Paul's Letters 1 Corinthians

Identifying Strongholds

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ The Last Adam 1 Corinthians 7 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 509 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

1-ቆሮንቶስ ምዕራፍ 7 ብዙ ስብከቶች እና ትምህርቶች የሰማሁበት አንድ ምዕራፍ ነው ፤ በጋብቻ ላይ ሲያነሳሳ እና ስለ ቅድመ ጋብቻ ሲመክር የምትሰሙት ምዕራፍ ነው ፡፡ በጥልቅ ከመጀመራችን በፊት መፅሀፉን እንድንረዳዉ የሚረዱንን ሁለት ሀሳቦች ማስቀመጥ እፈልጋለሁ - የምዕራፉ አገባብ/አገላለፅ እና የጳዉሎስ ሐዋሪያዊ አመለካከት፡፡ በምዕራፉ ዉስጥ ስናጠና/ስናነብ መጀመሪያ አንዳንድ ይዘቶችን መረዳት ያስፈልገናል ፤ አገባቡ/ይዙት ሲኖረን በዚያ ዉስጥ በተለያዬ እይታ/አመለካከት እንድንመለከተዉ እፈልጋለሁ - በሐዋሪያዊ እይታ ፡፡

አገባብ፡ ከክርስቶስ ሞት በኋላ በ51 ጳዉሎስ መጀመሪያ ቆሮንቶስን ጎበኘ (ሐዋሪያት ስራ 18) ፤ እግዚአብሄርም በቆሮንቶስ ጳዉሎስ በድፍረት አገልግሎትን እንዲያደርግ ነገረው ፡፡ ለአንድ አመት ከግማሽ እዚያ ነበር - ጳዉሎስ ኢንቨስት አድርጓል ፤ እግዚአብሄር የቆሮንቶስን ከተማ ለጳዉሎስ አደራ ሰጠው ፡፡ በቆሮንቶስ የነበረዉ ባህል ጣዖት አምላኪነት እና ልቅነት/ዝምብሎ ሁሉንም በማድረግ መደሰት ነበር ፡፡ ይህ ምዕራፍ ስለ ጋብቻ ብዙ ነገር ይናገራል ፡፡ ማክአርቱር ይህን ባህል መግለፅ ይራዳል፡ “ በጊዜዉ በሮማዉያን ባህል አራት ተጨማሪ የጋብቻ ችግሮች/ሁኔታዎች አሉ ፤ ከባሪያ/ከአገልጋይ የሆነ በአንድ ላይ እንዲኖር ተፈቅዷል፣ የጋብቻ ህግ በምንድን ይጠራናል የተለመደና ጥሩ የሆነ ጋብቻ ከአባት በመግዛት የሆነ ጋብቻ “ ፡፡ በቆሮንቶስ ያሉት አማኞች የወቅቱን ባህላቸዉን እንዴት ከአዲሱ እምነታቸዉ ጋር አጣጥመዉ እንደሚሄዱ ብዙ ግራ መጋባቶች የነበሩ ይመስላል ፤ ለዚያ ነዉ ጳዉሎስ በደንብ ይዳስሰዉ የነበረው ፡፡ ጳዉሎስ ይህን መልዕክት ከአምስት አመት ቆይታ በኋላ ከክርስቶስ ሞቶ በ57 ፃፈው ፤ ጳዉሎስ የነበሯቸዉን ጥያቄዎች እየደረሰ/እየመለሰላቸዉ ነበር ፡፡

ሐዋሪያዊ አመለካከት፡ ጳዉሎስ ለአዲስ አማኝ እን ቅዱሳን የሚፅፍ አንድ ሐዋሪያ ነበር (1ቆሮ 1፡ 1-2) ፡፡ ሐዋሪያ የሚለዉ ቃል “ አፖስቶሎ “ ከሚል የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም “ የተላከ “ ማለት ነው ፤ ይህ በመጀመሪያ በሮማዉያን ስለተገኘ አዲስ ምድር ባህል እንዲያጠና የተላከን ሰዉ ለመግለፅ ጥቅም ላይ የዋለ የአለም ቃል ነበር ፡፡ የሐዋሪያት ተግባራት በኤፌ (4፡ 11-13) ላይ ይገኛሉ ፤ እነዚህ ጥቅሶች በሐዋሪያት ስራ 18 እግዚአብሄር ለጳዉሎስ ከነገረዉ ጋር ይመሳሰላሉ ፡፡ የጳዉሎስ ተግባር እንደ ሐዋሪያ ቅዱሳንን ማዘጋጀት ነበር ፡፡

