Paul's Letters 1 Corinthians

Unity In The Body of Christ

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ The Last Adam 1 Corinthians 12 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 514 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የዚህ ሳምንንት ጥናት ጳዉሎስ ለቤተ ክርስቲያን “ ወተት “ ብሎ ስለሚጠራዉ ሳይሆን “ እዉነተኛ ስጋ “ ስለሆነዉ ነገር ነው ፡፡ በምዕራፍ 10 እስራኤላዊያን እንዴት የእግዚአብሄርን መገኘት እንደ የቀመሱ ቢሆኑም ለእርሱ ያልታዘዙ እንደ ነበሩ ተመልክተናል ፤ እግዚአብሄር አድርጎላቸዉ የነበረዉን እንደ ዋስትና ወሰዱት ፡፡ በምዕራፍ 11 ጳዉሎስ ቆሮንቶሳዊያንን እርሱ ክርስቶስን እንደሚመስል እኔን ምሰሉ ብሎ ነገራቸው ፤ ከዚያም ቀጥሎ እግዚአብሄር ራሷ የነበረና ሴቶች እና ወንዶች የራሳቸዉ ተግባር የሚኖርባትን የቤተ ክርስቲያንን መዋቅር ዉስጥ ሰራ ፡፡ ዋረን ዋይርስቤ “ የአንድ ግለሰብ የማደጊያ መለኪያው የሚያድግ መረዳቱ እና አካላዊ ለዉጡ ነው ፤ በመንፈሳዊ ህይወትም ተመሳሳይ ነገር ነው፡ በክርስቶስ ስንበስል የክርስቶስ አካል ስለ ሆነችዉ ቤተ ክርስቲያን የተሸለ መረዳት እንደምናገኝ “ ይፅፏል ፡፡ በመፅኀፍ ላይ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ክርስቶስ አካል ከመጥቀስ በተጨማሪ ሌሎች ቃላቶችን ተጠቅሟል ለምሳሌ “ እንደ አንድ ቤተሰብ፣ እንደ አንድ ሰራዊት፣ እንደ አንድ ቤተ መቅደስ እና እንደ ሙሽራ “ ፡፡

በእነዚህ ሰዎስት መልዕክቶቹ ላይ (1ቆሮንቶስ 12-13, ሮሜ 12, ኤፌ 4) ጳዉሎስ ሰዎስት ፍሬ ነገሮችን/ዋና ዋና ሀሳቦችን አብሯርቷል (አንድነት፣ ብዙሀንነት እና እድገት/ብስለት) ፡፡ ዛሬ በ 1ቆሮንቶስ 12 ላይ ከእነዚህ ሰዎስት ፍሬ ነገሮች ዉስጥ ሁለቱን እንመለከታለን ፤ ሰዎስተኛዉን ፍሬ ነገር (እድገት) የሚለዉን በምዕራፍ 13 እንሸፍነዋለን ፡፡ የእነዚህ ሰዎስት ጭብጥ ነገሮች እድገት/ለዉጥ - ከአንድነት ወደ ብዙሀንነት ከዚያ ወደ እድገት - ከላይ በጠጠቀሱት በሰዎስቱም የጳዉሎስ መልዕክቶች ላይ የሚገኙ ናቸው ፡፡ ይህ መነሻ ኃሳብ በምዕራፍ 12 ሁለተኛ ክፍል ላይ የተዘረዘሩትን መንፈሳዊ ስጦታዎች ለመረዳት አስፈላጊ ነው ፡፡

ትምህርት

1-ቆሮንቶስ (12፡ 1-7)፡ በአካል ዉስጥ አንድነት ፤ ጳዉሎስ መንፈስ ቅዱስ ለአማኞች የሆነ ነገር ሰጥቷቸዉ እንደ ነበር ፃፈ (ቁጥር 1) ፡፡ ዋይርስቤ “ በበዓለ ሀምሳ ቀን ለአካሉ እስትንፋስን የሰጠው እና በአካል ዉስጥ እና በኩል ያከለከለዉ መንፈስ ነበር ፤ በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን በሚያሳዝን ሁኔታ አባላቱ መንፈሳዊ ስጦታዎችን እየተጠቀሙ በስጋ መንገድ እየሄዱ መንፈስ ቅዱስን እያሳዘኑት ነበር ፤ ዋጋ ባላቸዉ መሳሪያዎች ጎልማሶች መሆን ሲገባቸው በአሸንጉላሊት ህፃናትን መስለዉ ስለ ነበር ማደግ/መብሰል አስፈለጋቸዉ “ በማለት ይገልፃል ፡፡

