The Writing Of 2 Corinthians
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Treasure 2 Corinthians 1 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ለ 2ቆሮንቶስ የሜንዲ ስዕል አንድ የተሰበረ የሸክላ እንስራ፣ መንፈስ ቅዱስን የሚወክል ወፍራም ልብስ እና ክርስቶስ በሞተ እና በተነሳ ጊዜ ተነስቶ/ተገፎ ስለ ነበረዉ መጋረጃ ያካትታል ፡፡ በዚህ ብዙ ያለዉን ዘዉድ እና ሳንቲም/ገንዘብ እናገኛል ፡፡ ልክ እንደ 1ቆሮንቶስ 2ቆሮንቶስ የሚረብሽ ቃላት አይደለም ፤ በመፅሀፍ ቅዱስ በአዲስ መፅሀፍ ላይ በዚህ የመጀመሪያ ክፍል በፊት እንዳደረግነው በፀኃፊዉ እና ተፅፎበት ስለ ነበረዉ ጊዜ መነሻነት ብዙ ጊዜን እናሳልፋለን ፡፡ ዛሬ ለጥናታችን ድምፅን/መልዕክትን ለቆሮንቶሳዊያን ስለሚያስቀምጠው “ ስለ ጠፋዉ መልዕክት “ እናወራለን ፡፡ ጳዉሎስ በቆሮንቶስ ካለችዉ ቤተ ክርስቲያን ጋር ንግግሩን ለመቀጠል ምክንያት ነበረው ፡፡ በካርታ ላይ ስንመለከት ቆሮንቶስ ከአቴንስ በጣም ብዙ የማትርቅ እና በአገና እና አድርያተክ በሀር መካከል የምትገኝ እንደ ነበረች እናያለን ፤ ይቺ ከተማ ለማንኛዉም ከንቱ ነገር ቋት ነበረች ፡፡
ጳዉሎስ የዚህ የአዲስ ኪዳን ሁለተኛ መልዕክት ፀሀፊ ነበር ፡፡ ዮሐንስ ማክአርቱር የዚህ መልዕክት በጣም የሚመሳሰለዉን ቀን ይለያል ፡፡ በሐዋ (18፡ 12) ጋልዮስ እንደ አካይያ አገረ ገዢነት የተለዬ ነበር ፤ በቆሮንቶስ የጳዉሎስ ፍርድ በእርሱ ፊት ምናልባትም በአጭሩ ጋልዮስ ገዢ ከሆነ በኋላ ተከናወነ/ተካሄደ ፡፡ በግምት ከክርስቶስ ሞት 52 በኋላ ጳዉሎስ ቆሮንቶስን በመልቀቅ በመርከብ ወደ ቄሳሪያ ተጓዘ (ሐዋ 18፡ 18-22) ስለሆነም ሁለተኛ የአገልግሎት ጉዞዉን ያጠቃልለዋል ፤ ከክርስቶስ ሞት በኋላ በ52 በሰዎስተኛ ጉዞዉ ላይ ለሁለት አመት ከግማሽ ያክል እተቀመጠበት ስፍራ ወደ ኤፌሶን ተመለሰ (ሐዋ 19፡ 8-10) ፡፡ ጳዉሎስ በኤፌሶን እያለ ከክርስቶስ ሞት በኋላ በ55 አካባቢ 1ቆሮንቶስን ፃፈ (1ቆሮ 16፡ 8) ፡፡ ጳዉሎስ ኤፌሶንን ከለቀቀ በኋላ ምናልባትም ከክርስቶስ ሞት በኋላ ከ55 ዘግየት ብሎ ወይም ከክርስቶስ ሞት በኋላ ከ56 ቀደም ብሎ በግምት ቆሮንቶስን ከጎበኘ ከአምስት አመት በኋላ ሁለተኛ ቆሮንቶስ ተፃፈ ፡፡