ምዕራፍ ወደ ሰዎስት ክፍል ወይም ተደራሽ/አድማጭ ሊከፈል ይችላል፡ ያገቡ (ቁጥር 1-11)፣ ሳይመጣጠኑ የተጠመዱ/አብረዉ ያሉ (ቁጥር 12-24) እና ያላገቡ (ቁጥር 25-40) ፡፡

ትምህርት

1-ቆሮንቶስ (7፡ 1)፡ ይህ የመጀመሪያዉ ቁጥር ቆሮንቶሳዊያን ለጳዉሎስ መልዕክት እንደ ፃፉለት ያመለክታል ፤ ጳዉሎስ ይህን መልዕክት ለመልዕክታቸዉ እንደ ምላሽ አካል በማድረግ እየፃፈ ነበር ፡፡ ድንግልና በአዲሱ ቤተ ክርስቲያን ባህል ዋና ርዕስ የሆነ ነበር ምክንያቱም ሰዎች ድንግልናን እንደ ከፍተኛ የመንፈሳዊነት ቅርፅ ስለተመለከቱት ፡፡ አራት አይነት ጋብቻዎችን ታስታዉሳላችሁ ? እነዚህ አማኞች ይህን በትክክል ማግኘት ስለፈለጉ በህግ መጡ ፤ ከህጎቹ አንዱ በከፍተኛ ክብር በጋብቻ ዉስጥ ድንግልናን መጠበቀ ነበር ፡፡

ቆሮንቶሳዊያን ትክክል ምንድን ነው ? እያሉ እየጠየቁ ነበር ፤ ላግባን ? ድንግል ሆኜ ልኑር ? የጳዉሎስ መልስ መሰረታዊ ነበር “ ድንግል መሆን መልካም ነዉ በማግባትም ከባለቤታችሁ ጋር ወሲባዊ ግንኙነት ማድረግ መልካም ነው “ በማለት መለሰ ፡፡

1-ቆሮንቶስ (7፡ 2)፡ ምኞት ወደ ኃጢዓት ሊመራ ይችላል ፡፡ ጳዉሎስ የሰማይ ባህልን እና የቆሮንቶስን ባህል ለማስተሳሰር /ለማገናኘት እየሞከረ ነበር ፡፡ ጳዉሎስ በቆሮንቶስ በአጠቃላይ ልክ እንደ ዝሙት እና ሴተኛ አዳሪነት የሚመስል ምኞቶች እንደ ነበሩ አመለከተ ፡፡ ቆሮንቶሳዊያንን እንደ እግዚአብሄር ፍቃድ የሆነ ጋብቻ እንዲኖራቸዉ አበረታታቸው - ሌላ ቁባት እንደማያስፈልግ፣ ሌላ ጉዳይ እንደማያስፈልግ እና መዳራት እንደማያስፈልግ ፡፡ አንድ ባለቤት በማግኘት ከእነርሱ ጋር መጣበቅ ከእነርሱ ጋር ብቻ ፡፡ ጳዉሎስ በእግዚአብሄር መንግስት ዉስጥ አንድ ጓደኛ በማግኘት ከእነርሱ ጋር እንደምትጣበቁ ወይም ብቻችሁን ሆናችሁ እንደምትቀመጡ ያውቃል ፤ ጳዉሎስ መሰረትን ለመመስረት እየሞከረ ነበር ፡፡

