Money And Opportunities
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ The Last Adam 1 Corinthians 16 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በ1ቆሮንቶስበዚህሳምንንትጥናታችንበአንዳንድጠንካራፅሁፎችላይተነጋግረናል፡፡ ዛሬ ጥናታችንን በምዕራፍ 16 ለመጨረስ በተለያዬ አቅጣጫ እንጓዛለን ፡፡ በምዕራፍ 16 ጳዉሎስ ቆሮንቶሳዊያንን በክርስቶስ ተባርከዉ እንደ ነበረዉ በኢየሩሳሌም ያሉትን አይሁዶች እንዲባርኳቸዉ አበረታታቸው ፤ በኢየሩሳሌም ለድሆች ለችግር መዋጮ እንዲሰጡ ጠየቃቸው ፡፡
ትምህርት
1-ቆሮንቶስ (16፡ 1-4)፡ ጳዉሎስ በሰዎስተኛዉ አገልግሎት ጉዞዉ ላይ ለቤተ ክርስቲያን በእያንዳንዱ ቤተ ክርስቲያን በደረሰ ጊዜ እንዲሰበስብ ገንዘብ እንዲሰጡት ተናግሮ እንደ ነበር ገለፀ (ቁጥር 1-2) ፤ ስለ ተጠያቂነት ሲል ድጋፉን ተቀብሎ እንደ ነበር እንዲያዉቁ ለሰጡት መልዕክቱን ይልክላቸዋል (ቁጥር 3) ፤ ሌላ ከመረጡም ኢየሩሳሌም እስኪደርስ ድረስ የገንዘብ መስመሩን/አሰባሰቡን ለመጠበቅ ከጳዉሎስ ጋር ሰዉ መላክ ይችላሉ (ቁጥር 4) ፡፡
ጳዉሎስ ለኢየሩሳሌም ገንዘብ ለምን እየሰበሰበ ነበር ? ዋይርስቤ ለመሰብሰብ ጳዉሎስ ሁለት ምክንያቶች እንደ ነበሩት ይናገራል ፤ የመጀመሪያው ጳዉሎስ አሕዛብ አማኞች ለአይሁዶች የቁስ /የማቴሪያል ስጦታ በመስጠት መንፈሳዊ ጥቅሞችን እንዲቀበሉ ስለፈለገ (ሮሜ 15፡ 25-27) ፤ ሁለተኛው በኢየሩሳሌም ኮንፈረንስ ላይ ጳዉሎስ ድሆችን ለማስታወስ ቃል ስለገባ (ገላ 2፡ 10) ፡፡
ዋይርስቤ በኢየሩሳሌም ስለሚያስፈልገዉ ሰዎስት ምክንያቶችን ይሰጣል፡
- በኢየሩሳሌም የሚያስፈልገዉ ታላቅ ስለ ነበር - በበዓለ ሀምሳ ላይ ብዙ አዲስ አማኞች (3,000 እና ከዚያ በላይ) ወደ ኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን ይመጡ ስለ ነበር ፤ ያ ቤተ ክርስቲያኒቱ በኢየሩሳሌም ቤት እና ስራ ያልነበራቸዉን ለመሸከም ተዳክማ እንደ ነበር ያመለክታል (ሐዋ 2፡ 41-47, 4፡ 33-37, 11፡ 27-30) ፡፡
- አካባቢዉ ርሀብ ደርሶበት ስለ ነበር በኢየሩሳሌም ተጨማሪ ፍላጎቶችን ጨምሯቸዋል ፡፡
- “ ስጦታዎችን የመዉሰድ የጳዉሎስ ታላቅ ፍላጎት አይሁዶችን እና አሕዛቦችን በአንድ ለመርዳት ነበር “ (ሐዋ 17፡ 21-25) ፡፡
ዋይርስቤ ከእነዚህ ከመጀመሪያዎቹ አራት ጥቅሶች የክርስቲያን ባላደራነትን አምስት መርሆች ወይም መመሪያዎች ይዘረዝራል ፡
