LOVE: The Superior Way
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ The Last Adam 1 Corinthians 13 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ይህ ክፍል በትናትናው በምዕራፍ 12 መንፈስ ቅዱስ ለእያንዳንዱ አማኝ ስለሰጠዉ ስጦታ በሚያወራዉ ትምህርት ላይ የተመሰረተ ነው ፡፡ ዘጠኝ ስጦታዎች በ 1ቆሮንቶስ 12 ላይ ተዘርዝረዋል፡ ጥበብ፣ እዉቀት፣ እምነት፣ ፈዉስ፣ ተዓምራትን የማድረግ፣ ትንቢት የመናገር፣ የመለየት (መልካሙን ከክፉዉ)፣ በልሳን የመናገር እና በልሳን የተነገረዉን የመተርጎም ፡፡ እነዚህ ሁሉ ስጦታዎች ወደ አንድ ነገር ይመራሉ ወደ ፍቅር ፡፡
ትምህርት
1-ቆሮንቶስ (13፡ 1)፡ ሰዎች “ በሰዉ ወይም በመለዓክት “ ቋንቋ (ቁጥር 1) ወይም ደግሞ ከፍቅር ዉጪ በሆነ በእናንተ ላይ ሲፀልዩ ግራ የሚያጋባ ጩኸት ብቻ ነዉ የሚሆን ፤ ይህ ያለ ፍቅር በሆነ ጊዜ አንድ ሰዉ “ ሄይ ወደኔ ተመልከት ፤ በልሳን መፀለይ እችላለሁ “ በማለት በሚፀልይ እና በሚናገር ጊዜ በትዕቢት ይሆናል ፡፡ ይህ በአስተማሪ ቻርለስ ብራዉን እንደተፈበረከዉ የሚመስል ድምፅ ነው ፤ በሌላ ቋንቋ መረዳት አትችሉም ፡፡
1-ቆሮንቶስ (13፡ 2)፡ የትንቢት ስጦታን (1 ቆሮንቶስ 14፡ 1 ላይ ሁሉን ይህ ፀጋ እንዲኖረዉ እንዲፈልግ ተናግሯል) ያለ ፍቅር የሚሰራ ከሆነ ምንም አይደለም ፡፡ 1ቆሮ (14፡ 1) አማኞችን መጀመሪያ ፍቅርን እንዲከታተሉ ያዛቸዋል ፤ ፍቅር በጣም አስፈላጊ ነው፣ ራሳችሁ ከመንፈሳዊ ፀጋ ስጦታችሁ ቀጥላችሁ ከሆናችሁ የወንጌልን ሙሉ መልዕክት ስታችሁታል ፡፡
በቀጥታ ትንቢት ማለት “ …ቀድሞ ስለሚሆን ነገር መናገር ፤ የትንቢት ስጦታ እዉነትን ለመግለፅ እና በትክክለኛዉ ጊዜ የመናገር እንዲሁም ለማስተዋል፣ ለማስተካከል፣ ለንስኃ ወይም ለማነቃቃት አስፈላጊ ሁኔታ/ነገር ነው ፤ ወዲያዉኑ ወይም የወደፊት ትርጓሜ ሊኖረዉ የሚችል ነው “ ፡፡ “ ለማስታረቅ/ለማስተካከል አላማ በሰዎች ላይ ኃጢዓትን ወይም ማጭበርበርን ለማጋለጥ ስትናገሩ “ ከዚህ ኋላ ፍቅር አይኖርም ትልቅ ጩኸት ስለሚኖር ማንም ሰዉ ለመስማት አይፈልግሞ ፤ ነገር ግን ልብ ኖሯችሁ ከእግዚአብሄር ለማሳመን፣ ለንስኃ ወይም ለማነቃቃት ምክንያት የሚሆንን ለመናገር ስትፈልጉ ብዙ ጊዜ ሌሎች ለማየት የማይችሉትን እና ምላሽ ለመስጠት የሚሞግታቸዉን እዉነት በማየት ይህን በፍቅር ስታደርጉት ወደ ክርስቶስ ይሳባሉ ፡፡ “ ይህ ትንቢታዊ ቃል አለኝ “ በሚል አመለካከት በመምጣት በሆነ ሰዉ ላይ ልታደርጉት ከሞከራችሁ ወይም መንፈስ ቅዱስ ምን ያክል እንደተሰጣችሁ ልታሳዩ ከሞከራችሁ መንፈሳዊ ስጦታችሁን ያለ አግባብ ትጠቀማላችሁ ፤ ነገር ግን ሰዎችን በምትወዱ ጊዜ ተቀባይ ሊሆን ይችላል ፡፡ ሰዎች “ እግዚአብሄር በወሰዳቸዉ ነገሮች በኩል የእግዚአብሄርን ፍቅር እና ሀሳብ እንዲረዱ ከፈለጋችሁ “ ሁሉም ነገር በእግዚአብሄር ፍቅር የተሰራጨ መሆን አለበት ፡፡ በፍቅር ላይ በተመሰረተ ትንቢት በምንጓዝ ጊዜ ትለያላችሁ፣ ታስገድዳላችሁ፣ የማያወላዉል፣ በኃይል የሚናገር፣ በስልጣን የሆነ፣ የሚያሳምን እና የሚያሸንፍ ነዉ - እነዚህ ሁሉ ስለሚወዷቸዉ ይሆናሉ ፡፡ የትንቢት፣ የእዉቀት፣ የእምነት እና ራስን ለእሳት አሳልፎ እስከመስጠት የሚያደርስ ስጦታ ሊኖር ይችላል ነገር ግን መፅሀፍ ፍቅር ከሌለዉ ከንቱ ነዉ ይላል ፡፡
1-ቆሮንቶስ (13፡ 3)፡ ለድሆች ያለን ሁሉ ቢሰጥ፣ ራስንም መሰዋት እንኳን ቢሆን ፍቅር ከሌለ ግን ምንም ጥቅም አያስገኝም ፤ እነዚህ ሁሉ ስጦታዎች ከፍቅር ዉጪ ዋጋ ቢስ ናቸው ፡፡ በእነዚህ ሰዎስት ጥቅሶች ቶም ኮንስታብል “ ጳዉሎስ ስለ ፍቅር አስፈላጊነት እና የበላይነት እየተናገረ ነበር “ ብሏል ፡፡
1-ቆሮንቶስ (13፡ 4-7)፡ በእነዚህ ቁጥሮች ዉስጥ “ የፍቅርን ባህሪይ “ እናያለን ፡፡ ስለ እነዚህ የፍቅር ባህሪያት ስናወራ በአይምሮአችን ዉስጥ ትልቅ ምስል ማስቀመጥ አስፈላጊ ነው ፡፡ ጳዉሎስ በጊዜዉ እዚህ ስፍራ ላይ ህዝቦቻቸው ምንም ፍቅር እያሳዩ ላልነበሩት ነገር ግን ስጦታዎችን እያወኩ ለነበሩት ለቆሮንቶሳዊያን ቤተ ክርስቲያን እያወራ ነበር ፡፡ በቤተ ክርስቲያን መከፋፈል ነበር ፤ በሌሎች ስጦታዎች ላይ እየቀኑ ነበር ፤ ባህሪያቸዉ እግዚአብሄርን የማያከብር ነበር ፡፡ በእነዚህ ችግሮች መካከል ላይ ጳዉሎስ የዚህ ባህሪይ ባለቤት እንዲሆኑና እዉነተኛ ፍቅር ምን እንደ ነበር እና እንዴት እንደሚገለፅ እንዲረዱት ፈለጋቸዉ ፡፡ በእነዚህ ጥቅሶች ዉስጥ ፍቅርን የሚገልፁ 15 ቃላቶች አሉ ፡፡ 1ቆሮ (13፡ 4-7) ስትይዙ በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ አንድነትን ታያላችሁ ፡፡ እነርሱን ማክአርቱር በዚህ መንገድ ይገልፃቸዋል ፡
- “ ፍቀር ይታገሳል “ ፤ በማንኛዉም ሁኔታ ዉስጥ ያለምንም በቀል የአንድን ሰዉ አስቸጋሪ ባህሪይ ይሸከማል፡፡
- “ ፍቅር ቸርነት ነው “ ፤ ለሌላዉ ሰዉ ህይወት በኃይል የሚጠቅምን መንገድ በትጋት ይፈልጋል ፡፡
- “ ፍቅር አይቀናም “ ፤ ለሌላ ሰዉ በተሰጠ ነገር ክብር እና ከፍተኛ አድናቆት በመስጠት ደስተኛ መሆን ፡፡
- “ ፍቅር አይመካም “ ፤ ሌሎችን ሳያካትት ወደ ራስ ብቻ ትኩረትን አይስብም ፡፡
- “ ፍቅር አይታበይም “ ፤ አንድን ማወቅ ከሌሎች በጣም አስፈላጊ አይደለም ፡፡
