Paul's Letters 1 Corinthians

My Brother's Keeper

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ The Last Adam 1 Corinthians 8 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 510 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በአለፉት ጥቂት ምዕራፎች ዉስጥ እንዳየነው በቆሮንቶስ የነበረችዉ ቤተ ክርስቲያን ጳዉሎስ በቀጥታ ሊያወጣዉ እየሞከረ የነበረ ጉዳዮች ነበሯት ፡፡ የ 1ቆሮንቶስ አምስቱን ችግሮች እንዳትረሱ፡ 1) መከፋፈል፣ 2) ወሲባዊ ቅሌት፣ 3) ምግብ፣ 4) የቤተ ክርስቲያን ባህል እና 5) የክርስቶስ ትንሳኤ ፡፡ ምዕራፍ 8 በአጠቃላይ ለጣዖት ተሰዉቶ ስለ ነበር ምግብ ነው ፡፡

ትምህርት

1-ቆሮንቶስ (8፡ 1-3)፡ በቆሮንቶስ ለግርክ -ሮማዉያን አፈታሪኮች ለአማልዕክት፣ ለጣዖት እና ለሰይጣን ኃይል ሳይቀር መስዋዕት ይደረግባቸዉ የነበሩ ብዙ መስዋዕቶች ነበሩ ፤ በጊዜዉ ይህ የተለመደ ስፍራ ነበር ፡፡ በ 1ቆሮንቶስ ዉስጥ በቆሮንቶስ ለህይወት የተለመዱ የነበሩ ጥቂት ምሳሌዎች በመጠቀስ ጥቅም ላይ ዉለዋል ፤ በቁጥር 1 ጳዉሎስ ሌላን ተጠቀመ፡ “ ሁላችን እዉቀት አለን “ ፤ ለጣዖት የተሰዋን ምግብ ስለ መብላት የተለያዩ እምነቶች ነበሩ፡፡ ስለዚህ እምነትን የያዙት ስለ ጉዳዩ “ እዉቀት እንደ ነበራቸዉ “ ያስባሉ ፡፡ ስለዚህም ጳዉሎስ ፍቅር እንደሚያንፅ እዉቀት ግን በትዕቢት እንደሚነፋ ጨመረ (ቁጥር 1) ፡፡ ጳዉሎስ ቆሮንቶሳዊያንን የሆነ ነገር እንደሚያዉቁ “ ስያስቡ “ ምናልባትም ሁሉንም ነገር እንደማያውቁ ነገራቸው (ቁጥር 2) ፡፡ ሁልጊዜ ተቆጣጣሪዬ “ ሁላችንም በማጭበርበር መለኪያ እና በመገለጥ መጠን እንጓዛለን ፤ ልክ እንደሆንክ ታስቡ ይሆናል ነገር ግን በስህተት የሞትክ ትሆናለን “ አለ ፡፡ ጳዉሎስ እግዚአብሄርን ከወደድነው በእርሱ እንታወቃለን ብሏል (ቁጥር 3) ፡፡

በዚህ ሁኔታ ቤተ ክርስቲያንን ወደ ሁለት ቡድን መክፈል እፈልጋለሁ ፤ (ቀድመዉ የነበሩትን ሁሉንም መከፋፈሎች ታስታዉሳላችሁ ?) ፡፡ የመጀመሪያዉ ቡድን በቀድሞ ባህል የታሰሩ የነበሩ፣ ሁለተኛዉ ቡድን በቀድሞ ባህል ያልታሰሩ ፤ ሁለቱም ቡድኖች ትክክልም ስህተትም ነበሩ ፡፡ ለእግዚአብሄር የተሰዋን መግብ መብላት ትልቅ ጉዳይ እንደ ነበር የሚያስቡት በቀድሞ ባህል የታሰሩት ቡድኖች ዉስጥ ሲሆን፣ ትልቅ ጉዳይ እንዳልነበር የሚያስቡት ደግሞ በዚያዉ ቡድን ዉስጥ ነበሩ ፡፡ ሁለቱም ቡድን ትክክል ነበሩ ፡፡

1-ቆሮንቶስ (8፡ 4-6)፡ በቁጥር 4 ሁለቱም የታወቁ አባባሎች ናቸው፡ “ ጣዖት በአለም ከንቱ ነው “ የሚለዉ እና “ አንድ እንጂ ሌላ አምላክ የለም “ የሚሉት ናቸው ፡፡ ጳዉሎስ ጣዖት ከንቱ እንደ ነበር እና እግዚአብሄር አንድ ብቻ እንደሆነ ገለፀ ፡፡ ስለዚህም ለእነዚህ ለሌሉት ነገሮች ምንም ነገር ማድረግ ከንቱ ነበር ምክንያቱም አንድ እዉነተኛ እግዚአብሄር እና አንድ አምላክ ብቻ ስለሆነ (ቁጥር 5-6) ፡፡ እኛም “ ለእርሱ “ እና “ ከእርሱ “ ነን ፤ ሁሉም ነገር “በእርሱ ዉስጥ “ ስለሆነ እኛም “ በእርሱ ዉስጥ “ ብቻ እንኖራለን (ቁጥር 6) ፡፡