በቁጥር 2 ጳዉሎስ የአሕዛብነት ዉርሳቸዉን/ታሪካቸዉን ጠቀሰ ፤ የኔልሰን ማብራሪያ “ አሕዛቦች ጳዉሎስ ያለመቀበል ሁኔታቸዉን ለመግለፅ እንደተጠቀመው እንደ አረመኔ እና እንደ ተማሩ ይታዩ ነበር ፤ ባለመቀበላቸዉ ምክንያት እግራቸዉ እንዳመራቸዉ ይሄዱ ወይም ያደርጉ ነበር “ በማለት ይናገራል ፡፡ “ መናገር የማይችሉ ጣዖቶች “ የሚለዉ ሀረግ “ በብሉይ ኪዳን ጣዖት አምልኮ የተለመደ የሆነ ቆሮንቶሳዊያን በፍጥነት እንደ ሚያስተዉሉት “ “ ዱዳ ጣዖት “ በሚለዉ ገለፃ ሊተረጎም ይችላል ፡፡ ጳዉሎስ ከእነርሱ ዉስጥ ጥቂቶች በመንፈስ ቅዱስ ብቻ “ ኢየሱስ ጌታ ነው “ ማለት እንደሚችሉ እና ማንም በእግዚአብሄር መንፈስ “ ኢየሱስ የተረገመ ነው “ ማለት እንደማይችል አብራራ ፡፡

ጳዉሎስ መንፈስ ለአማኞች ያከፋፈላቸዉ የተለያዩ የፀጋ ስጦታዎች እንደ ነበሩ ተናገረ (ቁጥር 4) ፤ የተለያዩ አገልግሎቶች ነበሩ ነገር ግን ተመሳሳይ/አንድ ጌታ አለ (ቁጥር 5) እንዲሁም በአንዱ/በተመሳሳዩ እግዚአብሄር የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ስራዎች ነበሩ (ቁጥር 6) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ አብ ስጦታዎቹን በመተግበር ለአማኞች ጉልበትን/ኃይልን እንደሚሰጥ “ ይገልፃል ፡፡ እያንዳንዱ አማኝ ለቤተ ክርስቲያን ጥቅም እንዲጠቀም ከመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ተሰጥቶቷል (ቁጥር 7) ፤ ያ ማለት “ እግዚአብሄር በአማኞችቤተ ክርስቲያንን(መላዉን አካል) ለመጥቀም እንጂ ግለሰብ የሆነ ክርስቲያንን ለመጥቀም አይሰራም “ ማለት ነው ፡፡

1-ቆሮንቶስ (12፡ 8-10)፡ እነዚህ ስጦታዎች ለእግዚአብሄር ክብር የሚያመጡ በቁጥር (8-10) ያሉ ዘጠኝ ስጦታዎች ናቸው ፡፡ በእነዚህ ስጦታዎች ላይ ማስተማር እፈልጋለሁ ምክንያቱም አብዛኞቻችን ስጦታዎችችንን የት ጋር መፈለግ እና መረዳት እንዳለብን ስለማናውቅ ፤ ይህ መንፈስ ቅዱስ ስለሚያስፈራን ነዉ ግን አያስፈራም (ሮሜ 8፡ 14) ፡፡ እነዚህ ስጦታዎች በፍቅር መገለጥ አለባቸው (1ቆሮንቶስ 13) ፤ እነዚህ ስጦታዎች ለእኛ ዛሬም ይገኛሉ ፡፡

  • ከመንፈስ ቅዱስ የጥበብ ስጦታ (ቁጥር 8)፡ መንፈሳዊ እዉነቶችን በተጋባር የማዋል ችሎታ ፡፡
  • ከመንፈስ ቅዱስ የእዉቀት ስጦታ (ቁጥር 8)፡ “ ምናልባትም ይህ ስጦታ በመጀመሪያዉ ክፍለ ዘመን መግለጥ ነዉ ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ ከእግዚአብሄር መገለጥ ተለይቶ ሊታወቅ የማይችለዉን በቃሉ ዉስጥ ያሉትን ሚስጥሮች በማስተዋል የእግዚአብሄርን እዉነት የመረዳት እና የመናገር ችሎታ ነው “፡፡
  • ከመንፈስ ቅዱስ የእምነት ስጦታ (ቁጥር 9)፡ “ ላልተለመዱ ተግባሮች እግዚአብሄርን የማመን አቅም ነው “ ፡፡

በእነዚህ ስጦታዎች ዉስጥ ምንም አይነት ደረጃ የለም ፤ ከየትኛዉም ከሌላዉ የሚበልጥ ስጦታ የለም ፡፡ እነዚህ ሁሉም በክርስቶስ አንድነትን ለማምጣት ጠቃሚዎች ናቸው ፡፡

