The Resurrection Of The Dead
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ The Last Adam 1 Corinthians 15 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በቤተክርስቲያንዉስጥአንድነትእንዳይኖርምክንያትስለሆኑከባድጉዳዮችላይተመልክተናል ፡፡ ጳዉሎስ ቆሮንቶሳዊያንን በክርስቶስ አካል ዉስጥ በአንድነት መኖር ምን እንደሚመስል ነገራቸው ፡፡ ጳዉሎስ ቤተ ክርስቲያንን የሚያነሳሳዉ ፍቅር እንደ ነበር አብራራ ፡፡ በምዕራፍ 14 ጳዉሎስ ስለ ትንቢት መናገር ቅድሚያነት አወራ ፤ ቀጥሎም ወደ ምዕራፍ 15 ገብተናል ፡፡ ኮንስታብል “ ጳዉሎስ በዚህ ምዕራፍ ካለዉ ነገር አንዳንድ ቤተ ክርስቲያኖች ከሐዋሪያዊ ትምህርት ተቃራኒ በነበረው ስለ አትኩረዉበት ስለ ነበረዉ ትምህርት በግልፅ ያውቃል ፤ ከሙታን መነሳት/ትንሳኤ እንደለሌ አምነዋል “ በማለት ይገልፃል ፡፡ እነዚህ አማኞች ክርስቶስ የተነሳ ቢሆንም አማኞች እንደማይነሱ ያምኑ ነበር ፡፡ “ ይህ ምዕራፍ የቀድሞ የክርስቲያን አስተምሮ ሙከራ በመባል ይጠራል፣ ይህም ከአስተምሮ ጋር በቀጥታ የሚያወራ ብቸኛዉ የመልዕክት አካል ነው “ ፡፡
ትምህርት
1-ቆሮንቶስ (15፡ 1-9)፡ ጳዉሎስ ቀድሞ ይህን መረጃ ለቆሮንቶሳዊያን አድርሷቸዉ እንደ ነበር እና በዚህ የክርስቶስ መሰረት ላይ እንዲፀኑ እንደጠበቀ አመለከተ (ቁጥር 1) ፤ ቀድመዉ በዚህ መልዕክት ድነዉ ነበር (ቁጥር 2) ፡፡ ጳዉሎስ አጥብቆ የተናገረዉ በጣም አስፈላጊዉ ነገር ክርስቶስ ስለ ኃጢዓታችን ሞቶ እንደነበር፣ እንደ ተቀበረ እና መፅሀፍ እንደሚለዉ በሰዎስተኛዉ ቀን እንደ ተነሳ ነበር (ቁጥር 3-4) ፡፡ ቁጥር 3-4 መልካም ዜናን ይሰጣል - የኢየሱስን ሙሉዉን ወንጌል - እስካሁን ካነበባችሁት ቀላል የሆነ ነው፡ ክርስቶስ ስለ ኃጢዓታችን ሞተ፣ ተቀበረ፣ በሰዎስተኛዉም ቀን ተነሳ ፤ በዚህ ላይ ሊጨመር ወይም ሊቀየር የሚያስፈልግ ምንም ነገር የለም ፡፡ መልዕክቱ ይህ ነው ፡፡ ቀጥሎም ጳዉሎስ የትንሳኤዉ ክርስቶስ ምስክሮች የነበሩትን/የሖኑትን ሁሉንም አስቀመጠ (ቁጥር 5-8) ፡፡ ማክአርቱር ሁሉንም ኢየሱስ በመልኩ የተገለጠላቸዉን/የታየላቸዉን ይለያል/ ያስቀምጣቸዋል፡ መቅደላዊት ማሪያም፣ ሌሎቹ ሴቶች፣ ጴጥሮስ፣ አስሩ ደቀ መዛሙርት፣ አስራ አንዱ ደቀ መዛሙርት ቶማስን ጨምሮ፣ በኤማሆስ መንገድ ላይ ለነበሩት ደቀ መዛሙርቶች፣ በገሊላ፣ ለ500 ሰዎች፣ ለያዕቆብ እና ሐዋሪያቶች፣ በደማስቆ መንገድ ላይ ለጳዉሎስ እና ወደ ላይ ከፍከፍ ሲል ለነበሩት ሁሉ ፡፡
1-ቆሮንቶስ (15፡ 10-19)፡ ጳዉሎስ ምክርነቱን በመጀመር ቆሮንቶሳዊያንን እንዴት ቤተ ክርስቲያንን ያሳድድ እንደ ነበር እና በእግዚአብሄር ፀጋ እንደዳነ አሳሰባቸው (ቁጥር 9-10) ፡፡ ጳዉሎስ በአገልግሎቱ ለዉጤታማነቱ የእግዚአብሄር ፀጋ እንደ ነበር ገለፀ (ቁጥር 10-11) ፡፡
