Permissible But Not Beneficial
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ The Last Adam 1 Corinthians 6 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ምዕራፍ (1-4) በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ስላለ መከፋፈል ያወራል ፤ ምዕራፍ (5-7) ስለ ወሲብ ከተለመደ ዉጪ በላይ በሆነዉ ጭብጥ ላይ ያወራል ፡፡ የቆሮንቶሳዊያን ቤተ ክርስቲያን የወሲብ ግንኙነትን በያዙበት መንገድ ላይ ጭብጡ ጉዳይ ነበር ፡፡ በዛሬዉ ምዕራፍ ጳዉሎስ በአማኞች መካከል ስላለ ሙግት በማዉራት ወደ ጭብጡ ይመለሳል ፡፡
ጳዉሎስ መልዕክቱን ለቆሮንቶሳዊያን የፃፈው የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ብዙ ችግሮች ስላሉባት እንደ ነበር እናስታዉሳለን ፡፡ የመጀመሪያዉ ችግራቸዉ በክርስቶስ እንደ ህፃን ይኖሩ/ይሰሩ ነበር ፤ ከጳዉሎስ የተማሩትን የክርስቶስን መንፈሳዊ እዉነቶችን በአለም ካለዉ ከስጋ ፍላጎት እና ፍልስፍና ጋር ቀላቅለዉታል ፤ ከቤተ ክርስቲያን ዉጪ የሆኑትም ባህሪያቸዉ/ፀባያቸዉ አለማዊ ስለ ነበር ቆሮንቶሳዊያን ምን እንዳመኑ መናገር አልቻሉም ነበር ፡፡ ለቆሮንቶሳዊያን ቃላችን/ሀረጋችን ሁለተኛዉ አዳም ነው “ ፊተኛዉ ሰው አዳም ሕያዉ ነፍስ ሆነ ተብሎ ተፅፏል ፤ ኋለኛው አዳም ህይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ “ (1ቆሮ 15፡ 45) ፡፡ ጳዉሎስ ያስገርም ነበር አሁንም ለቆሮንቶሳዊያን ስለ እነዚህ ስጋዊ ስለሆኑ ጉዳዮች እየፃፈ ነበር ፡፡
ትምህርት
1-ቆሮንቶስ (6፡ 1-8)፡ ዋይርስቤ ጳዉሎስ የቆሮንቶሳዊያንን ቤተ ክርስቲያን “ የጠፋትን ኃጢዓተኞችን “ እንዲመለከቱ እንዳዘዛቸዉ ተመልክቷል ፡፡ የቆሮንቶሳዊያን ቤተ ክርስቲያን ሲቪል የሆኑ አለመስማማታቸዉን ወደ ፍርድ ቤት የመዉሰድ ልምድን አሳድገዋል/አዳብረዋል ፤ ጳዉሎስ አንዱ ከሌላዉ ጋር ያለዉን አለመስማማታቸዉን በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ እንዲፈቱ አስጠነቀቃቸው / ገሰፃቸው ፡፡ ዮሐንስ ማክአርቱር “ ሌላ አማኝን በፍርድ ቤት መክሰስ ትርጓሜዉ ከሁሉም ኃጢዓት ጋር የተገናኜ ስለሆነ ያለመታዘዝ የድፍረት ድርጊት ነበር - እግዚአብሄርንም ቅር የሚያሰኝ “ በማለት ፅፏል ፡፡ በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ያለን አለመስማማት ለመፍታት እንዲረዷቸዉ ወደ ማያምኑ የሚሮጡ አማኞች በእምነት አለመብሰላቸዉን ያሳያሉ ፡፡ ዋይርስቤ “ በቅርብ በአንድ 12 ወራት ጊዜ ዉስጥ የፌደራል ፍርድ ቤት 200,000 ሲቪል ክሶችን መዝግቦ እንደ ነበር ፤ 1,000,000 የሚሆኑ ዳኞችም እንዳስተናገዷቸው ፤ በአንድ አመት ዉስጥ 12,000,000 ክሶች በሀገሪቱ ፍርድ ቤት እንደ ተመዘገበ “ አመልክቷል ፡፡