በመንፈስ ቅዱስ የመፈወስ ስጦታ (ቁጥር 9)፡ ብዙ አማኞች በፈዉስ ያምናሉ ግን አይጠሩትም ፤ ፈዉስን እንዲያመጣ ለእግዚአብሄር ይፀልያሉ ነገር ግን በሰዉ በኩል እግዚአብሄር እንዲፈዉስ አይጠብቁም ፡፡ ኢየሱስ በአገልግሎቱ ዉስጥ የፈዉስ ስጦታን ተጠቅሟል ፡፡ ሰዎች የፈዉስ ስጦታን ያለ አግባብ በሚጠቀሙበት ወይም በሚያስቀምጡት ጊዜ ሰዎች በሁሉም ስጦታዎች ላይ መጠየቅ ይጀምራሉ ፡፡ ፈዉስ ማለት በሆነ ሰዉ ላይ የእግዚአብሄር መንካት ማለት ነው ፡፡

የተዓምራት ስጦታ (ቁጥር 10)፡ “ እንደ ሙሴ፣ እንደ ነቢያት ወይም ደግሞ በወንጌል ላይ እንደሆኑት አይነት ተግባራትን የማድረግ ችሎታ ነው “ ፡፡

የትንቢት ስጦታ (ቁጥር 10)፡ ለማበረታታት/ለማነፅ በመንፈስ ቅዱስ የሆነ መገለጥ ፡፡

የመለየት ስጦታ (ቁጥር 10)፡ በመናፍስቶች መካከል የመለየት ፡፡

በልሳን የመናገር ስጦታ (ቁጥር 10)፡ በተለያዩ ቋንቋዎች መናገር ፡፡

የመተርጎም ስጦታ (ቁጥር 10)፡ የልሳኖች ትርጉም ፡፡

በቁጥር 11 ጳዉሎስ በእያንዳንዳቸዉ ስጦታዎች ዉስጥ አንድ መንፈስ ይሰራ እንደ ነበርና ለመረጣቸዉ ስጦታን እንደሰጣቸዉ አብራርቷል ፡፡ እነዚህ ሁሉም ስጦታዎች አሁንም አሉ መንፈስ ቅዱስም ለሚመርጣቸዉ ይሰጣቸዋል / ያሰራጫቸዋል ፤ እነዚህ ስጦታዎች የክርስቶስ አካል የተለያዩ ክፍሎች ሲሆኑ አካሉንም ሙሉ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ናቸው ፡፡

1-ቆሮንቶስ (12፡ 14-20)፡ በአካሉ ዉስጥ ብዙሀንነት ፡፡ በዚህ ፅሁፍ ዉስጥ የአካል ክፍሎች ከቀረዉ ክፍል በመለያየት በራሳቸዉ ለመስራት ከሞከሩ ምን ሊሆን እንደሚችል በጣም ብዙ ነገር አለ ፡፤ ሁላችንም የአካሉ አስፈላጊ ክፍሎች ነን ፡፡

መደምደሚያ

በአዲስ ኪዳን የተዘረዘሩት የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች አሁንም የተሰጡ ሲሆኑ ለቤተ ክርስቲያን አንድነት ለማምጣት በእግዚአብሄር ጥቅም ላይ እንደዋሉ በቀላሉ ተቀምጧል ፡፡

  1. Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1989), p. 607.

  2. Wiersbe, p. 607.

  3. Wiersbe, p. 607.

  4. Wiersbe, p. 607.

  5. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1478.

  6. Nelson’s Commentary, p. 1478.

  7. Nelson’s Commentary, p. 1478.

  8. Nelson’s Commentary, p. 1478.

  9. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1592.

  10. Nelson’s Commentary, p. 1478.

  11. Nelson’s Commentary, p. 1478.

ጥያቄዎች

  1. በዉስጣቸዉ የሚያድር መንፈስ ቅዱስ ያላቸዉ ጥላቻን የማያደርጉ ናቸው ? መንፈስ ቅዱስ ያላቸዉ ሰዎች ምን ይላሉ ወይስ ያደርጋሉ ? (1ቆሮ 2፡ 8-14, ዮሐ 15፡ 26, 1ዮሐ 5፡ 6-8)
  2. ጳዉሎስ ቤተ ክርስቲያንን የገለፀባቸው ሁለት መንገዶች ምንድን ናቸው ? (1ቆሮ 12፡ 4-6, 11, 27-31)
  3. ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ አካል ከሆነች ሰዎች ቤተ ክርስቲያንን ሳይሆን ኢየሱስን እወደዋለሁ ሲሉ እንዴት ይሰማችኋል /ትረዱታላችሁ ? ይህ ቀላል/የሚቻል ነዉን ?
  4. ጳዉሎስ ክርስቲያን ችላ ሊላቸዉ ወይም ላያዉቃቸዉ የሚገባ ነገሮች በማለት የጠቀሳቸዉ ሰዎስት ነገሮች ምንድን ናቸው ? (ሮሜ 11፡ 25, 1ቆሮ 12፡ 1, 1ተሰ 4፡ 13)
  5. በዚህ ምዕራፍ ላይ የተጠቀሱት ጥቂት መንፈሳዊ ስጦታዎች ምንድን ናቸው ? ሁላችንም የተለዬ ስጦታ መሰጠታችን ለቤተ ክርስቲያን ለምን አስፈላጊ/ጠቃሚ ሆነ ? እርስ በእርስ ባለዉ ስጦታ ከመቅናት ምን አይነት ጉዳይ ሊነሳ ይችላል ?
  6. በ 1ቆሮንቶስ 12 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Corinthians 12:11–12