“ መስጠት አንዱ የአምልኮ ተግባር ነው “ ፤ ጳዉሎስ የቆሮንቶስ አማኞችን በሁሉም ሳምንት መጀመሪያ ቀን ላይ እንደ ግዴታ ሳይሆን “ ለእግዚአብሄር እንደ መንፈሳዊ መስዋዕት “ ለብቻ እንዲያስቀምጡ ነገራቸው (ፊል 4፡ 18) ፡፡
“ መስጠት በስርዓት መሆን አለበት “ ፤ ጳዉሎስ አማኞችን ለቤተ ክርስቲያን በሁሉም ሳምንንት በስርዓት ገንዘብ እንዲያመጡ ነገራቸው ያከሆነ በደረሰ ጊዜ ስጦታዉ ሙሉ ይሆናል ፡፡
“ መስጠት ግላዊ እና ግለሰባዊ ነው “ ፤ ጳዉሎስ የገንዘብ ችግራቸዉን ሳያስቡ ሁሉም አባል እንዲሰጥ ፈለገ ፡፡
“ መስጠት የተመጣጠነ መሆን አለበት “ ፤ ጳዉሎስ አማኞችን በተወሰኑ ሁኔታዎቻቸዉ መሰረት የሚችሉትን እንዲሰጡ አዘዛቸዉ (1ቆሮ 16፡ 2, 2ቆሮ 8-9) ፡፡
“ ገንዘብ በታማኝነት መያዝ አለበት “ ፤ ጳዉሎስ የተቀበላቸዉን ስጦታዎች ያለአግባብ በመያዝ ጠላቶቹ ለመክሰስ ምክንያት እንዳልነበራቸዉ እርግጠኞች አደረጋቸው ፡፡
በ 2ቆሮንቶስ (8-9) ስለ ኢየሩሳሌም ማሰባሰብ ብዙ መረጃ የተሰጠ ነው ፡፡
1-ቆሮንቶስ (16፡ 5-9)፡ ጳዉሎስ ቀጣዩን የጉዞ እቅዱን እንዲሁም ስለ አንዳንድ ሐዋሪያት የጉዞ እቅድ ገለፀ (ቁጥር 5) ፡፡ በእነርሱ በኩል ከማለፍ ይልቅ ከአማኞች ጋር በዚያ በቆሮንቶስ ጊ ለማሳለፍ ክረምትን እንዲሆን ፈለገ (ቁጥር 6-7) ፤ ይሁን እንጂ መጀመሪያ ጳዉሎስ የአገልግሎት በር ተከፍቶለት ስለ ነበር እስከ በዓለ ሀምሳ ቀን ድረስ በኤፌሶን ይቀመጣል (ቁጥር 8-9) ፡፡ የጳዉሎስ የመጀመሪያ የጉዞ እቅድ በሜቄዶኒያ አድርጎ ወደ ቆሮንቶስ ማለፍ ክረምቱን በዚያ በመቆየት ወደ ይሁዳ ማቅናት ነበር ፤ ይሁን እንጂ በሚሄድበት ጊዜ የመጀመሪያ እቅዱን ቀጥታ ወደ ቆሮንቶስ መሄድ ከዚያ መቄዶንያን መጎብኘት ተመልሶ በቆሮንቶስ በማለፍ ወደ ይሁዳ መሄድ በማለት ከለሰው (2ቆሮ 1፡ 15-16) ፡፡ ያም እቅድ የተከለሰ ነበር ፤ ጳዉሎስ “ ወደ ኤፌሶን ከተመለሰ በኋላ ፈጣን እና ህመም የተሞላ ጉብኝት በቆሮንቶስ አደረገ ፤ ቀጥሎም ቲቶን (ወደ ቆሮንቶስ ተልኮ ወደ ነበረው 2ቆሮ 2፡ 12-13, 7፡ 5) ለመጠበቅ ወደ ጢሮስ ሄደ, ሜቅዶንያን በመጎብኘት ወደ ይሁዳ ሄደ ፤ ተስፋ አድርጎት እንደ ነበረዉ ወይም ጠብቀዉት እንደ ነበረው በቆሮንቶስ ብዙ ጊዜን አላሳለፈም “ ፡፡ ጳዉሎስ የራሱን የጉዞ እቅድ የሰራ ቢሆንም እንኳን እግዚአብሄር እቅዱን ቀየረው ፡፡
1-ቆሮንቶስ (16፡ 10-24)፡ ጳዉሎስ የ 1ቆሮንቶስ መፅኀፍን ስለ ሰዎቹ በመፃፍ ዘጋው ፡፡ ዋይርስቤ “ ገንዘብ እና እድሎች ያለ ሰዉ ዋጋ ቢሶች እንደሆኑ “ አመለከተ ፡፡ ሲጎበኛቸዉ ስለ ጢሞቲዎስ አቀባበላቸዉ እና አጵሎስ እድል ሲኖረዉ እንደሚመጣ ፃፈላቸው (ቁጥር 10-12) ፡፡ እነዚህን ሰዎች ሲያገኟቸው በፍቅር እንዳደረጉ እርግጠኞች እንዲሆኑና “ እንዲያድጉ “ ነገራቸው (ቁጥር 13-14) ፡፡
