Get The Leaven Out Of The Mix!
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ The Last Adam 1 Corinthians 5 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በምዕራፍ 4 ላይ በብዙ መንፈሳዊ አባቶች የሚመሩ/ቁጥጥር ዉስጥ የነበሩ ቢሆንም በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ በነበረዉ ኃጢዓት ላይ ተመልክተናል ፡፡ ይህን ክፍል ካስተማርኩ በኋላ እንደ መንፈሳዊ አባት እና እናት በእኛ ዉስጥ ስለሚሞሉት/በደንብ ስለሚያስተምሩን እፀልያለሁ በተጨማሪም መስማት የሚያስፈልገንን ማበረታታትም ሆነ ግሳፄን እንድንሰማ ትሁት ልብ እንዲኖረንም እፀልያለሁ ፡፡
ቀድሞ ካይል እንዳስተማረው በ 1ቆሮንቶስ አምስት ክፍሎች አሉ፡
- በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ያለ መከፋፈልን (1ቆሮንቶስ 1-4) ፡፡
- ያልተገባ የወሲብ ግንኙነትን (1 ቆሮንቶስ 5-7) ፡፡
- ከምግብ ጋር የተገናኘ ጉዳይን (1 ቆሮንቶስ 8-10) ፡፡
- የቤተ ክርስቲያን ስነ ምግባርን (1 ቆሮንቶስ 11-14) ፡፡
- የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ (1 ቆሮንቶስ 15) ፡፡
ምዕራፍ 16 ለቅዱሳን እርዳታ የማሰባሰብ፣ የጉዞ እቅዱን እና የመጨረሻ ማበረታቻ የጳዉሎስ ትዕዛዝን ያካትታል ፡፡
የቆሮንቶስ ግልፅ ታሪክ የሚያካትተው፡
ቆሮንቶስ ከክርስቶስ ልደት 146 በፊት በሮማዉያን የጠፋች ነበረች ፡፡
ከክርስቶስ ልደት 44 በፊት በጁሊየስ ቄሳሪያ መልሳ ተመሰረተች ፡፡
ከተማዋ በሁለት ወደቦች መካከል የነበረች እና መርከቦቹም ከግሪክ ዋና ምድር የፌሎፎኔሺያን ፔኒንሱላርን ከቆሮንቶስ ጋር በሚያገናኘው በደሴቱ ላይ በትልቅ ግንድ ይንሽከረከሩ ነበር ፤ ይህ ለተጓዦች እና ለጉዞ አስፈላጊ ስፍራ ነበረች ፡፡
በአዉግስቶስ ቄሳር ስር ከክርስቶስ ልደት 27 በፊት የአኪያን ክፍለ ሀገር ቤተ መንግስት ተደርጋ ነበር ፡፡
የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን በሐዋሪያት ስራ 18 በጳዉሎስ፣ በጵርስቅላ፣ በአቂላ እና በአጵሎስ እርዳታም ተመሰረተች ፡፡
የ 1 ቆሮንቶስ መፅሀፍ መንፈሳዊ ስጦታ እጥረት ያልነበረባቸዉ ነገር ግን በሚገባ በመንፈሳዊ ነገር ላልበሰሉ “ ቅዱሳን “ አማኞች የተፃፈ መልዕክት ነበር ፡፡
ጳዉሎስ በለጋ ቤተ ክርስቲያኖች ዉስጥ አንዳንድ ጉዳዮች ላይ ለማገልገል እየሞከረ ነበር ፡፡
ትምህርት
1-ቆሮንቶስ (5፡ 1-2)፡ ቁጥር አንድ በትንሹ እንግዳ/የተለዬ ነው ፡፡ ጳዉሎስ በአልተገባ/ብልግና በሆነ ወሲባዊ ግንኙነት አብረዉ ስለነበሩ እንጀራ ልጅ እና እንጀራ አባት አመለከተ …. አምላክ የለሽ አሕዛቦች በሆኑት ሰዎች ደረጃ እንኳን ሊደረግ የማይገባዉ (ቁጥር 1) ፡፡ የጳዉሎስ ሀሳብም በስፋት ሪፖርት ተደርጎ የተደረገ ነበር ! ምንም እንኳን በግሪክ-ሮም ባህል ዉስጥ አድስ የሆነ ምንም ነገር ባይኖርም እንኳን በጊዜዉ በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን አንዳንድ የሚያስፈሩ ነገሮች ነበሩ ፡፡ የቆሮንቶስ ከተማ ለሮማን አለም እምብርት ሆኗ ነበር ፡፡ ቁጥር 2 ግራ የሚያጋባ ነው ፡፡ ጳዉሎስ በቆሮንቶስ ያሉ ቅዱሳን በዚህ ክፉ/መጥፎ ተግባር በኃዘን ከመሞላት ይልቅ በትዕቢት ተነፍተዉ/ተኩራርተዉ እንደ ነበር ጨምሮ ተናገረ ፡፡ እነዚህ ድርጊቶች ቤተ ክርስቲያንን በትዕቢት የተሞላች ሊያደርጓት በምን ይችላሉ ? ጳዉሎስ ያልተገባ ድርጊት የሚያደርጉ ጥንዶች ከቤተ ክርስቲያን እንዲወገዱ ተናገረ (ቁጥር 2) ፤ ምናልባትም ቤተ ክርስቲያን የመንፈሳዊነት አለማደግ ድርጊቶቹን ስለማትረዳ ይህ ለእነርሱ ተቀባይነትን እና ፀጋን እያሳዬ እንደ ነበር ስላሰቡ ይሆናል ፡፡ ዛሬ/በአሁኑ ጊዜ ያለ ተግሳፅ/ቅጣት የእግዚአብሄርን ፍቅር ለማሳየት በመሞከር ዉስጥ ብዙ ፍቃዶችን አናደርግምን ? በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ግራጫ/የደበዘዘ አካባቢ የሚሆነዉን ነጭ እና ጥቁር የሆነዉን ነገር አልፈቀድንም ? ሐዋሪያዉ ጳዉሎስ እንደሚለዉ ለእግዚአብሄር ቃል ታዛዦች መሆን አለብን ፡፡
1-ቆሮንቶስ (5፡ 3-5)፡ በእኛ ህይወት ላይ የሚናገሩ የአባት/የተቆጣጣሪ/የባለ ራዕይ መንፈሳዊ ስልጣናቸው በአካል እንኳን በማይኖሩ ጊዜ ክብደቱን እስከመሸከም ድረስ ነው ፡፡ አቋማችንም ጥበብን፣ ማስተካከያን እና ስልጠናን ለመቀበል ክፍት መሆን አለበት (ቁጥር 3) ፡፡ ጳዉሎስ ቤተ ክርስቲያንን በኢየሱስ ስም በአንድ ላይ በመሰብሰብ “ ስለ ስጋዉ ጥፋት “ (ቁጥር 5) በጥፋቱ መልሶ ለሰይጣን እንዲሰጥ ነገራቸው ፡፡ በዚህ ጉዳይ የጳዉሎስ ስም በጭቃ ዉስጥ መድኃኒት የሆነ እንደ ነበር ….. እንዲሁም የቤተ ክርስቲያን ምስክሮችም ነበር (ቁጥር 4-5) ፡፡ ይህ በጣም አስቸጋሪ ቢሆንም አንዳንድ ጊዜ እንዲያነቋቸው ስጋቸዉ የነደደ/የተጎዳ እንዲሆን ሰዎችን ለጠላቶቻቸዉ አሳልፈን መስጠት አለብን ፤ እግዚአብሄር ይህን በተደጋጋሚ በብሉይ ኪዳን በእስራኤል ላይ አድርጎታል ፡፡
1-ቆሮንቶስ (5፡ 6-8)፡ ጳዉሎስ ቤተ ክርስቲያን በትክክል በምን እየተመኩ እንደ ነበር ጠየቃቸው ፤ ምናልባትም ለተግሳፅ ክፍት/የተጋጁ አልነበሩምን ? ጳዉሎስ ጥቂት እርሾ ሙሉዉን የዳቦ ሊጥ ልታበላሸዉ እንደምትችል ገለፀ (ቁጥር 6) ፡፡ ዳቦዉ መልካም/ጥሩ እንዲሆን ቤተ ክርስቲያን አሮጌዉን እርሾ (ብልሹ የሆነዉን የወሲብ ግንኙነት) ማንፃት አስፈለጋት ፡፡ እርሾዉ በፍጥነት ስለሚያድግ አዲሱን ሊጥ ኃጢዓት ከማበላሸቱ በፊት ኃጢዓቱን ማስወገድ ያስፈልጋቸዋል (ቁጥር 7) ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ከብዙ የኃጢዓት ዝርዝሮች/አይነቶች ጋር ስምምነት አድርገናል - ከጋብቻ በፊት ከሚደረግ ወሲብ ጋር፣ ከፖርኖግራፊ፣ ከዝሙት፣ ከፍቺ እና ከግብረ ሰዶምነት ጋር ፤ በዉሲብ ነፃነት ላይ ብዙ ፍቃዶችን አድርገናል ፡፡
ኢየሱስ ፋሲካችን ስለሆነ የክፋት እና የግፍ እርሾን እናስወግድ ፤ ሁላችንም ያልቦካ/እርሾ የሌለበት ቂጣ/ዳቦ እንድንሆን ተጠርተናል (ቁጥር 8) ፡፡ አሰራሩ በጣም ቀላል ነው፡ የክርስቶስ ዱቄት፣ የመንፈስ ዘይት፣ የእግዚአብሄር እዉነት ዉሃ፣ የቅንነት ጨዉ (በተገቢዉ እና በቅንነት እግዚአብሄርን መከተል ) ፡፡
