The Problem Of Spiritual Immaturity
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ The Last Adam 1 Corinthians 3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በ 1ቆረንቶስ 3 ላይ ማክአርቱር ማብራሪያዉን “ በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ የችግር መንስኤዎች ከዉጨኛዉ እና አለማዊ ከሆነዉ ተፅዕኖ በላይ የሚበልጥ ነበር ፤ በተጨማሪም ዉስጣዊ ስጋዊነትም ነበር ፤ የአለም ግፊት ከስጋ ደካማነት ጋር የተጣመረ ነበር “ በማለት በዚህ መንገድ ይጀምራል ፡፡ ቆሮንቶስ ከሚታወቀዉ ማንኛዉም አለም ለሚመጡ እና ለሚሄዱ ከሮም፣ ከአቴንስ እና ከኤፌሶን ለሚመጡ ተጓዦች መከል ላይ ነበረች ፡፡ በከተማዋ ዙሪያ እየሄዱ በነበሩት በእነዚያ ሁሉ የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን በዚያ ተሰራጭቶ ለነበረዉ ብልሹ ምግባር እንደ መደበቂያነት እየጀመረች ነበር ፡፡
ከምዕራፍ 2 ዋይርስቤ ሁለት ቡድኖችን ይገልፃል - ከእግዚአብሄር ዉጪ በተፈጥሮ መኖርን በመምረጥ እንደ “ ተፈጥሮ “ መረዳት የሚችሉ የእግዚአብሄር መንፈስን የማይቀበሉ አላማኞችን እና ለመንፈስ ቅዱስ ክፍት በመሆናቸው እንደ “ መንፈሳዊነት “ መረዳት የሚችሉ አማኞችን (ቁጥር 14-15) ፡፡ እነዚህ ሁለቱ የዳኑ እና ያልዳኑ ተብለዉ የተከፋፈሉ ናቸው ፡፡
ዋይርስቤ በምዕራፍ 3 የተሸፈነ ሌላ መከፈልን ያመለክታል - የበሰሉ /የጠነከሩ ወይም ያልበሰሉ/ያልጠነከሩ አማኞች በማለት ፡፡ የበሰሉት/የጠነከሩት “ መንፈሳዊ “ ሲሆኑ ያልበሰሉት ደግሞ “ ስጋዊያ “ ወይም በስጋ ፈቃድ የሚኖሩ ናቸው ፤ በእነዚህ መከፋፈል መሰረት ዋይርስቤ ምዕራፉን ወደ ሰዎስት ክፍል ይከፋፍለዋል፡ ቤተሰብ፣ እርሻ እና ቤተ መቅደስ ፡፡
ትምህርት
1-ቆሮንቶስ (3፡ 1-4)፡ ዋይርስቤ እነዚህን ክፍሎች “ የቤተሰብ -ብስለት “ በማለት ይገልፃቸዋል ፡፡ ጳዉሎስ እንደ መንፈሳዊ ሰዎች ቆሮንቶሳዊያን ሊናገራቸዉ እንዳልቻለ ያመለክታል ምክንያቱም በክርስቶስ ህፃናት ስለ ነበሩ ….. ስጋዊ አስተሳሰብ ስለ ነበራቸው (ቁጥር 1) ፡፡ ማክአርቱር በእምነት ህፃናት የሆኑ “ የበሰሉ ስላለመሆናቸዉ ምክንያት ስላልነበራቸው ጳዉሎስ አስተምሯቸዉ በነበረዉ ብርሃን ሁሉ እንደ በሰለ አማኝ ሊፅፍላቸዉ እንደሚገባ እንዳመለከተ “ ያመለክታል ፡፡
ጳዉሎስ በመንፈሳዊ ነገር የተዘጋጁ ስላልነበሩ ከጠንካራ ምግብ ይልቅ ወተትን ሰጥቷቸዉ እንደ ነበር ተናገረ - አሁንም በስጋ እየኖሩ የነበሩና እንደማያምኑት በቅናት፣ በክርክር እና በራስወዳድነት እየኖሩ ነበር (ቁጥር 2-3) ፡፡ ወተት “ ለሆነ አስተምሮ ማጣቀሻ/ማሳያ አልነበረም ነገር ግን ለአዲስ አማኞች ይሰጥ የነበረ በቀላሉ ሊገባ የሚችል የአስተምሮ እዉነት ሲሆን “ ጠንካራ ምግብ ደግሞ “ የመፅኀፉን አስተምሮ የጠለቀ መልክን ያካተተ ነው “ ፤ ያ ማለት እዉነቱ የተለያየ ነዉ ማለት አይደለም አስተምሮዉ/ትምህርቱ በእነዚህ እዉነቶች ላይ በጥልቀት ሊሄድ ይችላል ማለት ብቻ ነው (ዕብ 5፡ 11-14) ፡፡ ስለዚህ አንድ መሪ ደቀ መዝሙርን በሌላዉ ላይ መምረጥ መንፈሳዊ ያለመሆን ምልክት ነው (ቁጥር 4) ፡፡ ብስለት ከመሪ ወይም ከፓስተር አይመጣም በመንፈስ ቅዱስ በኩል ከክርስቶስ ብቻ እንጂ ፡፡
1-ቆሮንቶስ (3፡ 5-9)፡ ዋይርስቤ ይህን ክፍል “ የእርሻ - ብዛት “ በማለት ይገልፃቸዋል ፡፡ ጳዉሎስ እሱና አጵሎስ እያንዳንዳቸዉ እግዚአብሄር እንዲሰሩ የጠራቸዉን የሚያደርጉ አገልጋዮች እና እያንዳንዳቸው እንዲፈፅሙት የተለያየ ተግባር ተሰጥቷቸዉ የነበሩ አገልጋዮች እንደ ነበሩ አመለከተ (ቁጥር 5-7) ፡፡ እግዚአብሄር እድገትን በመስጠት ክብርን ተቀበለ ፤ በተጨማሪም እግዚአብሄር እያንዳንዳችንንበእግዚአብሄር እርሻ ላይ “ ለአንድ አላማ “ እንደ አብሮ ሰራተኛ በአንድ እንድንሰራ ጠርቶናል (ቁጥር 8-9) ፡፡ ዋይርስቤ “ በአገልግሎት ዉስጥ ልዩነት “፣ “ በአላማ አንድነት “ እና “ የመንፈስ መታዘዝ “ እንዳለ ያመለክታል ፡፡