“But one and the same Spirit is active in all these, distributing to each person as He wills. For as the body is one and has many parts, and all the parts of that body, though many, are one body—so also is Christ.”

እንደ መንፈስ ቅዱስ ስጦታ ፣ ለክርስቶስ አካል ጥቅምና የእግዚአብሔርን መንግስት ለመገንባት ፣ እያንዳንዱ ሰው ስጦታን ተቀብሏል ፡፡ እግዚአብሔር ለአካሉ ጥቅምን ለማስገኘት በመንፈስ ቅዱስ በኢያንዳንዱ ሰው ውስጥ ያለውን ስጦታ ይቀሰቅሳል ፡፡ እርሱ ለህዝቦቹ ጥበብ ፣ እውቀት ፣ እምነት ፣ ፈውስ ፣ ታምራት ፣ ትንቢት ፣ ልሳን እናም ልሳንን መተርጎም ይሰጣል ፡፡ እግዚአብሔር ትላንት ዛሬም ነገም ያው ነው ፡፡ ስለዚህም መንፈሱ ከአመታት በፊት እንዳደረገው ሁሉ ዛሬም የክርስቶስን አካል ኃይል ያስታጥቃል ፡፡

ለአካሉ የእኔ ስጦታ ምንድን ነው ? በማለት ትጠይቁ ይሆናል ፡፡ ልክ እያንዳንዱ የአካል ክፍላችሁ ለሚበልጠው ለመላ አካላችሁ ደህንነት በጋራ እንደሚሰራ ሁሉ ፣ የክርስቶስም አካል የእግዚአብሔርን መንግስት ለመገንባት በአንድነት ይሰራል ፡፡ ሁሉም ስጦታዎች በአንድነት ይሰራሉ እናም ሁሉም አስፈላጊ ናቸው ፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ ፣ በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ድርሻ አለህ ፡፡ ፍቃዱን ትፈጽም ዘንድ መንፈስ ቅዱስ በስጦታዎቹ እንድያስታጥቅህ እንድያጎለብትህ በቅንነት ጠይቅ ፡፡ ከዚያም ወደ ሚጎተጉትህ ወደ መንፈስ ቅዱስ ራስህን ዝቅ በማድረግ በትህትና ሂድ ፡፡ እርሱን ታመን በእምነትም ውጣ ፡፡ ለፈውስ ጸልይ ፡፡ ጌታ በሁኔታዎች ውስጥ ጥበብን እንዲሰጥህ ጸልይ :: በእምነት ካልወጣህ በቀር እንዴት የእግዚአብሔር ኃይልና ስጦታ እንደሚሰራ ፈጽሞ ልታውቅ አትችልም ፡፡

" ይህን ሁሉ ግን ያ አንዱ መንፈስ እንደሚፈቅድ ለእያንዳንዱ ለብቻው እያካፈለ ያደርጋል። አካልም አንድ እንደ ሆነ ብዙም ብልቶች እንዳሉበት ነገር ግን የአካል ብልቶች ሁሉ ብዙዎች ሳሉ አንድ አካል እንደ ሆኑ፥ ክርስቶስ ደግሞ እንዲሁ ነው "

  • 1ኛ ቆሮንቶስ 12 : 11-12

ተጨማሪ ጥቅስ

ሮሜ 12፡4-5 -“ በአንድ አካል ብዙ ብልቶች እንዳሉን፥ የብልቶቹም ሁሉ ሥራ አንድ እንዳይደለ፥ እንዲሁ ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን፥ እርስ በርሳችንም እያንዳንዳችን የሌላው ብልቶች ነን።

1ኛ ቆሮንቶስ 12፡17-20 –“ አካል ሁሉ ዓይን ቢሆን መስማት ወዴት በተገኘ? ሁሉም መስማት ቢሆን ማሽተት ወዴት በተገኘ? አሁን ግን እግዚአብሔር እንደ ወደደ ብልቶችን እያንዳንዳቸው በአካል አድርጎአል። ሁሉም አንድ ብልት ቢሆንስ አካል ወዴት በሆነ? ዳሩ ግን አሁን ብልቶች ብዙዎች ናቸው አካል ግን አንድ ነው ። “

ኤፌሶን 4፡11-13 – “ እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤ ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥ ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ።