Paul's Letters 1 Corinthians

The Priority Of Prophecy

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ The Last Adam 1 Corinthians 14 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 516 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ጳዉሎስ በሀቀኝነት ስለ ቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ተጠነቀቀላቸው ፤ አሁንም አማኞቹ ከቀድሞ አምልኳቸዉ የእግዚአብሄር ነገርን ከስጋ ነገር ጋር ለማደበላለቅ በመሞከር ጣዖትን እየተከታተሉ ነበር ፡፡ በአጠቃላይ በመልዕክቱ ዉስጥ ጳዉሎስ እንደ ክርስቶስ አካል በምን በነገሮች ላይ መጓዝ አስፈላጊ እንደ ሆነ ዋና ሀሳቡን ለቆሮንቶሳዊያን አስጠነቀቃቸው ፡፡ ዛሬ በተለዬ ስለ ትንቢት ስጦታ ላይ ትኩረት አደርጋለሁ ፡፡

ትምህርት

1-ቆሮንቶስ (14፡ 1-11)፡ ጳዉሎስ አንባቢዎቹን መጀመሪያ ፍቅርን እንዲከታተሉ እና መንፈሳዊ ስጦታዎችን እንዲፈልጉ ነገራቸው (ቁጥር 1) ፡፡ ሰዉን ለመዉደድ ምርጫ ነው ፡፡ ይህም ምናልባት ትንቢት መናገር ሊሆን ይችል ነበር (ቁጥር 1) ፡፡ ጳዉሎስ ትንቢት መናገርን እንደ ሚበልጥ ስጦታ አሳይቷል ፡፡ በልሳን የሚናገሩ ለሰዉ ሳይሆን ለእግዚአብሄር ይናገራሉ ምን እያሉም እንደሆነ ማንም አያስተዉልም (ቁጥር 2) ፤ ትንቢት የሚናገሩ ግን ለማነጽ (በስነልቦናም በእዉቀትም ሰዉን ለማዘዝ ወይም ለመምራት)፣ ለማበረታታት (ድጋፍ፣ ተስፋ እና ማበረታታት ለመስጠት) እና ለማጽናናት (ከማጣት ወይም ከብስጭት በኋላ ለሰዉ መጽናናትን መስጠት) በቀጥታ ለሰዉ ይናገራሉ ፡፡ ጳዉሎስ ልሳን የሚናገር ራሱን ሲያንጽ ትንቢት የሚናገር ግን ቤተ ክርስቲያንን ያንጻል አለ (ቁጥር 4) ፡፡ ጳዉሎስ ሁሉም በልሳን እንዲናገሩ ተመኘ ምክንያቱም በጌታ እነርሱን ስለሚያንፃቸው ይሁን እንጂ በፍቅር ሌሎችን እና ቤተ ክርስቲያንን ስለሚያንፅ ትንቢትን የሚናገር ይበልጣል (ቁጥር 5) ፡፡ (1ቆሮንቶስ 13፡ 8 - ፍፁሙ ሲመጣ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ብቻ በልሳን መናገር እና ትንቢት መናገር ይቆማል) ፡፡

አሁንም ቢሆን ምዕራፍ 14 ትርጉም ያለዉ ለዚያ ነው ፡፡ ቀጥሎም ጳዉሎስ በልሳን የሚናገር ከሆነ እንዴት መረዳት እንደሚችል ጠየቀ፣ ጳዉሎስ በመለኮታዊ መገለጥ፣ እዉቀት፣ ትምህርት ወይም ትንቢት ዉስጥ ብቻ በአማኞች ልዩነት ማድረግ ይችላል (ቁጥር 6) ፡፡ አንድ የሙዚቃ መሳሪያ መለየት እንዲቻል በሚደረደር ጊዜ ብቻ የተረዳ እንደሚሆን ማሳያን አቀረበ (ቁጥር 7-8) ፤ ጳዉሎስ በአለም ላይ ብዙ ቋንቋዎች ቢኖሩም ትርጉማቸዉን የሚያዉቀዉን ብቻ እንደተረዳቸዉ አብራራ (ቁጥር 9-11) ፡፡

