Paul's Letters 1 Corinthians

Bringing Glory To God

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ The Last Adam 1 Corinthians 1 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 503 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ዛሬ በቆሮንቶስ በመጀመሪያዉን ክፍል/ትምህርት እና በጳዉሎስ መልዕክት በአስራ ሰባተኛዉን እ እንጀምራለን ፡፡ ቆሮንቶስ ወደ ሁለት መልዕክት ተከፋፍሏል ከግርክ ከተማ በቆሮንቶስ የተሰየመ ነበር ፡፡ ለቆሮንቶስ የሜንዲ ስዕል ሌላ የሚመሳሰል ሁለት ገፅ ላይ የተፃፈ ነው - ሁለቱ ስዕሎች በአንድ ላይ ሲቀመጡ ሙሉ ታሪክን ይናገራሉ ማለት ነው ፡፡ በመጀመሪያዉ ስዕል ዘጠኙ እጆች በፍቅር ብቻ ሊገኙ የሚችሉትን ዘጠኙን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች ይወክላሉ ፤ በሁለተኛዉ ስዕል ላይ ያለዉ መሸፈኛ በመጀመሪያዉ ስዕል ከላይ የታዬ ሲሆን በክርስቶስ አካል ዉስጥ ሁላችንንም በመንፈስ ቅዱስ መሸፈናችንን ይወክላል ፡፡ በ 1ቆሮንቶስ ዉስጥ ለመሲሁ ቃላችን (ከ 1ቆሮ 15፡ 45) ኋለኛው አዳም ነው ፡፡ የመጀመሪያዉ አዳም በሰዉ ላይ ኃጢዓትን አመጣ ፤ ኋለኛው አዳም ያን ኃጢዓት በራሱ ከሰዉ ላይ አስወገደ ፡፡

ማክአርቱር “ በግል ከሚያደርሰዉ መልዕክት ዉጪ ለጢሞቲዎስ፣ ለቲቶ እና ለፊልሞና ካደረሰዉ ዉጪ የጳዉሎስ መልዕክቶች ተደራሽ የምትደረገዉ ቤተ ክርስቲያን የምትገኝበትን ከተማ እንደሚያመለክት “ ይገልፃል ፡፡ ጳዉሎስ በቁጥር 1 እና 13 (1ቆሮ 3፡ 4 -6፣ 4፡ 15) መጠራቱን አወጀ/ተናገረ ፡፡ ጳዉሎስ 55 ከክርስቶስ ሞት በኋላ በመጨረሻዉ ግማሽ ላይ በሰዎስተኛ የአገልግሎቱ ጉዞ ጊዜ (1ቆሮ 16፡ 21) ከኤፌሶን መልዕክትን ፅፏል ፡፡ ጳዉሎስ በፀደይ በበዓለ አምሳ ቀን ላይ በመዉጣት በኤፌሶን ለሰዎስት አመታት ለመቆየት ከዚያም ወደ ቆሮንቶስ ለመጓዝ አቀደ ፡፡

የቆሮንቶስ ከተማ ከግሪክ ዋና ምድር ከፊሎፌሌንስ ጋር ከተገናኘችዉ ቀጭን ጠባብ ምድር ከቆሮንቶስ ልሳነ ምድር ከአቴንስ በስተ ደቡብ 45 ማይል ርቀት ላይ የምትገኝ ነበረች ፤ ያ ማለት የቆሮንቶስ ከተማ ሁለት የባህር ወደቦች ነበሯጽ ማለት ነዉ - በምስራቅ በኩል የሳሮኒክ ባህር ወደብ እና በስተ ምዕራብ በኩል የቆሮንቶስ ወደብ ፡፡ ይህ አንድ ዋና እና አደገኛ አጭር መንገድ ነበር ፤ መርከቦቹ ትልቅ የሚሽከረከር ግንድ በየብሱ ላይ መርከቦቹን ለማሽከርከር በመጠቀም፣ ጊዜ ለመቆጠብ እና ከአደጋ ለማምለጥ በደሴቶቹ ላይ አቋራጭን መንገድ ስለሚወስዱ የቆሮንቶስን ከተማ ጠቃሚ የንግድ ከተማ ያደርጋታል ፡፡ ቆሮንቶስ የደሴቶቹን ጨዋታ፣ በዚያን ዘመን የአትሌቲክስ ይዘት ያለዉ ጨዋታ (ሌላዉ ኦሎምፒክ ጨዋታ ነበር) አዘጋጅታለች ፡፡ ማክአርቱር “ በአምላክ የሌሽዎች በራሳቸዉ ባህል መስፈርት እንኳን ቆሮንቶስ ስሟም እንኳን ወራዳ እና ነዉረኛ ከሚለዉ ጋር የሚመሳስል እስከ መሆን በጣም የተበላሸች ሆናለች ፤ ለቆሮንቶሳዊነት በአጠቃላይ ብልግናን እና የስካር ወራዳነትን በመወከል እንደ መጣ “ ፅፏል ፡፡ ጳዉሎስ ይህን ብልሹ ምግባርን በሮሜ (1፡ 18-32) ገልፆታል ፡፡