1-ቆሮንቶስ (8፡ 7-13)፡ ጳዉሎስ ለቆሮንቶሳዊያን ሁሉም ሰዉ ይህ እዉቀት እንደሌለዉ ገለፀላቸው (ቁጥር 7) ፤ ወዲያዉኑ ከጣዖት አምልኮ እና መስዋዕት እየመጡ ስለ ነበሩ ሰዉን በቀድሞ ህይወታቸዉ ተግባር ላይ ሲሳተፍ ቢመለከቱት በከፍተኛ ደረጃ በእነዚህ ነገሮች ሌሎች ክርስቲያን ወንድሞች እና እህቶችን ሲካፈሉ ማየት ያሰናክላቸዋል ወይም ይፈትናቸዋል ፤ ምክንያቱም አይምሯቸው ደካማ ስለነበር የረከሱ ይሆናሉ ፡፡ ጳዉሎስ ቆሮንቶሳዊያንን የበሉት ነገር ቅዱስ ወይም ርኩስ ሊያደርጋቸዉ እንደማይችል አሳሰባቸው (ቁጥር 8) ፡፡ ምግብ ልክ እንደ ገንዘብ ወይም እንደ አልኮል ወይም እንደ ሙዚቃ ወይም ሚድያ ኒዉትራል የሆነ ነገር ነው ፡፡ እነዚህ ነገሮች ሁሉንም ለመልካም ወይም ለመጥፎ ነገር መጠቀም ይቻላል ነገር ግን በራሳቸው ኒዉትራል ናቸው ፡፡

ይሁን እንጂ ጳዉሎስ አንባቢዎቹን ለእነርሱ መልካም የነበረዉ ነገር ለሌሎች ወንድሞቻቸዉ ወይም እህቶቻቸዉ መልካም ላይሆን እንደሚችል አስጠነቀቃቸው (ቁጥር 9) ፡፡ አማኞች ስለ ንግግሮች፣ አርማን ስለ ማሳየት እና ትልቅ የክርስትና ቃል ስለ መጠቀም የተለያዬ የግል አስተያዬት አላቸው ፡፡ ደካማ የሆነን ሰዉ የሚያደናቅፍ ስራን ላለማድረግ ጠንቃቆች መሆን ይጠበቅብናል ፤ የሆነን ነገር ማወቅ መልካም ወይም መብታችን ቢሆንም ለአንድ ወንድም/እህት መሰናከል ምክንያት ከሆነ አናደርግም (ቁጥር 10) ፡፡ በቁጥር 11 “ ክርስቶስ ለሞተለት ወንድምህ “ የሚል እናነባለን - ይህ ስለ ንፅፅር አይደለም ራስን ትሁት ስለ ማድረግ እና አንዱ ስለ ሌላዉ የተሸለ ስለማድረግ እንጂ (ሮሜ 14፡ 1-22) ፡፡ በሌሎች ላይ ኃጢዓት ስናደርግ (ደካሞች በመሆናቸዉ ምክንያት እንዲሰናከሉ ምክንያት ስንሁን) በክርስቶስ ላይ ኃጢዓት እናደርጋለን (ቁጥር 12) ፡፡ ጳዉሎስ በክርስቶስ ሌላ ወንድሜን የሚያሰናክል ከሆነ ምንም ነገር አልብላ በማለት ደምድሟል (ቁጥር 13) ፡፡

መደምደሚያ

በዘፍጥረት 4 የቃየል እና የአቤል ታሪክ ተመዝግቧል ፤ በቁጥር 9 እግዚአብሄር ቃየልን ወንድም የት ነበር በማለት ጠየቀው ቃየልም “ የወንድሜ ጠባቂ እኔ ነኝን ? “ በማለት መለሰ ፡፡ በጌታ የሆኑትን ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን ለመጠበቅ ተግባር፣ ግዴታ፣ መብት እና አክብሮት አለን ፡፡

ጥያቄዎች

  1. በ 1ቆሮ (8፡ 1) ጳዉሎስ “ እዉቀት ያስታብያል “ ሲል ምን ማለቱ ነዉ ብላችሁ ታስባላችሁ ? ብዙ እዉቀት ያለዉ ነገር ግን እንዴት በሚገባ እንደሚጠቀም ጥበብ የሌለዉ ሰዉ ታዉቃላችሁ ? ያ ሰዉ ልትሆኑ ትችላላችሁ ? በኢየሱስ ቀን ምን አይነት የሰዎች ቡድን እንደዚህ መስለዉ ታዉቀዉ ነበር ? (ማቴ 23፡ 1-8, ዮሐ 7፡ 45-49)
  2. ጳዉሎስ ለጣዖት የተሰዋን ስጋ ስለ መብላት ምን አለ ? በአሁኑ ጊዜ ለምን “ ጣዖት “ ነዉ ራሳችሁንታቀርባላችሁ ?
  3. በ 1ቆሮ (8፡ 9) ጳዉሎስ የጠቀሳቸዉ “ ደካሞች “ እነማን ነበሩ (ሮሜ 14፡ 1, 1ቆሮ 10፡ 27-28) ? ለማሰናከል ምክንያት የምትሆኑባቸው ሰዎች በህይወታችሁ ዉስጥ አሉ ?
  4. በ 1ቆሮ (8፡ 12) ጳዉሎስ “ እንዲህም ወንድሞችን እየበደላችሁ ደካማም የሆነዉን ሕሊናቸዉን እያቄሰላችሁ ክርስቶስን ትበድላላችሁ “ (መዝ 51፡ 4) ለምን እንዳለ ምን ታስባላችሁ ? ይህ ስለ እግዚአብሄር ልብ ምን ይላል በተጨማሪም ከህብረቱ አማኞች ጋር በግንኙነት እንዴት እንድንኖር ይፈልጋል?
  5. በ 1ቆሮንቶስ 8 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Corinthians 8:1–3

