Equal But Different Roles
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ The Last Adam 1 Corinthians 11 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በምዕራፍ 10 ጳዉሎስ ቆሮንቶሳዊያን አማኞችን እስራኤላዊያን እንዴት በእግዚአብሄር ላይ ጀርባቸዉን እንዳዞሩበት እና የእግዚአብሄርን ደስ አለማሰኘት እንዳገኙ ነገራቸው ፤ በሚያናድድ ሁኔታ ቆሮንቶሳዊያንም ያን ቅር ማሰኘት እያገኙት ነበር ፡፡ በምዕራፍ 11 ጳዉሎስ ትኩረታቸዉን ክርስቶስን ወደ መምሰል አመጣው ፡፡
ትምህርት
1-ቆሮንቶስ (11፡ 1-12)፡ ጳዉሎስ ቆሮንቶሳዊያንን እርሱ ኢየሱስን ስለሚመስል እርሱን መምሰል እንደሚችሉ ነገራቸው (ቁጥር 1) ፡፡ ይህ ልጆቻችን እንዲያደርጉት የምንፈልገዉ አይደለም - እኛን እንዲመስሉ በእምነታቸዉ እና በባህሪያቸዉ ሞደል እናደርጋቸዋለን ? በዚህ ላይ ብቻ ለማስተማር ስለማስብ ይህን ጥቅስ በጣም እወደዋለሁ ፡፡ ኢየሱስን ሙሉ ለሙሉ ህይወቴ ስለሚመስል ሰዎችን እኔን መስሉ ብዬ መናገር እችላለሁ ? በብዙ የኢየሱስን ህይወት ለመምሰል ላስወግዳቸዉ ወይም ልሸሻቸው ወይም ልንቋቋመዉ የምንችላቸዉ ነገሮች ምንድን ናቸው ? በቁጥር 1 ጳዉሎስ እስከዚህ ስፍራ እያስተማረ የነበረዉን ሁሉንም በአንድ ላይ እኔ ክርስቶስን እንደምመስልእኔንምሰሉ በማለት ጠቀለለው ፡፡
በቁጥር 2 ጳዉሎስ አንዳንድ ሰዎች በሚናገሩት ወቀሳና ግሰፃ መካከል መናገር ጀመረ - መልካም በሆነ ነገር ይጀምራል ከዚያ ወቀሳ ቀጥሎም በመልካም ነገር ያበቃል ፡፡ ስላስታወሱት እና አስተምሯቸዉ የነበረዉን ልምድ ስለጠበቁ አመሰገናቸው ፤ “ (ሌሎች ማጣቀሻዎች እንደሚያሳዩት) ልምዶቹ ለመለወጥ ከመምህራን እና ከወንጌላዊያን በቃል እዚህ ደረጃ ላይ የደረሱ የክርስትና እምነት ማዕከላዊ እዉነቶች ነበሩ “ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ቆሮንቶሳዊያን ብዙ ስህተቶችን አድርገዉ እንደ ነበር ነገር ግን ሙሉ ለሙሉ የተበላሹ እንዳልነበሩ ፤ በአንዳንድ ስፍራዎች ቆሮንቶሳዊያን ሐዋሪያዊ ትዕዛዞችን ተከትለዉ እንደ ነበሩ “ ይገልፃል ፡፡
በቁጥር 3 ጳዉሎስ ክርስቶስ የሰዉ ሁሉ እራስ እንደ ሆነ፣ ወንድ ደግሞ የሴት ራስ እንደሆነ እና እግዚአብሄር ደግሞ የክርስቶስ ራስ እንደ ሆነ አመለከተ ፤ “ ራስ “ የሚለዉ ቃል ስልጣን ወይም መነሻ ማለት ሊሆን ይችላል ፡፡ በአንድ ወንድ እና በአንድ ሴት መካከል ያለዉ ግንኙነት በበታችነት ላይ የተመሰረተ አይደለም - ኢየሱስ ከእግዚአብሄር ያነሰ አይደለም ሴትም ደግሞ ከወንድ ያነሰች አይደለችም ፡፡ ሁለቱንም ከመሰረዝ ዉጪ ከእነዚህ ንግግሮች ዉስጥ አንዱን መተዉ/መሰረዝ አትችሉም ያ ደግሞ መፅኀፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሄር እና ስለ ኢየሱስ ከሚያስተምረን በተቃራኒዉ ይሄዳል ፡፡
