Warnings From Israel's Past
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ The Last Adam 1 Corinthians 10 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በዚህ ሳምንት ትምህርት ዉስጥ ለቆሮንቶስ በጳዉሎስ ፅሁፍ በብዙ ግራ የሚያጋቡ ምዕራፎችን እንሸፍናለን ፡፡ በመፅሀፍ ቅዱስ ዉስጥ እያነበቡ መቀጠል በጣም ቀላል ነዉ ነገር ግን የእግዚአብሄር ቃል ለእናንተ ምን እንዳላችሁ እንድታገኙ እሞግታችኋለሁ ፤ እኔ የምላችሁን ከማዳመጥ በተጨማሪ ለራሳችሁ የእግዚአብሄርን ቃል በመቆፈር በመልካም አፈር ላይ ቃሉ እንደተተከለ ስትሆኑ አስቸጋሪ ጊዜ በሚመጣ ጊዜ ያመናችሁትን ታውቁታላችሁ ፡፡
ቆሮንቶስልክ እንደ ላስቬጋስ አይነት ከተማ ነበረች ፡፡ ጳዉሎስ በቆሮንቶስ ያሉት አማኞች ከቀድሞ አባቶቻቸዉ ከእስራኤላዊያን እንዲማሩ ፈለገ ፤ እስራኤላዊያን ብዙ በረከቶችን አገኙ - ከእግዚአብሄር ጥበቃን፣ ከእግዚአብሄር ምሪትን እና ከእግዚአብሄር ታምራትን - ይሁን እንጂ “ እግዚአብሄር ከእነርሱ በሚበዙት ደስ አላለዉም “ (ቁጥር 5) ምክንያቱም በእግዚአብሄር ላይ ጀርባቸዉን ስላዞሩ ፡፡ ለቆሮንቶስ በጳዉሎስ መልዕክት ዉስጥ በቆሮንቶስ በነበሩት አማኞች እግዚአብሄር ደስተኛ እንዳልነበር እናያለን ፤ ለእነርሱ “ ህይወት ሰጪ መንፈስ “ በነበረዉ በሁለተኛዉ አዳም (1ቆሮ 15፡ 45) በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የተትረፈረፈ ፀጋን እና ሞገስን ሰጣቸው ፤ ይሁን እንጂ ቆሮንቶሳዊያን እስራኤላዊያን አድርገዉት እንደ ነበረው ወደ ማህበረሰቡ እና ለአባቢዉ ባህል ሰጡት ፡፡ የእግዚአብሄር እጅ በእነርሱ ላይ ብትሆንም እንኳን እርሱን አለመቀበልን በመምረጥ እንደ ባህል እንደ ስጋ እና እንደ ሰይጣን ፈተና ኖሩ ፡፡
ትምህርት
1-ቆሮንቶስ (10፡ 1-2)፡ ጳዉሎስ እስራኤልን እንደ ምሳሌ ተጠቀመ ፡፡ ሁሉም እስራኤላዊያን ከደመናዉ ስር እና በዉሃዉ ዉስጥ ያለፉ ነበሩ (ቁጥር 1) ፡፡ ሁሉም በደመናዉ እና በባህሩ በሙሴ የተጠመቁ ነበሩ (ቁጥር 2) ፤ ደግመዉ ደግመዉ እስራኤላዊያን የእግዚአብሄርን በረከት አግኝተዉታል ፡፡ ከአዲስ ኪዳን አመለካከት ኮንስታብል ቶም “ ጥምቀት በእምነቱ ወይም በእምነቷ የአማኞች ነለያ ዉጫዊ የመግለጫ አላማ ነው “ ብሏል ፡፡ እስራኤላዊያን እርሱን እንደተከተሉት በሚያመለክት ሁኔታ “ ወደ ሙሴ የተጠመቁ ነበሩ “ ፤ ልምምዳቸዉ “ የደረቅ ጥምቀትን ይዟል “ ፡፡ ሙሴ የኢየሱስ ጥላን እንደሚሆን መስሏል ፤ ሙሴን በመከተል ለስልጣኑ በመታዘዝ በእርሱ መለያቸዉን ገለፁ ፤ በጌታ ያለዉን እምነት አገኙት ነገር ግን በሙሴ በኩል መጣ ፡፡