1-ቆሮንቶስ (3፡ 9-23)፡ ዋይርስቤ ይህን ክፍል “ የቤተ መቅደስ ጥራት “ በማለት ይገልፃቸዋል ፡፡ አማኞች ክርስቶስ በመሰረተዉ መሰረት ላይ የሚገነቡ የእግዚአብሄር ህፃዎች ናቸው (ቁጥር 9-11) ፡፡ ቤተ መቅደሱ የተሰራዉ በተመረጠ የተገነባ/የተሰራ ነው - ዋጋ በማይገኝለት እና ሊጠፋ በማይችል (ቁጥር 12-13) ፡፡ ማንም ሰዉ በሰራዉ አይመካም ይልቁንም ሁሉም ነገር ከእግዚአብሄር እንደሚመጣ ያስተዉላል እንጂ (ቁጥር 21-23) ፡፡
መደምደሚያ
ስለዚህም እናንተ በክርስቶስ ናችሁ ክርስቶስ ደግሞ በእግዚአብሄር ነው ፤ ይህ ጳዉሎስ የሚስለዉ አስደናቂ መልክ ነው ፡፡ የቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያንን ሲያድጉ፣ ሲበስሉ፣ በፍሬ ሲበዙ እና በቤተሰብ፣ በእርሻ እና በቤተ መቅደስ በጥራት ሲሆኑ ማየት ፈለገ ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1569.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 1989), p. 577.
Wiersbe, p. 577.
Wiersbe, pp. 577.
MacArthur, p. 1569.
MacArthur, p. 1569.
Wiersbe, p. 578.
Wiersbe, p. 579.
Wiersbe, p. 579.
ጥያቄዎች
-
ጳዉሎስ ቆሮንቶሳዊያንን በክርስቶስ እንደ ህፃን ሲገልፃቸው ያለመብሰላቸዉ/ያለማደጋቸዉ ምልክቶች ምን ነበሩ ? (1ቆሮ 3፡ 1-4)
-
በ 1ቆሮ (3፡ 9) ጳዉሎስ ቆሮንቶሳዊያንን የእግዚአብሄር እርሻዎች እና የእግዚአብሄር ህንፃዎች ናችሁ በማለት ጠራቸው ፤ በዚህ ምን ማለቱ እንደሆነ ምን ታስባላችሁ ? አንድ ገበሬ ከእርሻዉ ምን እንደሚያገኝ ይጠብቃል (ማቴ 13፡ 8) ? አንድ ገንቢ/ሰራተኛ/ግንበኛ ህንፃዉን በመስራት ምን እንደሚያገኝ ይጠብቃል ? (1ጴጥ 2፡ 4-5)
-
በ 1ቆሮ (3፡ 10-17) ጳውሎስ ኢየሱስ መሰረቱ ስለሆነዉ ሕንጻ ፅፏል ፤ ይህ ህንፃ ከግል ክርስቲያናዊ ህይወት ጋር እንደ ሚቃወም የተለመደ/አካባቢ ላይ ያለ ቤተ ክርስቲያን ሊሆን እንደሚችል ታስባላችሁ ? (ኤፌ 2፡ 19-22)
-
የወርቅ፣ የብር እና የከበሩ ድንጋዮች ጥራታቸዉ ምንድን ነው (1ቆሮ 3፡ 12) ? የእንጨት፣ የሳር እና የሰንበሌጥ ጥራትስ ምንድን ነው ? በእነዚህ በእያንዳንዳቸዉ ማቴሪያሎች ላይ የእሳት ተፅዕኖዉ/የሚያደርሰዉ ነገር ምንድን ነው ? እነዚህ ማቴሪያሎች/ቁሶች ምን እንደሚወክሉ ምን ታስባላችሁ ? (ምሳ 3፡ 13-15, 1ቆሮ 1፡ 30, 2ጢሞ 2፡ 15-21)
-
በ1ቆሮንቶስ (1-3) ዉስጥ ጳዉሎስ ስለዚህ አለም ጥበብ እና ስለ እግዚአብሄር ጥበብ እንዲሁም ምንም የሚያስመካን እንደሌለ ብዙ አዉርቷል ፤ 1ቆሮ (3፡ 21-23) ለመመካት ማንኛዉንም መሰረት ብቻ ሳይሆን በአማኞች መካከል ሁሉንም ፉክክር እንዴት ያስወግዳል ? (ዮሐ 17፡ 22-23)
-
6፣ በ 1ቆሮንቶስ 3 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Corinthians 3:5–7
“What then is Apollos? And what is Paul? They are servants through whom you believed, and each has the role the Lord has given. I planted, Apollos watered, but God gave the growth. So then neither the one who plants nor the one who waters is anything, but only God who gives the growth.”