የኔልሰን ማብራሪያ “ መታዘዝ/መሸነፍ መተዉን እንጂ የበታችነትን አያመለክትም ፤ ክርስቶስ እና አግዚአብሄር እኩል መለኮት እንደሆኑ ወንድና ሴትም እኩል ሰዉ ናቸው ፤ ነገር ግን ኢየሱስ እና እግዚአብሄር አብ በእግዚአብሄር የማዳን እቅድ ዉስጥ የተለያዬ ተግባር ሴት እና ወንድም የተለያዬ ስራ ተሰጥቷቸዋል “ በማለት ይናገራል ፡፡ አንዳንድ ጊዜ የተሰጠንን ሚና እንደማንወደዉ አስባለሁ ፤ ነገር ግን እግዚአብሄር ለእያንዳንዳችን ግልፅ የሆነ ተግባር አለዉ ፡፡
በቁጥር 4 “ ፀሎት የአንድን ሰዉ ሀሳብ እና ፍላጎት ለእግዚአብሄር በመግለፅ ይከናወናል በተለይም እግዚአብሄርን በመጠየቅ “ ፡፡ ራሱን ተሸፍኖ የሚፀልይ/ትንቢት የሚናገር አንድ ወንድ እግዚአብሄርን ያዋርዳል ፤ ነገር ግን ራስዋን ሳትሸፈን የምትፀልይ/ትንቢት የምትናገር ሴት እግዚአብሄርን ታዋርዳለች (ቁጥር 5) ኮንስታብል የሴቶች ራስ ለምን መሸፈን እንደ ነበረበት ሰዎስት ምክንያቶችን ያቀርባል ፡፡ የመጀመሪያው ራሷን ለመሸፈን ልብስ ወይም አንገት ልብስ ትረሳ ይሆናል ፤ ሁለተኛው ምናልባትም ፀጉሯ ባጭር የተቆረጠ ስለሚሆን ራሷን ሙሉ ለሙሉ ስለማይሸፍንላት ፤ ሰዎስተኛው ሴቶች በአደባባይ ለምደዉት እንደ ነበረዉ ፀጉሯን ወደ ላይ ከማድረግ ይልቅ ወደታች ትታዉ ስለሚሆን ( 1ቆሮ 14፡ 34, 1ጢሞ 2፡ 12, 1ጢሞ 5፡ 16, ቲቶ 2፡ 3-4) ፡፡ በእነዚህ ጥቅሶች መሰረት ሴቶች በሴቶች እና በልጆች ላይ ትምህርትን ማድረግ ይችላሉ እያለ ይመስላል ፤ ይህ የሚያወዛግብ/ግራ የሚያጋባ ነው ፡፡ እንደ ማክአርቱር ገለፃ “ በቆሮንቶስ ባህል ስታገለግል እና ስታመልክ ፀጉሯን የተሸፈነች ሴት ለባሏ የተገዛች መሆኗን የሚያሳይ ምልክት ነበር “ ፤ ራስን መሸፈን የራስን ተግባር የመያዝ ምልክት ነው ፡፡ ማክአርቱር “ ሐዋሪያዉ በሁሉም ጊዜ በሁሉም ቤተ ክርስቲያን መሸፈኛ ወይም መከለያ እንዲለብሱ በሴቶች ላይ ፍፁም የሆነን ህግ እያወረደ አይደለም ነገር ግን በሴት እና በወንድ መካከል ያለዉ የተከበረ ተግባራቸዉ የመለኮት መሰረት ምልክት ስለሆነ በሁሉም ባህል የተከበረ እንዲሆን እየተናገረ ነው “ በማለት ቀጥሎ ገልፆአል ፡፡ የራስ መሸፈኛ ባይኖርም አሁንም እግዚአብሄር በቤተ ክርስቲያን እያንዳንዳቸዉ የተለያዬ ተግባር አላቸዉ እያለ እንደሆነ አስባለሁ ፡፡ በአሁኑ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን እየሆነ ያለዉ ግን እነዚህ ተግባሮች ተቀላቅለዉ እያየናቸዉ ነው ፡፡
ወደ ኋላ 1ቆሮ (11፡ 3) ላይ በመመለስ ወንድ ራሱን መሸፈን የለበትም ምክንያቱም የእግዚአብሄር ክብር ማሳያ ሲሆን ሴት ደግሞ የወንድ ክብር እንደሆነች የሚገልፀዉን ቁጥር 7 ላይ መመልከት ያስፈልገናል ፡፡ ቁጥር 8 እነዚህን ሁሉንም በአንድ ላይ ይጎትታቸዋል- ወንድ ከሴት አልመጣም ሴት ከወንድ መጣች እንጂ ፡፡ ጳዉሎስ ወንድ ለሴት አልተፈጠረም ሴት ለወንድ ተፈጥራለች እንጂ አለ ፡፡ ራስን በመሸፈን ላይ ብቻ በማናተኩር ጊዜ ወንድ እና ሴት እንዲፈፅሟቸዉ የተሰጧቸዉን የተለያዩ ተግባሮች እናያለን የተለያዬ ነዉ ነገር ግን አስፈላጊና ጠቃሚ ነው ፡፡ ይህ ሴት በቤት ላይ ብቻ የምታሟላው ተግባር አላት ሌላ ህይወት የላትም ማለት አይደለም ብዙ ሰዎች ያላቸዉ ስዕል ያ ቢሆንም እንኳን ፡፡ በዚህ መፅኀፍ መሰረት ሴት ለወንድ ስለተፈጠረች በአንድ ላይ የእግዚአብሄርን ክብር ማንፀባረቅ ይችላሉ ፡፡
