Paul's Letters 1 Corinthians

A Worker Worthy

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ The Last Adam 1 Corinthians 9 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 511 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ትናትና ምዕራፍ 8 እና ለጣዖት የተሰዋን ምግብ ስለ መብላት የጳዉሎስ ትምህርትን አጥንተናል ፡፡ ኮንስታብል ምዕራፍ 9 ከምዕራፍ 8 የሚቀጥል ዉይይት እንደ ሆነ ይገልፃል ፤ “ በማስረጃነት የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ሌሎችን ለመርዳት የድርጊቱን ነፃነት የመገደብ ፖሊሲዉን በሚገባ ተረድተዉት እንዳልነበር (8፡ 13) ፤ አንዳንዶች በቤተ ክርስቲያን በግልፅ መብቱን ማድረግ ስላልቻለ አየሉትም በማለት በግልፅ ደምድመዋል፡ ለምሳሌ ለማቴሪያል ድጋፍ ያለዉን መብቱን (2 ቆሮ12፡ 13) “ በማለት ይገልፃል ፡፡ ስለዚህም አንዳንድ ቆሮንቶሳዊያን ለጳዉሎስ ስልጣን ለመታዘዝ አልፈለጉም ፡፡

ትምህርት

1-ቆሮንቶስ (9፡ 1-14)፡ ጳዉሎስ በስልጣኑ ላይ ላላቸዉ እምነት ማጣት ስልጣኑን ለማሳየት አራት ጥያቄዎችን በመጠየቅ፣ እኔ ነጻ አይደለሁምን ? ሐዋሪያስ አይደለሁምን ? ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አላየሁትምን ? እናንተስ በጌታ ስራዬ አይደላችሁምን ? (ቁጥር 1) በማለት መለሰላቸው ፡፡ እነዚህ ሁሉም ጥያቄዎች አዎንታዊ የሆነ መልስ ይጠብቃሉ ፡፡ ሐዋሪያዊ ማንነቱን ማረጋገጫ ያካተታቸው፡

  • ያረገዉን/የተነሳዉን ጌታ በአካል አይተዉት የነበሩት ብቻ ሐዋሪያ የሚለዉን ስያሜ ተቀብለዋል (ሐዋ 1፡ 21-22) ፡፡
  • ጳዉሎስ የተነሳዉን ክርስቶስን በደማስቆ መንገድ ላይ አግኝቶቷል (ሐዋ 22፡ 14-15) ፡፡
  • ጳዉሎስ ቤተ ክርስቲያንን በቆሮንቶስ መስርቷል (ሮሜ 15፡ 15-21) ፡፡

በኤፌ (4፡ 11-12) መሰረት እግዚአብሄር አንዳንድ የሀዋሪያነት ስጦታዎችን ሰጥቷል ፤ በአሁኑ ጊዜ ሐዋሪያቶች አሉ ? አሁንም በፍፁም ስለ ወንጌል ያልሰሙ ሰዎች ያሉባቸዉ ሀገራት አሉ ፤ በእነዚህ ሁኔታዎች ዉስጥ አሁንም እግዚአብሄር የሐዋሪያነትን ስጦታ ሰጥቷል ማለት ቀላል ነው ፤ ሐዋሪያት እና ነቢያት አያስፈልጉንም ማለት እንደምንችል አላዉቅም ፡፡

ቀጥሎም ጳዉሎስ ሌሎች ጥያቄዎችን በመጠቀም የሐዋሪያነት መብቱ ወዳለባቸዉ ስፍራዎች ቀጠለ (ቁጥር 4) ፡፡ የመጀመሪያዉ ጥያቄው “ …በሌሎች ወጪ የመብላት ወይም የመጠጣት መብት እንደ ነበረዉ ነበር ፤ ይህ ማለት በአገልግሎቶ የፋይናንስ ድጋፍ ይቀበላል ማለት ነው “ ፡፡ ሁለተኛዉ ጥያቄው አንድ ክርስቲያን ሚስት የመኖር መብት እንደ ነበረው ነው (ቁጥር 5) ፡፡ የሐዋሪያት ክርስቲያን ሚስጦች ከተጠቀሱባቸዉ ከጥቂት ስፍራዎች ዉስጥ ይህ አንዱ ነው ፤ በዚህ መሰረት ጴጥሮስ ከሚስቱ ጋር ተጓዘ ፡፡ ኮንስታብል ጳዉሎስ በአገልግሎት ከሚስቶቻቸዉ ጋር መጓዝን በመዘርዘሩ የአካባቢዋ ቤተ ክርስቲያን የአገልጋዮቹን እና የሚስቶቻቸዉን ወጪ መሸፈን ይህ ለቤተ ክርስቲያን መሪዎች የተለመደ እንደ ነበር ይገልፃል ፡፡ ማር (1፡ 29-31) ፤ በአገልግሎታቸዉ ሚስቶች ተፅዕኖ አድርገዋል ፡፡