ስለዚህ የሙታን ትንሳኤን እንዴት መካድ ይችላሉ ? ያን ከካዱ የክርስቶስን ትንሳኤም ክደዋል ስለዚህም እምነታቸዉ ዋጋ/ትርጉም የለሽ ነበር (ቁጥር 12-19) ፡፡
ማክአርቱር የኢየሱስ ትንሳኤ እዉነት ባይሆን ኖሮ ምንሊሆን እንደሚችል ስድስት ምን ይሆናል “ የሚሉ ንግግሮችን ይሰጣል፡
- የክርስቶስ ስብከት ትርጉም የሌለዉ እና ዋጋ የሌለዉ ይሆናል ፡፡
- አሁንም የሞተ ከሆን በክርስቶስ ማመን ጥቅም አይኖረዉም ፡፡
- ሁሉም የትንሳኤ ምስክሮች እና አስተማሪዎች/ሰባኪዎች ዉሸታሞች ይሆናሉ ፡፡
- ከኃጢዓት ማንም የዳነ አይሆንም ፡፡
- ሁሉም የቀድሞዉ አማኞች ሞኝ እንደሆኑ ሞተዋል ፡፡
- በአለም ላይ ክርስቲያን በጣም የተጠቃ ህዝብ ይሆናል ፡፡
1-ቆሮንቶስ (15፡ 20-28)፡ ጳዉሎስ ሙሉዉን ህይወቱን ክርስቶስ ከሞት እንደተነሳ እና እኛም እንደምንነሳ እያከማቸ/እያስተማረ ነበር ! ክርስቶስ በመስቀሉ ላይ አይደለም እንደ ተቀበረም አይደለም ፤ በአባቱ ቀኝ ነዉ ፡፡ ክርስቶስ ከሞት ተነስቷል (ቁጥር 20) ፤ ጳዉሎስ እኛም ከሞት እንዴት እንደምንነሳ ለመግለፅ ሰዎስት ምስሎችን ተጠቅሟል ፤ መጀመሪያው ክርስቶስ “ ላንቀላፉት በኩራት ነበር “ (ቁጥር 20) ፤ “ ኢየሱስ ከሞት ሲነሳ የወደፊቱ መከር አካል በመሆን አንድ ቀን እኛም እንደምንነሳ የእግዚአብሄር ማረጋገጫ ነበር “ ፡፡ ለአማኞች ሞት “ ማንቀላፋት “ ብቻ ነው፣ “ አካል ሲያንቀላፋ ነፍስ ግን ከጌታዋ ጋር በቤቷ ትሆናለች “ ፡፡ ሁለተኛው “ ሞት በአንድ ሰዉ በኩል በአዳም ሲመጣ “ “ የሞት ትንሳኤ ደግሞ በአንድ ሰዉ በኩል በኢየሱስ መጣ “ (ቁጥር 21-23) ፡፡ ሰዎስተኛው ኢየሱስ መንግስትን ለመመስረት ወደ ምድር መጣ ተመልሶ በመጣ ጊዜ ደግሞ “ ሁሉም አስተዳደር፣ ሁሉም ስልጣናት እና ኃይላት ይጠፋሉ “ (ቁጥር 24) ፡፡ ኢየሱስ ሁሉም ጠላቶቹ ሞትን ጨምሮ የእግር መረገጫዎቹ እስኪሆኑ ድረስ ይገዛል (ቁጥር 25-26) ፤ ይህ በሆነ ጊዜ በምድር ላይ ያለዉ ሁሉም ነገር ለክርስቶስ ሲገዛ ክርስቶስ ደግሞ ሁሉ በሁሉ ለሆነለት ለእግዚአብሄር ይገዛል (ቁጥር 27-28) ፡፡
1-ቆሮንቶስ (15፡ 29-34)፡ ስለዚህ ለምን የሞቱት ይነሳሉ (ቁጥር 29) ? ጳዉሎስ በዚህ ክፍል ላይ ለምን የሚለዉን በሰዎስት ጥያቄ መለሰ ፤ መጀመሪያው ዘላለማዊ ተስፋ ከሌለ ለምን ወንጌልን እንሰብካለን ? ሁለተኛዉ ተስፋ ከሌለ እለት እለት ስለ ክርስቶስ ለምን መከራን እንቀበላለን (ቁጥር 30-31) ? ሰዎስተኛው በኑሮአችን ኃጢዓት ለምን ጉዳይ ይሆናል (ቁጥር 32-34) ? አራተኛዉ ምክንያት በቁጥር 50-57 ላይ የሚገኝ ነው ፡፡