ጳዉሎስ ክርስቲያን ክርስቶስ አለምን በሺዉ አመት መንግስት ላይ ሲፈርድ እንዲሚረዱ አመልክቷል ነገር ግን የቆሮንቶሳዊያን ቤተ ክርስቲያን በመካከላቸዉ ያለዉን ጥቃቅን ግጭቶች መፍታት አልቻሉም ነበር ፡፡ “ ድል ለነሳዉና እስከ መጨረሻም ስራዬን ለጠበቀዉ እኔ ደግሞ ከአባቴ እንደ ተቀበልሁ በአሕዛብ ላይ ስልጣንን እሰጠዋለሁ በብረትም በትር ይገዛቸዋል እንደ ሸክላ እቃም ይቀጠቀጣሉ “ (ራዕ 2፡ 26-27) ፡፡ “ እኔ ደግሞ ድል እንደነሳሁ ከአባቴም ጋር በዙፋኑ ላይ እንደ ተቀመጥሁ ድል ለነሳዉ ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ ይቀመጥ ዘንድ እሰጠዋለሁ “ (ራዕ 3፡ 21) ፡፡
በተጨማሪም ጳዉሎስ ቆሮንቶሳዊያንን አማኞች የሚፈርዱ መለዓክት አካል እንደሚሆኑ ነገራቸው ፤ “ በፈረሱም የተቀመጠውን ጭፍራዎቹንም ይወጉ ዘንድ አዉሬዉና የምድር ነገስታት ጭፍራዎቻቸዉም ተከማችተዉ አየሁ “ (ራዕ 19፡ 19) ፡፡ በክርስቶስ የሚያምኑት በወደቁት መለዓክቶች ላይ የመምራት ድርሻቸዉን ይወስዳሉ ፡፡
ጳዉሎስ አማኞችን ግጭቶቻቸዉን በአለማያን ባለስልጣናት ፊት ይዘዉ ከመሄድ በሌሎች አማዮች የተበደሉ ወይም የተገፉ ቢሆኑ የተሻለ አይደለምን በማለት ሞገታቸው (ቁጥር 7-8) ፡፡ እንደዚህ አይነቶቹ ግጭቶች በማያምኑት ፊት የኢየሱስን ስም የሚያቆሽሹ እና አማኝ መሆንን የማይወዱ እንዲሆኑ ያደርጉአቸዋል ፡፡
1-ቆሮንቶስ (6፡ 9-20)፡ ዋይርስቤ “ ጌታን ለመመልከት/ለመምሰል “ የጳዉሎስን ምክር አስቀምጧል ፡፡ ጳዉሎስ “ የእግዚአብሄርን መንግስት የማይወርሱ “ ሰዎች ድርጊቶችን ዘርዝሯል (ቁጥር 9-10) ፤ አንዳንድ ጊዜ ክርስቲያኖች እነዚህን ድርጊቶች ይፈፅማሉ፣ ማክአርቱር “ በእነዚህ ኃጢዓቶች የሚታወቁ ሰዎች አልዳኑም ፤ አማኞች እነዚህን ኃጢዓቶች ቢያደርጉም እነርሱን እንደማይሰበሩ የህይወት ሂደት አያደርጉአቸዉም …. ኃጢዓት የሚያደርግ እዉነተኛ አማኝ ያን ኃጢዓት በመተዉ በኃጢዓቱ ላይ እንደ ገና አሸናፊ ለመሆን ይፈልጋል “ በማለት ፅፏል ፡፡ ሁላችንም ኃጢዓት የምናደርግበት ክስተት ይኖረናል ፤ ማንም ሰዉ ፍፁም አይደለም ፡፡ ይህ ዝርዝር የተፈጥሮ ሰዉ ባህሪን ያሳያል ፤ ያልዳነ ሰዉ የህይወት አኗኗርን ይገልፃሉ ፡፡ የተፈጥሮ ሰዉ አኗኗርን እና የመንፈሳዊ ሰዉን አኗኗር መቀላቀል የሚቻል አይደለም ፡፡ የቆሮንቶሳዊያን ቤተ ክርስቲያን የድሮ የህይወት አኗኗራቸዉን በመቀጠል ከክርስቶስ ጋር ሊቀላቅሉ ሞከሩ ፡፡ ብዙ አማኞች ተመሳሳይ ነገር እያደረጉ ነው ፤ መልካም መስሎ የሚታየንን ማንኛዉንም ነገር ለመተዉ አንፈልግም ነገር ግን ኢየሱስን ለመቀላቀል እንፈልጋለን ፡፡ ጳዉሎስ አንዴ ክርስቶስን ስንቀበል “ እንደ ታጠብን “፣ “ እንደ ፀደቅን “ እና “ እንደ ነፃን “ አመልክቷል ፡፡ አሁን አማኞች የተለዩ ናቸው ፤ በቁጥር (9-10) የተዘረዘሩት ባህሪዎች ያልዳኑትን ለመግለፅ የሚጠቅሙ ናቸዉ የዳናችሁ ከሆናችሁ ግን ይህ የአኗኗራችሁ ስታይል አካል ሊሆን አይችልም ፡፡