ጳዉሎስ ሴት በመለዓክት ምክንያት በራሷ ላይ የስልጣን ምልክት እንደሚኖራት መግለፁን ቀጠለ ፤ ይህ ማለት መለዓክት እየተመለከተ በነበር ጊዜ ለአንድ ወንድ የምትታዘዘን አንዲት ሴት ብቻ ይመለከታሉ ማለት ነው ፡፡ ሴት ያለወንድ የሆነች አይደለችም ወንድም ደግሞ ያለ ሴት አይሆንም (ቁጥር 10-11) ፡፡ ኮንስታብል “ በራሷ ላይ ያለዉ የዚያ ስልጣን ምልክት “ ምን ሊሆን እንደሚችል አራት ነገሮችን አጋርቷል
- ምልክቱ በእርሷ ላይ ስልጣን የተሰጠዉ ወንዱ ሊሆን ይችላል ፡፡
- ምልክቱ በራሷ ላይ ያለዉ መሸፈኛዉ ሊሆን ይችላል ፡፡
- የራስ መሸፈኛዉ በክርስቶስ አዲስ ነፃነት እንደነበራት ሊያሳይ ይችላል ፡፡
- ሴቷ በራሷ ላይ ስልጣን ስለ ነበራት የየሚያስደስታትን ሁሉ ማድረግ ትችላለች ፡፡
ሴት እና ወንድ በጌታ እኩል ግን የተለያዩ ናቸው ፡፡ በማህበረሰቡ ዉስጥ እየሆነ ያለዉ ወንድ ቤተሰቡን ትቶ ይሄዳል ሴት ደግሞ የወንድን ተግባር እንዲሁም የራሷን የመዉሰድ ነው ፡፡ ሴት ከወንድ መጣች ወንድ ደግሞ በሴት በኩል መጣ ሁሉም ነገር ደግሞ ከእግዚአብሄር መጣ (ቁጥር 12) ፡፡
መደምደሚያ
ዋናዉ ሀሳብ ሁል ጊዜ ስራችን ክርስቶስን ማንፀባረቅ ነዉ የሚል ነው ፡፡ የግል ጉዳዮቻችን መወገድ አለባቸው ምክንያቱም እኛ ስለምንፈልገዉ ነገር ሳይሆን እግዚአብሄር ስለሚፈልገዉ ስለሆነ ፡፡ ኑሮአችን ከክርስቶስ ጋር የግል ግንኙነት ያለዉ መሆን አለበት ፡፡
1 Charles Kingsley Barrett, A Commentary on the First Epistle to the Corinthians, Harper’s New Testament Commentaries series (New York: Harper & Row, 1968), p. 247; quoted in Thom- as L. Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes, p. 186; available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/1corinthians.pdf.
6 Gordon D. Fee, The First Epistle to the Corinthians, New International Commentary on the New Testament Series (Grand Rapids: Wm. B. Eerdman’s Publishing, 1987), pp. 495–97, 509–501; cited in Constable, p. 189.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1475.
Nelson’s Commentary, p. 1476.