- “ ፍቅር የማይገባዉን አያደርግም “ ፤እግዚአብሄራዊ ባልሆነ ተግባር ማንንም ሰዉ አያስገባም ፡፡
- “ ፍቅር የራሱንም አይፈልግም “ ፤ በሌሎች ላይ የተመሰረተ ነው ፡፡
- “ ፍቅር አይበሳጭም “ ፤ በእኔና በሌሎች መካከል ለሚያስቸግሩ ነገሮች እንደ መፍትሄ ብስጭትን አያዘወትርም ፡፡
- “ ፍቅር በደልን አይቆጥርም “ ፤ በፍፁም በሌሎች ላይ ክፋትን አይይዝም/አይመዘግብም ፡፡
- “ ፍቅር በዓመፅ ደስ አይለዉም “ ፤ በሌላ ሰዉ ፅድቅ በሌለዉ ባህሪይ በፍፁም አይደሰተም እንዲሁም ይህን ገለፃ እቀላቀላለሁ አይልም ፡፡
- “ ፍቅር በእዉነት ደስ ይለዋል “ ፤ እዉነት በሌላ ሰዉ ህይወት ላይ በተገለጠ ጊዜ ታላቅ ደስታን ያገኛል ፡፡
- “ ፍቅር ሁሉንም ይታገሳል “ ፤ በአደባባይ ላይ ስለሌላ ሰዉ ህይወት ዉድቀት/ስህተት ዝም ይላል ፡፡
- “ ፍቅር ሁሉን ያምናል “ ፤ በሌሎች ላይ የማይናወጥ ልበ ሙሉነት እና እምነትን ይገልፃል ፡፡
- “ ፍቅር ሁሉን ተስፋ ያደርጋል “ ፤ የአሁኑን ፍፁም አለመሆንን ባለመመልከት በሌሎች ህይወት ላይ በልበ ሙሉነት ወደፊታቸዉን ይጠብቃል ፡፡
- “ ፍቅር በሁሉም ይፀናል “ ፤ ግንኙነትን ለመስበር ሁሉንም የሰይጣንን ማጥቃቶች ይቋቋማል ፡፡
1-ቆሮንቶስ (13፡ 8-13)፡ እነዚህ ቁጥሮች “ ስለ ፍቅር ቀጣይነት “ ያሳያሉ ፤ ፍቅር በፍፁም አያበቃም ፤ ትንቢት፣ በልሳን መናገር እና እዉቀት መጨረሻቸዉ ይመጣል ፡፡ የሆነ ስፍራ ላይ ስጦታዎቹ ወደ መጨረሻ ላይ ይመጣሉ፡ “ ፍፁሙ በመጣ ጊዜ “ ፤ የኔልሰን ማብራሪያ ቁጥር 10 ለመተርጎም ጥቂት አማራጮችን ያቀርባል፡
ስጦታዎች በሐዋሪያት ዘመን መጨረሻ ላይ ያበቃሉ ፡፡
ስጦታዎች የመፅሀፍት ህግ መጠናቀቅ ላይ ይጠናቀቃሉ - ሁሉም 66 የመፅሀፍ ቅዱስ መፅሀፍት መጠናቀቅ ላይ ፡፡
ስጦታዎች “ የሁሉም አማኞች እና የቤተ ክርስቲያን ግንኙነት እና ተግባር በሚቀየርበት እና ከዚህ በኋላ በከፊል አስፈላጊ በማይሆንበት በክርስቶስ ሁለተኛ መምጣት ላይ ያበቃሉ “ ፡፡
በቁጥር 11 አምስት ጊዜ ከልጅነት ወደ ጎልማሳነት ስላለዉ ጊዜ ያወራል ፤ የእግዚአብሄርን መገለጥ ፊት ለፊት እስከምናየዉ ድረስ እስከ መጨረሻዉ ድረስ ሙሉ አይሆንም (ቁጥር 12) ፡፡ ፍጹምነት እስኪመጣ ድረስ በእነርሱ እነዚህ ስጦታዎች እና ተግባሮች አሉን ፤ ከእነዚህ ሁሉ ስጦታዎች እምነት፣ ተስፋ እና ፍቅር ፀንተዉ ይቆማሉ - ታላቁ ስጦታ ግን ፍቅር ነው (13) ፡፡
መደምደሚያ
ቃሉን ለራሳችሁ እንድታጠኑት ላበረታታችሁ እፈልጋለሁ ፤ ወደ 1ቆሮንቶስ በደንብ በጥልቀት አንብቡ ፡፡ እንደ ምን ታዩታላችሁ ? ከእነዚህ ቃላቶች ኋላ ያለዉ እዉነት ምንድን ነው ?