ጳዉሎስ “ ሁሉም ነገር ተፈቅዶልኛል “ ሲል ቆሮንቶሳዊያን “ በማንኛዉም ነገር ቁጥጥር ስር እንዳይሆኑ “ አበረታታቸው (ቁጥር 12) ፡፡ “ ወንድሞች ሆይ እናንተ ለአርነት ተጠርታችኋል ፤ ብቻ አርነታችሁ ለስጋ ምክንያትን አይስጥ ነገር ግን በፍቅር እርስ በእርሳችሁ እንደ ባሪያዎች ሁኑ “ (ገላ 5፡ 13) ፡፡
መደምደሚያ
የኔልሰን ማብራሪያ ከተፈቀዱ ነገር ግን የማይጠቅሙ አምባገነናዊ ከሆኑ ነገሮች ነፃ የምንወጣባቸዉን አምስት ምክሮች ዘርዝሯል፡
- ገደባችሁን/መጠናችሁን ወስኑ ፡፡
- ዉሳኔ እና ድርጊትን ከመፈፀም በፊት ጊዜ መስጠት ፡፡
- ከባለቤታችሁ ወይም ከወዳጆቻችሁ/ከአጋሮቻችሁ ጋር ለመስማማት ወይም ላለመስማማት ትኩረት መስጠት ፡፡
- የምታደርጉትን ነገር ለማስተዳደር፣ ምንን ለመተዉ ፍቃደኞች ናችሁ ?
- እንደምንቀበለዉ የመንተወዉንም መተው ፡፡
ክርስቲያን በክርስቶስ ብዙ ነፃነት አለዉ ነገር ግን ያ ነፃነት በኃጢዓት የሚታወቅ ህይወት ለመኖር ምክንያት አይደለም ፡፡ በዋጋ ተገዝተናል ፤ ጥያቄአችን “ መንግስቱን ምን ይገነባዋል “ የሚል እንጂ “ ምንድን ነዉ የተፈቀደዉ “ የሚል አይደለም ፡፡
Warren W. Wiersbe, Wiersbe’s Exposition Outlines on the New Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 1989), p. 587.
John MacArthur, “The MacArthur Bible Commentary” (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1574.
Wiersbe, p. 587.
Wiersbe, p. 587.
MacArthur, p. 1575.
Earl Radmacher, et. al. Nelson’s Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 1999), p. 1468.
ጥያቄዎች
-
1ቆሮ (6፡ 1-11) እርስ በእርስ ስላለ ሙግት ይናገራል ፤ በመፅሀፍ ቅዱስ ላይ ይህ ርዕስ ስፍራ ለምን እንደያዘ ምን ታስባላችሁ ? ማህበረሰባችን በዚህ ሙግት ላይ እነዚህን ደንቦች ይከተላሉ ? ለምን ወይስ ለምን አይከተሉም ?
-
1ቆሮ (6፡ 5) ምን እያለ ነው ? በአሁኑ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ሊሆን የሚችል ነገርን የሚወስን አንድ አስተዋይ እንዳለ ታስባላችሁ ? ይህ ለአማኞች እና ለማያምኑ ለሁለቱም ይሰራል ? ለምን ወይም ለምን አይሆንም ?
-
በ 1ቆሮ (6፡ 7) ጳዉሎስ “ የእርስ በእርስ ሙግቱ ዉድቀት “ ነዉ በሚለዉ ሀረግ ምን ማለቱ ነዉ ብላችሁ ታስባላችሁ ? የሚሆነዉ ዉጤት ምን ይሆናል ? ማቴ (18፡ 15-17) መልስ ሊሆን ይችላል ? ለምን ወይስ ለምን አይሆንም ?
-
1ቆሮ (6፡ 12) ለሰዉ እንዴት ትገልፁታላችሁ ? “ ተፈቅዶልኛል “ የሚለዉ ትርጓሜዉ ምንድን ነው ? ይህ በመፅሀፍ ቅዱስ ላይ ሌላ የት ስፍራ ተጠቅሷል ? (ማቴ 5፡ 29, 1ቆሮ 10፡ 23, 1ጢሞ 4፡ 8, 2ጢሞ 3፡ 16, ቲቶ 3፡ 8)
-
ግብረ ገብ ያልሆነ ነገር ማለት ምን ማለት ነው ? ከዚህ እንድንሸሽ ለምን ተነገረን ?
