The Need For Accountability In The Church
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Treasure 2 Corinthians 2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ቤተ ክርስቲያን በምዕራብ በተለይም በአሜሪካ ለ 1 እና 2 ቆሮንቶስ የተለዬ ትኩረት ይሰጣሉ ምክንያቱም አሜሪካ ቆሮንቶስ ልትሆን ስለምትችል ፡፡ ለመቀጠል እና ለመወዳደር ከምንሞክርበት ማንኛዉም ስፍራ ተፅዕኖ አለብን ፡፡ የአሜሪካ ቤተ ክርስቲያን ታላቅ ተግዳሮት አለባት ነገር ግን ከተጠያቂነት ጋር የምንታገል እንመስላለን ፡፡ ጳዉሎስ ይህን መልዕክት በፃፈ ጊዜ እርምጃዉን ወደ ፊት ማስቀመጥ ፈለገ ፤ በልቡ ዉስጥ በልቡ ያለዉን መሻት እና ቀንበር ያውቃል ፡፡ ፈተናዉ ያን እንዴት በወረቀት ላይ ላስቀምጠዉ የሚል ነበር ፡፡
ትምህርት
2-ቆሮንቶስ (2፡ 1-2)፡ ጳዉሎስ ደግሞ ወደ ቆሮንቶስ ለእነርሱ ለኃዘን ወይም ለቅሶ ምክንያት በሚሆን በሚያም ጉብኝት አልመጣም አለ ፤ መከራን ሊያመጣባቸዉ አልፈለገም ፡፡ ጳዉሎስ ወደ ቆሮንቶስ የመጣው በእነርሱ ላይ ወደ ጌታ እርማትን ለማምጣት ብቻ እንደ ነበር እንዲያስቡ አልፈለገም ፤ ይልቁንም ቆሮንቶሳዊያን የእርሱ ደስታ እንደ ነበሩ እንዲያዉቁና ከእነርሱ የሚወጣዉን ብርሃን (የክርስቶስን) እንዲያዩ ፈለገ ፡፡ ነገር ግን በነበሩበት መንገድ ወደ ታች ለመቀጠል ከፈቀዱ ጳዉሎስ የመዝገቡ ብርኃን በተሰበረ መተላለፊያ ዉስጥ ከማብራት ይልቅ በእስራ ስባሪ የተሸፈነ እንዳይሆን ፈርቶ ነበር ፡፡
2-ቆሮንቶስ (2፡ 3)፡ ጳዉሎስ በትክክል ለማየት የፈለገው በእምነታቸዉ አፍርተዉ ነበር ነገር ግን ካላስተካከላቸው እንዲሆኑ ተመርጠዉ ወደ ነበሩበት መዝገብ አይሆኑም ፤ አዎ ብዙ ተፅዕኖዎች ወደ ቆሮንቶስ መጥተዋል ነገር ግን ብዙ ተፅዕኖዎችም ከቆሮንቶስ ወጥተዉ ሄደዋል ፡፡ ወንጌል በትክክል ቅርፁ ከነበር ከቆሮንቶስ ወጥቶ ይሄዳል/ይሰራጫል ፤ ነገር ግን ጳዉሎስ ወደ ቆሮንቶስ መጥቶ የነበረዉ ተፅዕኖ እየቀጠለ ያለዉን ወንጌል እያጠፋዉ ስለ ነበር ፈራ ፡፡ ሀሰተኛ መምህራን ወንጌልን ካጣመሙ መዝገባቸዉ ይበላሻል ፡፡
2-ቆሮንቶስ (2፡ 4)፡ ይህ ጥቅስ ለመፃፍ የጳዉሎስን ፍላጎት/መነሳሳት ገልፆታል ፡፡ ለእነርሱ ይህን መልዕክት በመፃፍ ተጨንቋል ፤ ጳዉሎስ ይህንን ከባድ መልዕክት ለእነርሱ ብዙ ፍቅር ስላለዉ ፅፎት እንደ ነበር እንዲያዉቁ ፈለገ ፡፡
2-ቆሮንቶስ (2፡ 5-7)፡ በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ የሖነ ሰዉ ለኃዘን ምክንያት ቢሆንም ያ ጳዉሎስን አይጎዳዉም ምክንያቱም በዚያ ስላልነበር ይሁን እንጂ የመዝገቡን መልዕክት እና የቤተ ክርስቲያንን ምስክርነት ይበክላል ፡፡ በኃይለኛዉ/በደንብ ጳዉሎስ በ 1ቆሮንቶስ 5 በጉባኤዉ መካከል ከሆነው የወሲባዊ ብልሹነት ክስተትን እየጠቀሰ ነበር ፤ ጳዉሎስ እንዲህ አይነቱን “ መንፈሱ እንድትድን ስጋዉ እንዲጠፋ ለሰይጣን እንዲሰጥ “ (1ቆሮ 5፡ 5) ነግሯቸው ነበር ፡፡ ያን አድርገዉ ከነበር ጳዉሎስ አሁን “ ከልክ በላይ በሆነ ኃዘን እንዳይዋጡ “ (ቁጥር 7) ኃጢዓተኞችን እንዲያፅናኑ እና ይቅር እንዲሉ አሳሰባቸው ፡፡
በእሱ/በእሷ ህይወት አማኞችን ስለ ኃጢዓት ማፅናናት በፍፁም ቀላል አይደለም ነገር ግን መዝገቡ የሚከላከል ስለሚሆን መልዕክቱ ያነፃል ፡፡ ስለዚህ ፍፁም የሆነ ንስኃ በምታዩ ጊዜ ይቅርታ ለማለት እና “ ቤታችሁ እንኳን በደህና መጣችሁ “ ለማለት ጊዜዉ ነው ፡፡ እንደ አማኝ ለሌሎች ከእግዚአብሄር ጋር የመጓዝ ፍላጎታችንን በመግለፅ ቃላችን፣ አመለካከታችን እና ድርጊታችን መታረም በሚያስፈልገዉ ጊዜ ተጠያቄዎች አድርገዉ እንዲይዙን እንጋብዛቸው ፡፡ ከሁሉም በኋላ ማንኛችንም ለፈተና/ለምኞት የተጋለጥን ነን ፤ ነገር ግን የልባችን ፍላጎት እግዚአብሄርን ማስደሰት ከሆነ፣ የፍላጎታችን ንፁህነት የእግዚአብሄርን መንገድ ለመከተል ከሆነ እርስ በእርሳችን በተጠያቂነት መያያዝ እንችላለን ፡፡
2-ቆሮንቶስ (2፡ 8-11)፡ መዋጀት ጣፋጭ ስለሆነ የተጋፈጠ አንድ ሰዉ ንስኃ በመግባት እርሱ/እርሷ ተመልሰዉ በመጡ ጊዜ ለእርሱ/ለእርሷ እንደ ገና ፍቅራችሁን አረጋግጡላቸው ፡፡ በመፃፍ የጳዉሎስ የተሰወረ ፍላጎት በሁሉም ነገር ታዛዥ ሆነዉ ማግኘት ነበር (ቁጥር 9) ፤ ጳዉሎስ ይቅር ብለዉት የነበረዉን ሰዉ ጳዉሎስም ይቅር እንደሚለዉ በመናገር ስለ እርሱ እንዲናገሩ ፍቃድ ሰጣቸው (ቁጥር 10) ፡፡ የሰይጣን ታላቁ መሳሪያ ወይም ሴራ የሚከፍለዉ እና የሚቆጣጠረው ዉሸት ሲሆን ግንኙነትን የሚለይ በትዕቢት እና በባለቤትንት የሚመጣ የአንድ ፋሽን ወይም የሌላ ማጭበርበር/መዋሸት ነው ፡፡ የሰይጣን መሳሪያዎች በሌሎች ላይ ለመለየት በጣም ቀላል ናቸዉ ይሁን እንጂ በራሳችን ላይ ለማየት ግን አስቸጋሪ ነው ፡፡ ሰይጣን በቤተ ክርስቲያን መከፋፈል ማምጣት ስለሚፈልግ የወንጌል ዝና የቆሸሸ ነበር እንዲሁም ወንጌል በቆሮንቶስ መሰራጨት/ርቆ መሄድ አልቻለም ፡፡