1-ቆሮንቶስ (10፡ 3-5)፡ ተመሳሳይ መንፈሳዊ ምግብን በሉ ተመሳሳይ መንፈሳዊ መጠጥንም ጠጡ (ቁጥር 3-4) ፤ ይህ ከኃላ ከቁጥር 2 ጋር የተሳሰረ/የተገናኘ ነው ፡፡ ሁሉም የእግዚአብሄርን መገኘት አግኝተዉ/ቀምሰዉታል ፤ ሁሉም በሙሴ ይህን የእምነት አካል ቀምሰዉታል ምክንያቱም ሙሴ በእግዚአብሄር እምነት ስለነበረው ፡፡ መንፈሳዊ ምግቡ ከሰማይ የወረደዉ መና ነበር (ዘዳ 8፡ 2-4) ፤ መንፈሳዊ መጠጡ ደግሞ እግዚአብሄር ከአለቱ ዉስጥ ያመጣዉ/የሰጣቸው ዉሃዉ ነበር (ዘጸ 17፡ 1-7) ፡፡ ይህ መግለጫ ህዝቡ በሙሴ እምነት ላይ መነዳታቸዉን ስለሚያሳይ ሙሴ እግዚአብሄርን በሕዝቡ ላይ ስለሚያደርገዉ ነገር እንደ መካከለኛ ተራመደ ፡፡ አዎ መናዉ እና ዉሃዉ በግልፅ ነበሩ ነገር ግን በሁለቱም ሁነቶች እግዚአብሄር ጣልቃ እንዲገባ ስለ ህዝቡ ለእግዚአብሄር የሙሴ ንግግር ነበር ፡፡ እስራኤላዊያን ከመንፈሳዊ አለት ጠጡ - ያም አለት ክርስቶስ ነበር (ቁጥር 4) ፤ በሁሉም ጊዜ ክርስቶስ ከእነርሱ ጋር ነበር ፤ “ እግዚአብሄር ግን ከእነርሱ በሚበዙት ደስ አላለዉም በምድረ በዳ ወድቀዋልና “ (ቁጥር 5) ፤ ካሌብ እና ኢያሱ ብቻ ይህን በምድረበዳ አድርገዉታል ፡፡
1-ቆሮንቶስ (10፡ 6-13)፡ ጳዉሎስ ቆሮንቶሳዊያንን እስራኤላዊያን በወደቁበት ተመሳሳይ ኃጢዓት እንዳይወድቁ አስጠነቀቃቸው - ጣዖትን በማምለክ (ቁጥር 7)፣ በወሲብ ብልግና (ቁጥር 8)፣ ጌታን እና ትዕግስቱን መፈታተን (ቁጥር 9) እና በማጉረምረም/በማንጎራጎር (ቁጥር 10) ፡፡ ልክ እንደ እስራኤላዊያን ቆሮንቶሳዊያን እግዚአብሄር በፍፁም አይበቃም የሚሉ መስለዋል ፤ በአሁኑም ዘመን አብዛኛዉን ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ተመሳሳይ ነገር የምትል ትመስላለች ፡፡ በዘፀዓት እና በዘኁልቁ አስር ጊዜ በእግዚአብሄር ላይ ስለ እስራኤላዊያን ማንጎራጎር/ማጉረምረም ተነግሮናል ፡፡ እግዚአብሄር አላማ ነበረዉ - ከስህተታችን እንድንማር ስለሚፈልግ እንደ እነርሱ ለነገሮቹ አንሰጥም (ቁጥር 11) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ እንደሚለው “ እግዚአብሄር የሁሉንም ነገር መጨረሻ የሚያመጣ ነው “ ፡፡ ጳዉሎስ ጠንካራ ሆነዉ እንደቆሙ የሚያስቡትን እንዳይወድቁ እንዲጠነቀቁ አስጠነቀቃቸው (ቁጥር 12) ፤ ሰዎች ከእርሱ በላይ እንደሆኑ በሚያስቡ ጊዜ እግዚአብሄር ሁልጊዜ ስለ ተግሳፅ ያመጣዋል ፤ የማንጠነቀቅ ከሆነ በተመሳሳይ ኃጢዓት ልንወድቅ እንችላለን ፡፡ ኢየሱስ ስላለን በራሳችን መንገድ መሄድ ችግር እንደሌለዉ እናስብ ይሆናል ፤ ወደ ፈተና ከመሰጠት ይልቅ ከነገሩ ሊያስመልጠል ተስፋ በገባል በእግዚአብሄር እንሳባለን (ቁጥር 13) ፡፡
1-ቆሮንቶስ (10፡ 14-15)፡ ጳዉሎስ ፈተና እንደገጠማቸዉ የተረዳ ቢሆንም ቆሮንቶሳዊያንን በፈተናዎቹ ላይ ማስጠንቀቁን ቀጠለ (ቁጥር 14-15) ፡፡ ሪክ ፔትሪሰን በምኞት/በፈተና ላይ ለማሸነፍ አራት ቀላል መንገዶችን ሰጥቷል፡ የመጀመሪያው በተቻለ ጊዜ ምኞትን ማስወገድ ፤ ምሳሌ (4፡ 14-15) የክፉዎችን መንገድ አስወግድ ይላል፡፡ ሁለተኛው ከኃይለኛ ምኞት/ፈተና መሸሽ ፤ ሰዎስተኛው አደገኛ ፈተና/ምኞት ለክርስቶስ ልናቀርበዉ እና ልንናዘዘዉ ያስፈልጋል እንዲሁም የእርሱን የማንፃት ስራ መጠየቅ ያስፈልገናል ፡፡ በመጨረሻም ፈተናዉ እስኪጠፋ/እስኪሄድ ድረስ መቋቋም ፡፡