1-ቆሮንቶስ (7፡ 3)፡ ይህ ቁጥር በዚህ አገባብ ጳዉሎስ ስለ ጋብቻ እንዴት እንዳስተማረ ነው ፡፡ የጋብቻ መብት በጣም የተቀራረበ ግንኙነትን ይወክላል ፤ በጋብቻ ዉስጥ 100 ፐርሰንት ግልፅነት መኖር አለበት ፤ ያ ማለት የእኔ የሆነዉ የእርሷ/የእሱ የእርሷ/የእሱ የሆነዉ ደግሞ የእኔ ነዉ ማለት ነው ፡፡ የሚደበቅ ነገር ምንም ስለሌለ ሁሉም ነገር ይጋራሉ ፡፡ ከኢየሱስ ጋር የኪዳን ግንኙነት አስቡ ፤ ፍቅሩን መልሶ አይወስደዉም ፤ ብዙ ሊሰጠን ይፈልጋል ፤ በጋብቻም ዉስጥ የግል/የብቻ የሖነ ወሲባዊ መቀራረብ መኖር አለበት ፡፡

የጋብቻ መብትን የሚይዙ ብዙ ምክንያቶች አሉ፡ ቁጥጥር፣ ፍርኃት፣ እፍረት፣ መጠማዘዝ ፤ ከእነዚያ ነገሮች ዉስጥ ማንኛዉም ከእግዚአብሄር እንደመጣ የሚናገሩ ናቸው ? አይደለም ፡፡ በቅድመ ጋብቻ ምክር ላይ ፓስተራችን “ ከማግባታችሁ በፊት ሰይጣን ወሲብ እንድታደርጉ የሚችለዉን ማንኛዉንም ነገር ያደርጋል ፤ ካገባችሁ በኋላ ደግሞ ሰይጣን ወሲብ ከማድረግ እንድትቆጠቡ ማንኛዉንም የሚችለዉን ነገር ሁሉ ያደርጋል “ በማለት አጋርቶናል/አስተምሮናል ፡፡ በትዳራችሁ ዉስጥ ለጠላት ምንም አይነት ስፍራ /መቆሚያ ቦታ/ መግቢያ ቀዳዳ እንዳትሰጡ ፡፡ ጳዉሎስ ጠላት የሚጠቀምበት ታላቅ ምሽግ/የተከለከለ ስፍራ ከሚሻሻለዉ ከእግዚአብሄር መንቀሳቀስ/መኖር ማራቅ እንደሆነ ለይቷል ፡፡ በቆሮንቶስ የወሲብ ምሽግ ትልቅ ነበር ፡፡

1-ቆሮንቶስ (7፡ 4)፡ ይህ ጥቅስ ለመቆጣጠር ፍቃድ አይደለም - አካላዊን ወይም ስሜታዊን ፤ እርስ በእርስ ለመከባበር እና ለመሞጋገስ የጋራ ስምምነት ነው ፡፡

1-ቆሮንቶስ (7፡ 5)፡ ይህ እንደ ገና ስለዚያ ምሽግ ይናገራል ፡፡ በትዳራችን ዉስጥ 100 ግልጽነት በማይኖር ጊዜ ጠላት ራሱን ለማስገባት ትንሽ ቀዳዳ ይኖረዋል ፡፡ እርስ በእርስ ስትከላከሉ ያን ጊዜ በፀሎትና በፆም በመሙላት በተቻለ መጠን በፍጥነት እንደ ገና በአንድ ላይ መምጣት ካልተፈለገ የምኞት ፈተና ይጠብቃችኋል ፡፡ በደህና እና በጤነኛ ትዳር አገላለፅ/አዉድ ከወሲባዊ ግንኙነት ባለቤታችሁን መከልከል ደረጃ ላይ ከደረሳችሁ ኃጢዓት ሆኗል ፤ ቁጣ፣ ብስጭት እና ፍርኃት የታረቁ መሆን አለባቸው ፡፡