“About food offered to idols: We know that ‘we all have knowledge.’ Knowledge inflates with pride, but love builds up. If anyone thinks he knows anything, he does not yet know it as he ought to know it. But if anyone loves God, he is known by Him.”

ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ታላቋን ትዕዛዝ ፡- ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ ፣ በፍጹም ነፍስህና ፣ በፍጹም አሳብህ ውደድ የምትለው ናት በማለት አስተማረ ፡፡ ቀጥሎም ሁለተኛዋ ታላቅ ትዕዛዛ ፡- ባልንጀራን እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ ፡፡ የምትለው እንደሆነች አስተማረ ፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስም በቆሮንቶስ ላለች ቤተ ክርስቲያን ተመሳሳይ የሆነ መመሪያን ይሰጣል ፡፡ የመጀመሪየው ማንም እግዚአብሔርን ቢወድድ ፣ እርሱ በእግዚአብሔር ይታወቃል ፡፡ ሁለተኛው ደግሞ እውቀት ያስታብያል ፍቅር ግን ያንጻል ነው ፡፡

በዚህ ህይወት ውስጥ ከኢያሱስና ከሌሎች ጋር ስትኖሩ ከኢየሱስና ከጳውሎስ የምትማሩት ምንድን ነው ፡፡ ቀለል አድርጉት ፤ ይህ ስለ እውቀት ፣ ስለ ስራ ወይም ህግን ስለመጠበቅ አይደለም ፡፡ እግዚአብሔርን ስትወዱ እርሱን ታውቃላችሁ እናም እርሱም ያውቃችኋል ፡፡ ከማስተማር በላይ ፣ ከመስዋዕትነት በላይ እግዚአብሔር እናንተ እንድትወዱት ይሻል ፡፡ እናም ከዚያ የጌታ ፍቅር ከእናንተ በዙሪያችሁ ወደሉት ይፈሳል ፡፡ በእነርሱ ላም እውቀትን ፣ ፍትህንና ዳኝነትን ማስገደድ አይጠበቅባችሁም ፡፡ እግዚአብሔርን ስትወዱ ለሌሎች በሚሆን ጥበብና ጸጋ ይሞላችኋል ፡፡ እነርሱም በእናንተ ህይወት ኢየሱስ ፍቅርን እያሰራጨ እንደሆነ ይገነዘባሉ ደግሞም ለምትሰጧቸው ፍቅር ይራባሉ ፡፡ ዛሬ እግዚአብሔርንና ሌሎችን በመውደድ ላይ አትኩሩ ደግሞም እግዚአብሔር የእናንተን እና የእነርሱን ልብ እንድለውጥ እመኑ ፡፡

“ ለጣዖት ስለ ተሰዋ ስጋም ሁላችን እውቀት እንዳለን እናውቃለን ፡፡ እውቀት ያስታብያል ፍቅር ግን ያንጻል ፡፡ ማንም እዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም ፤ ማንም ግን እግዚአብሔርን ቢወድ እርሱ በእርሱ ዘንድ ጣወቀ ነው ፡፡ “ - 1ኛ ቆሮንቶስ 8፡1-3

ተጨማሪ ጥቅስ

  • 1ኛ ሳሙኤል 15:22 — “ ሳሙኤልም ፡- በውኑ የእግዚአብሔር ቃል በመስማት ደስ እንደሚለው እግዚአብ\ሄር በሚቃጠልና በሚታረድ መስዋዕት ደስ ይለዋልን ? እነሆ መታዘዝ ከመስዋዕት ፣ ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ ከማቅረብ ይበልጣል ፡፡ “
  • ማቴዎስ 22:36–39 — ከህግ ማናቻይቱ ትዕዛዝ ታላቅ ናት ? ብሎ ጠየቀው ፡፡ ኢየሱስም እንዲህ አለው ፡- ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ ፣ በፍጹም ነፍስህም ፣ በፍጹም አሳብህም ውደድ ፡፡ ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትዕዛዝ ይህቺ ናት ፡፡ ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች ፣ እርስዋም ፡- ባልነጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ የምትለው ናት ፡፡ “
  • ሮሜ 12:2 — “ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደሆነ ምን እንደሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን አለም አትምሰሉ ፡፡