በጳዉሎስ በሁለተኛዉ የአገልግሎት ጉዞ በቆሮንቶስ ላይ ቤተ ክርስቲያንን ጀምሯል ፤ በዚያ ከተማ 18 ወራትን አሳልፏል ፡፡ ከቆሮንቶስ ከሄደ በኋላ በቆሮንቶስ በአማኞች መካከል ስለ ብልሹ ተግባር፣ ስለ ጣዖት አምልኮ እና ትዕግስት ማጣት ሰማ ፡፡ በ 1ቆሮ (5፡ 9) ጳዉሎስ ምግባረ ብልሹ ከሆኑ ሰዎች እንዳይተባበሩ የሚነግር መልዕክት ፅፎላቻ እንደ ነበር ተናገረ ፤ ብዙ ሰዎች ይህን ለቆሮንቶስ “ የጠፋዉ መልዕክት “ በማለት ይጠሩታል ፤ ይህ የመፀሀፍ ክፍል አልሆነም ፡፡ ጳዉሎስ በኤፌሶን እንደ ነበር በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ስላለ ብዙ ችግሮች ሰማ (1ቆሮ 1፡ 11) ከስነ ምግባር ብልሹነት በተጨማሪ መከፋፈል እና ፍክክርን አካትቷል ፡፡ ቆሮንቶሳዊያን ለጳዉሎስ የመጀመሪያ መልዕክት ነገሮችን ግልፅ እንዲያደርግ በመጠየቅ ምላሽ ሰጥተዉ ነበር (1ቆሮ 7፡ 1) ፤ ቀጥሎም ጳዉሎስ ከቆሮንቶሳዊያን ለሆነዉ መልዕክት 1ቆሮንቶስ ብለን በምናዉቀው መለሰላቸው ፡፡ ይህ የኋላ መረጃ ለ 2ቆሮንቶስ መልዕክቱን ያስቀምጣል ፤ ጳዉሎስ በኤፌሶን ትንሽ መቆየት አስፈልጎት ስለ ነበር በእነርሱ ላይ እንዲያረጋግጥ ጢሞቲዎስን ላከው ፡፡
ጳዉሎስ በቆሮንቶስ ማህበረሰብ ዉስጥ ስለ ሐሰተኛ ሐዋሪያቶች የሚረብሽ ሪፖርትን ሰማ (2ቆሮ 11፡ 13) ፡፡ እነዚህ ሐሰተኛ ሐዋሪያቶች ስለ ጳዉሎስ ባህሪይ በመጠየቅ ከክርስቶስ እና ከጳዉሎስ እንዲመለሱ ሰዎቹን አስተማሯቸው ፡፡ ስለዚህ 2ቆሮንቶስ የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን መጀመሪያ እምነታቸዉን ካስቀመጡበት በጣም አርቆ አርቆ እየወሰዳቸዉ ለነበረው ሪፖርት ምላሽ የተፃፈ ነበር ፤ ጳዉሎስ ወደ ቆሮንቶስ ተመልሶ ለመሄድ በመወሰን ከኤፌሶን ሄደ ፡፡ 2ቆሮ (2፡ 1) ይህንን እንደ “ ሚያሳዝን/እንደሚያም ጉብኝት “ ይጠቅሰዋል ፡፡ ከኤፌሶን ጳዉሎስ ለቆሮንቶስ በቲቶ የላከዉን “ የመከራ መልዕክት “ ተብሎ የተጠራዉን መልዕክት ፅፏል (2ቆሮንቶስ 7) ፡፡ ጳዉሎስ ከለዉጡ በኋላ ኤፌሶንን በመዉጣት (ሐዋሪያት ስራ 19) ከቆሮንቶስ ጉብኝቱ ከቲቶ ለመስማት እርሱን ለመገናኘት ወደ ጢሮስ ሄደ ፡፡ በ 2ቆሮ (7፡ 7) ጳዉሎስ ቆሮንቶሳዊያን በእርሱ ላይ ስለማመፃቸዉ ንስኃ ገብተዉ አገኛቸው ፤ ማክአርቱር ጳዉሎስ 2ቆሮንቶስን ከፍልጲስዮስ ፃፈ አለ ፡፡
በ 2ቆሮንቶስ በመጀመሪያዎቹ ሰባት ምዕራፎች ጳዉሎስ ሐዋሪያነቱን በመከላከል አገልግሎቱን ገለፀ ፤ በምዕራፍ ስምንንት እስከ ዘጠኝ ጳዉሎስ ለኢየሩሳሌም ገንዘብ መሰብሰብ ዝግጅትን እንደ ገና እንዲቀጥሉ አሳሰባቸው ፡፡ በምዕራፍ 10-13 ጳዉሎስ ሰዎችን ከክርስቶስ እየመለሱ የነበሩትን ሀሰተኛ ሐዋሪያትን ገጠማቸው ፡፡
ትምህርት