2-ቆሮንቶስ (2፡ 12-13)፡ ጳዉሎስ ወንጌልን ለመስበክ ወደ ጢሮአድ ሄዶ ነበር ነገር ግን በዚያ ቲቶን ባላገኘዉ ጊዜ ወደ መቄዶንያ ሄደ ፡፡
2-ቆሮንቶስ (2፡ 14-17)፡ ወደ መቄዶንያ መሄዶ መልካም ነገር በመሆን አበቃ ምክንያቱም እግዚአብሄር በዚያ ጳዉሎስን ወንጌልን እንዲሰብክ ስለፈቀደለት ፡፡ ጳዉሎስ አማኞችን “ የክርስቶስ መዓዛ ነንና “ በማለት ቀጠለ (ቁጥር 15) ፤ ወንጌልን ለማይቀበሉት አማኞች “ ለሞት የሚሆን የሞት ሽታ “ ወንጌልን ለሚቀበሉት ደግሞ አማኞች “ ለህይወት የሚሆን የህይወት ሽታ “ (ቁጥር 16) ፤ አማኞች ጳዉሎስን “ ለዚህ ብቁ የሆነ ማነው ? “ ብሎ እንዲጠይቅ የመራውን የእነዚህን የሁለቱንም ምላሽ ይሸከማሉ ፤ ጳዉሎስ በመስመሩ ላይ ዝናዉን በማስቀመጥ እዉነትን እንጂ ሌላ ምንም ነገር እዉነቱን ተናገረ፣ ሁሉንም እዉነት ፡፡ የክርስቶስን እዉነተኛ መልዕክት ተናገረ (ቁጥር 17) ፡፡
መደምደሚያ
እነዚህ የእግዚአብሄር ቃል ሸክም ናቸው ፤ ይህ በአሁኑ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ የፅድቅ መንገድ ነው ፡፡ በአሁኑ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ በእኛ መካከል እና በቤተ ክርስቲያን መሪዎች ዉስጥ እግዚአብሄር የተጠያቂነት በርን እንዲከፍት እፀልያለሁ ፡፡
ጥያቄዎች
-
በ 2ቆሮ (2፡ 4) ጳወሎስ በቆሮንቶስ ለነበረችዉ ቤተ ክርስቲያን የነበረዉን ፍቅር ገለፀ ፤ በቤተ ክርስቲያናችሁ ዉስጥ ላሉ ሰዎች እንደዚያ አይነት ፍቅር ታጋራላችሁ ? አይደለም ከሆነ የቻላችኋቸዉ አንዳንድ ተግባራዊ ድርጊቶች ምንድን ናቸው ?
-
በ 2ቆሮ (2፡ 5-11) ጳዉሎስ የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን አባላትን ለኃዘን ምክንያት የሆነባችሁን ሰው ይቅር እንዲሉ ታዘዋል ፤ ይህን ለምን አደረገ ? ይቅር ባይሉ ለቤተ ክርስቲያን አካል ዉጤቱ ምን ሊሆን ይችላል ? በቤተ ክርስቲያናችሁ ዉስጥ በሌላዉ ህዝብ መካከል ለኃዘን/ለተስፋ መቁረጥ/ለመከፋፈል ምክንያት የሆነ አንድ ቡድን/ግለሰብ አለ ? የለም ከሆነ ዉጤቱ ምን ነበር ?