ጳዉሎስ በቆሮንቶስ በሁለተኛ የአገልግሎት ጉዞዉ ላይ ቤተ ክርስቲያንን መሰረተ (ሐዋ 18፡ 1) ፡፡ ጳዉሎስ መጀመሪያ የአይሁድ አማኞችን ርስቅላን እና አቂላን ባገኘበት በምኩራብ አገለገለ ፤ ቆይቶም በዚያ በአገልግሎት ሲላስ እና ጢሞቲዎስ ተቀላቀሉት ፡፡ አብዛኛዎቹ አይሁዶች ስለ ክርስቶስ የጳዉሎስን መልዕክት ባይቀበሉም የምኩራቡ አለቃ/መሪ ቀርስጶ፣ ቤተሰቦቹ እና ሌሎች በመቀበል ወደ አዲስ ቤተ ክርስቲያን ጳዉሎስን ተከተሉት (ሐዋ 18፡ 5-8)፡፡ ጳዉሎስ በአይሁድ መሪዎች በኃይማኖት ወንጀል በሮማን ፍርድ ቤት ከመከሰሱ በፊት ለአንድ አመት ከግማሽ በቆሮንቶስ ቆየ ፡፡ የጳዉሎስ ክሶች ተሰረዙ ምክንያቱም ምንም አይነት ሲቪል ህግ ስላልጣሰ ፡፡ ከዚያ በኋላ በቀላሉ ቆሮንቶስን በመልከክ ኤፌሶን ከዚያም ጵርስቅላ እና አቅላን ከእርሱ ጋር በመያዝ ወደ እስራኤል ሄደ ፡፡ በቆሮንቶስ ያለች ቤተ ክርስቲያን የተከፋፈለች እና አለማዊ የሆነች ነበረች ፤ ጳዉሎስ እነዚህን ጉዳዮች በዚህ መልዕክት ደረሰ/ዳሰሰ ፡፡

ትምህርት

1-ቆሮንቶስ (1፡ 1-9)፡ ዋይርስቤ ቁጥር 1-9 “ ቅዱስ ለመሆን ተጠርታችኋል “ በማለት ያጠቃልላቸዋል ፡፡ ጳዉሎስ ራሱን እና የምኩራቡን አለቃ ሶስቴንስን በመለየት ጀመረ (ቁጥር 1) ፡፡ የሮም ፍርድ ቤት በጳዉሎስ ላይ የነበሩትን ክስች ከሰረዛቸዉ በኋላ እነዚያን ክሶች ያመጡት አይሁዶች በፍርድ መስጫዉ ፊት ሶስቴንስን መቱት (ሐዋ 18፡ 17)፡፡ ጳዉሎስ በቆሮንቶስ ላሉ ለሁሉም በኢየሱስ እንደ ጌታ ለተጠሩት ለሁሉም ይህን መልዕክት ተደራሽ እንዲሆን ፅፏል (ቁጥር 2) ፡፡ ኮንስታብል ቁጥር 3 የጳዉሎስን ሁሉንም ስነ መለኮታዊ ምልከታ እንደሚያጠቃልለዉ ይገልፃል ፡፡ ጳዉሎስ በቆሮንቶስ ስላለች ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሄርን በማመስገን (ቁጥር 4) ኑሮአቸዉ ከእግዚአብሄር በሆነ የንግግር እና የእዉቀት ስጦታ እንደ በለፀገ አመለከተ (ቁጥር 5) ፡፡ ጳዉሎስ በኢየሱስ ተመልሶ መምጣት ጊዜ ከሚጠብቋቸዉ ዘጠኝ ስጦታዎች ዉስጥ ምንም እንደማይጎድልባቸዉ ተስፋ ገባላቸው (ቁጥር 6-7) ፡፡ በኢየሱስ መመለስ ላይ ስንጠባበቅ በዚያን ጊዜ የእርሱን ስራ እንድንሰራ የሚያስፈልገን ማንኛዉንም መንፈሳዊ ስጦታ ይሰጠናል ፡፡ ጳዉሎስ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያንን እንደሚያበረታ እና አሁንም ኃጢዓት ቢኖርብን እንኳን ከክርስቶስ የተነሳ ያለ ክስ/ያለ ነቀፋ እንደ ምንሆን ተናግሯል (ቁጥር 8) ፡፡ ቀጥሎም ጳዉሎስ እግዚአብሄር የታመነ እንደ ነበር ቤተ ክርስቲያንን አሳሰበ (ቁጥር 9) ፡፡

