God's Hidden Wisdom
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ The Last Adam 1 Corinthians 2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ትናትና እንደ ተመለከትነው ቆሮንቶስ ወደ ሁለት መፅሀፍ የተከፈለ እና በግሪክ ለቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን በጳዉሎስ የተፃፈ ነበር ፡፡ የጳዉሎስ ትክክለኛ የአገልግሎት ጊዜዉ በቆሮንቶስ በሐዋሪያት ስራ 18 የተመዘገበ ነው ፡፡ መልዕክቶቹ በዚያ ላለዉ አገልግሎቱ ምላሽ እና ቤተ ክርስቲያንን ትቶ ከሄደ በኋላ ስለ ሰማዉ ነገር ነበሩ ፡፡ ሲያገለግል ጳዉሎስ ወንጌልን የመስበክ የክርስቶስ ተልዕቆዉን ታዝዟል ፡፡
ዋይርስቤ በክርስቶስ ተልዕኮ እና በጳዉሎስ አገልግሎት መካከል ያለዉን ተመሳሳይነት ያመለክታል ፤ ከማቴ (28፡ 18-20) የክርስቶስ ተልዕኮ የሚያካትተዉ፡ ስለዚህ ሂዱ (ቁጥር 18)፣ ደቀ መዛሙርት አድርጉ (ቁጥር 18)፣ እንዲያጠምቋቸው (ቁጥር 19) እና እንዲያስተምሯቸዉ (ቁጥር 20) የሚሉትን ያካትታል ፡፡ ከሐዋሪያት ስራ 18 የጳዉሎስ አገልግሎት በቆሮንቶስ ያካተተው፡ ወደ ቆሮንቶስ ሄደ (ቁጥር 1)፣ በምኩራብ አስተማረ/ሰበከ ከዚያም ብዙዎች ሰምተዉ በማመን ተጠምቀዉ ነበር (ቁጥር 8)፣ ከእነርሱ ጋር ለ18 ወራት በመቀመጥ ደቀ መዛሙርት በማድረግ አስተማራቸው (ቁጥር 11) ፡፡
ጳዉሎስ የክርስቶስ ተልዕኮ ትዕዛዝን ፈፅሟል ፡፡ በአሁኑ ጊዜ በፍፁም እምነታቸዉን የማያጋሩ፣ በፍፁም ሰዉን ወደ እምነት የማይመሩ እና ማንንም የማያጠምቁ የአማኞቹን ቁጥራዊ መረጃ ከፍተኛ እንደሆነ ታውቃላችሁ ? ጳዉሎስ በክርስቶስ ተልዕኮ በመጓዝ በመታዘዝ ፈፀመ ፡፡
ትምህርት
1-ቆሮንቶስ (2፡ 1-16)፡ ጳዉሎስ ከመጀመሪያው ኃይለኛ ተናጋሪ ስለ ነበር ወደ እነርሱ እንዳልምጣ ነገር ግን ከእነርሱ ጋር የኢየሱስ ክርስቶስን መልዕክት ሊነግራቸዉ እንደመጣ ገለፀ (ቁጥር 1-2) ፡፡ ጳዉሎስበድካምና በፍርኃት እንደመጣ ነገር ግን ቃሉ በእርሱ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ የኃይል ማሳያ እንደ ነበር አሳወቃቸው (ቁጥር 3-4) ፤ ስለዚህም የአማኞች እምነት ጳዉሎስ ካደረጋቸዉ ማንኛዉም ነገር ይልቅ በእግዚአብሄር ኃይል ብቻ ላይ ይሆናል (ቁጥር 5) ፡፡
ምናልባትም እነዚህ ቁጥሮች በመፅኀፍ ቅዱስ ዉስጥ አንዱ ምርጥ የወንጌል ትምህርት ናቸው ፡፡ ጳዉሎስ የመናገር ችሎታ ተሰጥቶት ያልነበር እና እስከመንቀጥቀጥ ድረስ ይፈራ እንደ ነበር ይሁን እንጂ እግዚአብሄር ጳዉሎስን መልዕክቱን በሚገባ እንዲናገር ኃይልን እንደሰጠው አሳወቀ/ተናገረ ፡፡ ጄን ቦንስታር ሙሴ በዘጸዓት (3-4) እግዚአብሄር የጠየቀዉን (ሁሉንም ጳዉሎስ ሊጠቀምባቸዉ ችሏል) ለምን ማድረግ እንዳልቻለ ያቀረባቸዉን አምስት ምክንያቶች ይዘረዝራል፡ 1) በሚገባ በቂ አልነበረም (3፡ 11)፣ 2) የሚያደርገዉን በሚገባ አያውቅም (3፡ 13)፣ 3) የሚለዉን ሰዎች እንደማያምኑት ማሰቡ (4፡ 1)፣ 4) ኮልታፋ ተናጋሪ ነበር (4፡ 10) እና 5) የበቃ አልነበረም (4፡ 13) ፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሄር ኃይሉን በሁሉለቱም ሰዎች በኩል አሳየየ/ገለፀ ፡፡