1-ቆሮንቶስ (5፡ 9-13)፡ ጳዉሎስ ቤተ ክርስቲያን አግባብ ያልሆነ ወሲብ ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር እንድትተሳሰር አልፈለገም (ቁጥር 9) ፡፡ እነዚህን ጉዳዮች መፍታት ለቀድሞዋ ቤተ ክርስቲያን ብዙ ጠቀሜታ ነበረው (ራዕ 2፡ 6) ፡፡ ጳዉሎስ ይህንን በዉጪ በአለም ዉስጥ ካሉት ሰዎች ጋር በማገኛኘት ልዩነት እንዳለዉ በማሳየት ግልፅ አደረገው ፤ ክርስቶስን ለመናገር እንኖራለን እንጂ ያለስርዓት አይደለም ፡፡ ጳዉሎስ በተለዬ መልኩ አሁንም እንደ “ አማኝ “ ወይም “ ወንድም “ የተጠሩ ነገር ግን በተበላሸ ስነ ምግባር እየኖሩ ስላሉ እየተናገረ ነበር (ቁጥር 10-11) ፡፡
ጳዉሎስ በዉስጥ ያሉትን ብቻ እንጂ ከቤተ ክርስቲያን ዉጪ ያሉትን እንደ ማይዳኙ አሳሰባቸው ፤ ከቤተ ክርስቲያን ዉጪ ያሉት መዳኘት የእግዚአብሄር ኃላፊነት ነው (ቁጥር 12-13) ፡፡ ፍርድ ከእግዚአብሄር ቤት ይጀምራል ፤ በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ያሉትን እንወዳለን፣ እንደርሳለ እንዲሁም እናስተካክላለን እንጂ (ገላ 6፡ 1, 1ጴጥ 4፡ 17) ፡፡
መደምደሚያ
ኢያሱ 7 በእስራኤል ዉስጥ ስላለ ኃጢዓት ይናገራል ፤ ከወታደሮቹ ዉስጥ የሆነዉ አንዱ አካን ከድል በኋላ ምንም አንወስድም የሚለዉን የእግዚአብሄር ትዕዛዝ በመተው ለእግዚአብሄር ተለይቶ ከነበረዉ ነገር ለራሱ ወሰደ ፤ በቀጣዩ ጦርነትም ላይ በአካን ስዉር ኃጢዓት ምክንያት መላዉ የእስራኤል ሰራዊት ተሸነፈ ፡፡ በቀጣዩም ማለዳ ኢያሱ የአካንን ጥፋተኝነት ለመወሰን በእስራኤል ነገዶች ዉስጥ ሰራ ፤ አካን እና መላዉ ቤተሰቡ በመገደል በድንጋይ ተሸፈኑ ፡፡
እንዲመራን አዲስ ኪዳን ስላለን ደስተኞች አይደለንምን ? የዉጭዉን የፍርድ ስራ ለእግዚአብሄር እንተዉ ምክንያቱም በዉስጥ ያለን ጉዳይ ስለሚበቃን ፡፡ ዘዳ (17፡ 7) “ ክፉን ከእናንተ አስወግዱ “ ይላል፣ ትርጉሙም በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ያለዉን ማለት ነው ፡፡
ጥያቄዎች
-
በዚህ ምዕራፍ ላይ ኃጢዓትን ምን በጣም መጥፎ አደረገው (1ቆሮ 6፡ 18-20) ? ኃጢዓቱስ ምን ነበር ?
-
በቆሮንቶስ የነበረችዉ ቤተ ክርስቲያን ይህን ኃጢዓት እንዴት ምክንያታዊ ወይም ይቀንሰዉ ነበር ? በአሁኑ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ኃጢዓትን እንዴት ምክንያታዊ ታደርገዋለች ?
-
ይህን ሰዉ እስከተቻለ ድረስ በኃጢዓት ለመቅጣት ጳዉሎስ ምን እንዲደረግበት ፈረደ ? በአሁኑ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን እንዴት በሚገባ በፍቅር እንደምትቀጣ ታስባላችሁ ? የቤተ ክርስቲያን መቅጣት አላማዉ ምን እንዲሆን ነው ? (2ቆሮ 7፡ 7-10, 1ጢሞ 1፡ 20)
-
በ 1ቆሮ (5፡ 6-13) የእርሾ ስዕል ምንን ያስተላልፋል (ዘጸዓት 12, ዮሐ (1፡ 29), 1ጴጥ 1፡ 18-25) ? እርሾ የምን መልክ ነው ?