በቁጥር 15-18 ጳዉሎስ ጳዉሎስ አጥምቋቸዉ የነበሩትን እስጢፋኖስን እና ቤተሰቦቹን ጠቀሰ (1ቆሮ 1፡ 16) ፡፡ ጳዉሎስ አማኞችን “ ቅዱሳንን ለማገልገል “ ራሳቸዉን ለሰጡት ሰዎች (ለእነዚህ እና ለሌሎች) እንዲታዘዙ አሳሰባቸው ፡፡ ጳዉሎስ አማኞችን “ ቅዱሳንን ለማገልገል “ ራሳቸዉን ሰጥተዉ ለነበሩት ሰዎች እንዲታዘዙ አሳሰባቸው ፤ ጳዉሎስ ለራሱ የአገልግሎት ሰራተኛ ቡድን ቸር እንዲሆኑ እያበረታታቸዉ ነበር ፡፡
ጳዉሎስ ከእስያ ቤተ ክርስቲያን፣ ከአቅላና ከጵርስቅላ እንዲሁም በዚያ ላሉ ሌሎች አማኞች ሰላምታ ላከ (ቁጥር 19-20) ፤ በተጨማሪምጳዉሎስ የራሱን ሰላምታ በመላክ መልዕክቱ ከራሱ እጅ የመጣ እንደ ነበር አንባቢዎቹን አስታወሰ (ቁጥር 21) ፡፡ በመባረክም ጨረሰ፡ አምላካችን ይመጣል ፤ የጌታችን የኢየሱስ ፀጋ ከእናንተጋር ይሁን (ቁጥር 22-24) ፡፡
መደምደሚያ
ነገ ለቆሮንቶስ የጳዉሎስ ሁለተኛ መልዕክቱ ላይ እንቀጥላለን ፡፡
Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1989), p. 621.
Wiersbe, p. 621.
Wiersbe, p. 622.
Wiersbe, p. 623.
Wiersbe, p. 624.
ጥያቄዎች
-
በ 1ቆሮ (16፡ 10-11) ጳዉሎስ ቆሮንቶሳዊያንን ያለ ፍርሀት እና ሳይንቁት ጢሞቲዎስን እንዲቀበሉት ለምን ነገራቸው (ሐዋ 16፡ 1, 1ጢሞ 1፡ 2, 4፡ 12) ? እኛ እንደ አንድ ማህበረሰብ በአሁኑ ጊዜ ወደ ታች ወደ ወጣቶች እንመለከታለን ? ላለመመልከታችን/ለመመልከታችን ምክንያት አለ ?
-
ጳዉሎስ በ 1ቆሮ (16፡ 13-14) ላይ ያለዉ በአሁኑም ጊዜ ይሰራል ብላችሁ ታስባላችሁ ? እንድንነቃ/በተጠንቀቅ እንድንቆም/በንቃት እንድንሆን ስለ መፈለጉ ምን ታምናላችሁ ? ሁሉንም ነገር እንዴት በፍቅር ታደርጉታላችሁ ?
-
በ 1ቆሮንቶስ 16 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Corinthians 16:7–9
“I don’t want to see you now just in passing, for I hope to spend some time with you, if the Lord allows. But I will stay in Ephesus until Pentecost, because a wide door for effective ministry has opened for me—yet many oppose me.”