1-ቆሮንቶስ (10፡ 16-22)፡ ከመናዉ እና ከመንፈሳዊዉ ዉሃ እስራኤል በእግዚአብሄር መገኘት እና ስጦታዉ ላይ ተሳትፏል ነገር ግን አሁንም ወደ ጣዖት ተሰጡ/ተመለሱ (ቁጥር 3-4) ፤ በተመሳሳይ ቆሮንቶሳዊያን የክርስቶስን ፅዋ እና እንጀራ ቢካፈሉም (ቁጥር 16) እነርሱም በጣዖት አምልኮ ተሳተፉ ((ቁጥር 18-20) ፡፡ ጳዉሎስ ቆሮንቶስን “ የጌታን ጽዋና የአጋንንትን ጽዋ ልትጠጡ አትችሉም ፤ ከጌታ ማዕድና ከአጋንንት ማዕድ ልትካፈሉ አትችሉም “ በማለት አስጠነቀቃቸው (ቁጥር 21) ፡፡
1-ቆሮንቶስ (10፡ 23-24)፡ የሆነ ነገር ተቀባይነት ያለዉ ነገር ትክክል የሚያደርግ ነዉ ማለት አይደለም ይላል ፡፡
አጠቃላይ ሀሳቡ በምዕራፍ 10 በአለም ዉስጥ ካለዉ ነገር ጋር መቀላቀል እንደማንችል ነው ፤ በአንድ መንፈስ ከተጠመቅን እና በክርስቶስ አካል አንድ ከሆንን በእምነት ከጌታ ጋር መጓዝን ከአለም ጋር በመጓዝ መቀላቀል አንችልም ፡፡ ጳዉሎስ የማንጠነቀቅ ከሆነ የእግዚአብሄር ቁጣ/ፍርድ በመምጣት እንደሚወርድብን ተናግሯል ፡፡
መደምደሚያ
ምኞትን/ፈተናና በማስወገድ መሸሽ ፡፡ በወዳጃችሁ ወይም በባለቤታችሁ ተፈትናችሁበት የነበረዉን ነገር ትናዘዛላችሁ ? ፈተናዎቹን በመናዘዝ ተቋቋሟቸው ምክንያቱም በተቋቋማችኋቸው ጊዜ ጠላት ከእናንተ ይሸሻል ይላል መፅሀፍ ፡፡
Thomas L. Constable, Dr. Constable’s Exposition Bible Study Notes: 1 Corinthians, p. 168; available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/1corinthians.pdf.
Constable, p. 168.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1475.
Rick Peterson, “Pay Attention to Temptation!” available from https://www.slideshare.net/LindleyPreacher/nov-30dec-608-pay-attention-to-temptation-presentation.
ጥያቄዎች
-
በ 1ቆሮ (10፡ 1-10) ጳዉሎስ ለቆሮንቶሳዊያን ማስጠንቀቂያን ሰጣቸው ፤ በመፅሀፍ ላይ እነዚህ ክስተቶች የት ነበሩ (ዘኁ 21፡ 5-9, 25፡ 1-9) ? በኃይለኛዉ እስራኤል የተቀጣችዉ በምን ነበር ?
-
1ቆሮ (10፡ 12-13) እንዴት ትገልፁታላችሁ ? በእነዚህ ጥቅሶች ትስማማላችሁ ? መሸከም እንችላለን ብላችሁ ካሰባችሁት በላይ እንደ ተፈትናችሁ ተሰምቷችሁ ያውቃል ? ምን አደረጋችሁ ? እግዚአብሄር የማመልጫ መንገድ አዘጋጀ ? ለእርዳታ ወደ እርሱ ተመለሳችሁ ? ለምን ወይም ለምን አልተመለሳችሁም?