የጳዉሎስ ሰዎስተኛ ጥያቄ የራሳቸዉን ወጪ ለመሸፍን በርናባስ እና እኔ አለመስራት አንችልምን የሚል ነበር (ቁጥር 6) (ሐዋ 18፡ 3) ፡፡ ጳዉሎስ አንባቢዎቹን የራሱን ወጪ ራሱ እንደ ሸፈነና ከቤተ ክርስቲያንም ምንም እንዳልወሰደ አሳሰባቸው (ቁጥር 7) ፡፡ በጉባኤዉ ወጪዉ የመሸፈን መብት እንዳለዉ ለማሳየት ሰዎስት ማሳያዎችን ተጠቀመ፡ ወታደርን፣ ገበሬን እና እረኛን ተጠቀመ ፡፡ በቁጥር (9-10) ጳዉሎስ ያንን በሙሴ ህግ መሰረት ለመግለፅ ዘዳ (25፡ 4) “ እግዚአብሄር ሌሎችን ስለሚያገለግሉት መቋቋሚያ ትኩረቱን ለመግለፅ እየሞከረ ነበር እንጂ ስለ በሬዬ ሊያወራ አይደለም “ ፤ (ፊል 4፡ 15-16) ፡፡

በቁጥር (11-12) ጳዉሎስ ስለ ገንዘብ እየጠየቀ አልነበረም ይልቁንም በአገልግሎቱ እርዳታን አግኝቶ እንደ ነበር እያመለከተ ነበር እንጂ (ሮሜ 15፡ 25-27) ፡፡ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎትን የምትረዳዊ ለዚህ ነው ፡፡ ሰዎች ወደ መነቃቂያ ጊዜ እና ሪቫይቭ ት/ቤት በመዝራታቸዉ ደስተኞች ነን ፤ ኮንስታብል “ ጳዉሎስ ራሱን መደገፍን ስለመረጠ ቤተ ክርስቲያንን የመመስረት ስራው በመለወጡ ስለሚያገኘዉ የማቴሪያል ጥቅም እያገለገለ ስለ ነበር የሚገጥመዉ ችግር እንዳልነበር “ ይገልፃል ፡፡ ጳዉሎስ እግዚአብሄር ወንጌልን የሚሰብኩ መኖሪያቸዉን በወንጌል እንደሚያገኙ ማዘዙን ፅፏል (ቁጥር 13-14) ፡፡

በሉቃ (10፡ 5-8) ኢየሱስ ወደ ከተማ እንዲሄዱ የላካቸዉን የሰላምን ሰዉ ሲያገኙ የተሰጣቸዉን እየበሉ እና እየጠጡ እንዲቀመጡ ነገራቸዉ ምክንያቱም “ ለሰራተኛዉ ደሞዙ ይገባዋል “ ፡፡ የመነቃቃት ጊዜ አብረዉን በሚጡ እና አገልግሎታችንን በሚደግፉ የሰላም ሰዎች ላይ የተመሰረተ ነው ፤ ማድረግ ያለብንን ከእነርሱ ዉጪ ማድረግ አንችልም ፡፡ ወደ አንድ ከተማ በምንመጣ ጊዜ ጌታ የሚያስፈልገንን እንደሚያሟላ እናምናለን ፡፡

