Paul's Letters 1 Corinthians

Keys To Spiritual Fathering

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ The Last Adam 1 Corinthians 4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 506 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ትናትና በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን እየተከናወነ በነበረዉ መከፋፈል ላይ ጳዉሎስ በጣም አስቦ እንደ ነበር ተምረናል ፤ ዛሬ በምዕራፍ 4 በእነዚያ መከፋፈሎች የጳዉሎስ ትምህርቶች ላይ እንቀጥላለን ፡፡ ይህን ምዕራፍ መንፈሳዊ አባት እና መንፈሳዊ እናት ለመሆን 9 ቁልፎች ላይ በመመልከት እንመለከተዋለን/እንዳስሰዋለን ፡፡

ትምህርት

  1. መንፈሳዊ አባት / እናት በታማኝነት ያገለግላል (1ቆሮ 4፡ 1-2) ፤ እንደ ክርስቶስ አገልጋዮች የታየን መሆን አለብን ፡፡
  2. መንፈሳዊ አባት / እናት ለእግዚአብሄር ተጠያቂነት ያለባቸዉ ናቸው ( 1ቆሮ 4፡ 3-5) ፤ በማንም ሳይሆን በእግዚአብሄር ተጠያቂነት አለብን ፡፡ የሚመዝነን/የሚገመግመን ጌታ ብቻ ነው ፡፡
  3. መንፈሳዊ አባት / እናት ዋጋ በመክፈል በሚገባ በመሙላት ስልጣንን ያስተላልፋሉ (1ቆሮ 4፡ 6-8) ፡፡ ጳዉሎስ፣ አጵሎስ እና ኬፋ/ጴጥሮስ ሁሉም በቆሮንቶስ ጊዜ ነበራቸው ፤ ሰዎስቱም በቤተ ክርስቲያኗ ዉስጥ አስተምረዋል ፤ አንዱን ከሌላዉ ማወዳደር አንችልም ?
  4. መንፈሳዊ አባት/እናት ሌሎች ትካሻዎቻቸዉን ያስጀምራሉ ፤ ጥሪአቸው የቀጣዩ ትዉልድ መነሻ/ወለል ነው (1ቆሮ 4፡ 8) ! ስለ ክርስቶስ እኛ ከፈፀምነዉ በብዙ የሚበልጥ ልጆቻችን እንዲፈፅሙ እንፈልጋለን ፡፡
  5. መንፈሳዊ አባት/እናት ትህትናን እና ልበ ሙሉነትን ሁለቱንም ያሳያሉ (1ቆሮ 4፡ 9-13) ፡፡ የጳዉሎስ በራስ መተማመን ጠርቶት በነበረዉ እግዚአብሄር ነበር ፤ ትህትናው የኋላ ስፍራን ለመያዝ የእርሱ ፍቃደኝነቱ ላይ ነበር ፡፡
  6. መንፈሳዊ አባት/እናት ሞኝነት የሆነ እምነት ያሳያሉ (1ቆሮ 4፡ 10) ፤ በአስቸጋሪ ጊዜያት በእምነት መጓዝ ለማያምኑት የሚያምኑት ሞኞች የመሰሉ ሊያደርጋቸዉ ይችላል ፡፡
  7. መንፈሳዊ አባት/እናት የሚያስተምሩ መምህራንን ይቀርፃሉ…(1ቆሮ 4፡ 14-16) ፤ እግዚአብሄር ቀጣዩ ትዉልድ በክርስቶስ የሆነ እንዲሆን የሚጋደሉ እናቶች እና አባቶችን ያስነሳል - እንደ እግዚአብሄር የሆነ እምነት እንዲኖራቸዉ የሚያደርጉ ፡፡
  8. መንፈሳዊ አባት/እናት መንፈሳዊ አባት/እናትን ይፈጥራል/ይወልዳል (1ቆሮ 4፡ 17) ፤ ጢሞቲዎስ የጳዉሎስ ቁጥጥር ዉጤት ነበር ፡፡
  9. መንፈሳዊ አባት/እናት በፍቅርና በጥብቅ ይገስፃል (1ቆሮ 4፡ 18-12) ፡፡ መንፈሳዊ አባት/እናት በፍቅር ለመገሰፅ አይፈሩም (ዕብ 12፡ 7-13) ፡፡

መደምደሚያ

ሚል (4፡ 6) ይህ ጠቅላላ ምዕራፍ “ መጥቼም ምድርን በእርግማን እንዳልመታ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል “ ብሎ ይጠቀልለዋል ፡፡ ምናልባትም ቀጣዩን ትዉልድ የምናስነሳ መንፈሳዊ አባት እና እናት እንሆናለን ፡፡