1-ቆሮንቶስ (14፡ 12-19)፡ ጳዉሎስ ሰዎችመንፈሳዊ ስጦታዎቻቸዉን ቤተ ክርስቲያንን ለማነፅ እንዲጠቀሙ አጥብቆ ነገራቸው (ቁጥር 12) ፤ እግዚአብሄር የስርዓት አምላክ ስለሆነ በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ስርዓትን ይፈልጋል ፡፡ ስለዚህም የሚለዉን የሚተረጉም ሰዉ ከሌለ በልሳን አይናገር (ቁጥር 13) ፤ ጳዉሎስ በልሳን በሚፀልይ ጊዜ መንፈሱ እንደሚፀልይ በልሳንም እንደሚዘምር ገለፀ (ቁጥር 14-15) ፡፡ በሌሎች አማኞች ዙሪያ እያለ ያለዉ ለመግለፅ እና ሌሎችን ለማነፅ (ቁጥር 17) የተተረጎመ መሆን ያስፈልገዋል (ቁጥር 16) ፡፡ መንፈሳዊ ብስለት ከሌሎች ጋር የልሳን ስጦታን በስርዓት መጠቀም ማለት ነው (ቁጥር 18-19) ፡፡

1-ቆሮንቶስ (14፡ 20-40)፡ በቁጥር 20 መጀመሪያ ላይ ጳዉሎስ በመቀጠል በማያምኑት ፊት እንዴት በልሳን መናገር እንዳለባቸው መናገር ቀጠል ፤ ቆሮንቶሳዊያንን በአዕምሮ ሳይሆን በክፋት ህፃናት እንዲሆኑ አዘዛቸው (ቁጥር 20) ፡፡ ዋይርስቤ ቁጥር 21-25 “ ጳዉሎስ በልሳን መናገር ላይ ስለ ትንቢት መናገር ብልጫ ሌላ ሀሳብን አመለከተ ፤ በልሳን መናገር የሚመጣዉ መልዕክት (ካልተተረጎመ በቀር) ለጠፉት ኃጢዓተኞች በፍፁም ማሳመን ሊያመጣ አይችልም ፤ በእርግጥ ያልዳነ ሰዉ ትርጓሜዉ ከመሰጠቱ በፊት ሙሉዉን ጉባኤዉን እንደ እብድ በመቁጠር አገልግሎቱን ትቶ ይወጣል ፡፡ በልሳን መፀለይ ወንጌልን ለመስበክ፣ በበዓለ ሀምሳ ቀን ላይ በተጨማሪም በቀድሞ ቤተ ክርስቲያን መሰባሰብ ላይ ጥቅም ላይ የዋለ አልነበረም “ በማለት በዚህ መንገድ ገልፆታል ፤ የኔልሰን ማብራሪያም “ የማያምኑት (በጉባኤዉ የተገኙት) የጉባኤዉን ትንቢት በሰሙ ጊዜ መልዕክቱ ስለሚያሳምናቸው በግንባራቸዉ በመደፋት እግዚአብሄር ያመልካሉ “ ብሎ ይጨምራል ፡፡

በልሳን መናገር በሩን አይዘጋም ምክንያቱም ለማያምኑት እንደምልክት የሚሰጥ ስለሆነ ፡፡ አማኞችን እና የማያምኑትን ለማነቃቃት ለመተርጎም ተርጓሚ መኖር አለበት ፡፡ ፍቅር ራስ ወዳድ አይደለም፣ ቁጡ አይደለም ወይም የሚመካ አይደለም ፡፡ ስለዚህ በልሳን መናገርን እና ትንቢት መናገርን ቤተ ክርስቲያንንለማነፅ ብቻ እንጠቀማለን ፡፡ በቁጥር 26 ጳዉሎስ አምልኮ ምን ማካተት እንደሚገባዉ መመሪያን ሰጠ - ሁሉም ነገር ማነቃቃትን ስለ ማምጣት ስለ ነበር ሁለት በልሳን ተናጋሪዎች ብቻ ከተርጓሚ ጋር እንዲሆኑ ነበር (ቁጥር 26-27) ፡፡ ተርጓሚ ከሌለ በልሳን የሚናገረዉ ሰዉ ዝም ይበል (ቁጥር 28) ፡፡ ከሁለት እስከ ሰዎስት ሰዎች ትንቢት ሲናገሩ ሌሎቹ ስለሚለዩአቸዉ ሁሉም የተበረታታ እና የተማረ መሆን ይችላል (ቁጥር 29-31) ፡፡ በተጨማሪም ጳዉሎስ ሴቶች በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ዝም ይበሉ አለ - ዝም በማለት እንዲገዙ (ቁጥር 34) ፤ ጥያቄአቸዉን ባሎቻቸዉን በቤት ይጠይቅ (ቁጥር 35) ፡፡ ይህ የሚያወዛግብ/ግራ የሚያጋባ ጉዳይ ሊሆን እንደሚችል አዉቃለሁ እኔም እንደዚያ አልልም ሴቶች የተሰጡ አስተማሪዎች አይደሉም ብዬ አላስብም ፡፡ ይህ ለመሰባሰብ ብቻ ጳዉሎስ ያስቀመጠዉ ስርዓት ነው ፡፡ ይህ ለእናንተ ምን ማለት እንደሆነ እግዚአብሄርን በመጠየቅ መፈለጋችሁን ቀጥሉ ፡፡ ቀጥሎም ነቢይ ወይም መንፈሳዊ እንደ ነበር ያስተማረ ምንኛዉም ከእግዚአብሄር የመጣዉን ጳዉሎስ የፃፈዉን ማስተዋል አለበት ይላል (ቁጥር 36-37) ፡፡ ስለዚህ ሁሉም ነገር እግዚአብሄር እንደሚፈልገዉ በስርዓት መፈፀም/መሆን አለበት (ቁጥር 39-40) ፡፡