2-ቆሮንቶስ (1፡ 1-11)፡ ጳዉሎስ ራሱን “ በእግዚአብሄር ፍቃድ “ የክርስቶስ ሐዋሪያ እንደሆነ እና በጌታም ጢሞቲዎስ ወንድሙ እንደሆነ ገለፀ (ቁጥር 1) ፡፡ ጳዉሎስ በቁጥር 2 የተለመደዉን ሰላምታዉን ተከተለ ፡፡ በሁሉም በጳዉሎስ መልዕክት ሰላምታዎቹ የፀሀፊዉን ንግግር የመልዕክቱ ተቀባዮችን እና ሰላምታን አካትቷል ፡፡ በቁጥር 3 ጳዉሎስ “ እግዚአብሄር ለእነርሱ ምን እንደሆነ “ እንዲያስታዉሱ አሳሰባቸው ፤ ይህ ትንሽ ጥቅስ በኑሮአችን አስቸጋሪ ጊዜን ሁላችንም መቋቋም የምንችልበትን መንገድ ያብራራል ፡፡ ከሁሉ መጀመሪያ አምላክ ስለሆነ እግዚአብሄርን ማመስገን ፤ ሁለተኛዉ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት ስለሆነ ማመስገን ፤ ሰዎስተኛ የምህረት አምላክ ስለሆነ እግዚአብሄርን ማመስገን ፤ አራተኛው የመፅናናት ሁሉ አምላክ ስለሆነ ማመስገን ፡፡ ምህረት እግዚአብሄር የሚያሳየዉ ሲሆን መፅናናት ደግሞ የምንቀበለዉ ነው ፡፡ ጳዉሎስ እግዚአብሄርን ያመሰግናል ምክንያቱም በባህሪዉ፣ በአገልግሎቱ እና በነፍሱ ላይ በእነዚህ ጥቃት መካከል ላይ እግዚአብሄር ከእርሱ ጋር ስለሆነ ፡፡
በቁጥር 4-11 ዉስጥ በያዘው በሁሉም ነገር እዚህ ላይ የምናብራራው፡ ለ 2ቆሮንቶስ ቃላችን መዝገብ የሚለዉን ነው፡፡ 2ቆሮ (4፡ 7) በእያንዳንዳችን ዉስጥ መዝገብ አለ ይላል ፤ በእነዚህ መቅሰፍቶች፣ ህመሞች እና መከራዎች ዉስጥ ስናልፍ በእኛ ዉስጥ መዝገቡ ክርስቶስ ስላለ እናልፋለን ፡፡ ያ ጳዉሎስ ሊይዘዉ የቻለዉ ተስፋ ነበር፣ ይህ እንዲሄድ የፈቀደለት የተለዬ/የላቀ ኃይል ነበር ፡፡
መደምደሚያ
በ 2ቆሮንቶስ ዉስጥ ስታነቡ ጳዉሎስ በጊዜዉ የከበደ አይነት ችግር የደረሰበት እንደሆነ ትሰማላችሁ ፤ ነገር ግን በመዝገቡ በክርስቶስ ምክንያት በዚህ ሂደት ዉስጥ ምህረትን፣ ፀጋን እና መፅናናትን ያሳያል ፡፡ ይህ ጳዉሎስ በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ማስተማሩን ለምን እንደቀጠለ የሚገልፅ መነሻ ሀሳብ ነው ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1614.
MacArthur, p. 1614.
MacArthur, p. 1614.
MacArthur, p. 1615..
Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1989), p. 502.
ጥያቄዎች
-
እግዚአብሄር ችግርን እና መከራን ለምን እንደሚፈቅድ ምን ታስባላችሁ ? (ሮሜ 8፡ 16-18, ፊል 3፡ 8, ዕብ 10፡ 32-36)
-
በ 2ቆሮ (1፡ 4) መሰረት እግዚአብሄር በችግራችን በሚሰጠን መፅናኛ ከእርሱ በተቀበልነዉ መፅናናት ሌሎችን ማፅናናት እንችላለን ፤ በጊዜዉ አስቸጋሪ በነበረ ነገር ግን አልፋችሁበት ስለ ነበር ሌሎችን አፅናንታችሁበት በምታዉቁት አልፋችሁ ታውቃላችሁ ?
-
ቆሮንቶሳዊያንን በመድረስ በኤስያ ጳዉሎስ እና ጢሞቲዎስ ያን ያክል ሸክም መታገሳቸዉን ለምን እንዳጋራ ምን ታስባላችሁ ?
