ህይወት እና በክርስቶስ ነፃነት ነው ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1614.
Warren Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: New Testament (Nashville, David C Cook, 2007) p. 510.
Wiersbe, p. 510.
Wiersbe, p. 511.
ጥያቄዎች
-
የአዋቂዎች/የአይሁድ አዋቂዎች ትምክት ስለ ምን ነበር ? ጳዉሎስን በምን ከሰሱት ? ጳዉሎስ የአገልግሎቱን እዉነተኝለት ለማረጋገጥ ምን አለ ? (ኤር 31፡ 33, 32፡ 38-39, ሕዝ 11፡ 19, 36፡ 26-27)
-
ጳዉሎስ በጣም የተማረ እና ጎበዝ የነበረ ሰዉ ስለ ነበር ለምን በራሱ ችሎታ አልተደገፈም (ሐዋ 22፡ 3) ? ከእግዚአብሄር ከመጣዉ ብቃት ይበልጥ የተደገፋችሁበት ነገር አለ ?
-
በ 2ቆሮንቶስ 3የተጠቀሱት አረቱ የመንፈስ ቅዱስ ባህሪያት ምንድን ናቸው ? ጳዉሎስ የጌታን መንፈስ ሲጠቅስ ምን ገለፀ ?
-
አንድ ሰባኪ ጉባኤዉን በህግ ደንብ እና አስተዳደር ስር በሚያደርግ ጊዜ ምን ይፈጠራል ? በክርስቲያኖች መካከል ጤናማ ያልሆነ ፉክክር ሲኖር ምን ይፈጠራል ? ህይወት መለወጥ ይሚችልበት እና ነፃነት ሊኖረዉ የሚችልበት ብቸኛዉ መንገድ ምንድን ነው ?
-
2ቆሮ (3፡ 7-11) እና ዘጸ (34፡ 29-35) አወዳድሩ ፤ አዲሱ የፀጋ ኪዳን ከአሮጌዉ ኪዳን በጣም ርቆ የሚበልጠዉ ለምንድን ነው ? (ገላ 2፡ 16, 21, 3፡ 2, 18, 21, 4፡ 8-10)
-
በ 2ቆሮንቶስ 3 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 2 Corinthians 3:15–17
“Even to this day, whenever Moses is read, a veil lies over their hearts, but whenever a person turns to the Lord, the veil is removed. Now the Lord is the Spirit, and where the Spirit of the Lord is, there is freedom.”
ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ቤተክርስቲያን የመንፈስን አገልግሎት ከህግ በታች ከመኖር ጋር እያወዳደረ ያብራራላቸዋል ፡፡ ጳውሎስ የአይሁድ ህዝብን ከእውነቱና በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከሚገኘው ነጻነት መጋረጃ ልባቸው እንደሸፈነ ይገልጻል ፡፡ ነገር ግን በእምነት እግዚአብሔር በማንኛውም ሰው ልብ ላይ ያለውን መጋረጃ ማንሳት ይችላል ፡፡ እናም እርሱ ሲያነሳው ነጻነት ይገኛል ፡፡ ኢየሱስ የመጣው በአድስ የጸጋና የፍቅር ኪዳን ነው ፡፡ የጌታ መንፈስ ነጻነትን ይሰጣል ፡፡
በጌታ ስላለህ ነጻነት አስበህ ታውቃላህ ? ወይስ ራስህን ለመቆም ሲታገል ፣ ጥሩ ለመስራት ሲሞክርና በራሱ ብቃትን ለማግኘት ሲሞክር ነው የምታገኘው ? እውነቱ ለእግዚአብሔር ብዙ መስራት አይጠበቅብህም ፡፡ ብቃትህ ከእርሱ የተገኘ ነው ፡፡ እርሱ የመጣው ነጻ ሊያወጣህ ነው ፡፡ እስኪ አስብ ፡- የአምስት አመት ህጻን ልጅ ዙሪያውን በታጠራ ቦታ ውስጥ ሲሮጥ ፡፡ በመጫወቻ ቦታው ዙሪያ ያለው አጥር ህጻኑን ከጉዳት ይጠብቀዋል ፡፡ ነገር ግን በአጥሩ ውስጥ ልጁ በነጻነትና በደስታ መሮጥ ፣ መጫወት እናም መሽከርከር ይችላል ፡፡ ዛሬም ለእንተ ተመሳሳይ ስዕል ነው ፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ በክርስቶስ በተሰጠህ ነጻነት ውስጥ ተሸከርከር ፡፡ ትግሉን አቁም እግዚአብሔር ያገኘኽ ልክ እንዲሁ እንዳለህ እንደሆነ እወቅ ፡፡ እርሱ ለአንተ ስላለው ፍቅርና በእግዚአብሔር መንፈስ ውስጥ ስላለህ ነጻነት እርግጠኛ ሁን ፡፡
“ ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ የሙሴ መጸሐፍት በተነበቡ ጊዜ ሁሉ ያ መጋረጃ በልባቸው ይኖራል ፤ ወደ ጌታ ግን ዘወር ባለ ጊዜ ሁሉ መጋረጃው ይወሰዳል ፡፡ ጌታ ግን መንፈስ ነው ፤ የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ ፡፡ “
- 2ኛ ቆሮንቶስ 3፡15-17
ተጨማሪ ጥቅስ
ዮሐንስ 8፡36 –“ እንግዲህ ልጁ አርነት ቢያወጣችሁ በእውነት አርነት ትወጣላችሁ ፡፡ “
ሐዋርያት ሥራ 13:38–39 — “ እንግዲህ ወንድሞች ሆይ ፣ በእርሱ በኩል የኃጢአት ስርየት እንዲነገርላችሁ ፣ በሙሴም ህግ ትጸድቁበት ዘንድ ከማይቻላችሁ ሁሉ ያመነ ሁሉ በእርሱ እንዲጸድቅ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን ፡፡ “
2ኛ ቆሮንቶስ 3:4–6a — “ በክርስቶስም በኩል ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ያለ እምነት አለን ፡፡ ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ ፣ በገዛ እንደሚሆን አንዳችን እንኳ ልናስብ ራሳችን የበቃን አደለንም ፤ እርሱም ደግሞ በመንፈስ እንጂ በፊደል ለማይሆን ለአዲስ ኪዳን አገልጋዮች እንሆን ዘንድ አበቃን ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።