1-ቆሮንቶስ (7፡ 6-9)፡ ጳዉሎስ የሁሉንም የተለዬ መሆን ተናገረ ነገር ግን ሁሉም ባያገቡ ተመኘ ፡፡ ልክ እንደ ጳዉሎስ አለማግባት መልካም/ችግር የለዉም ፤ ያላገባችሁ እንድትሆኑ እንደተጠራችሁ የማይሰማችሁ ከሆነ እና በምኞት የምትወድቁ ከሆነ ጋብቻን/ትዳርን ተከታተሉ/ያዙ ፡፡ ባለቤትን በማደን አትቀጥሉ/አትሯሯጡ ለማግባት ራሳችሁን ያዘጋጃችሁ ብቻ ሁኑ ፡፡ ጳዉሎስ እንደ ወሲባዊ ሱስ አይነት ነገሮችን አልዳሰሰም ፤ ይህ ካስፈለጋችሁ ትረዳላችሁ ፡፡

1-ቆሮንቶስ (7፡ 12-14)፡ እግዚአብሄር በአንድ ያጣመረዉን ሰዉ አይለየዉም ፡፡ ሁላችንም አንዱ ባለቤት አማኝ እና አንዱ ባለቤት ደግሞ የማያምን የሆኑ ጥንዶችን እናዉቃለን ( ያልተመጣጠነ መጠመድ) ፤ ጳዉሎስ በጋብቻዉ ውስጥ አማኞች የሆኑት በትዳራቸዉ ዉስጥ እምነትን እና የእግዚአብሄርን ፍቅር እያጋሩ እንዲቀጥሉ አበረታታቸው፡፡ ልክ/ባማይመጣጠን ቀንበር የተጠመዱ ጥንዶች አስቸጋሪ ወይም ታላቅ ጋብቻ ሊኖራቸዉ ይችላል ፤ የምታዉቃቸዉን እነዚህን ጥንዶች በማንኛዉም መንገድ አበርቷቸው ፤ ለእነርሱ በመፀለይ በተግባራችሁ ባለቤቶቻቸዉን አካቷቸዉ ፡፡

1-ቆሮንቶስ (7፡ 25-40)፡ ቁጥር 26 ሳያገቡ ለመኖር የተጠሩትን ይጠቅሳል ፤ ሳታገቡ ለመኖር የተጠራችሁ ከሆናችሁ ያዙት ፡፡ ራሳችሁን በመሆን እንድትሆኑ እግዚአብሄር የፈጠረላችሁን ያዙ ፡፡ ያላገባችሁ ከሆነ ትኩረታችሁን ለእግዚአብሄር አድርጉ ፤ ትዳር ከአገልግሎት ሊያዘገይ ወይም ሀሳብን ሊያምታታ ይችላል ፡፡ ያላገባ በመሆን ወደ ምሬት ራሳችሁን ለማስገባት አትፍቀዱ ፡፡

መደምደሚያ

አብዛኞቹ ሰዎች እንዲያገቡ ተጠርተዋል ፡፡ ስታገቡ ትኩረታችሁ የተከፋፈለ እንደሚሆን እወቁ ፤ ላገቡ አገልግሎት ከባድ/አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል ነገር ግን እግዚአብሄር በዚያ ዉስጥ ያገኛችኋል ፡፡ ለማመጣጠን አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል ፡፡ በእነዚህ ጥቅሶች ላይ በጳዉሎስ ሐዋሪያዊ እይታ በምትመለከቱ ጊዜ ጳዉሎስጰሰማይን ባህል ወደ ምድራዊ ባህል ለማምጣት ሲሞክር ለትዳር ካለዉ መልክም ነገር የሚበልጡ ናቸው ፤ ለአካል በመሰረት ላይ ለሚገነባ ህንፃ ሀሳቦች ናቸው ፡፡ በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን አገላለፅ ጠንካራ ጋብቻ በጠንካራ ጣዖት እና ወሲባዊ ብልግና ላይ ጠንካራ ምሽግን የሚገነባ ነው ፡፡ መፅሀፍን ስታጠኑ የፀሀፊዉን እይታ ለመረዳት ሞክሩ ፡፡ ጳዉሎስ ጠንካራ ምሽግን በመለየት አዲስ ክርስቲያኖችን ማበረታታት ችሎ ነበር ፡፡

  1. John MacArthur, To Marry or Not to Marry, Grace to You, November 30, 1975; available at https://www.gty.org/library/sermons-library/1828/to-marry-or-not-to-marry.