1-ቆሮንቶስ (15፡ 35-49)፡ ስለዚህ ሙታን እንዴት ይነሳሉ ? አማኞች ምን አይነት ሰዉነት ይኖራቸዋል ? ይህን ጥያቄ ለመመለስ ጳዉሎስ ሰዎስት ተመሳሳይ ምክንያቶችን ሰጥቷል ፤ የመጀመሪያው ጳዉሎስ ዘር በተተከለ ጊዜ የሚያድገዉ ከእዉነተኛዉ/ከመጀመሪያዉ የተለዬ እንደ ሆነ ገለፀ (ቁጥር 36-38, 42-48) ፤ ስለዚህም ሰማያዊ አካል እና ምድራዊ አካል አለ (ቁጥር 39-40) ፡፡ ሁለተኛው ጳዉሎስ በሰዉ፣ በእንሰሳት፣ በአዕዋፍ እና በአሳ ስጋ ልዩነቱን አወዳደረ (ቁጥር 39) ፤ ሰዎስተኛው ጳዉሎስ የሰማያዉ አካልን ከምድራዊ አካል ጋር በማወዳደር (ቁጥር 40) ይህን ንፅፅር ለማጠንከር ብዙ ጥንድ ነገሮችን ተጠቀመ (ቁጥር 40-41) ፡፡ የሙታን ትንሳኤ እንዳለ በምንጠይቅ ጊዜ እምነታችንን እየጠየቅን ነው - ኢየሱስ ማን እንደሆነ እና ለእኛ ምን ሊያደርግ እንደመጣ ሙሉ መረዳታችንን እየጠየቅን ነው ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ኢየሱስ መንፈስ ሆነ ማለትም ስጋዊ መኖሩ እና ቅርፁ መንፈሳዊ ወደ ሆነ ነገር ተቀይሮ ነበር ማለት ነው ፤ አሁን እንደ አንድ በከበረ አካል በመንፈስ አንድ ነው፣ ኢየሱስም በሚሞተዉ አካሉ ከዚህ በኋላ የሚሄድ አይደለም ፤ ለሚያምኑት ሁሉ ህይወት ለመስጠት በመንፈስ ህያዉ ነው ፤ ለዚህ ነዉ በኢየሱስ ክርስቶስ ስላለዉ የህይወት መንፈስ የተናገረው (ሮሜ 8፡ 2) “ በማለት ይገልፃል ፡፡
በትንሳኤ ብዙ ሰዎች ችግር አላቸው ፡፡ ማክአርቱር የኢየሱስን ትንሳኤ እንዴት እንደ ሚመለከቱ ሰዎስት አማራጮችን ይሰጣል፡ “1) ታላቅ የፈጠራ ወሬ (ትንሳኤው ሀሰት ነዉ የሚል)፣ 2) አፈታሪክ (ትንሳኤዉ ልብወለድ ነው የሚል) እና 3) የታሪክ የበላይ ክስተት (ትንሳኤዉ እዉነት ነው) “ ፡፡ ማክአርቱር የሚከተሉትን ቲዎሪዎች መዝግቧል፡
ኢየሱስ በእዉነት አልሞተም ፡፡
አካሉ ሳይሆን የኢየሱስ መንፈስ ብቻ ተነስቷል ፡፡
ደቀ መዛሙርቱ ራዕይ እያዩ ነበር ፡፡
የኢየሱስ ትንሳኤ እዉን ባልሆነዉ ኢየሱስ ላይ እንኳን ያልተመሰረተ ታሪክ/ተረት ብቻ ነበር ፡፡
የኢየሱስ የሞተዉ አካሉ ከመቃብሩ ዉስጥ ተሰርቋል ፤ አካሉን ለመዉሰድ ሮማዊያንን፣ ደቀ መዛሙርቱ፣ የአርማቲዎስ ዮሴፍ እና አይሁዶችን ጨምሮ ምክንያት ነበራቸው ፡፡
ደቀ መዛሙርቱ ግራ ተጋብተዉ ስለ ነበር ባዶ ሆነ ወደ ሆነዉ የተሳሳተ መቃብር ሄዱ ፡፡
ደቀ መዛሙርቱ የኢየሱስን የትንሳኤ ታሪክ ሆን ብለዉ ገንዘብ ለማግኛነት አደረጉት ፡፡
ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስን የሚመስል ሌላ ሰዉ በማየት እርሱ እንደ ነበር አሰቡ ፡፡
ኢየሱስ በእግዚአብሄር መለኮታዊ/ከተፈጥሮ በላይ በሆነ ኃይል ከሞት ተነስቷል ፡፡
1-ቆሮንቶስ (15፡ 50-57)፡ ሁላችን አናንቀላፋም ነገር ግን ሁላችንም እንቀየራለን (ቁጥር 51) ፡፡ የኃጢዓት መቅጫዉ ሞት ነዉ ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድል አድርገነዋል ፡፡
መደምደሚያ
ስለ ክርስቶስ ወንጌል ሁልጊዜ መልሶ ወደ 1ቆሮ (15፡ 3-4) ይመልሳል ፤ ክርስቶስ እንደ ተነሳ ታምናላችሁ ?