Bruce L. Bugbee and Don Cousins, Network: The Right People, in the Right Places, for the Right Reasons, at the Right Time (Grand Rapids: Zondervan, 1994, 2005), p. 91.
Bugbee and Cousins, p. 91.
Bugbee and Cousins, p. 91.
Bugbee and Cousins, p. 91.
Thomas L. Constable, Dr. Constable’s Exposition Bible Study Notes: 1 Corinthians, p. 247; available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/1corinthians.pdf.
Constable, p. 247.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1598.
Constable, p. 251.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1481.
ጥያቄዎች
-
በፍቅር ያልተያዘ መንፈሳዊ ስጦታ መኖር ችግሩ ምንድን ነው ?
-
በ 1ቆሮ (13፡ 4-7) እንደ ተጠቀሰው የመፅኀፍ ቅዱሳዊ እዉነተኛ ፍቅር ጥራቶች ምንድን ናቸው ? ከእነዚህ ጥራቶች ዉስጥ እናንተን ለመርዳት እግዚአብሄር የሚፈልገዉ የትኛዉን ጥራት ነው ?
-
ጳዉሎስ ፍቅር ይበልጣል በምን አለ ? ፍቅር ከእነዚህ ነገሮች ለምንድን ነዉ የበለጠው ? (1ዮሐ 4፡ 8, 16)
-
የክርስቲያን ህይወት ሰዎስቱ ታላላቅ ክትትሎች/የሚይዛቸዉ ምንድን ናቸው ? የክርስትና ህይወታችሁ በምንድን ላይ ያተኮረ ነው ? በእዉነት በይበልጥ የምትፈልጉት ምንድን ነው ?
-
በ 1ቆሮንቶስ 13 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Corinthians 13:2–3
“If I have the gift of prophecy and understand all mysteries and all knowledge, and if I have all faith so that I can move mountains but do not have love, I am nothing. And if I donate all my goods to feed the poor, and if I give my body in order to boast but do not have love, I gain nothing.”
የመንፈስ ስጦታዎች ሁሉ ሊኖሩህ ይችላል እናም ለመንግስቱ ስራም ልትጠቀማቸው ትችላለህ ነገር ግን ፍቅር ከሌለህ ምንም አይጠቅምህም ፡፡ ፍቅር አስፈላጊ ነው ከመንፈስ ስጦታዎችም ይበልጣል ፡፡ ፍቅር ከሌለ ፣ የትኛውም ስጦታ ከንቱ ነው ፡፡
ስለዚህ እንዴት ነው የምትወደው ? ሌሎችን የምትወደው ከሰማዩ አባትህ በተሰጠህ ፍቅር ነ ው ፡፡ የእግዚአብሔርን ፍቅር ስትቀበል ፣ በመንፈስ ስትመላለስ ሌሎችን መውደድ እስከምትችል ድረስ ይሞላሃል ፡፡ በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ፍቅር አንደኛ ነው ፡፡ እግዚአብሔር የሰጠኝን ስጦታ አላውቅም ብለህ የምታስብ ከሆነ ፣ ክርስቶስ እንደወደደህ ሁሉ ሌሎችን በመውደድ ጀምር ፡፡ አስታውስ የእግዚአሔር ታላላቆቹ ትዕዛዛት እርሱን መውደድና ሌሎችን መውደድ ናቸው ፡፡ ዛሬ በደንብ ተንፍስና የአባትህን ፍቅር ተቀበል ፡፡ ከዚያም ሂድና ሌሎችን ውደድ !
" ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም ። “
-1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13 :2- 3
ተጨማሪ ጥቅስ
- ማርቆስ 12 : 29-31 -“ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው። ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ። እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው፥ አንተም በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም አሳብህ በፍጹምም ኃይልህ ጌታ አምላክህን ውደድ የምትል ናት። ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት። ሁለተኛይቱም። ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የምትል እርስዋን የምትመስል ይህች ናት። ከእነዚህ የምትበልጥ ሌላ ትእዛዝ የለችም
- 1ኛ ቆሮንቶስ 13፡4-8 –“ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም፤ የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤. ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤ ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል ።ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም ፡፡
- ቆላስይስ 3፡14- “በእነዚህም ሁሉ ላይ የፍጻሜ ማሰሪያ የሆነውን ፍቅርን ልበሱት።
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።