ጥያቄዎች

  1. በ 1ቆሮ (7፡ 4) የጳዉሎስ ተገቢ ትርጉም ምን ነበር ? ይህን ለማያምኑት እንዴት ትገልፁታላችሁ ?
  2. 1ቆሮ(7፡ 20) (1995 አዲሱ መደበኛ ትርጉም) “…. በተጠራበት መጠራት እንደዚሁ ይኑር “ ይላል ፤ ይህ ጥቅስ ምን ማለት ነው ?
  3. በ 1ቆሮንቶስ መሰረት ማግባት ወይስ ያላገባ መሆን የተሻለ ነው ? ለሁለቱም ተግባራቸዉ እና ሙያቸዉ ምን ነበር ?
  4. በ 1ቆሮንቶስ 7 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Corinthians 7:5

“Do not deprive each other except perhaps by mutual consent and for a time, so that you may devote yourselves to prayer. Then come together again so that Satan will not tempt you because of your lack of self-control.”

ትዳር አንድ ወንድና ሴት የህይወት ዘመናቸውን በሙሉ እንደ አንድ ስጋ ሆነው ለማሳለፍ የሚጣመሩበት ኪዳን ስምምነት ነው ፡፡ ለህይወት ዘመናችሁ ሁሉ መጣመር ከማድረግ ይልቅ ለማለት ይቀላል ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ምንም የማይቻል ነገር እንደሌለ ተናግሯል ! አዎን ጠንካራ የሆነ የተዋሃደ ትዳር መመስረት ይቻላል ! ስለዚህም በትዳር ተጣምራችሁ አይኖቻችሁን በክርሰቶስ ላይ በማድረግ በእርሱ መንፈስ ተራመዱ ፡፡

የእግዚአብሔርን መንግስት ለመገንባት ትዳር አንድኛው ቁልፍ ነው ፡፡ ለዚህ ነው ጠላት ትዳርን ለማፍረስ የሚሻው ፡፡ ጠላት ጥፋትን ያደርስ ዘንድ በክፍተቱ ወደ ትዳር ለመግባት ያሴራል ፡፡ ስለዚህም ከትዳር አጋራችሁ ምንም ነገር አትደብቁ ፡፡ መረጃን በግልጽ ከመናገር አትቆጥቡ ፡፡ አንዳችሁ ሌላችሁን ከማገልገል አትለግሙ ፡፡ ከወሲባዊ ትስስራችሁ አታቋርጡ ፡፡ ጌታን ስትታመኑ እና በመንፈስ ስትመላለሱ ከትዳር አጋራችሁ ጋር ግልጽ መሆን ለትዳራችሁ ጥንካሬን ይሰጣል እንዲሁም በክፍተቱ ውስጥ ጣላት ዘልቆ እንዳይገባ እድሎችን ይዘጋል ፡፡ በየትኛውም የትዳር ክፍላችሁ ውስጥ ለክርስቶስ ፍጹምና ንጹህ የሆነ መሰጠት ይኖራችሁ ዘንድ ፈልጉ ፡፡ ወደ እርሱ ስትቀርቡ ክርስቶስ በየቀኑ የሚያስፈልጋችሁን ብርታትና ጥበብ ይሰጣችኋል ፡፡

“ ለጸሎት ትተጉ ዘንድ ተስማምታችሁ ለጊዜው ካልሆነ በቀር ፣ እርስ በእርሳችሁ አትከላከሉ ፤ ራሳችሁን ስለ አለመግዛት ሰይጣን እንዳፈታተናችሁ ደግሞ አብርችሁ ሁኑ ፡፡ “ - 1ኛ ቆሮንቶስ 7፡5

ተጨማሪ ጥቅስ

  • 2ኛ ቆሮንቶስ 11:3 — “ ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት ፣ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽህና ምናልባት እንዳለወጥ ብዬ እፈራለሁ ፡፡ “
  • ገላትያ 5:16 — “ ነገር ግን እላለሁ በመንፈስ ተመላለሱ ፣ የስጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ ፡፡ “
  • ኤፌሶን 5:31-33 — “ ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ሁለቱም አንድ ስጋ ይሆናሉ ፡፡ “