2 Archibald Robertson and Alfred Plummer, A Critical and Exegetical Commentary on the First Epistle of St. Paul to the Corinthians (International Critical Commentary series), 2nd ed. (Edin- burg: T. & T. Clark, 1963), p. 329; quoted in Constable, p. 281.
Thomas L. Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: First Corinthians, p. 280-281; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/1corinthians.pdf.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1605.
MacArthur, p. 1607.
Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1989), p. 618.
Wiersbe, p. 618.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1487.
MacArthur, p. 1609.
MacArthur, p. 1609.
ጥያቄዎች
-
የ 1ቆሮንቶስ 15 የመጀመሪያዉ ክፍል ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞት እና ትንሳኤ ስለ ብዙ የአይን ምስክሮች ተናግሯል ፤ ለምን እንደ ነበሩ እና በአሁኑም ጊዜ በዚህ የማያምኑ ብዙ ሰዎች ለምን እነዳሉ ምን ታስባላችሁ? በኢየሱስ ሞት እና ትንሳኤ የማያምኑ ሰዎች ራሳቸው ከት/ቤት ከታሪክ መፅሀፍ ስለተማሩት ይጠይቃሉ ብላችሁ ታስባላችሁ ?
-
በ 1ቆሮ (15፡ 7) ኢየሱስ ለያዕቆብ (ለወንድሙ) ተገለጠለት በማለት ቀጠለ ፤ ኢየሱስ ለራሱ ወንድም ለምን ተገለጠለት (ዮሐ 7፡ 5) ? ያዕቆብ ለምን እንዳላመነ ምን ታስባላችሁ ? በኋላስ ያዕቆብ ምን/የትኛዉን የአዲስ ኪዳን መፅሀፍት ፃፈው ?
-
በ 1ቆሮ (15፡ 8) “ እንደ ጭንጋፍ ለተወለድኩ “ የሚለዉ ሀረግ ምን ማለት ነው (ሐዋ 9፡ 3-6) ? ይህ አሁንም በአሁኑ ጊዜ ሊሆን ይችላል ብላችሁ ታስባላችሁ እናም አዎ ካላችሁ እስካሁን በእናንተ ላይ ሆኗል ወይስ በምታዉቁት ሌላ ሰዉ ላይ ?
-
1ቆሮ (15፡ 21) ምን ማለት ነው ? (ዘፍጥረት 3, ሮሜ 5፡ 12-21)
-
በ 1ቆሮ (15፡ 24-28) ከሚለዉ ጋር ተመሳሳይ መግለጫ በመፅሀፍ ላይ ሌላ የት ስፍራ ላይ ልታገኙ ትችላላችሁ (ራዕ 20፡ 13-14) ? ይህ መልዕክት ዮሐንስ ራዕይን ከመፃፉ በፊት መፃፉን በመመልከት ጳዉሎስ እንዴት እንዳወቀዉ ምን ታስባላችሁ ? (መዝ 8፡ 6, ኤፌ 1፡ 22, ዕብ 2፡ 8)
-
በ 1ቆሮ (15፡ 52) የመለከት መነፋት አስፈላጊነቱ ምንድን ነው ? (ዘሌ 23፡ 24, ዘኁ 10፡ 9-10, 29፡ 1-6, ኢዩ 2፡ 1, ሶፎ 1፡ 14-16)
-
ሁሉም ሰው አካላዊ ሞት ይሞታል (1ቆሮ 15፡ 51-52) ? አካላዊ ሞት ከማይሞቱት ሰዎች ዉስጥ አንዶቹ መሆን መቻል ቀላል ነው ብላችሁ ታምናላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አታምኑም ?