-
ጳዉሎስ ከቤተ ክርስቲያን ዉጪ ባሉት ላይ ስለ መፍረድ ወይም ስለ መክሰስ ምን ፃፈ ? የተገሰፀዉ ሰዉ የቤተ ክርስቲያን አባል ከነበር ቅጣቱ የተደረገዉ በኢየሱስ ስርዓ ስልጣን ነው (2ቆሮ 2፡ 1-11) ? ከቤተ ክርስቲያን ወጪ ባሉ ላይ እና እንደ ጌታ በኢየሱስ በተጠሩት መካከል የመፍረድ ልዩነቱ ምንድን ነው ?
-
በ 1ቆሮንቶስ 5 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Corinthians 5:8
“Therefore, let us observe the feast, not with old yeast or with the yeast of malice and evil but with the unleavened bread of sincerity and truth.”
የሆነ ነገር የምትወዱትን ደስ የሚያሰኛችሁን መጠጥ እንደሚበክልባችሁ ብታውቁ ፣ ንጹህ ደስ የሚያሰኘውን ጣዕም ማጣጣም ትችሉ ዘንድ ከእርሱ ትርቃላችሁ ፡፡ ማነው የቀዘቀዘ ሻይን ከትንስ የእቃ ሳሙና ጋር አድርጎ የሚጠጣ ? ያስጠላላ ! የክርስቲያንም ህይወት እንድሁ ፡፡ ጌታ ከተወሰኑ ነገሮች እንድትሸሹ ያስጠነቅቃል ፡- ከዝሙት ፣ ከግፍ ደግሞም ከክፋት ፡፡ እነዚህ ነገሮች ከጌታ ጋር ያለውን ምልልሳችሁን ያቆሽሻሉ ፡፡
ክርስቶስ ከእርሱ ጋር ያለው ህይወታችሁ በቅንነትና በእውነት እንድሞላ ይፈልጋል ፡፡ እርሱ በቃሉ እውነት ላይ በማትኮር እና እርሱን ከልባችሁ ፣ ከፍ ባለ ስሜት እንድሁም በቅንነት እንድትወዱት ይፈልጋል ፡፡ በዝሙት ፈተና እና በኃጢአት ውስት ስትሳተፉ ፤ ሌሎችን በቅናት ስትመለከቱ ወይም ደግሞ የክፋትን አሳብ ስታስቡ ፣ ከጌታ ጋር ያለውን መንገዳችሁን ታቆሽሻላችሁ ፡፡ እርሱ ለእናንተ ያዘጋጀውን ሁሉ ትቀበሉ ዘንድ ጌታ ከእርሱ ጋር በቅንነት እንድትመላለሱ ይሻል ፡፡ እግዚአብሔር የፍቅር ፣ የጸጋና የምህረት አምላክ ነው ፡፡ ዛሬ ፈተና ሲገጥማችሁ ራሳችሁን ጠይቁ ፡- “ ይህንን በብርጭቆ ያለ የቀዘቀዘ ሻይ ማቆሸሽ እፈልጋለሁን ? “ ለመበርታት ፣ ለመጽናት ደግሞም ለክርስቶስ ንጹህ ሁኖ ለመቆየት ወስኑ ፡፡ በመንፈስ ስትመላለሱ እርሱ ብርታትን እንደሚሰጣችሁ ተናግሯል ፡፡
“ ስለዚህ በቅንነትና በእውነት ቂጣ በዓልን እናድርግ እንጂ በአሮጌ እርሾ በክፋትና በግፍ እርሾም አይደለም ፡፡ “
- 1ኛ ቆሮንቶስ 5፡8
ተጨማሪ ጥቅስ
1ኛ ቆሮንቶስ 5:1–2 — “ በአጭር ቃል በእናንተ ዘን ዝሙት እንዳለ ይወራል የዚያም አይነት ዝሙት በአህዛብስ እንኳ የማይገኝ ነው ፣ የአባቱን ሚስት ያገባ ሰው ይኖራልና ፡፡ እናንተ ታብያችኋል ፤ ይልቅስ እንድታዝኑ አይገባችሁምን ? ይህን ስራ የሰራው ከመካከላችሁ ይወገድ ፡፡ “
ገላትያ 5 :16 — “ ነገር ግን እላለሁ ፣ በመንፈስ ተመላለሱ ፣ የስጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ ፡፡ “
2ኛ ጢሞቴዎስ 2:21–22 — “ እንግዲህ ማንም ራሱን ከእነዚህ ቢያነጻ ፣ ለክብር የሚሆን የተቀደሰም ለጌታውም የሚጠቅም ለበጎም ስራ ሁሉ የተዘጋጀ ዕቃ ይሆናል ፡፡ ከክፉ የጎልማሳነት ምኞት ግን ሽሽ ፣ በንጹህም ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን እምነትን ፍቅርን ሰላምን አትብቀህ ተከተል ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።