-
በ 2ቆሮንቶስ 1 መሰረት እግዚአብሄር በተስፋዉ ላይ ተመልሶ ሊሄድ ይችላል (ዘኁ 23፡ 19, ኤር 4፡ 28) ? ተስፋዉን እዴት እናዉቃለን ? (ዘዳ 6፡ 9, ዕብ 10፡ 16)
-
በ 2ቆሮ (1፡ 23) ጳዉሎስ “ እኔ ግን ልራራላችሁ ስል እንደ ገና ወደ ቆሮንቶስ እንዳልመጣሁ በነፍሴ ላይ እግዚአብሄርን ምስክር እጠራለሁ ? “ ሲል ምን ማለቱ ነው ?
-
በ 2ቆሮንቶስ 1 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 2 Corinthians 1:3
“Praise the God and Father of our Lord Jesus Christ, the Father of mercies and the God of all comfort.”
ስለ መጽናናት ስታስቡ ፣ ምንድን ነው ወደ አምሯችሁ የሚመጣው ? ምናልባት በምቹ ሁኔታ ጥቅልል ብሎ መተኛት ፣ በእሳት ዳር ለስላሳ ብርድ ልብስ ለብሶ መቀመጥ ፣ የምትወዱትን ሻይ ወይም ቡና መጠጣት ፣ ከባድ ቀን ካሳለፋችሁ በኋላ በምትወዱት ሰው መታቀፍ ወይም ከቡችላዎ ጋር መንከባለል ሊሆን ይችላል ፡፡ እነዚህ ሁሉ ጥሩ ናቸው ነገር ግን ሁሉም ዘላቂ ያልሆነ መጽናናትን የሚሰጡ ናቸው ፡፡ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔር የመጽናናት ሁሉ አምላክ እንደሆነ ይነግራቸዋል ፡፡
ስትበሳጩ ወይም ተስፋ ስትቆርጡ ፤ ሲደብራችሁ ወይም ስላጣችሁት ነገር ስታዝኑ ፣ የእግዚአብሔር መገኘት ያጽናናችኋል ፡፡ እግዚአብሔር በዚያ አለላችሁ ደግሞም ፈጽሞ አይተዋችሁም ምክንያቱም እርሱ ስለማይለወጥ ፡፡ ስለዚህ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ ፡፡ ቃሉን አንብቡ ፤ የምስጋና መዝሙርን አድምጡ ፡፡ በጸሎት በእርሱ መገኘት ውስጥ እረፉ ፡፡ እግዚአብሔርን በመፈለግ ከሌሎች ጋር አብራችሁ ጊዜን አሳልፉ ፡፡ ብዙውን ጊዜ የምትጨነቁላቸው የምታዝኑላቸው ሲጎዱ ትጎዳላችሁ ፡፡ እግዚአብሔር እንድያጽናናቸውና ጸልዩ እንድሁም ለህይወታቸው የእርሱን ተስፋ እንድያምኑ እንድቀበሉ ጸልዩላቸው ፡፡ እያንዳንዱ እንድሁም ሁሉም እግዚአብሔር የሰጠው ተስፋ አዎን ነው ፡፡ ማለትም እያንዳንዱ እግዚአብሔር የሰጠው ተስፋ ተፈጽሟል ፡፡ ሁሉም ተስፋ አዎን ነው ፡፡ ይህንን እውነት በማሰብ ፣ በጌታ ተጽናኑ ፡፡ በእርሱ ታማኝነት ላይ ተደግፋችሁ “ አሜን ! “ በሉ ፡፡ ህይወታችሁ እየወደቀ እንደሆነ በሚሰማችሁ ጊዜ እንኳ ሳይቀር እግዚአብሔር ይወዳችኋል ፡፡ ዛሬ እግዚአብሔር ያጽናናችሁ ይርዳችሁም ፡፡
“ የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ ፡፡ “
- 2ኛ ቆሮንቶስ 1፡3
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 23:4 — “ በሞት ጥላ መካከል እንኳን ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም ፤ በትርህና ምርኩዝህ እነርሱ ያጽናኑኛል ፡፡ “
መዝሙር 86:17 — “ ምልክትንም ለመልካም ከእኔ ጋር አድርግ ፤ የሚጠሉኝ ይዩ ይፍሩም ፣ አቤቱ ፣ አንተ ረድተኸኛልና፣ አጽናንተኸኛልምና ፡፡ “
2 ቆሮንቶስ 1:20 — “ እግዚአብሔር ለሰጠው የተስፋ ቃል ሁሉ አዎን ማለት በእርሱ ነውና ፣ ስለዚህ ለእግዚአብሔር ስለ ክብሩ በእኛ የሚነገረው አሜን በእርሱ ደግሞ ነው ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።