ጳውሎስ ለእግዚአብሔር ፈቃድ የተማረከን ህይወት ያሳያል ፡፡ ስለ ጉዞ እቅዱ እንኳን ሲያወራ ፣ በእርግጠኝነት ሳይሆን የሚሆነው የእግዚአብሔር ፍቃድ ብቻ ከሆነ እንደሆነ በማሳወቅ ነበር ፡፡ በተጨማሪም እርሱ ለአገልግሎት የተከፈተ በር አይቶ ነበር ፡፡ ሰውን አይፈራም ነበር ተቃውሞም ስለገጠመው የተዘጋ በር ብሎ አልተናገረም ፡፡ ይልቁንም ውጤታማ የሚያደርግ ሰፊ የአገልግሎት በር ብሎ ጠራው ፡፡ እርሱ ስደትን ተቀበለ ፣ በድፍረትና በልበ ሙሉነት እግዚአብሔርን በመፍራት ተራመደ ፡፡
አንዳንድ ጊዜ እቅዶችን ታወጣለህ እናም ምንም አይነት ቀይ ምልክትን ብታይ ወይም በመንገድህ የተዘጋ በር ቢያጋጥምጥህ እናኳ ምናልባት እግዚአብሔር ወደ መልካም ፍቃዱ ወይም አላማው ትኩረትህን እንድታዞር ለማድረግ እየሞከረ ሊሆን ይችላል ብለህ አታስብም ፡፡ ነገር ግን ጌታ የእርሱ የሆኑት እንዲጸልዩ ይመክራል ስለዚህም “ ይከናወናሉ “ ፡፡ እቅድን ወይም አቅጣጫን እንኳ መቀየር ቢያስፈልግ መንገድህን ንጹህ እንደሚያደርግልህ እመን በትህታንም ተራመድ ፡፡ ዋናው ነገር ላሉህ ዕቅዶች ልብህን መክፈትና እነርሱንም ለጌታ አሳልፈህ መስጠት ነው ፡፡ አንተ መቆጣጠሩን ተውና እርምጃውን እርሱ እንዲወስድ ተውለት ፡፡ ጌታ በሮችን እንድከፍትልህ ጸልይ እናም እርሱ ከፈቀደልህ ብቻ ሂድ ፡፡ ለእግዚአብሔር ፍቃድ ራሱን አሳልፎ የሰጠን ህይወት ስትኖር ተቃውሞ የለብህም ወይም ደግሞ መከራ አያጋጥምህም ማለት አይደለም ፡፡ ነገርግን ከክርስቶስ ጋር እርሱ እየመራ ፣ ድልን ትቀዳጃለህ ፡፡
“ አሁን እግረ መንገዴን ሳልፍ ልጎበኛችሁ አልወድምና ፤ ጌታ ቢፈቅደው የሆነውን ዘመን በእናንተ ዘንድ ልሰነብት ተስፋ አደርጋለሁና ፡፡ በኤፌሶን ግን እስከ በዓለ ኀምሳ ድረስ እሰነብታለሁ ፡፡ ስራ የሞላበት ትልቅ በር ተከፍቶልኛልና ተቃዋሚዎችም ብዙ ናቸው ፡፡ “ - 1ኛ ቆሮንቶስ 16፡7-9
ተጨማሪ ጥቅስ
- ምሳሌ 3:5–6 — “ በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፣ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ ፣ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ ፣ እርሱም ጎዳናህን ያቀኛልሃል ፡፡ “
- ማቴዎስ 6:9–10 — “ እንግዲህ እናንተስ እንዲህ ጸልዩ ፡፡ በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ ፣ ስምህ ይቀደስ ፤ መንግስትህ ትምጣ ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን ፡፡ “
- ያዕቆብ 4:13–15 — “ አሁንም ፡፡ ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህ ከተማ እንሄዳለን በዚያም ዓመት እንኖራለን እንነግድማለን እናተርፍማለን የምትሉ እናንተ ፣ ተመልከቱ ፣ ነገ የሚሆነውን አታውቁምና ፡፡ ሕይወታችሁ ምንድር ነው ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፍወለት ናችሁና ፡፡ በዚህ ፈንታ ፡፡ ጌታ ቢፈቅድ ብንኖርም ይህን ወይም ያን እናደርጋለን ማለት ይገባችኋል ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።