መደምደሚያ

ትንቢትን ዮሐንስ ፒፐር “ ለማነቃቃት፣ ለማበረታታት፣ ለማነፅ፣ ለማሳመን ወይም ለመምራት አላማ ከመንፈስ ቅዱስ በሰዉ ድንገተኛ መገለጥ ላይ የተመሰረተ በሰዉ ቃል የሚገለፅ ተቆጣጣሪ መልዕክት ወይም ሪፖርት ነዉ ነገር ግን በኃይለኛዉ ከሰዉ ስህተት መደበላለቅ የነፃ ስላልሆነ በሐዋሪያታዊ (መፅሀፍ ቅዱሳዊ) ትምህርት እና በበሰለ መንፈሳዊ ጥበብ ማጥናት ያስፈልገዋል “ በማለት ይገልፀዋል ፡፡ ፒፐር ስለ ትንቢታዊ ስጦታ ሰባት ተግባራዊ ምክሮችን ይሰጣል፡

  1. እግዚአብሄር ለመረጣቸዉ ስጦታን ይሰጣቸዋል ፡፡
  2. ሁሉም ነቢይ አይሆንም ፡፡
  3. ፍላጎት ስጦታ እንዲኖር ያደርጋል ፡፡
  4. ስለሰጣችሁ ስጦታ እግዚአብሄርን የምታመሰግኑ እና በሙሉ የምትጠቀሙ ሁኑ ፡፡
  5. በሁሉም ነገር ቀዳሚ ነገር ፍቅርን አድርጉ ፡፡
  6. እግዚአብሄር የነገራችሁን በድፍረት ተናገሩ ፡፡
  7. በመንፈሳዊነት በበሰሉ አማኞች ለመፈተሽ /ለመመዘን ለትንቢታዊ ቃል ትሁት መሆን ፡፡

እግዚአብሄር የሰጣችሁን እና ሌሎችን እንደ መንፈሳዊ ስጦታ ያዙ ፡፡

4 Ibid.

  1. Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1989), p. 614.

  2. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1483.