-
1ቆሮ (10፡ 21) ምን ማለት እንደ ሆነ የሚገልፅ ምሳሌ ማሰብ ትችላላችሁ ?
-
በ 1ቆሮ (10፡ 31) ላይ ለጥቂት ደቂቃ አሰላስሉ ፤ ሁሉንም ነገር ለእግዚአብሄር ክብር ታደርጋላችሁ ? አይደለም ከሆነ ለምን ? ክብርን ለእግዚአብሄር መስጠት የጀመራችሁባቸዉ አንዳንድ መንገዶች ምንድን ናቸው ?
-
በ 1ቆሮንቶስ 10 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Corinthians 10:14
“Therefore, my dear friends, flee from idolatry.”
ጳውሎስ የቆሮንቶስ አማኞችን ጣዖት ከማምለክ እንድሸሹ መከራቸው ፡፡ ጣዖት አምላኪነት ዛሬም ባለችው ቤተክርስቲያን ውስጥ ፈተና ነው ፡፡ ጠላት ሰዎች ሌሎች አማልክቶችን እንዲያመልኩ ያሴራል ያታልላልም ፡፡ ምናልባት እናንተ እንዲህ ታስቡ ይሆናል ፡- ምን ? ጣዖት ማምለክ እኔ ? እኔ ለሌሎች አማልዕክቶች በመስገድና በማምለክ አልፈተንም ! ሌሎች አምላኮችን ማምለክ ማለት በህይወታችሁ ያለ ማንኛውም ነገር ጊዜያችሁን የሚፈልግ ፣ ታማኝነታችሁን የሚፈልግ ወይም ከእውነተኛው አምላክ ከአዳኛችሁ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያላችሁን ህብረት የሚያስተው ማለት ነው ፡፡ ምናልባት የእናንተ ጣዖት ደህንነት የጸጥታ ጉዳይ ፣ ገንዘብ ፣ ጤና ፣ ስኬት ፣ የተስተካከለ የሰውነት አቋም ወይም የሆነ የምትደግፉት የሰፓርት ቡድን ሊሆን ይችላል ፡፡ በተጨማሪ የልጆቻችሁ አንቅስቃሴ ወይም የቤተሰብ ጊዜ ሳይቀር እግዚአብሔርን ከማመስገናችሁ በፊት ለዚህ ነገር ቅድሚያ ሰታችሁት ራሳችሁን ካገኛችሁት ይህ ነገር ጣዖት ሊሆንባችሁ ይችላል ፡፡
ጌታ “ በነገር ሁሉ እኔን አክብሩ “ ይላል ፡፡ እርሱ በግማሽ ልባችሁ ብቻ እርሱን እንዲታመልኩትና በግማሹ ደግሞ ሌሎች አማክትን እንድታመልኩ አላለም ፡፡ ጣዖትን በማምለክ ፈተና እየተቸገራችሁ ከሆነ ጌታ ከእናንተ ጋር እንደሆነና እንደሚረዳችሁ አስታውሱ ፡፡ ራሳችሁን ዝቅ ስታደርጉና ጣዖት የማምለክ ኃጢአታችሁን ስትናዘዙ ጌታ በይቅርታና በሰላም ይባርካችኋል ፡፡ ከየትኛውም አይነት ጣዖት እንድትሸሹ ይፈልጋል ! ስለዚህ ዛሬ የመሮጫ ጫማችሁን አድርጋችሁ ከሁሉም ነገር ቅዲምያን በመስጠት ባላችሁ ነገር ሁሉ ኢየሱስን ተከተሉ ፡፡
“ ስለዚህ ወዳጆች ሆይ ጣዖትን ከማምለክ ሽሹ ፡፡ - 1ኛ ቆሮንቶስ 10፡14
ተጨማሪ ጥቅስ
- ዘጸአት 34:14 — “ ስሙ ቀናተኛ የሆነ እግዚአብሔር ቅንዓት ያለው አምላክ ነውና ለሌላ አምላክ አትስገድ ፡፡ “
- 1ኛ ቆሮንቶስ 10:12–13 — “ ስለዚህ እንደ ቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ ፡፡ ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም ፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘን ማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው ፣ ትታገሱም ዘንድ እንዲትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል ፡፡ “
- 1ኛ ቆሮንቶስ 10:31 — “ እንግዲህ ደግሞ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትሆኑ ወይም ማናቸውን ነገር ብታደርጉ ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።