-
በ 2ቆሮ (2፡ 14) እንደተገለፀው እንደ ክርስቲያን የድል አድራጊነት/የአሸናፊነት ህይወት መኖር ለምን አስቸጋሪ ነው ? (ሮሜ 7፡ 19)
-
በ 2ቆሮንቶስ 2 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 2 Corinthians 2:14–15
“But thanks be to God, who always puts us on display in Christ and through us spreads the aroma of the knowledge of Him in every place. For to God we are the fragrance of Christ among those who are being saved and among those who are perishing.”
ምን ምን እንደምትሸቱ አስባችሁ ታውቃላችሁ ? በአካል አይደለም በመንፈስ እንጂ ? ጳውሎስ የቆሮንቶስ ሰዎችን “ የክርስቶስ መዓዛ “ ብሎ ይጠራቸዋል ፡፡ ልክ የንብረት ክፍሉ ጸሀፊ በክፍሉ ማስቀመጫ ውስጥ የሽቶ ጠርሙስን ለእይታ እንደሚያስቀምጥ ሁሉ እግዚአብሔርም እናንተን በዙሪያችሁ ላለው ዓለም ክርስቶስን ትወክሉ ዘንድ እንደ ልጆች፣ እንደ አምባሳደሮች ፣ ልክ እንደ ቧንቧ አሳቡን ማስተላለፊያዎች ፣ እንደ ራሱ መዓዛዎች አስቀምጧችኋል ፡፡ ዛሬ መዓዛችሁ ምን ምን ይሆን የሚሸተው ? በክርስቶስ ስትኖሩ ፣ ሽታችሁ እንደ አንድነት ፣ ህይወት ፣ ይቅርታ ፣ ፍቅር ፣ ሰላም ወይም መጽናናት ሊሸት ይችላል ፡፡ ከጌታ ጋር ስትራመዱ በጣም ብዙ ድርብ ድሎች ይገኛሉ !
አስተውሉ ፣ ሰይጣን የሚመጣው የክርስቶስን አሳብ ሊገድል ፣ ሊዘርፍና ሊያጠፋ ነው ፡፡ ሰይጣን መዓዛችሁ ሞት ሞት ፣ መለያየት ፣ ይቅር አለመባባል ፣ ሁከት ደግሞም ጭንቀት እንድሸት ያሴራል ፡፡ ስለዚህ ነቅታችሁ ቁሙ ! በጠላት ወጥመድና ሴራ ውስጥ እንዳትወድቁ ፡፡ በውስጣችሁ ያለው የክርስቶስ ፍቅር “ያሸቱት” ዘንድ ለሁሉም ሲገለጥ ፣ በዙሪያችሁ ያሉት ሰዎች ወደ ንጹሁ ፣ ትሁት ወደ ሆነውና ወደ ተከበረው መዓዛችሁ ይቀርባሉ ፡፡
“ ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሳቱ ለሚያዞረን በእኛም በየስፍራው ሁሉ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ አምላክ ምስጋና ይሁን ፤ በሚድኑትና በሚጠፉት ዘንድ ለእግዚአብሔር የክርስቶስ መዓዛ ነንና ፡፡ “
- 2ኛ ቆሮንቶስ 2፡14-15
ተጨማሪ ጥቅስ
ዮሐንስ 10፡10 -“ ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም ፤ እኔ ህይወት እንዲሆንላችው እንዲበዛላቸውም መጣሁ ፡፡ “
2ኛ ቆሮንቶስ 2፡10-11 –“ እናንተ ግን ይቅር የምትሉትን እኔ ደግሞ ይቅር እለዋለሁ ፤ እኔም ይቅር ካልሁ ፣ ይቅር ያልሁትን ስለ እናንተ በክርስቶስ ፊት ይቅር ብዬአለሁ ፡፡ በሰያጣን እንዳንታለል ፤ እርሱን አሳብ አንስተውምና ፡፡ “
ኤፌሶን 5፡1-2 –“ እንግዲህ እንደ ተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትከተሉ ሁኑ ፣ ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መስዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ በፍቅር ተመላለሱ ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።