1-ቆሮንቶስ (9፡ 15-27)፡ በዚህ ክፍል ዉስጥ ጳዉሎስ በእዉነትም ሐዋሪያዊ መብቱን ፋይናንሽያል እርዳታ ተጠቅሞበት ያልነበረውን የሐዋሪያዊ እገዳ ርዕስ ላይ ቀጠለ (ቁጥር 15) ፡፡ ጳዉሎስ እግዚአብሄር ወንጌልን እንዲሰብ እንደ ጠራው እና ያን ጥሪ ያልተከተለ እንደሆነ የማይታዘዝ እንደሚሆን ተናገረ (ቁጥር 16, ሐዋ 9፡ 3-6) ፡፡ ጳዉሎስ በሌሎች እርዳታ ወይም በራሱ ጥረት ቢሆንም በእግዚአብሄር ስጦታ እንደሚኖር እንደሚያውቅ ተናገረ (ቁጥር 17)፡፡ ሽልማቱ ለሁሉም ያለ ክፍያ ወንጌልን መስበክ መሰጠቱ ነበር (ቁጥር 18) ፡፡

ጳዉሎስ ሐዋሪያዉ ነፃነት እንደ ነበረዉ እና ነፃ ሰዉ እንደ ነበር ነገር ግን ወንጌልን ለመስበክ ሲል የሁሉ አገልጋይ አድርጎ እንደ ነበር ገለፀ ፤ ከአይሁዶች እና ከአሕዛቦች ጋር ለመገናኘት ማንኛዉንም ነገር አደርጋለሁ አለ (ቁጥር 19-21) ፡፡ ጳዉሎስ ሰዎችን ወደ ጌታ ለመምራት ሲል ስለ ደካሞች ደካማ ሆኖ እንደ ነበር እና ስለ ሁሉም ሰዉ ሁሉንም ነገር ሆኖ እንደ ነበር ተናገረ (ቁጥር 22-23) ፡፡ ጳዉሎስ በሩጫ ዉስጥ አንድ አሸናፊ እንደሚኖር ሯጮችን በመግለፅ አንባቢዎቹን ሽልማቱን ለማሸነፍ “ ዉድድራቸዉን “ በሚገባ እንዲሮጡ ነገራቸው ፡፡ ወደ አምላኩ እስኪሄድ ድረስ በኃይል እንደሚሮጥ፣ ሰዉነቱን እንደሚጎስም እና እንደሚሰብክ ተናገረ (ቁጥር 24-27) ፡፡

መደምደሚያ

ጳዉሎስ እስከሚወድቅ ድረስ እንደ ሚሰብክ፣ እስከ ሚያንቀላፋም በማስተማር መልካሙን ዜና አደርሳለሁ አለ ፤ ይህን መልክ ወድጀዋለሁ ፡፡ ተመሳሳይ እናድርግ ፡፡

  1. Thomas L. Constable, Dr. Constable’s Exposition Bible Study Notes: 1 Corinthians, p. 156; available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/1corinthians.pdf.

  2. Constable, p. 157.

  3. Constable, p. 157.

  4. Constable, p. 157-158.

  5. Constable, p. 159.

ጥያቄዎች

  1. በ 1ቆሮ (9፡ 4-5) የግል መብት እንደተሰጠዉ ለማሳየት ራሱን ተጠቀመ ፤ ከክርስትና መብት አንፃር አቀራረቡ ምን ነበር ? እንደ ክርስቲያን ወንጌልን አለመስበክ የመምረጥ መብት እንዳለን ታስባላችሁ ?
  2. በ 1ቆሮ (9፡ 7-10) ጳዉሎስ ክርስቲያን ሰራተኞች ትክክለኛ እና በቂ ደሞዝ ይገባቸዉ እንደ ነበርይገባቸዋል አለ ፤ እንደዛ ከሆነ በ 1ቆሮ (9፡ 12-17) መሰረት እንደ ወንጌል አገልጋይ ለምን ክፍያ መቀበልን አልቀበልም እንዳለ ምን ታስባላችሁ ?
  3. በ 1ቆሮ (9፡ 19-22) ጳዉሎስ ምን እያለ ነበር ? ሁሉም ነገር ለሁሉም ሰዉ ሊሆን እንዴት ይችላል ?
  4. ለማሸነፍ “ ዉድድሩን “ ትሮጣላችሁ ? አያደለም ካላችሁ ለምን ?
  5. በ 1ቆሮንቶስ 9 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Corinthians 9:12

“If others have this right to receive benefits from you, don’t we even more? However, we have not made use of this right; instead we endure everything so that we will not hinder the gospel of Christ.”