ጌታ አባቶችን እና እናቶችን ያስነሳል ፡፡

ጌታ የሚማሩ ወንዶች እና ሴቶች ልጆችን ያስነሳል ፡፡

በምዕራፍ 5 ስንመለከት “ ለአባቶቻቸዉ “ ምኞት በሚያቀርቡ ጥቂት “ ልጆች “ ላይ ትንሽ ችግር ነበር ፡፡

ጥያቄዎች

  1. ጳዉሎስ ራሱን እና ሌሎች የቤተ ክርስቲያን መሪዎችን እንደ “ እግዚአብሄር ሚስጥር ባላደራዎች “ ገለፀ ፤ በዚህ አገላለፅ የባላደራ ትርጉሙ ምንድን ነው ? በጣም ከፍ ያለ ስፍራ/ስልጣን ነው ?
  2. በ 1ቆሮ (4፡ 5) መሰረት የተደበቀዉን ነገር ወደ ብርኃን በማምጣት የሰዉን ልብ መሻት መግለጥ የማን ኃላፊነት ነው ?
  3. በ 1ቆሮ (4፡ 6) ጳዉሎስ ቆሮንቶሳዊያንን ተፅፎ ከነበረዉ አትለፉ ሲላቸዉ ምን ማለቱ እንደሆነ ምን ታስባላችሁ ?
  4. 1 ቆሮ (4፡ 7) ስታነቡ ጳዉሎስ በቆሮንቶስ ለአማኞች ምንን ኃሳብ እያደረገላቸዉ እንደ ነበር ግለፁ ፡፡
  5. በ 1ቆሮ (4፡ 15) ጳዉሎስ በክርስቶስ ብዙ መሪ/አዛዥ እንደ ነበራቸው ነገር ግን ብዙ መንፈሳዊ አባቶች እንደሌሏቸዉ በተናገረ ጊዜ ምን ማለቱ እንደ ሆነ ምን ትላላችሁ ? የእናንተ “ መንፈሳዊ አባት/እናት “ ማነው ?
  6. በ 1ቆሮንቶስ 4 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Corinthians 4:10

“We are fools for Christ, but you are wise in Christ. We are weak, but you are strong! You are distinguished, but we are dishonored!”

ልክ እንደ ሐዋርያው ጳውሎስ ለክርስቶስ እንደ ሞኝ ኑሩ ፡፡ ያ ምን ማለት ነው ? ማለትም ምናልባት ህይወታችሁ ከውጪ ለሚያዩት ትርጉምን ላይሰጥ ይችላል ፡፡ ይህ ማለት ሌሎች ሊተቹዋችሁና ሊመዝኑዋችሁ ይችላሉ ነገር ግን እናንተ እውነተኛው ሚዛን ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደሆነ ታውቃላችሁ ፡፡ ለክርስቶስ ሞኝ መሆን ዳካማ ሊያስመስል ይችላል ነገር ግን እናንተ በእርሱ ብርቱ እንደሆናችሁ ታውቃላችሁ ፡፡ የተዋረዳችሁ ሊመስል ይችላል ነገር ግን ተለይታችኋል ፣ በእግዚአብሔር ፊት ቅዱስ ካህናት ናችሁ ፡፡ ልትሰደዱና ልትጣሉ ትችላላችሁ ነገር ግን እንደ ኢየሱስ መካራን ትቀበላላችሁ ፡፡ ምንም እንኳ የሚታየው ደስ ባያሰኝም ጌታ የማይታየውን ያያል ፡፡ የሚታየው ጊዜያዊ ነውና ነገር ግን የማይታየው ብዙ ክብርን ያስገኛልና ፡፡

ዙሪያችሁን ተመልከቱ ፡፡ ለክርስቶስ ሞኝ የሆነን ሰው ፈልጉ ፡፡ ሰውን ደስ ለማሰኘት የማይሰራ ነገር ግን ይልቁንም በፍጹም ትህትና እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት የሚኖርን ሰው ፡፡ እናም ያን ሰው ስታገኙት ፣ እርሱ ክርስቶስን እንደሚመስል እናንተም እርሱን ለመምሰል እሹ ፡፡ ክርስቶስ እንደኖረው ስትኖሩና እርሱ እንደወደደ ስትወዱ ፍጹም ደስታና ሰላም ታገኛላችሁ ፡፡ ዛሬ እንደ ሞኝ ውጡ…… ለክርስቶስ ሞኝ እንደሆነ ፡፡

“ እኛ ስለ ክርስቶስ ሞኞች ነን እናንተ ግን በክርስቶስ ልባሞች ናችሁ ፤ እኛ ደካሞች ነን እናንተ ግን ኃለኞች ናችሁ ፤ እናንተ የከበራችሁ ናችሁ እኛ ግን የተዋረድን ነን ፡፡ “

-1ኛ ቆሮንቶስ 4፡10

ተጨማሪ ጥቅስ

  • 1ኛ ቆሮንቶስ 4:15–16 — “ በክርስቶስ አእላፍ ሞግዚቶች ቢኖሩአችሁ ብዙ አባቶች የሉአችሁም እኔ በክርስቶስ ኢየሱስ ወንጌል ወልጄአችኋለሁና ፡፡ እንግዲህ እኔን የምትመስሉ ሁኑ ብዬ እለምናችለሁ ፡፡ “
  • 2ኛ ቆሮንቶስ 4:16–18 — “ ስለዚህ አንታክትም ፣ ነገር ግን የውጭው ሰውነታችን ቢጠፋ እንኳ የውስጡ ሰውነታችን ዕለት ዕለት ይታደሳል ፡፡ የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት ፣ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ያደርግልናልና ፤ የሚታየው የጊዜው ነውና ፣ የማይታየው ግን የዘላለም ነው ፡፡
  • ኤፌሶን 5:1–2 — “ እንግዲህ እንደተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትከተሉ ሁኑ ፣ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መስዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ በፍቅር ተመላለሱ ፡፡ “