  3. John Piper, “The New Testament Gift of Prophecy,” www.desiringgod.org; available online.

ጥያቄዎች

  1. በ 1ቆሮ (14፡ 1) መሰረት ጳዉሎስ የቆሮንቶስ አማኞችን በተለዬ ምን መንፈሳዊ ስጦታን እንዲፈልጉ አበረታታቸው (1ቆሮ 14፡ 5) ? እንዲከታተሉስ ምን ነገራቸው ? በእነዚህ ሁለት ነገሮች መካከል ግንኙነት አለ ?
  2. በ 1ቆሮ (14፡ 3) ላይ ስለ ትንቢት መናገር የተዘረዘረ ሰዎስት አላማ አለ ፤ ምንድን ናቸው ? ከእነዚህ ከሰዎስቱ አንድኛዉን ለማይሰጥ ትንቢታዊ ቃል መስክራችሁ ታውቃላችሁ ?
  3. ለክፉ ነገር ህፃን መሆን ማለት ምን ማለት ነው ? (1ቆሮ 14፡ 20)
  4. በ 1ቆሮንቶስ 14 “ ማነቃቃት “ ወይም “ ማነፅ “ የሚለዉ ምን ያክል ጊዜ ጥቅም ላይ እንደዋለ ታስታዉላላችሁ (1ቆሮ 14፡ 3, 4, 5, 12, 17, 26) ፤ ጳዉሎስ ይህን ለምን አጥብቆ እንደ ተናገረ ምን ታስባላችሁ ?
  5. 1ቆሮ (14፡ 34-35) አንብቡና 1ቆሮ (11፡ 5) ላይ ተመልከቱ ፤ የሴቶች ገደብ ምናልባትም በተለይ ትንቢት በሚነገርበት ጊዜ ነዉ ብላችሁ ታስባላችሁ ወይስ እነዚህን ጥቅሶች እንዴት ትገልፁአቸዋላችሁ ? (1ቆሮ 14፡ 29)
  6. በ 1ቆሮንቶስ 14 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Corinthians 14:39–40

“Therefore, my brothers, be eager to prophesy, and do not forbid speaking in other languages. But everything must be done decently and in order.”

መንፈስ ቅዱስ የክርስቶስን አካል ለመገንባት ልክ በልሳን እንደ መናገር ፣ ትንቢትን መናገር ያሉ መንፈሳዊ ስጦታዎችን ይሰጣል ፡፡ ሆኖም ግን ጳውሎስ ሁሉም ነገር በአግባብና በስርዓት መሆን እንዳለበት ለቤተክርስቲያን ያስጠነቅቃል ፡፡ ልክ በዛሬዋ ቸርች ውስጥ እንዳለው ጳውሎስ ስጦታዎች በቀላሉ ለመከፋፈልና ግራ ለመጋባት እንደሚዳርጉ እንድሁም ከዚያ በኋላ በእግዚአብሔር ከሚፈለግ ዓላማ እንደሚያስቀሩና እንደሚጠልፉ አውቋል ፡፡ ጳውሎስ አማኞኝችን በመንፈስ እንድመላለሱ ፣ ትንቢትን እንዳይንቁ እንድሁም ደግሞ ትንቢቶችን እንድፈትኑና መልካም የሆነውን እንድይዙ አዘዘ ፡፡ ልክ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ለማፍረስ ሳይሆን የክርስቶስን አካል ለመገንባት እንደሚጠቅሙ ሁሉ ትንቢትን የሚናገር ሰው ለሌሎች ለማነጽ ፣ ለማበርታት እና ለማጽናናት ይናገራል ፡፡

ለሆነ ሰው ትንቢታዊ መልዕክት ወይም ቃል እንደመጣልህ ካሰብክ ፣ መልዕክቱ ያንን ሰው ያንጸው ፣ ያበረታውና ያጽናናው እንደሆነ እግዚአብሔርን ጠይቅ ፡፡ ከመናገርህ በፊት ማረጋገጫን ጠይቅ ፡፡ መንፈስ ቅዱስ እመን እናም ልክ ሲያረጋግጥልህ ፣ ከእግዚአብሔር የሰማኸውን ነገር ተናገር ፡፡ ፍርሃትን ፣ ተስፋ መቁረጥንና ግራ መጋባትን ሊያስከትል የሚችል የትንቢት ቃል ካለህ ወድያውኑ ከመናገር ይልቅ ራስህን መቆጣጠርና ለሰውየው መጸለይን ተለማመድ ፡፡ የእግዚአብሔር ፍቃድ ነውና ሁልጊዜ ጸልዩ አመስግኑም ፡፡

" ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ትንቢት ለመናገር በብርቱ ፈልጉ፥ በልሳኖች ከመናገርም አትከልክሉ፤ ነገር ግን ሁሉ በአገባብና በሥርዓት ይሁን ። "

-1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 14 :39- 40

ተጨማሪ ጥቅስ

  • 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 14፡3 -" ትንቢትን የሚናገር ግን ለማነጽና ለመምከር ለማጽናናትም ለሰው ይናገራል።
  • 1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 5፡20-21-“ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና። መንፈስን አታጥፉ፤ ትንቢትን አትናቁ፤ ሁሉን ፈትኑ መልካሙንም ያዙ:: "
  • 2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1፡20-21 –" ይህን በመጀመሪያ እወቁ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም፤ ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።