ጳውሎስ ወንጌልን ከመሰከረላቸው ሰዎች ወይም አብሯቸው ካገለገላቸው ሰዎች ጥቅምን ያገኝ ዘንድ አገልጋይነቱ የሰጠውን እድል አልተጠቀመም ፡፡ እርሱ መብቱን አልተጠቀመም ፡፡ ስለ ወንጌል ሁሉንም ነገር ተሸክሟልና እንደውም ተቃራኒውን አደረገ ፡፡ ጳውሎስ ባለው ቦታ ፣ ኃይልና ደረጃ ላይ አልተደገፈም ፡፡ ይልቁንም በጌታ ኃይልና እገዛ ላይ ተደገፈ እንጂ ፡፡ በሚቻለው መንገድ ሁሉ ሰዎች ወንጌልን ይሰሙና ይቀበሉ ዘንድ ጳውሎስ ለሁሉም ሰዎች ሁሉንም ነገር ሆነ ፡፡

ኢየሱስ በልባቸው ንጹህ የሆኑ እግዚአብሔርን እንደሚያዩትና ደግሞም በመንፈስ ደሃ የሆኑ የእግዚአብሔርን መንግስት እንደሚወርሱ ተናግሯል ፡፡ ጌታ ልባችሁ እንድያመሰግነውና በመታዘዝ እንድታመንበት ይፈልጋል ፡፡ ልባችሁ ንጹህ ሲሆንና በትህትና ስትኖሩ ጌታ ከእርሱ እንድትሰሙ ፣ እርሱን እንድታውቁትና መንገስቱን እንድትወርሱ ያስችላችኋል ፡፡ ህግን መተው ፣ ማበጀት ፣ መዋሸት ፣ ማጭበርበር ወይም ነገሮችን በራሳችሁ ቁጥጥር ስር ማዋል አያስፈልጋችሁም ፡፡ በተቃራኒው ጌታ እንድትሄዱ የሚፈልገው ወደ የትም ይሁን ፣ በመታዘዝ ተራመዱ ፡፡ ጌታ ታዛዥነታችሁን ያከብራል ፡፡ እርሱ የትኛውንም ፍላጎት ያሟላል ፡፡ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንደሚሆንና እንደሚሸልማችሁ ተናግሯል ፡፡ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት ፤ በእርሱ አባት ለሆነው ለእግዚአብሔር ምስጋና አቅርቡ ፡፡

“ ሌሎች በእናንተ ላይ ይህን መብት የሚካፈሉ ከሆነ እኛማ ይልቁን እንዴታ ? “ - 1ኛ ቆሮንቶስ 9፡12

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ማቴዎስ 5፡3 ፤ 5፡8- “ በመንፈስ ድሆች የሆነ ብጹዓን ናቸው ፣ መንግስተ ሰማያት የእነርሱ ናትና ፡፡ “
  • ኤፌሶን 6፡5-8 -“ ባሪያዎች ሆይ ለክርስቶስ እንደምትታዘዙ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ በልባችሁ ቅንነት በስጋ ጌቶቻችሁ ለሆኑ ታዘዙ የእግዚአብሔርን ፍቃድ እንደሚያደርጉ እንደ ክርስቶስ ባሪያዎች እንጂ ለሰው ደስ እንደምታሰኙ ለታይታ የምትገዙ አትሁኑ ፡፡ ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምትገዙ በትጋትና በበጎ ፈቃድ ተገዙ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው እያንዳንዱ የሚያደርገውን መልካም ነገር ሁሉ ከጌታ በብድራት እንዲቀበለው ታውቃላችሁና ፡፡ “
  • ቆላስያስ 3፡17 – “ እግዚአብሔር አብን በእርሱ እያመሰገናችሁ ፣ በቃል ቢሆን ወይም በስራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት ፡፡ “