በቁጥር 8 ጳዉሎስ “ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቀን “ የሚለዉን ሀረግ ተጠቅሟል ፤ አዲሱ ስኮፊልድ የመፅኀፍቅዱስ ማጣቀሻ ሀረጉ ከዳግም ምፅዓት በኋላ ያለዉን ጊዜ እንደሚያመለክት ይገልፃል ፡፡ በተጨማሪም በመፅሀፍ ላይ “ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ቀን “ (1ቆሮ 5፡ 5, 2ቆሮ 1፡ 4)፣ “ በኢየሱስ ክርስቶስ ቀን (ፊል 1፡ 6)” እና “ በክርስቶስ ቀን (ፊል 1፡ 10, 2፡ 16 ) “ ተብሎ ይገኛል ፡፡ በእነዚህ ሁሉ ዳግም ምፅዓት የት ነዉ የሚሆነው ? የክርስቶስ ተመልሶ መምጣት መቼም ቢሆን አያሳስበንም ምክንያቱም መልሶ መምጣቱን በጉጉት የምንጠብቅ ስለምንሆን ፡፡

1-ቆሮንቶስ (1፡ 10-25)፡ ዋይርስቤ ቁጥር 10-25 “ ወደ ህብረት ተጠርተናል “ በማለት ያጠቃልላቸዋል ፡፡ ጳዉሎስ አንድ እንዲሆኑ እንጂ እንዳይከፋፈሉ ቤተ ክርስቲያንን አበረታታ (ቁጥር 10) ፤ ጳዉሎስ በአባላቱ መካከል ስለ ተፈጠረዉ ጠላትነት/ክርክር ስምቶ ነበር በተለይምጳዉሎስን፣ አጵሎስን፣ ኬፋን (ጴጥሮስን) ወይም የክርስቶስ ነኝ በማለት በሚከተሉት መካከል (ቁጥር 11-12) ፡፡ ጳዉሎስ ኢየሱስ ስለ እነርሱ ሞቶ እንደ ነበር እና በእርሱ ስም ብቻ ተጠምቀዉም እንደ ነበር አስታወሳቸዉ/አሳሰባቸው (ቁጥር 14) ፡፡ በእርግጥም ጳዉሎስ በአካል ቀርስጶስን እና ጋይዮስን እና የእስጢፋኖስን ቤተ ሰቦች ብቻ አጥምቆ ነበር (ቁጥር 14-16) ፡፡ ኢየሱስ ብቻዉን ቀዳሚ ነው ፡፡ ይልቁንም ክርስቶስ ጳዉሎስን በመስቀል ሞቱ መልዕክት ወንጌልን እንዲሰብክ ላከው (ቁጥር 17) ፤ የመስቀሉ መልዕክት/ቃል ለሚከተሉት ሞኝነት ነው ፤ የእግዚአብሄር ኃይል እንድንድን ለእኛ ተሰጠን (ቁጥር 18) ፡፡ ያ ሞኝነት የክርስቶስን ታሪክ ለመናገር የኛ የሰዎች ሙከራ ነው (ቁጥር 19-21) ፡፡ የተሰቀለዉ ክርስቶስ መልዕክት ለአይሁዶች ማሰናከያ ድንጋይ ነበር ለአሕዛቦች ደግሞ እንደ ሞኝነት ታዬ (ቁጥር 23) ፤ ይሁን እንጂ የእግዚአብሄር ኃይል እና ጥበብ ለተጠሩት ሁሉ ተሰጠ ምክንያቱም ከሰዉ ኃይል እና ጥበብ ስለሚበልጥ (ቁጥር 25) ፡፡