ልክ ጳውሎስ እንደ ተከለ ፤ አጵሎስ ደግሞ እንዳጠጣ ሁሉ አናንተም በመንግስቱ ውስጥ የክርስቶስን ደስታ ፣ ሰላምና ጽድቅ በማሳየት የምትጫወቱት ሚና አላችሁ ፡፡ ለተሰጣችሁ የስራ ድርሻ ሀላፊነት ውሰዱ ፡፡ ሌሎች ስለሚሰሩት ነገር አትጨነቁ ፡፡ ይልቁንም እግዚአብሔር የሰጣችሁን ስጦታ ተጠቀሙ ፡፡ እግዚአብሔር የሚያየው ምን እንደሆነ ለማየት ደግሞም እንዴት ሁሉም ሀላፊነቶች በአንድነት ለአንድ አላማ ፡- እግዚአብሔርን ለማክበር እንደሚሰሩ ፣ ለማየት አይኖቻችሁን ክፈቱ ፡፡
ራሳችሁን ሰውን ከፍ ከፍ ስታደርጉ ወይም ደግሞ በራሳችሁ ስትመኩ ካገኛችሁት ፣ አቁሙ ፤ በእግዚአብሔር ፊት ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ ፤ የትዕቢት አሳብህንም ተው እናም ምስጋና እና ክብርን ለእግዚአብሔር ስጡ ፡፡ የተሰጣችሁን ሀላፊነት በታማኝነት ስትወጡ ልክ የወንጌልን ዘር እንደምትዘሩበት ጊዜ ሁሉ ተስፋ መቁረጥ ይሰማችሁ ይሆናል ነገር ግን ውዲያውኑ እድገትን አታዩም ፡፡ አስታውሱ ኃይልን የሚሰጣችሁ እግዚአብሔር ነው ፤ ጸጋን የሚሰጣችሁ እግዚአብሔር ነው ፤ ጥበብን የሚሰጣችሁ እግዚአብሔር ነው ፡፡ በመጨረሻም እድገትንም እግዚአብሔር ይሰጣል ፡፡ መንግስት የእግዚአብሔር ነው እናም በእርሱ ያድጋል ይሰፋል ፡፡ ዛሬ ለተሰጣችሁ ሀላፊነት አመስግኑ እናም ማሳደግን ለእግዚአብሔር ተውለት ፡፡
“ አጵሎስ እንግዲህ ምንድር ነው ? ጳውሎስስ ምንድር ነው ? በእነርሱ እጅ ያመናችሁ አገልጋዮች ናቸው ፡፡ ለእያንዳቸውም ጌታ እንደ ሰጣቸው ያገለግላሉ ፡፡ እኔ ተከልሁ አጵሎስም አጠጣ ነገር ግን እግዚአብሔር ያሳድግ ነበር ፤ እንግዲያስ የሚያሳድግ እግዚአብሔር እንጂ የሚተክል ቢሆን ወይም የሚያጠጣ ቢሆን አንዳች አይደለም ፡፡ “
- 1ኛ ቆሮንቶስ 3፡5-7
ተጨማሪ ጥቅስ
ማቴዎስ 6:33 — “ ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግስት ጽድቁንም ፈልጉ ፣ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል ፡፡ “
ሉቃስ 6:20 — “ እርሱም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ዓይኑን አነሳ እንዲህም አላቸው ፡- እናንተ ድሆች ብጹአን ናችሁ ፣ የእግዚአብሔር መንግስት የእናንተ ነውና ፡፡ “
1ኛ ቆሮንቶስ 3:21–23 — “ ስለዚህም ማንም በሰው አይመካ ፡፡ ነገር ሁሉ የእናንተ ነውና ፡፡ ጻውሎስ ቢሆን አጵሎስም ቢሆን ኬፋም ቢሆን ዓለምም ቢሆን ሞትም ቢሆን ያለውም ቢሆን የሚመጣውም ቢሆን ፣ ሁሉ የእናንተ ነውና ፣ እናንተም የክርስቶስ ናችሁ ክርስቶስም የእግዚአብሔር ነው ፡፡
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።