-
ጳዉሎስ “ በዋጋ ተገዝታችኋል “ ብሎ በፃፈ ጊዜ ምን ማለቱ ነው (1ቆሮ 6፡ 20) ? ጳዉሎስ ምን አይነት ዋጋ እያለ ነው ? ትንሽ ደቂቃ በመዉሰድ ይህን ዋጋ በማስተዋል ለዚህ ነገር አመስግኑ ፡፡
-
በ 1ቆሮንቶስ 6 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Corinthians 6:11–12
“And some of you used to be like this. But you were washed, you were sanctified, you were justified in the name of the Lord Jesus Christ and by the Spirit of our God. ‘Everything is permissible for me,’ but not everything is helpful. ‘Everything is permissible for me,’ but I will not be brought under the control of anything.”
እንደ አማኝ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔርም መንፈስ ታጥባችኋል፣ ተቀድሳችኋል ደግሞም ጸድቃችኋል ፡፡ በክርስቶስ ሰላምና ነጻነት አላችሁ ፡፡ እግዚአብሔር በቅዱስ መንፈሱ በጥበብና በእውነት ትራመዱ ዘንድ ይሻል ፡፡ በየቀኑ በእርሱ አዕምሯችሁን ስታድሱ ያስታጥቃችኋል ፣ ኃይል ይሰጣችኋል ደግሞም ያበረታችኋል ፡፡
በክርስቶስ ነጻነት አግኝታችኋል ፡፡ ይህ ማለት ግን የኃጢአት ህይወትን ለመምረጥ ነጻነት አላችሁ ማለት አይደለም ፡፡ በክርስቶስ ያለው ነጻነት በመንፈስ እንድትመላለሱ እንጂ በስጋችሁ እንድትኖሩ አይፈቅድላችሁም ፡፡ ስለዚህ ረጋ በሉ ፡፡ ከማድረጋችሁ በፊት አስቡ ፡፡ ከመናገራችሁ በፊት አስቡ ፡፡ ሌሎችንም ተመልክታችሁ ምክርን ጠይቁ ፡፡ በጌታ ላይ አትኩሩ ፡፡ በፍቅር አንዳችሁ ሌላውን አገልግሉ ፡፡ ወደ ስጋ ፈተና ፡- ሴሰኝነት ፣ ጣዖት አምላኪነት ፣ አመንዝራነት ፣ ገንዘብን መውደድ ደግሞም ሰካራምነት ፤ እነዚህ ውስጥ ለመግባት ከመወሰናችሁ በፊት ጊዜ ውሰዱ ተረጋጉ ፣ አትቸኩሉ ፡፡ ፈጥናችሁ ከመግባታችሁ ድርጊትን ከመፈጸማችሁ በፊት አስቡ ፡፡ ከዚያም በጌታ ጽድቅ በፍጹም መመላለስና በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ማደግ ይሆንላችኋል ፡፡
“ ከእናንተም አንዳንዶቹ እንደ እነዚህ ነበራችሁ ፣ ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል ፣ ተቀድሳችኋል ፣ ጸድቃችኋል ፡፡ ሁሉ ተፈቅዶልኛል ሁሉ ግን አይጠቅምም ፡፡ ሁሉ ተፈቅዶልኛል ፣ በእኔ ላይ ግን አንድ ነገር እንኳ አይሰለጥንብኝም ፡፡ “
- 1ኛ ቆሮንቶስ 6፡11-12
ተጨማሪ ጥቅስ
ሮሜ 6:1–2 — “ እንግዲህ ምን እንላለን ? ጸጋ እንዲበዛ በኃጢአት ጸንተን እንኑርን ? አይደለም ፡፡ ለኃጢአት የሞትን እኛ ወደ ፊት እንዴት አድርገን በእርሱ እንኖራለን ? “
1ኛ ቆሮንቶስ 6:9–10 — “ ወይስ ዓመጸኞች የእግዚአብሔርን መንግስት እንዳይወርሱ አታውቁምን ? አትሳቱ ፤ ሴሰኞች ቢሆን ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ቀላጮች ወይም ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሰሩ ወይም ሌቦች ወይም ገንዘብን የሚመኙ ወይም ሰካራሞች ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ነጣቂዎች የእግዚአብሔርን መንግስት አይወርሱም ፡፡ “
ገላትያ 5:13 — “ ወንዲሞች ሆይ እናንተ ለአርነት ተጠርታችኋልና ፤ ብቻ አርነታችሁ ለስጋ ምክንያት ኤስት ፣ ነገር ግን በፍቅር እርስ በርሳችሁ እንደ ባሪያዎች ሁኑ ፡፡
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።