ጳዉሎስ እግዚአብሄር ለክብር አማኞች ለበሰሉት በእግዚአብሄር ጥበብ ሚስጥርን እንዲናገር እግዚአብሄር እንደላከዉ ገለፀ (ቁጥር 6-7) ፡፡ ማክአርቱር ቁጥር 7 በእነዚህ ቃላቶች “ ሚስጥር እንቆቅልሽ ስለሆነ ነገር አያመለክትም ነገር ግን እዉነቱን እግዚአብሄር ከጊዜዉ በፊት የሚያዉቀው እና ለእርሱ የሚገልጥበት ትክክለኛ ጊዜዉ እስኪደርስ ድረስ የሚደብቀው እንደሆነ “ ይገልፃል ፡፡
ዋረን ዋይርስቤ እግዚአብሄር ለትክክለኛዉ ጊዜ የሚጠብቅበትን የዚህን ጥበብ አምስት ባህሪያት ያመለክታል፡
- ከሰዉ ሳይሆን ቀጥታ ከእግዚአብሄር ስለሚመጣ (ቁጥር 7) ፡፡
- የእግዚአብሄር ጊዜ መጠበቅ የተሰወረ ስለሆነ (ቁጥር 7) ፡፡
- እግዚአብሄር በወሰነዉ ጊዜ ብቻ የሚሆን ነው (ቁጥር 7) ፡፡
- ለእግዚአብሄር ሰዎች በክብር ስለሚሆን (ቁጥር 7) ፡፡
- ካልዳነዉ አለም ተሰዉሮ ስለ ተቀመጠ እና ስላላገኙት ኢየሱስን ለመስቀል ፍቃደኞች ስለ ነበሩ (ቁጥር 8) ፡፡
በቁጥር 9 እግዚአብሄር ለሚወዱት ይህን ጥበብ አዘጋጀ (ኢሳ 64፡ 4, 65፡ 17) ፤ ያ ጥበብ ዛሬም በአማኞች ህይወት ላይ መተግበሩን ይቀጥላል ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ሁሉንም ሰዉ በመፈለግ የእግዚአብሄርን ጥበብ ይገልጥልናል ፡፡ ዋይርስቤ አራት የመንፈስ ቅዱስን ባህሪያት ፅፏል (ቁጥር 10-13)፡
መንፈሱ እንደ አማኝ በዉስጣችን በመኖር ያበረታናል ፡፡
መንፈሱ የእግዚአብሄር ጥበብን ጥልቀት ያለማቋረጥ በመመርመር ለእኛ ይገልጥልናል ፡፡
መንፈሱ ያለማቋረጥ የእግዚአብሄርን ጥበብ እና እዉነት ያስተምረናል ፡፡
መንፈሱ በመንፈሳዊ ነገር በመብሰል ሂደት ዉስጥ ይመራናል ፡፡
በሌላ በኩል የማያምኑ የእግዚአብሄርን መንፈስ አይቀበሉም - እንደ ሞኝ ነገር ይመለከቱታል (ቁጥር 14) ፡፡ ለመንፈስ ቅዱስ ክፍት የሆኑት አማኞች እንደ “ መንፈሳዊነት “ መረዳት ሲችሉ ከእግዚአብሄር ዉጪ በተፈጥሮ የሚኖሩት የማያምኑት ደግሞ እንደ “ ተፈጥሮ “ ሊረዱት ይችላሉ (ቁጥር 14-15) ፡፡
መደምደሚያ
በ 1ቆሮንቶስ (3፡ 1) “ ከተፈጥሮ “ ወይም “ ከመንፈሳዊነት “ ሰዎስተኛ አይነት ግለሰብ የተጨመረ ነው - በህይወቱ የመንፈስ ስራን ስላልፈቀደ በእምነት ህፃን የሆነዉ “ የስጋ ሰው “ ነው ፡፡ አማኞች በጌታ ሀሳብ ዉስጥ ምን እንዳለ ማወቅ ይችላሉ ምክንያቱም የክርስቶስ ሀሳብ ስላለን እና የእግዚአብሄርን ቃል በማጥናት ስለምንበስል እና የመንፈሱን ምሪት ስለምናዳምጥ ፡፡
Warren W. Wiersbe, Wiersbe’s Exposition Outlines on the New Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 1989), p. 573.
Jean Boonstra, “Moses’ Five Excuses,” April 18, 2014, www.VoiceofProphecy.com; available online.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1568.
Wiersbe, pp. 574–575.
Wiersbe, pp. 575–576.
Wiersbe, p. 577.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1463.
ጥያቄዎች
-
በ 1ቆሮ (2፡ 1-5) ለወንጌላዊነት የጳዉሎስ መመልመያ ምን ይመስላል ?
-
ለቆሮንቶሳዊያን የጳዉሎስ መልዕክት ዋናዉ/ማዕከላዊዉ ነገር ምን ነበር (ገላ 6፡ 14) ? በአሁኑ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ላይ ይህን ትኩረት እያያችሁት ነው ?
-
የእግዚአብሄር ባህሪይ የከበረ መሆንን ያካትታል (1ቆሮ 2፡ 8) ፤ ሌላ ምን ርዕስ የእግዚአብሄርን ክብር ያንፀባርቃል ? (መዝ 24፡ 7-10, ሐዋ 7፡ 2, ኤፌ 1፡ 17, 1ጴጥ 4፡ 14, 2ጴጥ 1፡ 17)
-
መፅኀፍ ስለ እግዚአብሄር ጥበብ እና ስለ ሰዉ ጥበብ የሚለዉን አወዳድሩ ፤ (1ቆሮ 1፡ 18-30, 2፡ 6-7, 13-14, 3፡ 18-19)
-
የተፈጥሮ ሰዉ የእግዚአብሄርን መንፈስ ነገሮች መቀበል የማይችለዉ ለምንድን ነው ? እነዚህን ነገሮች ማን ሊቀበል ይችላል ? የክርስቶስ ሀሳብ/ልብ አለን ማለት ምን ማለት ነው ? (ሮሜ 11፡ 33-36)
-
በ 1ቆሮንቶስ 2 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Corinthians 2:3–5
“I came to you in weakness, in fear, and in much trembling. My speech and my proclamation were not with persuasive words of wisdom but with a powerful demonstration by the Spirit, so that your faith might not be based on men’s wisdom but on God’s power.”
እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ተከታይ ፣ እናንተ የክርስቶስ ልብ አላችሁ ። በውስጣችሁ የመንፈስ ቅዱስ ሀይል አለ ። መንፈስ በውስጣችሁ ስለሚኖር ይመረምራችኋል ፣ ያስተምራችኋል ደግሞም ያበስላችኋል ። ስለዚህም ደግሞ በእግዚአብሔር በነጻ የተሰጣችሁ ስጦታ ምን እንደሆነ ትረዳላችሁ ።
ውድቀት ይሰማችሁ ይሆናል ። ደካማነት ፣ ፍርሃት ደግሞም ሽብር ይሰማችሁም ይሆናል ። በብዙ ጥበብ ጎበዝ ተናጋሪዎችም ላትሆኑ ትችላላችሁ ። ሆኖም ግን እምነታችሁ የተመሰረተው በሰው ጥበብና ሃይል ላይ ሳይሆን በእግዚአብሔር ሃይል ላይ ነው ። የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ እናም ከምታስቡት በላይ ማድረግ ትችላላችሁ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ሃይል በውስጣችሁ ስለሚኖር ። ጳውሎስ በድካም ፣ በፍርሃት ፣ በመንቀጥቀጥ ውስጥ ሁኖ በተጨማሪም በቂ እንዳልሆነ እየተሰማው እንኳ ወንጌልን መሰከረ ። ነገር ግን እርሱ ያ ነገር እንድያስቆመው አልፈቀደም ። በመንፈስ ሃይል ሄደ ። ስለዚህ ዛሬ በእምነት ውጡ ደግሞም “ ማድረግ ትችላላችሁ “ የምትለውን ያችን ትንስ ድምጽ እመኑ ። በጌታ ብርታት ፣ ሃይልና ጥበብ የተሞላ ፣ የክርስቶስ ልብ አላችሁ ። ይህን በእምነት ፈጽሙት እንድሁም ይህን ሀይለኛ አውነት ለህይወታችሁ እመኑ ።
“ እኔም በድካምና በፍርሃት በብዙ መንቀጥቀጥም በእናንተ ዘንድ ነበርሁ፤ እምነታችሁም በእግዚአብሔር ኃይል እንጂ በሰው ጥበብ እንዳይሆን፥ ቃሌም ስብከቴም መንፈስንና ኃይልን በመግለጥ ነበረ እንጂ፥ በሚያባብል በጥበብ ቃል አልነበረም።
- 1ኛ ቆሮንቶስ 2:3-5
ተጨማሪ ጥቀሰ
ዘጸአት 4 :10-12 -ሙሴም እግዚአብሔርን፦ ጌታ ሆይ፥ እኔ አፌ ኰልታፋ ምላሴም ጸያፍ የሆነ ሰው ነኝ፤ ትናንት ከትናንት ወዲያ ባሪያህንም ከተናገርኸኝ ጀምሮ አፈ ትብ ሰው አይደለሁም። እግዚአብሔርም፦ የሰውን አፍ የፈጠረ ማን ነው? ዲዳስ ደንቆሮስ የሚያይስ ዕውርስ ያደረገ ማን ነው? እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን? እንግዲህ አሁን ሂድ፥ እኔም ከአፍህ ጋር እሆናለሁ፥ የምትናገረውንም አስተምርሃለሁ አለው።
1ኛ ቆሮንቶስ 2፥13 --“መንፈሳዊውን ነገር ከመንፈሳዊው ነገር ጋር አስተያይተን መንፈስ በሚያስተምረን ቃል ይህን ደግሞ እንናገራለን እንጂ የሰው ጥበብ በሚያስተምረን ቃል አይደለም።”
1ኛ ቆሮንቶስ 2፥16 -- “እንዲያስተምረው የጌታን ልብ ማን አውቆት ነው? እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን።”
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።