ዲ.ኤ.ካርሰን “ አንድ ሴት በሂሮሽማ እንደ ወደቀዉ ቦንብ እንደ ሙሽሩም ጥላ ደመና በመልበስ በመማጌጥ ለመስራት ከመጣች ምን ታስባላችሁ ? …. የቤተ ክርስቲያን ህንፃ በአችዊዝ ላይ በሆነዉ የብዙ መቃብር አዳድስ ስዕል ቢያጌጥ ምን ታስባላችሁ ? …. በመጀመሪያዉ ክፍለ ዘመን ተመሳሳይ የሚያሳቅቅ አስደንጋጭ ነገር በመስቀሉ እና በስቅላቱ ላይ የተገናኜ ነበር “ ፅፏል ፡፡

ጎርደን ፊ፡ “ መስቀሉ ለ19 ክፍለ ዘመናት ያክል የእምነት ምልክት በነበረበት ስፍራ ለነበሩ በምዕራብ ክርስትናን ለማነሳሳት አስቸጋሪ ነው፣ ራሱን በመጀመሪያዉ ክፍለ ዘመን ግሪኮች ወይም ሮማዉያኖች በሚመስሉ በጠላቶቹ ተሰቅሎ ራሱን ያገኘዉን የእግዚአብሄርን መልዕክት እጅቅ በመቋመጥ እንዴት እንደያዙት ይበረታታል ፤ ነገር ግን ይህ ቆሮንቶሳዊያን ከዚህ ፈቀቅ በማለት ለምን ወደ ጥበብ ይሄዱ እንደ ነበር እና በክርስቲያኖች መካከል መስቀሉ ከመሆኑ አንድ ክፍለ ዘመን በፊት በሚገባ የእምነታቸዉ ምልክት ለምን እንደ ነበር ሁለቱን ስንረዳ ማድነቃችን የዚህ አሉባልታ እና ስህተት ጥልቀት ታላቅ መሆን ነው “ በማለት ፅፏል ፡፡

መደምደሚያ

ዋይርስቤ ቁጥር (26-31) “ ለእግዚአብሄር ክብር ተጠርተናል “ በማለት ያጠቃልለዋል ፤ እግዚአብሄር ደካሞችን፣ ሞኞችን፣ የማያስፈልጉ የሚመስሉትን እና የተናቁትን ለእርሱ ክብር እንዲያመጡ በዚህ አለም ላይ ይጠራቸዋል ፡፡ እነዚህ በራሳቸዉ ብቃት የሚመኩ አይሆኑም በጌታ ብቻ ግን ይመካሉ (ቁጥር 26-31) ፡፡ እኛም በይበልጥ ሁሉንም ለእግዚአብሄር ክብር ለማምጣት ተጠርተናል ፡፡

6 The New Scofield Reference Bible, ed. by E. Schuyler English, et al. (New York: Oxford University Press, 1967), p. 1233; quoted in Thomas L. Constable, Dr. Constable’s Bible Expository Study Notes; 1 Corinthians, p. 20; available online at https://planobiblechapel.org/constable-notes/.

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1561.

  2. MacArthur, pp. 1561–1562.

  3. MacArthur, p. 1562.

  4. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 1989), p. 568.

  5. Constable, p. 84.

    Wiersbe, p. 373.

  6. Wiersbe, p. 569.

  7. D. A. Carson, The Cross & Christian Ministry (Grand Rapids: Baker Book House, and Leicester, Eng.: Intervarsity Press, 1993), p. 12; quoted in Constable, p. 31.

  8. Gordon D. Fee, The First Epistle to the Corinthians (Grand Rapids, Wm. B. Erdmans Publishing, 1987), p. 76; quoted in Constable, p. 35.

  9. Wiersbe, p. 581.

ጥያቄዎች

  1. የ 1ኛ እና የ2ኛ ቆሮንቶስ ተደራሺዎች እነማን ነበሩ ? ጳዉሎስ ይህን መልዕክት ለምን ፃፈ ?
  2. ቅዱሳን እንዲሆኑ የተጠሩት እነማን ናቸው ? እንደ መፅሀፍ ቅዱስ አገላለፅ ቅዱሳን ምንድን ነዉ እንደነሱ እንደ አንዱ እንዴትስ ትኖራላችሁ ? (ኤፌ 4፡ 1, ቆላ 3፡ 15-17, 1ጢሞ 6፡ 12, ዕብ 10፡ 10)
  3. በዚህ ምዕራፍ ጳዉሎስ የዳሰሳቸዉ/የደረሳቸው አንዳንድ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ምን ነበሩ ? በአሁኑ ጊዜ ለእነዚህ ጉዳዮች ቤተ ክርስቲያን እንዴት ነዉ ምላሽ የምትሰጠው ?
  4. አይሁዶች ኢየሱስን ባዩበት እና አሕዛቦች እርሱን ባዩበት መካከል ልዩነቱ ምን ነበር ? አይሁዶች ምንጠየቁ አሕዛቦችስ ምን ፈለጉ ?
  5. በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን የኃጢዓት መኖር የተረጋገጠ ቢሆንም እንኳንማን እንደ ነበሩ ጳዉሎስ እንዴት አሳሰባቸዉ/አስታወሳቸው ? በክርስቶስ እንደ ነበሩ ጳዉሎስ ምን ነገራቸው ?
  6. በ 1ቆሮንቶስ 1 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Corinthians 1:6–9