-
በ 1ቆሮንቶስ 15 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Corinthians 15:55–57
“Death, where is your victory? Death, where is your sting? Now the sting of death is sin, and the power of sin is the law. But thanks be to God, who gives us the victory through our Lord Jesus Christ!”
ጳውሎስ የወንጌል ብቻ የሆነችውን ቤተክርስቲያን ደግሞ ያስታውሳል ፡፡ ዛሬም ጭምር የወንጌሉ መልዕክት በጣም ሊወሳሰብ ደግሞም ሊጠፋም ጭምር ይችላል ፡፡ እናንተን ነጻ ያወጣችሁን ይህንን አውነት ፡- ክርስቶስ ለእናንተ ኃጢአት እንደሞተ ደግሞም እንደተቀበረ ፣ እናንተም ድነትን ታገኙ ዘንድ በሶስተኛው ቀን ከሞት እንደገና እንደተነሳ ፣ እንዳትረሱ ፡፡ ጌታ ከሞት እንደተነሳ በልባችሁ አምናችሁ በአፋችሁ ከመሰከራችሁ ፣ ትድናላችሁ ፡፡ ይህ ነው የወንጌል መሰረት ፡፡ ይህ ቀላል እውነት ህይወታችሁን ይለውጣል …….. እናም በክርስቶስ ስትኖሩ ድልን ይሰጣችኋል ፡፡
አዎን ! ምክንያቱም ኢየሱስ ከሞት እንደተነሳ ስለምታምኑ ፣ ሞት አቅም ለውም ፡፡ ኢየሱስ በኃጢአት ላይ ድልን ሰጥቷችኋል ፡፡ ኢየሱስ በሞት ላይ ድልን ሰጥቷችኋል ፡፡ በክርስቶስ ላይ ባላችሁ እምነት በነገር ሁሉ አሸናፊዎች ናችሁ ! አለም ፣ ሰይጣንና ውሸቱ ሁሉም ተሸንፈዋል ምክንያቱም እናንተ በክርስቶስ ህይወት ፣ ድል እናም ሰላም ስላላችሁ ፡፡ ዛሬ እንደ ድል አድራጊዎቸ እንደ አሸናፊዎች ተመላለሱ ፡፡ እስኪ ተቃራኒ ቡድንን ያሸነፈ የስፓርት ቡድንን በሚያወድሱ ደጋፊዎች የተሞላ ስቴድየምን አስቡ ፡፡ ዛሬ ሃሌ ሉያ ፣ እግዚአብሔር ይመስገን ብላችሁ ጩኹ ፤ በእርሱ ድልን ተቀዳጅታችኋልና ምስጋናን ፣ ውዳሴንና ክብርን ለጌታ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስጡ !
“ ሞት ሆይ ፣ መውጊያህ የት አለ ? ሲዖል ሆይ ድል መንሳትህ የት አለ ? የሞት መውጊያ ኃጢአት ነው የኃጢአትም ኃይል ህግ ነው ፤ ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድል መንሳትን ለሚሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ፡፡ “ - 1ኛ ቆሮንቶስ 15፡55-57
ተጨማሪ ጥቅስ
- ሮሜ 10:9–10 — “ ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በእፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሳው በልብህ ብታምን ትድናለህ ፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና ፡፡ “
- 1 ቆሮንቶስ 15:3–6 — “ እኔ ደግሞ የተቀበልሁትን ከሁሉ በፊት አሳልፌ ሰጸኋችሁ እንዲህ ብዬ ፡፡ መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ ፣ ተቀበረም ፣ መጽሐፍ እንድሚል በሶስተኛው ቀን ተነሳ ፣ ለኬፋም ታየ በኋላም ለአስራ ሁለቱ ፤ ከዚም በኋላ ከአምስት መቶ ለሚበዙ ወንድሞች በአንድ ጊዜ ታየ ፤ ከእነርሱም የሚበዙት እስከ አሁን አሉ አንዳንዶች ግን አንቀላፍተዋል ፡፡ “
- 1 ዮሐንስ 5:4 — “ ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና ፤ ዓለምንም የሚያሸንፈው እምነታችን ነው ፡፡
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።