Nelson’s Commentary, p. 1476.
Thomas L. Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: 1 Corinthians, p. 188; available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/1corinthians.pdf.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1588.
MacArthur, p. 1588.
MacArthur, p. 1588.
ጥያቄዎች
-
በእናንተ የግል አስተያየት 1ቆሮ (11፡ 4-7) በግልፅ ስለ ወራሽ የሚያወራ ነዉ ወይስ ሌላ ነገር ሊያመለክት ይችላል ? ሌላ ምን ትርጉም ሊኖረዉ ይችላል ?
-
1ቆሮ (11፡ 20-22) ስታነቡ ከአሁኑ የቤተ ክርስቲያን መሰባሰብ ጋር ተመሳሳይ ነገር ይናገራል ? ይህ የአሁን ችግር ነዉ ብላችሁ ታምናላችሁ ? በምን መንገድ ?
-
በ 1ቆሮ (11፡ 27) ላይ “ በአካሉ ላይ ኃጢዓት ታደርጋላችሁ “ ሲል ምን ማለቱ ነው ? ስለዚህ ነገር ለመፈፀም ምን ማለት አስፈልጎታል ? ያ ምን ይመስላል ? ጥቂት ምሳሌ ስጡ
-
በ 1ቆሮንቶስ 11 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Corinthians 11:1
“Imitate me, as I also imitate Christ.”
ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች “ እኔ ክርስቶስን እንደምመስል ፣ እናንተ ደግሞ እኔን ምሰሉ ፡፡ “ ይላቸዋል ፡፡ ጳውሎስ ኢየሱስ በተመላለሰበት አካሄድ እንደዚያው ተመላለሰ ፡፡ ለአማኞች ኑሯቸውን እንዴት ሊኖሩ እንደሚገባቸው ያስቀመጠላቸውን ምሳሌ ፣ ጳውሎስ በትህትና ያውቀዋል ፡፡ ሌሎች የእናንተን ፍጹምነት እንድኮርጁና እንደ እናንተ ለመሆን እንድጥሩ እግዚአብሔር ፍጹም ህይወት እንድትኖሩ አልጠራችሁም ፡፡ “ የእግዚአብሔር ጸጋ ይበቃኛል ምክንያቱም ኃይሉ በድካሜ ስለሚገለጥ ፡፡” ጳውሎስ ይህንን በማለት የመጀመሪያው ነበር ፡፡ ጳውሎስ ጠንካራ ሆኖ ተገልጦ ሊሆን ይችላል ነገር ግን በጳውሎስ ድካም ውስጥ ፍጹም ሆኖ የተገለጠው የእግዚአብሔር ጸጋና ኃይል ነበር ፡፡ በቃ እንድህ ነው እግዚአብሔር የሚሰራው ፡፡
ስለዚህ ክርስቶስን መምሰል ሌሎችን ለመውደድ በእርሱ ኃይል መራመድን ፤ ሌሎችን ይቅር ማለትን እናም በትህትና ህይወትን ለሌሎች አሳልፎ መስጠትን ያካትታል ፡፡ በእርሱ ስትኖሩ በውስጣችሁ የሚሰራው የክርስቶስ ፍቅር ነው ፡፡ ሰዎች እናንተን ሲመስሉ ፣ ያለምንም ድካም ፍጹምነትን ማየት አያስፈልጋቸውም ፡፡ ሰዎች ድካማችሁን ፣ ክፍተታችሁን የተሰባበረውን ክፍላችሁን እንዲያዩ ፍቀዱላቸው ፡፡ በድካማችሁ ውስጥ ነው የኢየሱስ ፍቅርና ብርሃን የሚያንጸባርቀው ፡፡ እናም ይህ ሌሎች እንዲያዩት የምትናፍቀው የእግዚአብሔር አስደናቂ ጸጋና የክርስቶስ ኃይል ነው ፡፡
" እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ። "
- 1ኛ ቆሮንቶስ 11 : 1
ተጨማሪ ጥቅስ
- 2ኛ ቆሮንቶስ 12፡9— “ እርሱም። ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ።
- ፊልጵስዩስ -2፡5-8 — “ በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን። እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ። “
- 1ኛ ዮሐንስ 2፡6— “ በእርሱ እኖራለሁ የሚል እርሱ እንደ ተመላለሰ ራሱ ደግሞ ሊመላለስ ይገባዋል ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።