“In this way, the testimony about Christ was confirmed among you, so that you do not lack any spiritual gift as you eagerly wait for the revelation of our Lord Jesus Christ. He will strengthen you to the end, so that you will be blameless in the day of our Lord Jesus Christ. God is faithful; you were called by Him into fellowship with His Son, Jesus Christ our Lord.”

እግዚአብሔርን ለማገልገል በቂ እንደሆንክ ጠይቀህ ታውቃለህ ? ለምን እንደተጠራህ ጠይቀህ ታውቃለህ ? ምናልባትም በህይወትህ ውስጥ ስለ እግዚአብሔር ታማኝነት ልትጠይቅም ትችላለህ ? ጳውሎስ በቆሮንቶስ ያለችውን ቤተክርስቲያን ፣ በክርስቶስ ቅዱሳን የሆኑትን ባገኘ ጊዜ ቤተክርስቲያኑዋ እንደተከፈለች እንድሁም የተለያዩ አመለካከቶች እንደተንጸባረቁ አውቆ ነበር ። ስለዚህም ጳውሎስ ለአማኞች እነዚህን እውነቶች ተናገረ ፡- ክርስቶስ በመካከላችሁ ተገልጧል ። በጌታ ላይ ስትደገፉ ፣ አንድም የጸጋ ስጦታ አይጎድልባችሁም ። እግዚአብሔር ያበረታችኋል ። መድከማችሁ ምንም ማለት አይደለም ምክንያቱም ከክርስቶስ ፈጽሞ ይቅርታን እንዳገኘ ያለ ነቀፋ እንደሆነ ሰው ትሆኑ ዘንድ ክርስቶስ በየቀኑ ያበረታችኋል ። እግዚአብሔር ታማኝ ነው ። አትጠራጠሩ ። በእግዚአብሔር ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር ለሕብረት ፣ ለወዳጅነት እናም ለጓደኝነት ተጠርታችኋል ።

ዛሬ ወደ ምንድን ነው የተጠራችሁት ? ከእግዚአብሔር ጋር እንድትመላለሱ ። እርሱን እንድትወዱ ። እርሱን ለማወቅ ልትሹ ። ጳውሎስ ሮማውያንን ያስታወሳቸውን እውነቶች ስታስታውሱ ፣ ምን ሊሆን እንደሚችል ገምቱ እስቲ ? ከዚህ በኋላ ስለ እናንተ አይደለም ። ነገር ግን በጠቅላላው ስለ ጌታ ነው ደግሞም በሕይወታችሁ ስላለው የሚያጸድቅ ፣ የሚቀድስና የሚቤዥ ሀይልና ጸጋ ነው ። ስለዚህም በጌታና በታማኝነቱ ተመኩ ። ከዚህ በኋላ ራሳችሁን አትጠይቁ ። ድናችኋል እናም በህይወታችሁ ውስጥ የሚሰራ የእርሱ ሀይል አላችሁ ።

“ለክርስቶስ መመስከሬ በእናንተ ዘንድ እንደ ጸና፣ እንደዚህ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ ስትጠባበቁ አንድ የጸጋ ስጦታ እንኳ አይጎድልባችሁም፤ እርሱም ደግሞ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ያለ ነቀፋ እንድትሆኑ እስከ ፍጻሜ ድረስ ያጸናችኋል። ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው። “

  • 1ኛ ቆሮንቶስ 1:6-9

ተጨማሪ ጥቅስ

1ኛ ቆሮንቶስ 1፥30-31— “ነገር ግን፦ የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ ተብሎ እንደ ተጻፈው ይሆን ዘንድ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው።”

2ኛ ተሰሎንቄ 3፥3— “ነገር ግን የሚያጸናችሁ ከክፉውም የሚጠብቃችሁ ጌታ የታመነ ነው።”

2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥13 — “ባናምነው፥ እርሱ የታመነ ሆኖ ይኖራል፤ ራሱን ሊክድ አይችልምና።”